No summary available.
ሰኔ 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አድቬንቲስት የልማት የተረድኦ ድርጅት - ጠበቃ ዶ/ር ዘወድነህ በየነ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ገበየሁ ወ/ሚካኤል መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የቀረበው ጉዲይ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ሲሆን የቀረበው በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በአሁኑ ተጠሪ ከሣሽነት ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ በተከሣሽ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው በመስራት ላይ እንዲለ ያለአግባብ ከስራ የተሰናበቱ መሆኑን በመግለጽ የተለያዩ ክፍያዎች እንዱወሰንላቸው የጠየቁ ሲሆን በማስረጃም የጽሁፍ የሰው ምስክሮች ዝርዝር አቅርቧል የሚል ነው። ተከሣሽ ድርጅት ቀርቦ በሰጠው መልስ ከሣሽ የተቀጠሩት ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ ይሄው ሲያበቃ ያሰናብተዋል፤ ከሣሽ ለረሃብተኞች እንዱከፊፈል ተብል የተሰጣቸውን ስንዳ እንዱበላሽ በማድረጋቸው በስራ ቦታ ላይ አለቃቸውን በመሳደባቸው እንደሁም የስራ ሰዓት ባለማክበራቸዉ ተሰናበተዋል በማለት በአማራጭ የተከራከረ ሲሆን ከማስረጃም አኳያ የጽሁፍ ሰነድና የሰው ምስክሮች ዝርዝር ቀርቧል የሚል ነው።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከላይ እንደተመለከተው ካከራከረ በኋላ በግራቀኙ መካከል የነበረው የስራ ውል ለተወነ ጊዜ ሆኖ የሚቆየው ከሰኔ 2ዐዐዐ ዓ.ም እስከ ታህሣስ 2ዐዐ1 ዓ.ም ድረስ በመሆኑ ይሄ ጊዜ ሲያልቅ የሚቋረጥ በመሆኑ ስንብቱ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24/1/ መሰረት የተፈጸመ በመሆኑ ህጋዊ ነው በማለት ወስኗል። ክፍያን በተመለከተ የፔሮቪደንት ፈንድ ብር 5ዐ86,96 ተከሣሽ ድርጅት ለከሣሽ በአንድ ዓመት የአገልግልት ዘመን ውስጥ ለተሰራ የአራት ወር ከ2ዐ ቀን የአመት ፍቃድ ክፍያ እንዱከፍለው ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁን ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱም ካከራከረ በኋላ የቅጥር ውለ ለተወሰነ ጊዜ ቢሆንም የተቀጠሩት ለፔሮጀክቱ ስራ እስከ ሆነ ድረስ ፔሮጀክቱ ደግሞ የሚጠናቀቀው የስራ ዘመኑና የበጀት ዘመኑ አንድ ዓመት ነው በመባለ ፔሮጀክቱ ስለመጠናቀቁ ደግሞ ተጠሪ /የአሁን አመልካች/ ያቀረበው ማስረጃ ባለመኖሩ ከስራ ተጠሪን ያሰናበተው ያለአግባብ ነው በማለት የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ በመሻር አመልካች ለአሁን ተጠሪ ፔሮጀክቱ እስከሚጠናቀቅ ቢቆየ ኖሮ ሉከፈላቸው የሚችል የነበረው ደግሞ ማለትም ከታህሣስ 22 እስከ ሰኔ 3ዐ/01 ድረስ ያለውን ደሞዛቸው ታስቦ እንዱከፈላቸው በማለት ወስኗል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ሰኔ 16 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ተጽፍ በቀረበው ቅሬታ ተጠሪ በሙለ ፍቃድ ተቀብል የስራ ውል የገባው ለተወሰነ ጊዜ በመሆኑ ይሄ ጊዜ ደግሞ የሚያበቃው ታህሣስ 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በመሆኑ ስራውም የፔሮጀክት ስራ ሆኖ እያለ ስንብቱ ህጋዊ ነው መባል ሲገባው ተጠሪ ያልሰራበትን ደሞዝ እንዱከፈለው መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሞበታል የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ የተጠሪ ጠበቃ ታህሣስ ዐ4 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ መልስ ያቀረበ ሲሆን ፍሬ ሃሣቡ፡- የቀረበው ቅሬታ ግልጽነት የለውም የተቀጠርኩበት የውል ስምምነት ለተወሰነ ጊዜ ቢልም ተፈጻሚነት ያለው ግን የተቀጠርኩበት የስራ ጸባይ በመሆኑ የተቀጠርኩት ለፔሮጀክት ስራ ስለመሆኑ በመ/ደ/ፍ/ቤት ያልቀረበ በመሆኑ የስራ ውለ የተቋረጠው ያለአግባብ ነው በማለት የተሰጠው ውሣኔ በአግባቡ በመሆኑ እንዱጸና በማለት ተከራክሯል። የአመልካች ጠበቃ ታህሣስ 11 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በሰጠው የመልስ መልስ የቀረበውን ቅሬታ በማጠናከር የሰጠ ሲሆን በተጨማሪ ፔሮጀክቱ በአሜሪካ አለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት የሚታገዝ በመሆኑ ጊዜው የሚጠናቀቀው ማለትም የበጀት ዓመቱ ታህሣስ 2ዐዐ1 ዓ.ም ሆኖ ሣለ ሰኔ 3ዐ /2000/ ያልቃል በማለት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ የፋ/ከ/ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ እንዱሻርልን በማለት ተከራክሯል።
