No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሰይፊ ናስር ቀረቡ ተጠሪ፡- የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍትህ እና ህግ ጉዲዮች ነ/ፈጅ ዓለም ቱፊ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አዋጅ ቁጥር 515/99 ‛ን“ መሰረት አድርጎ የቀረበን የዱሲኘሉን ክርክርንና ይህንኑ መሰረት አድርጎ የተሰጠውን የቅጣት ውሣኔ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፉ አመልካችን የዱስኘሉን ግድፈት ፈፅሟል በማለት ከስራ እንዱሰናበቱ የሰጡትን ውሣኔ በመቃወም አመልካች ለአዱስ አበባ ከተማ ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ይኸው ፍርድ ቤት ተጠሪ መስሪያ ቤት አመልካችን ከስራ ያሰናበተው በአዋጅ ቁጥር 515/99 እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት በወጣው ደንብ ቁጥር 77/94 መሰረት ጉዲዩ በዱስኘሉን ኮሚቴ ተጣርቶ የውሣኔ ሀሣብ ሳይቀርብ ከባድ የዱስኘሉን ግድፈት ተፈጽሟል በሚል ምክንያት ነው፣ ይህ ደግሞ ሥነ ስርዓቱን ያሟላ አይደለም በማለት ጉዲዩ በዱስኘሉን ኮሜቴ ከታዬና ከተጣራ በሁዋላ ተገቢውን ውሣኔ ሉያገኝ ይገባል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ መስሪያ ቤት ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ያቀረበ ሲሆን ይህ ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በሁዋላ የአስተዲደር ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የቢሮ ኃላፉ የሰጡትን ውሣኔ አፅንቶ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ይኸው ሰበር ሰሚ ችልት የከተማው ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን ውሣኔ በማሻሻል በፍሬ ጉዲዩ ላይ የቀረበውን የአሁኑ አመልካች ቅሬታ ተገቢነቱ ሳይመረመር የቢሮው ኃላፉ ውሣኔ መጽናቱ ስነ ሥርዓታዊ አይደለም በዚህ ረገድ የቀረበው ክርክር ተጣርቶ ተገቢው እንዱወሰን በማለት ጉዲዩን ለአዱስ አበባ ከተማ የሲቪል ሰርቪስ አስተዲደር ፍርድ ቤት መልሶለት ይኸው ፍርድ ቤት ጉዲዩን እንደገና ተመልክቶ የቢሮው ኃላፉ በአመልካች ላይ ያስተላለፊት ቅጣት ተገቢነት የላለው መሆኑን ዘርዝሮ አመልካች የሶስት ወር ደመወዝ ተቀጥተው ወደ ስራቸው እንዱመለሱ ሲል ወስኗል። ከዚህም በሁዋላ የአሁኑ ተጠሪ ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ አመልካች ከስራ እንዱሰናበቱ ተብል በተጠሪ መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፉ የተሰጠው ውሣኔ ሕጋዊ ነው በማለት የስር ፍርድ ቤት ቅጣቱን አስመልክቶ የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም በችልቱ ላይ የተሰየሙት ዳኞች ጉዲዩን ገለልተኛ ሁነን ለማየት አንችልም በማለት መዝገቡን ዘግተውታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የተመለከተው የይግባኝ ጊዜ ከአለፈ በሁዋላ ከመሆኑም በላይ በዋናው ጉዲይ ላይ የሰጠው ውሣኔም በሕጉ የተሰጠውን ስልጣን ያላገናዘበ በመሆኑ ውሣኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው ። አቤቱታው በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታመኑም ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ በፅሐፍ መልሱ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለበትም ሉጸና ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ከአላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ ይህ ሰበር ሰሚ ችልት በአንድ ጉዲይ የተሰጠውን ፍርድ ማረም የሚችለው በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ሲሰጥና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈጸሙ ሲረጋገጥ ነው። በተያዘው ጉዲይ የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩ ቀርቦለት ዋናውን ጉዲይ ሳይመለከት የቀረው ጉዲዩን ዲኞቹ ገለልተኛ ሁነው ሉመለከቱ አይችለም በሚል ምክንያት ነው። በመሆኑም የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በጉዲዩ ላይ የመጨረሻ ፍርድ ያልሰጠበት ቢሆንም ችልቱ ካለው የመሰረታዊ የሕግ ስህተት የማረም ስልጣን አኳያ እና ጉዲዩ ከዚህ በፉት ከወሰደው ጊዜ እንዱሁም ከጉዲዩ ባህርይ አንጻር ይህ የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልትም መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም ሥልጣኑ በመሆኑ ጉዲዩን መመልከቱ ተገቢ ሁኖ አግኝተናል።
በዚህ ችልት ምላሽ ማግኘት ያለበት የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ጉዲዩን የተመለከተው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ጠብቆ ቀርቦለት ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ሁኖ ተገኝቷል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ተመልክቶ ተገቢ ነው ያለውን ውሣኔ የሰጠው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሲቪል ሰርቪስ ኤጀንሲ አስተዲደር ፍርድ ቤት ሲሆን ይህ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ውሣኔ የሰጠው ሰኔ ዐ7 ቀን 2002 ዓ/ም ነው። ይህ ፍርድ ቤት በሚሰጠው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ወገን ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ማቅረብ እንደሚችል ፣ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜም ውሣኔ ከተሰጠበት ጊዜ ጀምሮ የሚታሰቡ ሰላሳ ቀናት መሆናቸውን የአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 76/2/ እና የአዱስ አበባ ከተማ የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 6/2000 አንቀጽ 77/2/ ድንጋጌዎች ያሳያለ። ከላይ እንደተጠቀሰው የአስተዲደር ፍርድ ቤቱ በጉዲዩ ላይ ውሣኔ የሰጠው ሰኔ ዐ7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም ሲሆን ለከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኙ የቀረበው ደግሞ ሐምል 21 ቀን 2002ዓ/ም ነው። የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ ይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ስለማለፊ የአዋጅ ቁጥር 515/99 አንቀጽ 76/2/ ን በመጥቀስ ያረጋገጠው ሲሆን በዚህ ረገድ አመልካች ያቀረቡትን ክርክር ውድቅ ያደረገው አዋጅ ቁጥር 515/99 ተፈጻሚነት የሚኖረው ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለሚቀርቡ ቅሬታዎች ነው፣ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኙን የሚያየው በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 43/3/ መሰረት ሁኖ የሚመራውም በ1958ቱ የፍትሒብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ነው፣ እንዱህ ከሆነ ደግሞ ተፈጻሚነት የሚኖረው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ስልሳ ቀናት ነው፣ አዋጅ ቁጥር 515/99 ለጉዲዩ ተፈፃሚነት አለው ቢባል እንኳ የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ያለፈበት ማመልከቻ ወደያውኑ ለአመልካቹ በመዝገብ ቤት ሹሙ እንደሚመለስለትና በአስር ቀናት ጊዜ ውስጥ የይግባኝ ማስፈቀጃ እንዱያቀርብ የሚደረግ በመሆኑ በመዝገብ ቤት ሹም ተከፍቶ ወደ ችልት የቀረበ የይግባኝ መዝገብ በችልት የሚታረም አይደለም የስነ ስርዓት ግድፈቱ በችልት ሉስተካከል የሚገባው አይደለም በሚለ ምክንያቶች ነው። ይሁን እንጂ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያላቸው ሕጎች አዋጅ ቁጥር 515/99 እና አዋጅ ቁጥር 6/2000 ሲሆኑ ጉዲዩ የሚመራበትን ሥርዓትም በእነዚህ ሕጎች የተመለከተው ነው። የስር ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 