No summary available.
ግንቦት 30 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ዲሽን ባንክ አ.ማ - ነገረ ፈጅ ዓለማየሁ ገበየሁ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሀይለ ሽመልስ- ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/1996 “ን“ መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ የካቲት 01 ቀን 2002 ዓ/ም በተፃፈ የክስ ማመልከቻ ከሐምል 15 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ ተቀጥረዉ በመስራት ላይ ከቆዩ በኋላ አመልካች ድርጅት ከታህሳስ 28 ቀን 2002 ዓ/ም ያለአግባብ ከስራ አግደዋቸው ቆይቶ ከታገደበት ቀን ጀምሮ የተሰናበቱ መሆኑን ጥር 25 ቀን 2002 ዓ/ም በተፃፈ ደብቤ የገለፀላቸው መሆኑን ገልፀው ከህግ ውጭ የተከናወነ ስንብት በመሆኑ ወደ ስራ እንዱመለሱ እና ያልተከፈላቸው ደሞዝ ከኪሳራ ጋር እንዱከፍላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት ጠቀዋል። የአሁን አመልካች በክሱ በሰጠው መልስም ተጠሪ ባንኩን በተመለከተ ማንኛውንም መግለጫ የመስጠት ስልጣን ሳይኖራቸው በጋዜጣ የሰጡት አለታዊ መግለጫ በባንኩና በሰራተኞች ላይ መረብሽን፣በደንበኞች ላይ ደግሞ መደናገጥን፣ለወደፉቱ የባንኩ ደንበኞች ሉሆኑ የሚችለት ላይም ጥርጣሬን እና የህዝብ አመኔታን የሚያሳጣ በመሆኑ መሰናበታቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/1//ሸ/ መሰረት ባግባቡ ነዉ በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ተከራክረዋል።
የስር ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ ማስረጃዎችን በመመርመር አመልካች ለጉዲዩ ማስረጃዎችን ያለማቅረቡንና ጥር 25 ቀን 2002 ዓ/ም በተፃፈ የስንብት ደብዲቤ የገለፀላቸው ድርጊቶችም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/1/ስር ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት ከተጠቀሱት ህጋዊ ምክንያቶች ውስጥ የሚወድቁ አይደለም የሚለ ምክንያቶችን በመያዝ ስንብቱ ከህግ ውጭ የተከናወነ ነው ወደሚለው ድምዲሜ ደርሶ አመልካች ተጠሪን የስድስት ወር ደመወዝ እና በእገዲ ጊዜ ያልተከፈላቸው ደመወዝ ከፍሎቸው ወደ ስራቸው ሉመልስ ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋደራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ የካቲት 02 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፊት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረዋል። ይዘቱም በአጭሩ ተጠሪ በጋዜጣ ላይ የሰጡት መግለጫ ሀሰተኛ ሆኖ በባንኩ ክብርና እና ዝናው ላይ የተፈፀመ ሆኖ ይህም በባንኩ ንብረት ላይ ጉዲት መድረሱን የሚያረጋግጥ በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 27/1//ሸ ስር የሚወድቅ ሆኖ እያለ በበታች ፍርድ ቤቶች የታለፈው ያለአግባብ በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባል ተብል ተጠሪ ቀርበው ግራቀኙ በፁሁፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የአመልካችን የሰበር አቤቱታ አቤቱታው ከቀረበበት ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የስራ ውለ የተቋረጠው በህገወጥ መንገድ ነው ተብል መወሰኑ በአግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከመዝገቡ መገንዘብ የተቻለው