በግራቀኙ የቀረበው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም መዝገቡን መርምሮታል። እንደመረመረውም በተጠሪና በአመልካች መካከል የነበረው የስራ ውል ግንኙነት ለተወሰነ ጊዜ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
በዚሁ መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ ተጠሪ ፈጽሟቸዋል በማለት አመልካች ያቀረበችውን ጥፊቶች በተመለከተ ደግሞ ከስራ ለማሰናበት በቂ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የበታች ፍርድ ቤት ማጣራት ውስጥ ያልገባ በመሆኑ ይሄ ችልትም ወደዚህ ጭብጥ የሚያስመጣ አግባብ ካለ ከላይ በተያዘው ጭብጥ ውጤት ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ለጊዜው እናልፈዋለን።
ወደተያዘው ጭብጥ ስንመለስ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የስራ ውል በውላቸው ውስጥ በግልጽ እንደተቀመጠው ከሰኔ /2000 ዓ.ም እስከ ታህሣስ 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሚመለከት መሆኑ አላከራከረም። አከራካሪ የሆነው ጉዲይ ተጠሪ የውለ ቃል ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ መሆኑ ሣይሆን መታየት ያለበት ከተቀጠርኩበት የስራ ጸባይ አኳያ መሆን ይገባዋል የሚል ሲሆን በአመልካች በኩል የቀረበው ክርክር ደግሞ ውለ ግልጽ ከመሆኑም በላይ ስራው የፔሮጀክት በመሆኑ የሚጠናቀቀው በታህሣስ ወር 2ዐዐ1 ዓ.ም ሆኖ ተገምግሞ ይቀጠል አይቀጥል የሚለው ውሣኔ ሲያገኝ ብቻ የሚቀጥል በመሆኑ ፔሮጀክቱ የአንድ ዓመት ነው የበጀት ዓመቱ ደግሞ የሚያልቀው ሰኔ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ነው በማለት ፍርድ ቤቱ የደረሰበት መደምደሚያ አግባብነት የለውም የሚል ነው።
የቀረበውን ክርክር ስንመለከት በእርግጥ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 9 እና አንቀጽ 1ዐ አንድ ላይ ስናዬው አንድ የስራ ውል ለተወሰነ ጊዜ መደረጉ ብቻ የተወሰነ ጊዜ የስራ ውል እንደማያሰኘውና እንደስራው ባህሪ እየተየ መወሰን ያለበት ስለመሆኑ ያስገነዘበናል። በዚህ ጉዲይ ላይ ግን የስራ ውለ ተጠሪ እንደሚከራከረው ለተወሰነ ጊዜ ስለመሆኑ ማስረዲት ብቻ ሣይሆን ስራው የፔሮጀክት ስራ መሆኑና በውጪ ድርጅት የሚደገፍ በመሆኑ የዓመት ስራ እንቅስቃሴው ታይቶ ፔሮጀክቱ ይቀጥል ሲባል ብቻ የሚቀጥል እንደሆነ የበጀት ዓመቱም የሚጠናቀቀው ታህሣስ 2ዐዐ1 ዓ.ም እንደሆነ ከመከራከሩም በላይ በዚህ ነጥብ ላይ የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ማስረጃ ሰምቶ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ጉዲይ ነው።
የፔሮጀክቱ የበጀት ዓመት በታህሣስ ወር ላይ እንደሚጠናቀቅ ማስረጃን የመቀበልና የመመዘን ስልጣን ያለው የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ያረጋገጠው ሲሆን ተጠሪ ይሄንን የሚያስተባብል ማስረጃ ባልቀረበበት የፋ/ከ/ፍ/ቤት የበጀት ዓመቱ የሚጠናቀቀው ሰኔ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ነው ወደሚለው መደምደሚያ መድረሱ ወደዚህ መደምደሚያው ያደረሰውን በቂ ምክንያት ሣይገልጽ በመሆኑ መሰረታዊ የማስረጃ ምዘና መርሆዎችን የተከተለ ባለመሆኑ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በመሆኑም በተጠሪ እና በአመልካች መካከል የነበረው የስራ ውል ግንኙነት በተወሰነ ጊዜ በመሆኑ የውል ጊዜያቸው ከማለቁ በፉት በስራ ላይ ትብብር እንዱደረግላቸው የድጋፍ ደብዲቤ ለሚመለከተው ክፍል አመልካች መጻፊ እንደዚሁም የስራ ውለ ከተቋረጠ በኋላ ላልች ሰዎችን ድርጅቱ መቅጠሩ የስራ ውለ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ነው የሚያሰኝ አግባብ የለም ብለናል።
ከስራም የተገለለው በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 24/1/ መሰረት ነው ብለናል።
በዚሁ መሰረት የፋ/ከ/ፍ/ቤት ለተጠሪ በስራ ላይ ቢቆይ ኖሮ ይከፈለው የነበረው ደሞዝ ከታህሣስ 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም እስከ ሰኔ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ድረስ ያለውን ይከፈለው ማለቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል። በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ውሣኔ
የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 26-09-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 56140 ጥቅምት 16 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
በዚህ ችልት በግራ ቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.