No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ፕስታ አግልግልት ድርጅት ነ/ፈጅ ማስረሻ በለጠ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ በዲሶ መልካቶ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ታይቶ የተወሰነውን ውሳኔ አፈፃፀም የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአዲማ ቱለ ወረዲ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪ በዚሁ ፍርድ ቤት ያቀረቡት የፍርድ ይፈፀምልኝ ጥያቄ በስር ፍርድ ቤት በመ/ ላይ ቀርቦ የተወሰነውን ውሳኔ መሰረት ያደረገ ነው። በዋናው ጉዲይ ላይ የአሁኑ ተጠሪ የስራ ውላቸው ያላግባብ የተቋረጠባቸው መሆኑን በመግለጽ ወደ ስራ እንዱመለሱ ወይም ተገቢ ክፍያዎች እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የአሁኑ አመልካች የአሁኑን ተጠሪን ወደ ስራ እንዱመለስ ወይም ተገቢ ክፍያዎችን እንዱከፍል ሲል ተወስኗል። እንዱፈፀም የቀረበው ውሳኔውም ይህ ሲሆን ዋናውን ፍርድ ተጠሪ ከአገኙና ከመፈፀሙ በፉት ግን ተጠሪ የመንግስት ገንዘብ አጉድለው ተገኝተዋል በሚል ምክንያት በእምነት ማጉደል ወንጀል ተከሰው ጥፊጽ በመፈጸሙ ጥፊተኝነታቸውም በፍርድ ተረጋግጦ በአንድ አመት ጽኑ እስራት እና በብር 1000.00(አንድ ሺህ) የገንዘብ መቀጮ እንዱቀጡ ተወስኖባቸዋል። ይህንኑ ቅጣት ጨርሰው ከወጡ በኋዋላ በአስሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት የተሰጠው ውሳኔ እንዱፈጸምላቸው የአፈፃፀም ማመልከቻ ሲያቀርቡም የአሁኑ አመልካች ተጠሪ በወንጀል ተከሰው ጥፊተኛ ተብለው ተረጋጋጦባቸው ቅጣቱን ጨርሰው ከወጡ በሁላ ሉፈጸምላቸው የሚገባ ፍርድ የለም በማለት እንደ ፍርደ የማይፈጽምበትን ምክንያት ቀርቦ አስረድቷል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ፍርደ የማይፈፀምበት ምክንያት የለም በማለት ተጠሪን አመልካች ወደስራው እንዱመልሰው ሲል ትእዛዝ ሰጥቷል። በዚህ ትእዛዝ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 377 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ትእዛዝ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ መጋቢት 01 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ትእዛዝ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ተጠሪ በእምነት ማጉደል ወንጀል ጥፊተኛ ተብለው ተገቢው ቅጣት ተላልፍ ቅጣቱን ጨርሰው ከወጡ በሁዋላ ቀድሞ የተሰጠውን ውሳኔ መሰረት በማድረግ ወደ ስራ የሚመለሱበት ምክንያት የለም በማለት ዘርዝረው ትእዛዙ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም የፍርድ አፈፃፀም ሂደቱ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ስር የተመለከተውን ከፍተኛ የይርጋ ጊዜ መሰረት ያደረገ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጓአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ መጥሪያ ተልኮላቸው ተጠሪ ቀርበው በዋናው ጉዲይ ላይ የተሰጠው ፍርድ ባልተለወጠበት ሁኔታ ፍርድ ሉፈጽም አይችልም ልባል የሚችልበት ምክንያት የላለ መሆኑንና አመልካች ከፈለገ በአማራጭ የተለያዩ ክፍያዎችን በመክፈል ሉያሰናብታቸው የሚገባ መሆኑን በመዘርዘር የሰበር አቤቱታው ተቀባይነት የለውም ሲለ ግንቦት 23 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ ማመልከቻ ተከራክረዋል። የአመልካች ነገር ፈጅም ግንቦት 26 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት የመልስ መልስ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የመንግስት ገንዘብ አጉድለው በመገኘታቸው በወንጀል ተፈርድባቸው የእስራት ጊዜውን አጠናቅቀው ከወጡ ከአንድ አመት በሁዋላ በአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት ቀደም ብል የተሰጠውን ውሳኔ ለማስፈጸም አቤቱታ አቅርበው የስር ፍርድ ቤት ፍርደ እንዲይፈፀም የሚከለክለው ነገር የለም በሚል ምክንያት አመልካች ተጠሪን ወደ ስራ እንዱመልሳቸው ትእዛዝ መስጠቱን ነው።