የአሁኑ ተጠሪ ከስራ እንዱሰናበቱ የተደረገው ስለአመልካች ባንክ ጋዜጣዊ መግለጫ የመስጠት ሃላፉነት የላላቸው ከመሆኑም በላይ ሐሰተኛ የሆነ መግለጫ በመስጠት በባንኩ ሰራተኞች ላይ መደናገጥ፣በደንበኞቹ ላይ ጥርጣሬንና በህዝቡ አመኔታ እንዲይኖረው አድርገዋል በሚል ምክንያት መሆኑ ሲሆን ተጠሪ የሰጡት መግለጫ ሀሰተኛ ስለመሆኑ ሳይክደ ለስንብቱ ምክንያት ነው በማለት የሚከራክሩት በስንብት ደብዲቤ ጥር 25 ቀን 2002 ዓ/ም የተፃፈው ሳይሆን በሪፕርተር ጋዜጣ የካቲት 03 ቀን 2002 ዓ/ም ወጣ የተባለውን መግለጫ በሚል መሆኑን ተረድተናል። የስር ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው ተጠሪ የሰጡት ሀሰተኛ መግለጫ የለም በሚል ሳይሆን ሀሰተኛ መግለጫ መስጠታቸው መረጋገጡን ተቀብል ይኸው ድርጊት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/1//ሸ/ ስር አይወድቅም፣ በባንኩ ሰራተኞች ላይ መረበሽን፣በባንኩ ደንበኞች ላይ ደግሞ ጥርጣሬን መፈጠሩን አመልካች በማስረጃዎቹ አላስረዲም በሚል ነው።
እንግዱህ ለስራ ስንብቱ ምክንያትነት የተጠቀሰው የተጠሪ ስለባንኩ ሀሰተኛ መግለጫ በጋዜጣ መስጠትና ይኸውም ድርጊታቸው በባንኩ ሰራተኞችና ደንበኞች የፈጠረውንና ሉፈጥር የሚችለው ችግርን ነው። የስር ፍ/ቤትም የሀሰተኛ መግለጫ ፍሬ ጉዲይ በማስረጃ የተደገፈ መሆኑን ተገንዝቦ ምክንያቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ስር የሚወድቅ አይደለም ሲል ነው የስራ ስንብቱ ህገወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው። በርግጥ የስር ፍ/ቤቱ በስራ ስንብቱ ላይ የተመለከተው የተጠሪን ጥፊት ይዘቱን በተፃፈው መልክ ከተመለከትነው ጥፊቱ በአዋጁ መሰረት ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት ከሚያስችለ ምክንያቶች ውስጥ ሉካተት የማይችል መሆኑን መገንዘብ ይቻል ይሆናል። ይሁን እንጂ በተጠቃሹ አዋጅ ስር የተመለከቱት ምክንያቶች በክርክሩ ወቅት የሚረጋገጡ ፍሬ ጉዲዮችንና የአዋጁን አጠቃቀም አላማና አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎችን ይዘትና መንፈስ በመመርመር ሉተረጎም የሚችለ ስለመሆናቸው መገንዘብ አያዲግትም። አመልካች የሚከራከረው ተጠሪ የሰጠው ሀሰተኛ መግለጫ በባንኩ ስምና ክብር ላይ አለታዊ ተፅዕኖ ያለው ሆኖ በባንኩ ንብረት ላይ ጉዲት እንደደረሰ ሉቆጠር የሚገባው ነው በማለት ነው። ጉዲት ደረሰ የተባለውም የባንኩ መልካም ስም ጠፍቷል በሚልም ጭምር ሲሆን አመልካች ለዋቢነት የሚጠቅሰው ድንጋጌም በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀፅ 27/1//ሸ/ ስር የተመለከተውን ነው። በዚህ ድንጋጌ በአሰሪው ንብረት ወይም ከድርጅቱ ስራ ጋር በቀጥታ ግንኙነት ባለው ማናቸዉም ንብረት ላይ ሆነ ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ማድረስ ሰራተኛን ያለማስጠንቀቂያ ከስራ ለማሰናበት የሚያስችል ህጋዊ ምክንያት ነው። ንብረት ለሚለው ቃል በአዋጁ ስር የተመለከተ ትርጓሜ የለም። ይሁን እንጂ ከአዋጁ አላማና ከአሰሪው ድርጅት ባሀርይ እንዱሁም ከንብረት ህግ ፅንሰ ሀሳቦች ጋር በማዛመድ ለቃለ ትርጉም መስጠት ህጋዊነት ይኖረዋል። ምክንያቱም ንብረት ለሚለው ፅንሰ ሀሳብ ሁለንም የሚያስማማ ትርጉም መስጠት የሚቻል አይደለምና። በመሆኑም የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅን አጠቃላይ አላማም ሆነ አጠቃላይ የንብረት ህግ ፅንስ ሀሳቦች ባህርያት እንዱሁም በንግድ ህጉ ስለመልካም ስም(Good Will) የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ግንዛቤ ውስጥ ስናስገባ ንብረት ማለት ዋጋው ኢኮኖሚያዉ ጠቀሜታ ያለው እንዱሁም በአብዛኛው ሀብትነት ሉያዝ የሚችል ነገር መሆኑን ለመገንዘብ አስቸጋሪ አይሆንም። ዋጋው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ሆኖ በባለሀብትነት ሉያዝ የሚችል ነገር ላይ ሆን ብል ወይም በከባድ ቸልተኝነት ጉዲት ያደረሰ ሰራተኛ ከሆነ በአሰሪው ንብረት ላይ በህጉ አነጋገር ጉዲት አድርሷል ለማለት የማይቻልበት ምክንያት የለም።
