No summary available.
ሰኔ 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ካንትሪ ክለብ ዳቨልፏር የረር ቪው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፔሮጀክት - ነገረ ፈጅ ታማኝ የበነ - ቀረበ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ሲሆን በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የቀረበው በአሁኑ ተጠሪዎች ከሣሽነት ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ በተከሣሽ ድርጅት ውስጥ በአናጢነት ሙያ ተቀጥረን 1ኛ ከሣሽ በቀን ብር 36 ፣ 2ኛ ከሣሽ ብር 39 እና 3 ከሣሽ ብር 2ዐ እየተከፈለ በመስራት ላይ እያለን ነሐሴ 17 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ያለአግባብ ከስራ ላይ ያሰናበተን ስለሆነ ወደ ምድብ ስራችን እንድንመለስ ወደ ስራ የማይመልሰን ከሆነ ደግሞ በህጉ መሰረት ሉከፍለን የሚገባውን ክፍያዎች እንዱከፍለን የሚል ነው። ተከሣሽ /የአሁን አመልካች/ መጥሪያ ደርሷቸው በሰጡት መልስ ከሣሾች ከስራ የተሰናበቱት ድርጅቱ ከመዝገብ ቤት የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ አንቀበልም በማለታቸው በህብረት ስምምነቱ መሰረት ስለሆነ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ተከራክሯል።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከላይ እንደተመለከተው ካከራከረ በኋላ የግራ ቀኙን ምስክር በመስማት የተከሣሽ ምስክሮች ከመዝገብ ቤት ወጪ ሆኖ ለከሣሾች የተጻፈውን ማስጠንቀቂያ ደብዲቤ አንቀበልም ማለታቸውን አረጋግጫለሁ በልላ በኩል የተከሣሾች ምስክሮች ቃል እርስ በርስ የሚቃረን በመሆኑ ማስተባበል አልቻለም፤ ከድርጅቱ መዝገብ ቤት ተጽፍ የሚሰጠውን ማስጠንቀቂያ አልቀበልም ማለት ደግሞ በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 58/10/ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብት የሚችል በመሆኑ ስንብቱ ህጋዊ ነው በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የአሁን ተጠሪዎች ይግባኛቸውን ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የአሁን አመልካች እየሰጠ የነበረው ማስጠንቀቂያ ሣይሆን ቀደሞ በቅጥር ውላቸው ውስጥ የተጠቀሰውን በቀን 5 ካ.ሜ የአሁን ተጠሪዎች ለመስራት የገቡትን ግዳታ ወደ 1ዐ ካ.ሜ.
ለማሻሻል የተደረገ በመሆኑ የአሁን አመልካች በራሱ ተነሳሽነት በግራ ቀኙ መካከል የነበረውን የስራ ውል ስምምነት መጣሱን እንጂ በጥፊት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ባለመሆኑ የስራ ውለ የተቋረጠው ከህግ ውጪ ነው በማለት የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔን ሽሯል። የተጠየቀውን ክፍያ በተመለከተም የማስጠንቀቂያ ጊዜ ፣ የስራ ስንብት እና የካሣ ክፍያ እንዱከፍላቸው አመልካች ኃላፉነት እንዲለበት ወስኗል። አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች በቀን 23-5-03 ዓ.ም በነገረፈጅ በኩል በተጻፈ 4 ገጽ አቤቱታ ፍሬ ሃሣብ ከድርጅቱ መዝገብ ቤት ወጪ ሆኖ ለሰራተኞች የሚሰጠውን የማስጠንቀቂያ ደብዲቤ አልቀበልም ማለት በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 58/10/ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ የሚያሰናብት ሆኖ እያለ የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይሄንን በማለፍ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው በማለት የቀረበ ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪዎች ቀርበው መልስ እንዱሰጡበት ታዘው የካቲት 28 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ ባቀረቡት መልስ ፍሬ ሃሣብ ያቀረብኳቸው የሰው ምስክሮች የተባለው የማስጠንቀቂያ ደብዲቤ ተሰጠ ለተባለበት ያልነበርና እንቢ ያላልን መሆኑን መስክሮልናል ፤ አንፈርምም ያልነው ደግሞ ቀድሞ የተስማማንበት የስራ ውል በቀን 5 ካ.ሜ ሆኖ እያለ አሁን ደግሞ 1ዐ ካ.ሜ እንድንሰራ ያዘዘን በመሆኑ ከአቅማችን በላይ በመሆኑ እምቢ ማለታችን እንጂ በጥፊተኝነት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ ባለመሆኑ የፋ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ እንዱጸና በማለት ተከራክሯል። የአመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የቀረቡትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪዎች ከስራ የተሰናበቱት በህጋዊ መንገድ ወይስ በህገ-ወጥ መንገድ ነው? በሚል ጭብጥ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በመጀመሪያ ደረጃ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27 ስር ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብቱ የሚችለ ጥፊቶችን በዝርዝር አስቀምጧል። ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ 5 አንቀጽ 27/1/ ስር ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰብቱ የሚችለትን ጥፊቶች በህብረት ስምምነታቸው መደንገግ እንደሚችለና በዚሁ መሰረት በድርጅቱ ውስጥ ስራ ላይ ያለው የህብረት ስምምነት አንቀጽ 58/10/ ከመዝገብ ቤት የሚሰጠውን ማስጠንቀቂያ አልቀበልም ማለት እንደ አንድ በቂ ምክንያት የተቀመጠ መሆኑ ግልጽ ነው። የአሁን አመልካችም የሚከራከሩት ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው ይሄ የህብረት ስምምነት አንቀጽ እንደሆነና የተሰጠን ማስጠንቀቂያ ያለመቀበል በራሱ ከስራ ለማሰናበት በቂ መሆኑን ተከራክሯል። በልላ በኩል ተጠሪዎች የሚከራከሩት የተጻፈው ደብዲቤ ባጠፊነው ጥፊት የተሰጠ ሣይሆን በስራ ውላችን ውስጥ የተስማማንበትን በቀን 5 ካ.ሜ ለመስራት ውል የገባንበትን በመለወጥ በቀን 1ዐ ካ.ሜ እንድንሰራ የታዘዘንበት ነው በማለት የተጠቀሰው የህግ አንቀጽ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት እንደላለው ተከራክረዋል።
ከዚህ የግራ ቀኙ ክርክር አኳያ የተያዘውን ጉዲይ ስንመረምር የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ.