በመሰረቱ አንድ ፍርድ ስልጣን ባለው አካል እስካልተሻረ እና በሕጉ የተመለከተውን የይርጋ ጊዜ መሰረት አድርጏ ለአፈፃፀም እስከቀረበ ድረስ እንዱሁም የማይፈፀምበት ላላ ሕጋዊ ምክንያት እስከላለ ድረስ የማይፈፀምበት ምክንያት የላለ መሆኑን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉም ሆነ በላልች ተፈፃሚነት ባላቸው ሕጏች የተመለከተ ጉዲይ ነው። አፈፃፀሙ የሚመራበት ሁኔታም እንደጉዲዩ አግባብነት መታየት ያለበት ስለመሆኑ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በልላ አገላለጽ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው ልዩ ሕግ ካለ ተፈፃሚነት የሚኖረው ይኸው ልዩ ሕግ ነው። ጠቅላላ ሕግ ተፈፃሚነት የሚኖረው ጉዲዩን የሚገዛው ልዩ ሕግ በላለበት ሁኔታ ስለመሆኑ ተቀባይነት ያላቸው የሕግ አተረጓጏም መርሆዎች የሚሳዩት ጉዲይ ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ጉዲዩ መሰረት ያደረገው የአዋጅ ቁጥር 377/96 ‛ን“ ሲሆን ይህ ሕግ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚነሳን ክርክር የሚገዛ ነው። በዚህ ሕግ ውስጥ የተለያዩ የመብት ጥያቄዎች የሚቀርቡበት የዲኝነት አካልና የመብት ጥያቄዎች የሚቀርቡበት የጊዜ ገደብ ተመልክቷል። ሕጉ ግልጽ የሆነ የይርጋ ጊዜ ያልተቀመጠለት እና ምንጩ የአሰሪና ሰራተኛ የሆነ ማናቸውም የመብት ጥያቄ በአንድ አመት ጊዜ ውሰጥ እስካልቀረበ ድረስ የማይስተናገድ ስለመሆኑ በአንቀጽ 162 ስር አስቀምጧል። አዋጁ በግልጽ ላልተመለከቱ ጉዲዮች ከፍተኛውን የይርጋ ዘመን በተመለከተ አንድ አመት ስለመሆኑ ከማስቀመጡም በተጨማሪ በላልች አግባብነት ባላቸው ሕጏች ስር የተመለከቱት የይርጋ ጊዜያት ተፈፃሚ ሉሆኑ እንደሚችለ በአንቀጽ 162/5/ ድንጋጌ ስር አስፍሯል። በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ለሚቀርቡ ክርክሮች አግባብነት ካላቸው ሕጏች መካከል አንደ የፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ነው። ይህ ስነ ሥርአት ከያዛቸውና ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች አንደ ደግሞ በቁጥር 384 ስር የተመለከተው የአፈፃፀም ይርጋ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ፍርድ ለአፈፃፀም ላቀርብ የሚገባው በአስር አመት ጊዜ ውስጥ መሆኑ ተመልክቷል። በመሆኑም ሉነሳ የሚችለው ጥያቄ አንድ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ክርክር ሰሚ አካል የተሰጠ ውሳኔ ለአፈፃፀም ላቀርብ የሚገባው ውሣኔ ከተሰጠ በኋላ በስንት ጊዜ ውስጥ ነው የሚለው? ነው። አዋጅ ቁጥር 377/96 በዚህ ረገድ ያስቀመጠው ግልጽ ድንጋጌ የለም። ሆኖም ግን አዋጁ በግልጽ ባያስቀምጥም ተገቢውን የሕግ ትርጉም መስጠት የግድ የሚል ነው። እንዱህ በሆነ ጊዜ ተገቢውን የሕግ አተረጓጏም መንገድችን መከተል አግባብነት ይኖረዋል። ሕግ ሲተረጏምም ሕጉ ሉፈፀም የሚችል ውጤት እንዱኖረው በማድረግ ስለመሆኑም ጠቅላላ የሕግ አተረጓጏም ደንቦች የግድ የሚለት ነው። ከዚህ አንፃር የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ አይነተኛ ዓላማ ሲታይ የኢንደስትሪ ሰላምን በማስፈን አጠቃላይ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ለአገር ኢኮኖሚ አዎንታዊ ሚና መጫወት ስለመሆኑ በአዋጁ መግቢያ ላይ የተገለፀ ጉዲይ ነው። የሕጉ አይነተኛ አላማ ይህ ከሆነ ደግሞ በአዋጁ የተካተቱት ድንጋጌዎች ሉተረጏሙና ሉፈፀሙ የሚገባው ይህንኑ የሕጉን አላማ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። በዚህም መሰረት አንድ ሰራተኛ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርአት ሕጉ ስር በተመለከተው የአስር አመት የጊዜ ገደብ ውስጥ የአፈፃፀም መዝገብ ማስከፈት ይችላል ከተባለ አዋጅ ቁጥር 377/96 ሉያሳካ ያሰበውን ግብ ችግር ውስጥ የሚከተለው ይሆናል።