እጃችን ወዲለዉ ጉዲይ ስንመለስ የስር ፍ/ቤቶች የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረጉት የተጠሪ አድራጎት ለአመልካች ዋጋው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባለው ነገር ላይ ጉዲት አላደረሰም የሚል ግልፅ ምክንያት በመያዝ ሳይሆን በሀሰተኛ መግለጫ ምክንያት በባንኩ ሰራተኞች ላይ መረበሽ በባንኩ ደንበኞች ላይ ደግሞ ጥርጣሬ ስለመድረሱ አመልካች ማስረጃ አላቀረቡም በሚል ምክንያት ነው። ይሁን እንጂ በአመልካች በኩል የቀረበው የፅሁፍ ማስረጃ የተጠሪን ጥፊቶች በግልፅ የሚያሳይ ከመሆኑም በላይ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡት ፍሬ ነገሮችም ተጠሪ በሰራተኞች መተዲደሪያ ደንብ አንቀፅ 21.6 መሰረት ሀሰተኛ ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የማይችለ መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን ሐሰተኛ መግለጫ በባንኩ መልካም ስም ላይ አለታዊ ተፅእኖ ሉኖረው አይችልም ልባል የሚችል አይደለም። አንድ ሰው ሀሳቡን የመግለፅ ህገመንግስታዊ መብት ያለው ቢሆንም ሀሰተኛ ቃል በመስጠት ግን በልላ ሰው መልካም ስምና ክብር ላይ ወዱያውኑ ወይም ወደ ፉት ጉዲት ሉያደርስ የሚችል ተግባር ሉፈፅም አይገባም። የባንክ ስራ በተለይ ሲታይም የህዝብ ጥቅም የበለጠ የሚንፀባረቅበት በመሆኑ መልካም ስም ሉጠበቅለት የሚገባው ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበት ድምዲሜ በክርክሩ ሂደት የተረጋገጡትን ፍሬ ነገሮች ከህጉ መንፈስ ጋር ያላገናዘበ በመሆኑ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ላላው የስር ፍ/ቤት የአመልካችን እርምጃ ህገ ወጥነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው አንድ ሰራተኛ ከስራ የሚታገደው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ/18 መሰረት ነው፣የአመልካች እርምጃ ግን ይህንኑ ድንጋጌ የተከተለ አይደለም በሚል ነው። ይሁን እንጂ አንድን ሰራተኛ ጥፊት ፈፅሟል የሚል አሰሪ ሰራተኛውን ከስራው አግድ ለማቆየት የሚችል መሆኑን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27/4/ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያሳይ በመሆኑ የስር ፍ/ቤት በዚህ ረገድ የደረሰበት ድምዲሜም የህግ መሰረት የላለው ነው። በአጠቃላይ የስር ፍ/ቤት በተጠሪ የስንብት ደብዲቤ ላይ የተገለፀውን ምክንያት እንዲለ በመውሰድ የደረሰበት ድምዲሜ አግባብነት ያለውን ድንጋጌ ባለመምረጥና አጠቃላይ ይዘቱንና መንፈሱን ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ሆኖ ተገኝቷል። በዚህም ምክንያት የሚከተለውን ወስነናል።
በፋደራል መጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ ሕዲር 06 ቀን 2003 ዓ/ም ተሰጥቶ በፋደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 25 ቀን 2003 በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ተጠሪን ከስራ ያሰናበተው በአግባቡ ነው ብለናል።
አመልካች ወጪና ኪሳራ የራሱን ይቻል ብለናል።
No topics extracted.