43/3/ መሰረት ጉዲዩን የማየት የስረ ነገር ስልጣን ቢኖረውም ከዚህ አዋጅ በሁዋላ የወጡት አዋጅ ቁጥር 515/99 እና 6/2000 ጉዲዩ የሚመራበትን ሥርዓት በግልጽ ዘርግተው ይገኛለ። እንዱህ ከሆነ በሕግ ተዋረዲዊ አቀማመጥ/ hierarchy of Laws / በሁዋላ የወጣ ሕግ ቀድሞ የወጣውን ሕግ በመቀደም ስራ ላይ የሚል መሆኑን ተቀባይነት ያለው የሕግ አተረጓጎም መርህ የሚያስገነዝበን ጉዲይ ነው። በመሆኑም የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ለጉዲዩ ተፈጻሚነት ያለው አዋጅ ቁጥር 361/95 አንቀጽ 43/3/ እና በፍትሒ ብሓር ስነ ሥርዓት ሕጉ የተመለከተው የይግባኝ ማቅራቢያ ጊዜ ነው በማለት የሰጠው ምክንያት ከሕግ አተረጓጎም መርህ አንፃር ሲታይ ሕጋዊ አይደለም። ስለሆነም ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያለው አዋጅ ቁጥር 515/99 እና አዋጅ ቁጥር 6/2000 ሲሆኑ እነዚህ አዋጆች በጉዲዩ ላይ ይግባኝ የሚቀርበው ውሣኔ በተሰጠ በሰላሳ ቀናት መሆኑን ይደነግጋለ። የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አዋጆቹ ለጉዲዩ ተፈጻሚነት አላቸው ቢባል እንኳ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ስር በተመለከተው ሁኔታ ችልት የሥነ ሥርዓት ግድፈቱን ሉያስተካክል የሚችለው አይደለም በማለት ደምድሟል። ይሁን እንጂ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ መሰረት ለአንድ ፍርድ ቤት መዝገብ ሹም የተሰጠው ሥልጣን ይግባኝ ማቅራቢያ ጊዜ ማለፍ አለማለፊን በመመልከት ይግባኝ መዝገቡ እንዱከፈት ማድረግ ሲሆን ይግባኙ ጊዜውን ጠብቆ ያልቀረበ ከሆነ ማመልከቻውን መመለስ፣ ማመልከቻው የተመለሰበት ወገን የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሕጋዊ ምክንያት ካለው ማስፈቀጃ አቤቱታውን በማቅረብ ይኸው ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለማቅረብ እንዱፈቀድለት ራሱን የቻለ አቤቱታ አቅርቦና ይህ መዝገብ ተከፍቶ ጉዲዩ ለችልት ቀርቦ ችልቱ የይግባኝ ማስፈቀጃውን በመመርመር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 325 እና 326 መሰረት ተገቢ ነው ያለውን ትእዛዝ የሚሰጥበት ነው። በመሆኑም የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 325 እና 326 ድንጋጌዎች ጋር አንድ ላይ ሲነበቡ የመዝገብ ቤት ሹም ጊዜው ያለፈበት ይግባኝ ለችልት እንዱቀርብ የመፈቀድ ስልጣን የላለው መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ፊይለ ተከፍቶ ቀርቦ ከሆነም ችልት ጉዲዩን መርምሮ ይግባኙ የቀረበው ጊዜው ከአለፈ በሁዋላ ነው በማለት መዝገቡን ከመዝጋት የሚከለክለው አይደለም። ስለሆነም የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 324/1/ ድንጋጌን ይዘቱንና መንፈሱና ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ ቁጥር 325 እና 326 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ጋር አዛምድ ሳይመለከት የመዝገብ ቤት ሹም የይግባኝ ጊዜ ያለፈበትን ይግባኝ መዝገብ ከፍቶ ከአቀረበ ችልቱ ሉያስተካክለው የሚችለው አይደለም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ ሕጋዊ መሰረት የላለው ሁኖ አግኝተናል። በአጠቃላይ ለጉዲዩ ቀጥተኛ ተፈጻሚነት ያላቸው የፋዳራል መንግስት ሰራተኞች አስተዲደር አዋጅ ቁጥር 515/99 ፣ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 6/2000 በመሆናቸውና በእነዚህ አዋጆች መሰረት በሚታይ ጉዲይ ላይ ውሣኔ ሲሰጥ ይግባኙ የሚቀርበው በሰላሳ ቀናት ጊዜ ውስጥ መሆኑ የተደነገገ በመሆኑና የይግባኝ ጊዜው ያለፈበት ሁኔታ በስርዓቱ መሰረት የማስፈቀጃ አቤቱታ ለችልት ቀርቦ የሚታይ ከሚሆን በስተቀር በመዝገብ ቤት ሹም የሚታይ ባለመሆኑ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የተሰጠውን ውሣኔ የይግባኝ ጊዜው አልፍበት እያለ ተቀብል በዋናው ጉዲይ ላይ ውሣኔ መስጠቱ መሰረታዊ የሆነ የስነ ስርዓት ሕግ ግድፈት በመፈፀም ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.