No summary available.
ሰኔ 03 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንገሤ አመልካች፡- እምላለ ወረዲ ክንስትራክሽን አክሲዮን ማህበር ጠበቃ ሲሳይ ታደሰ ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
የአሁኑ አመልካች በሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ተከሣሽ ሲሆን ተጠሪዎች ደግሞ ከሳሾች ነበሩ።
ክሱም በተከሣሽ ድርጅት ተቀጥረን እየሰራን እያለ ተከሣሽ በራሱ አነሳሽነት የሥራ ውላችንን ያቋረጠብን ስለሆነ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍለን ይወሰንልን የሚል ነው።
ተከሣሽ በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ከሳሾች የተቀጠሩት ተከሣሽ ተስፊ የነጋዳዎች አክሲዮን ማህበር ከተባለው ጋር የሱቆች ህንፃ ግንባታ ለማድረግ በገባነው ውል መሰረት የሱቆች ህንፃ ለመገንባት ቢሆንም ከማህበሩ ጋር የተደረገው የሱቆች ህንፃ ግንባታ ውል በመቋረጡና ከሳሾችም የተቀጠሩት ለዚሁ ኘሮጀክት ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ የሚገባቸውን ክፍያ ማለትም የዓመት እረፍት በገንዘብ ተለውጦ እና የስንብት ክፍያ እንዱሁም የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶአቸው የሥራ ውለ ተቋርጧል ብሎል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም ተከሣሽ ከከሣሾች ጋር የነበረውን የቅጥር ውል ያቋረጠው ተስፊ ነጋዳዎች አክሲዮን ማህበር ጋር የነበረው የሱቆች ግንባታ ውል በመቋረጡ ነው ቢልም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 12 ላይ የተመለከተውን ግዳታ አልተወጣም ። የሥራ ውለ የተቋረጠው የኘሮጀክቱ ሥራ (የሱቆች ሕንፃ ግንባታ) በመጠናቀቁ አይደለም። ተከሣሽ ከማህበሩ ጋር ያደረገው የሱቆች ህንፃ ግንባታ ውለ መቋረጡ ከ3ኛ ወገኖች (ከሳሾች) ጋር የነበረውን ውል እንዱቋረጥ አያደርገውም በማለት የሥራ ውለ የተቋረጠው በህገወጥ መንገድ ነው ሲል ተከሣሽ ለከሳሾች ቀደም ብል ከከፈላቸው ክፉያዎች በተጨማሪ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ክፍያና ካሣ የ6 ወር ደመወዘ እንዱከፍል ወስኗል።
የሥር ተከሣሽም በዚህ በሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ያቀረበ ቢሆንም ከፍተኛው ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ተከራካሪዎች ካከራከረ በኋላ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔን አጽንቷል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ሲሆን በዋነኛነት አመልካች የጠቀሰው የቅሬታ ነጥብም፡- ተጠሪዎች ሙያቸው አናጢነትና ግንበኝነት ሲሆን የተቀጠሩትም ተስፊ የነጋዳዎች አክሲዮን ማህበር አባላት ሱቆችን ለመገንባት አመልካች ከማህበሩ ጋር በገባው ውል መነሻ ሲሆን ይኸው የግንባታ ሥራ የማህበሩ አሰሪ እንዱቋረጠ በማዘዙ ተቋርጧል። የተጠሪዎችም የሥራ ውል በዚሁ ምክንያት ተቋርጦ እያለ የሥር ፍ/ቤቶች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28/2/ሀ/ ሰራተኞቹ በተሰማሩበት ሥራ በሙለና በቀጥታ የሚያስቆም ሁኔታ የተከሰተ አንደሆነ አስሪው ለማሰናበት የሚችል መሆኑ ተደንግጏ እያለ ይኸንኑ ድንጋጌ በማለፍ የሥራ ውለ የተቋረጠው በህገ ወጥ መንገድ ነው ሲለ መወሰናቸው ያለአግባብ ነው የሚል ሲሆን የሥራ ውለ የተቋረጠው በህገ ወጥ መንገድ ነው በሚል መነሻም አመልካቾች ለተጠሪዎች እንዱከፍል የተባለትን ክፍያዎች ይህ ችልት ውድቅ እንዱያደርግ ጠይቋል።