377/96 አንቀጽ 27/1/ መግቢያን በምናይበት ጊዜ በልላ አኳኋን በህብረት ስምምነቱ የተካተተ ካልሆነ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብቱ የሚችለ ነገሮች በዚሁ አንቀጽ ስር የተዘረዘሩት ብቻ እንደሆኑ ያመለክታል። ለህብረት ስምምነቱ መውጣት መሰረት የሆነው የአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 27/ተ/ ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ሉያሰናብቱ ይችላለ ተብለው በህብረት ስምምነት የሚደነገጉት ላልች ጥፊቶች እንደሆነ ያመለክታል።
ይሄ ማለት ደግሞ በህብረት ስምምነት እንደምክንያት ሉደነገጉ የሚችለት ነገሮች ጥፊትን መሰረት ያደረገ መሆን እንዲለበት ያመለክታል።
አሁን ለተጠሪዎች ከስራ መሰናበት መሰረት የሆነውን የህብረት ስምምነት አንቀጽ 58 ስንመለከትም የአንቀፁ ርዕስ ከስራ የሚያሰናብቱ ከባድ ጥፊቶች በሚል ከመደንገጉም በላይ የዚሁ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ 1ዐ በተያያዘ መልኩ ‛ድርጅቱ ከመዝገብ ቤት የሚሰጠውን የማስጠንቀቂያ ወረቀት አልቀበልም ካለ“ በማለት ይደነግጋል። ይሄንን ሁለ አንድ ላይ ጠቅለል አድርገን ስንመለከት የስራ ስንብቱ የሰራተኛውን ጥፊት መሰረት ያደረገና የሚሰጠውም ማስጠንቀቂያ ጥፊትን መሰረት ያደረገ መሆን እንዲለበት ያመለክታል።
የአሁን ተጠሪዎች እንዱቀበለ የታዘዙትን ደብዲቤ አንቀበልም ማለታቸው በመጀመሪያ ጉዲዩን ባየው ፍርድ ቤትም ሆነ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ጉዲይ መሆኑ ቢታመንበትም እየተሰጣቸው ያለው ደብዲቤ ከላይ እንደተብራራው የህግ ድንጋጌዎች ጥፊትን መሰረት ያደረገ ነው ወይስ አይደለም ከሚለው አኳያ መታየት አለበት።
በዚህ መሰረት ተጠሪዎች እንዱቀበለ እየታዘዙ ያለት ቀድሞ በስራ ውላቸው ውስጥ በቀን ተጠሪዎች 5 ካ.ሜ ለመስራት የተስማሙበትን አመልካች በቀን 1ዐ ካ.ሜ እንዱሰሩ የጻፈባቸውን ደብዲቤ ስለመሆኑ የፋ/ከ/ፍ/ቤት በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው በመሆኑ የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ስልጣን ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 8ዐ/3/ /ሀ/ እና በአዋጅ ቁ. 25/88 አንቀጽ 1ዐ መሰረት መሰረታዊ የህግ ስህተት ሲኖር ማረም በመሆኑ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የደረሰበትን መደምደሚያ መቀበለ ተገቢ ይሆናል። በመሰረቱ አመልካችም የሚከራከረው የተጻፈው የደብዲቤ ይዘት ከዚህ የተለየ ስለመሆኑ ሣይሆን ደብዲቤውን ያለመቀበላቸው ብቻ ከስራ ለማባረር በቂ ነው ከሚለው ነጥብ አኳያ በመሆኑ አልፈነዋል።
የተጻፈባቸው ደብዲቤ ይዘት ከላይ የተመለከተው በመሆኑ አመልካችም ተጠሪዎች ሲቀጠሩ የነበረው ውል በቀን 5 ካ.ሜ ለመስራት እንደተስማሙ ባላስተባበለበት በራሱ ተነሣሽነት በውላቸው ውስጥ የተቀመጠውን የቀን የስራ መጠን በመተላለፍ በቀን 1ዐ ካ.ሜ እንዱሰሩ ማለቱና ቀድሞ የነበረውን የስራ ውል የሚያስቀይር ጉዲይ መኖሩን እንኳ ባላስረዲበት በራሱ መጻፍና አንቀበልም ብሎል በማለት ከስራ ማሰናበቱ ከተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎች ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ የፋ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝ/ቁ. 99340 በቀን ዐ9-05-2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካች ተጠሪዎችን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ያሰናበተው ህገ-ወጥ ነው ተብል ተያያዥ ክፍያዎች ለተጠሪዎች እንዱፈጸሙ መወሰኑ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት በቀን 01-06-2ዐዐ3 ዓ.ም በዋለው ችልት የተሰጠው ዕግድ ተነስቷል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
እ.ከ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.