ሰራተኛው በጊዜውና በቦታው ተገኝቶ ስራውን ካልሰራ አሰሪው ምርትና ምርታማነትን ያሳድጋል ተብል አይገመትም። በመሆኑም ለጉዲዩ አግባብነት የሚኖረው በአዋጅ ቁጥር 377/96 ስር የተመለከተው ከፍተኛው የአንድ አመት የይርጋ ጊዜ ለአፈፃፀም ማመልከቻም ተፈፃሚ እንዱሆን ማድረጉ የአዋጁ አላማ ግድ የሚለው ጉዲይ ነው። አፈፃፀም የሚቀርብለት ፍርድ ቤትም የፍርድ ይፈጸምልኝ ጥያቄው በዚህ ጊዜ ውስጥ የቀረበ መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ የፍርድ ይፈጽምልኝ ጥያቄውን በአንድ ጊዜ ውስጥ ያለማቅረባቸው የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። ይርጋውን ለማቋረጥ የሚያስችል ሕጋዊ ምክንያት የነበራቸው ስለመሆኑ የሚያሳይ ሁኔታም የለም። በመሆኑም አዋጅ ቁጥር 377/96 ከአንድ አመት በላይ የረዘመ ክርክርን የማያስተናግድ ሁኖ እያለ ተጠሪ ይህንኑ ጊዜ ያሳለፈ ፍርድ እንዱፈፀምላቸው ያቀረቡት አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ማግኘቱ የአዋጅ ቁጥር 377/96 ‛ን“ አይነተኛ አላማና በዚሁ አዋጅ መሰረት የተወሰኑት ውሳኔዎች የፈጸሙበትን አግባብ ያላገናዘበ በመሆኑ አመልካች ተጠሪን ወደ ስራ እንዱመልሳቸው የተሰጠው ትእዛዝ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ተገኝቷል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዲሚ ቱለ ወረዲ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 0925 ጥር 03 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 18 ቀን 2002 ዓ.ም የጸናው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች እንዱፈፀምላቸው ያቀረቡት የአፈፃፀም ጥያቄ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 162/1/ መሰረት በአንድ አመት ይርጋ የታገደ ነው ብለናል።
አመልካች ተጠሪን ወደ ስራ እንዱመልስ ወይም በአማራጭ የተለያዩ ክፍያዎች ከፍል እንዱያሰናብት አይገደድም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ቤ/ኃ
የካቲት 10 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ አሉ መሐመድአመልካች፣ የኢትዩጵያ ፔልፔና ወረቀት አ/ማ ታፈሰ አበበ ቀረበተጠሪ፣ ዓብደልቃድር አደም ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሳውን የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው በአመልካች ፊብሪካ ለ38 /ሰላሳ ስምንት/ ዓመት ካገለገልኩ በኃላ ለጡረታ አራት /4/ ዓመት ሲቀረኝ በራሴ ፍላጎት ሥራውን የለቀቅሁ በመሆኑ የሥራ ስንብት ክፍያ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ነው አመልካችም በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ከሣሽ ሉሟላ የሚገባው ሁለ ተሟልቶለት ጡረታ የወጣ በመሆኑ የስንብት ክፍያ ሉከፈለው አይገባም። የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጁ አይፈቅድለትም በማለት ተከራክሮአል። ከዚህ በኃላ ፍ/ቤት ክርክሩን የመረመረ ሲሆን በመቀጠልም የአመልካችን ክርክር ውድቅ በማድረግ ተጠሪ የሥራ ስንብት ይከፈለው በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች ውሣኔውን በመቃወም ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ ከተሰማ በኃላ ፍ/ቤቱ ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ አፅንቶአል። በመጨረሻው የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልትም ውሣኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት አይደለም በማለት አቤቱታውን ሰርዞአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ጥቅምት 29 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው ለተጠሪ የሥራ ስንብት ክፍያ ይከፈለው በማለት የተሰጠው ውሣኔ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ 377/96ን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁ 494/98 በአንቀጽ 2 ከተመለከተው ድንጋጌ አንፃር ሉመረመር የሚገባው ነው በመባለ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ተጠሪ በራሱ ፍላጎት የሥራ ውለን ያቋረጠው /ከሥራ የተሰናበተው/ 38 /ሰላሳ ስምንት/ ዓመት ካገለገለ በኃላ እንዱሁም ዕድሜው 60 /ስድሳ/ ዓመት ሉሞላ 4 /አራት/ ዓመት ሲቀረው እንደሆነ አላከራከረም የሥራ ስንብት ክፍያ ሉከፈለኝ ይገባል የሚለው በእርግጥም በአሁኑ ጊዜ የጡረታ አበል አላገኝም /አይከፈለኝም/ በማለት ሳይሆን ሥራውን በራሴ ፍላጎት በመለቀቄ እና በሕጉ የተመለከተውን የመጨረሻ የጡረታ መውጫ ዕድሜ 60 ዓመት ስላልሞላኝ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጁ መሰረት የሥራ ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት አለኝ በማለት እንደሆነም ከክርክሩ ይዘት ተገንዝበናል አመልካች ደግሞ ተጠሪ ሥራውን የለቀቀው /የተሰናበተው/ ሉሟላለት የሚገባው ሁለ ተሟልቶለት በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ የጡረታ አበል እየተከፈለው ነው። የጡረታ አበል የሚያገኝ ሰራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያም እንዱከፈለው ሕጉ አያዝም ይልቁንም ሁለቱ ክፍያዎች በአንድ ጊዜ እንዲይከፈለ ሕጉ በግልፅ ይከለክላል በማለት ተከራክሮአል።
እንደምንመለከተው አከራከሪው ጭብጥ የሕግ ነጥብ በመሆኑ ሉፈታ የሚችለው አግባብ ባለው የሕጉ ድንጋጌ ነው። ክርክሩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሳ በመሆኑም በቅድሚያ መታየት ያለበት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁ. 377/96 ነው በዚህ አዋጅ ስለሥራ ስንብት ክፍያ በሚመለከት ተደንግጎ የሚገኘው በአንቀጽ 39 ሲሆን ይህ ድንጋጌ አዋጁን ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁ. 494/98 ተሻሽልአል። በዚህ ማሻሻያ አዋጅ አንቀጽ 2/ሰ/ እና /ሸ/ የተቀመጡት ድንጋጌዎች ተጣምረው ሲታዩ አንድ ከሥራው የተሰናበተ ሰራተኛ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚከፈለው በጡረታ ሕግ የተመለከተው መደበኛ የጡረታ ዕድሜ ላይ ደርሶ ከሥራው በሚገለልበት ጊዜ የፔሮቪደንት ፈንድ ሽፊን ወይም የጡረታ መብት የላለው ሲሆን ወይም ደግሞ ቢያንስ አምስት ዓመት አገልግል በሕመም ወይም በፈቃደ ሲለቅ /ሥራው ላይ የሚያስቆይ ከሥልጠና ጋር የተያያዘ የውል ግዳታ ሳይኖርበት የለቀቀ ሲሆን/ እንደሆነ ነው በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ሥራውን የለቀቀው በገዛ ፈቃደ ሲሆን እንደለቀቀም በጡረታ መብት ተጠቃሚ ሆኖአል። በመንግስት ሰራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁ. 345/95 አንቀጽ 13/3/ እንደተመለከተው ቢንያስ ሃያ አምስት ዓመት ያገለገለ የመከላከያ ሰራዊት አባል ያልሆነ የመንግስት ሰራተኛ በራሱ ፈቃድ አገልግልት ካቋረጠ የጡረታ መውጫ ዕድሜው ሉደርስ አምስት ዓመት ከሚቀረው ጊዜ ጀምሮ እስከ ዕድሜ ልኩ የአገልግልት ጡረታ አበል ይከፈለዋል። ተጠሪ ሥራውን በራሱ ፈቃድ የለቀቀው 60 ዓመት ሉሞላው 4 ዓመት ሲቀረው በመሆኑ በዚህ ሕግ መሰረት አበለን እያገኘ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦአል።
ከፍ ሲል በዝርዝር እንዲመለከትነው የጡረታ አበል እና የሥራ ስንብት ክፍያ አንድ ላይ እንዱከፍለ ሕጉ አልፈቀድም። ሕጉ ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ደግሞ ከሕጉ መውጣት የሚቻል አይሆንም። የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ እንደምናየው ሕጉን መሰረት ያደረገ አይደለም። ይልቁንም ሕጉን በግልጽ በሚቃረን መልክ የተሰጠ ሆኖ ነው ያገኘነው። ከዚህ የተነሳም አቤቱታው የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የአዲማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 11 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ የምሰራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥቅምት 17 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በመ. ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽረዋል፡
ተጠሪ የሥራ ስንብት ክፍያ የሚያገኝበት የሕግ አግባብ የለም ብለናል።
ግራቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ። መዝገቡ ተዘግቶአል። ይመለስ።
ም.አ
No topics extracted.