ተጠሪዎች ለአመልካች የሰበር አቤቱታ በሰጡት መልስ አመልካች በተለያዩ ክፍልች ሰራተኞችን እየመደበ የሚያሰራ እንጂ የግንባታ ሰራዎችን ከአሰሪዎች እየተቀበለ የተቀበለውን ህንፃ ግንባታው እስከሚጠናቀቅ ብቻ ሰራተኞችን ውል በማስገባት የሚይሰራ አይደለም። ተጠሪዎች ሙያችን አናጢነት ሲሆን አመልካች የቀጠረን ከተስፊ ነጋዳዎች አክሲዮን ማህበር የተቀበለው የህንፃ ግንባታ ሥራ እስከሚጠናቀቅ በሚል ብቻ አይደለም ስለሆነም በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ብለዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ የተገለፀ ሲሆን እኛም በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የነበረው ውል የተቋረጠው በህጋዊ መንገድ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 4/1/ መሰረት ማንኛውም ሰው ደመወዝ እየተከፈለው በአሰሪ መሪነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለተወሰነ ወይም ላልተወሰነ ጊዜ ወይም የተወሰነ ሥራ ለአሰሪው ለመሥራት በሚያደርገው ስምምነት የሥራ ውል ይመሰረታል።
በአዋጁ አንቀጽ 1ዐ ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ በሚል መዋዋል የሚቻልባቸውን ሁኔታዎች የሚዘረዝር ሲሆን በዚሁ አንቀጽ ከተዘረዘሩት ሁኔታዎች በቀር የሚመሰረቱ ውልች በአዋጁ አንቀጽ 9 በተጠቀሰው መሰረት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረጉ የሥራ ውልች የሚቆጠሩ ናቸው።
ወደተያዘው ጉዲዩ ስንመለስ በሥር ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደሚቻለው አመልካች ተጠሪዎችን የቀጠራቸው አመልካች ተስፊ የነጋዳዎች አክሲዮን ማህበር ለተባለው የሱቆች ህንፃ ግንባታ ሲሆን ሥራው ሲጠናቀቀም ውለ የሚያበቃ ነበር። በመሆኑም ከዚህ በላይ ከፍ ተብል እንደተጠቀሰው በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የተደረገው ውል በአዋጁ አንቀጽ 1ዐ ሥር ለተወሰነ ጊዜ ወይም ለተወሰነ ሥራ ተብል የሚደረጉ ውልች ውስጥ የሚሸፈን ነው።
ይሁን እንጂ አመልካች የሱቆች ህንፃ ለመገንባት ከተስፊ ነጋዳዎች ማህበር ጋር የገባው ውል የግንባታ ውለ ፔሮጀክት ከመጠናቀቁ በፉት ተቋርጧል። ይህ አመልካች ከተስፊ የጋዳዎች አክሲዮን ማህበር ጋር የገባው የሱቆች ህንፃ ግንባታ ውል መቋረጡ የሥራ ውለ በልላ ምክንያት ድርጅቱ ለዘለቀታው ሲዘጋ በህግ የሚቋረጥ ስለመሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 24/4/ የተደነገገውን የሚያሟላ ነው።
ይህ ሆኖ ሣለ የሥር ፍ/ቤቶች በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የተደረገው ውል የተቋረጠው በአመልካችና በተስፈ ነጋዳዎች አክሲዮን ማህበር ተደርጏ በነበረው ውል መሰረት የተጀመረው የፔሮጀክት ሥራ ሳይጠናቀቅ ነው። በማህበሩና በአመልካች መካከል የነበረው ውል መቋረጥ አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የነበረውን ውል ለማቋረጥ በቂ ምክንያት አይሆንም በማለት ውለ የተቋረጠው በህገ ወጥ መንገድ ነው ሲለ የወሰኑት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። ስለሆነም የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል።
የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ/67044 በቀን 20/11/2002 በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ እና የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመዝገብ በቀን 22/6/2003 የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካችና በተጠሪዎች መካከል የነበረው የሥራ ውል የተቋረጠው በህጋዊ መንገድ ነው ብለናል። ስለሆነም አመልካች ለተጠሪዎች የስንብት ክፍያና የዓመት ዕረፍት ወደ ገንዘብ ተለውጦ በመክፈል እንደሁም የሥራ ልምድ የምስክር ወረቀት በመስጠት ተጠሪዎችን ያሰናበታቸው በአግባቡ ነው።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ የግራ ቀኙ ተከራካሪዎች የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.