No summary available.
ግንቦት 1 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን - አንበሴ መኯንን /ነገረ ፈጅ/ ቀረበ ተጠሪ፡- አያላው ሕብስት ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሣውን የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ነው። ተጠሪ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው ሚያዝያ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ሥራ ላይ በዋለው መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ መሰረት በተደረገው ምደባ ከደረጃ 11 ወደ ደረጃ 14 አድጌ እንድሰራ የተደረገ ቢሆንም ለቦታው የተመደበው ደመወዝ ግን አልተከፈለኝም በማለት ነው። በዚህ መሰረትም ያለአግባብ ሳይከፈለኝ ቀርቶአል የሚለውን የሁለት እርከን ጭማሪ ምደባው ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ ታስቦ እንዱከፍለው ይወሰንለት ዘንድ ጠይቆአል። አመልካች ለቀረበበት ክስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የሥረ ነገር ክርክር አቅርቦአል። በሥረ ነገር ረገድ ያቀረበው ክርክር ከሣሽ ደረጃውን ያገኘው በመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ አጠቃላይ ምደባ እንጂ በእድገት አይደለም። እድገት የሚሰጠው ወይም የሚገኘው በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 11 መሰረት ነው። በዚህ አግባብ የተሰጠ የደረጃ እድገት ስለላለ ክሱ ተቀባይነት ሉያገኝ አይገባም የሚል እንደሆነ ከመዝገቡ ተመልክተናል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤትም የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከመረመረ በኋላ፣ የአመልካችን ክርክር በመቀበል የተጠሪን ጥያቄ ውድቅ አድርጎአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ፍ/ቤቱ ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ በመሻር ተጠሪ የጠየቀው የሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይሰጠው በማለት ወስኖአል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ጥር 27 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው ተጠሪ የጠየቀው የሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ የሕግ መሰረት ያለው ነው ወይ? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ይህን ጭብጥ ግራቀኝ ወገኖች ካሰሙት ክርክር፣ አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ የተደረገውን የግራ ቀኝ ወገኖች ክርክር እና የተሰጡትን ውሳኔዎች በዝርዝር ተመልከተናል። ከዚህም መገንዘብ የቻልነው ተጠሪ ተመድቤበታለሁ የሚለው በደረጃ 14 የሚታወቀው (የተሰየመው) የሥራ መደብ በኮርፕሬሽኑ (አመልካች) ባለው የእድገት አሰጣጥ ሥርዓት እና ሂደት መሰረት የተገኘ አለመሆኑ በፍሬ ነገር መረጋገጡን ነው። በእርግጥ ኮርፕሬሽኑ አጠቃላይ የሆነ መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ በማካሄድ ከሥራ ሂደት ለውጡ መካሄድ በፉት የነበረው አደረጃጀትና የሥራ መደቦች ስያሜ ተለውጠዋል። ይህ ደግሞ የኮርፕሬሽኑ የሥራ አደረጃጀትን በተመለከተ የተደረገ አጠቃላይ ለውጥ እንጂ ሰራተኞችን ለማሳደግ (በእድገት ለማስቀመጥ) በሚል የተደረገ ነው ወደሚል መደምደሚያ የሚያደርስ ነው ተብል የሚወሰድ አይደለም። በግልጽ እንደሚታወቀው የደረጃ እድገት ሉገኝ የሚችለው እራሱን በቻለ የአሰራር ሥርዓት እና ደንብ መሰረት ነው። በመሆኑም መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ማካሄድ እና የደረጃ እድገት መሰጠት ወይም አሰጣጥ በዓላማም ሆነ በውጤት ረገድ የተለየዩ የየራሳቸውን ግብ ይዘው የሚነሱ እንደሆኑ መገንዘቡ ተገቢ ነው።
በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው በአመልካች ኮርፕሬሽን የእድገት አሰጣጥ ሥርዓት እና ደንብ መሰረት ተጠሪ የደረጃ እድገት አግኝቶአል አልተባለም። የደመወዝ ጭማሪ ሉገኝ የሚችለው በእድገት ወይም አሰሪው የደመወዝ ጭማሪ ማድረግ የሚችልበት አግባብ ኖሮት ሲጨምር ነው።
ተጠሪ የጠየቀው የሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ እንዱያገኝ በፍ/ቤት ሉወሰን የሚችለውም ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ አንደ ተሟልቶ ሲገኝ ነው። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሁለት እርከን ደመወዝ ጭማሪ ሉያሰጥ የሚችል የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር መሰረት አልነበረውም። ሲጠቃለል ተጠሪ የደመወዝ ጭማሪ ይሰጠኝ በማለት ያቀረበው ጥያቄ የህግ መሰረት ያለው አይደለም። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ጥር 12 ቀን 2003 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽሮአል።
ተጠሪ ያቀረበው የሁለት እርከን የደመወዝ ጭማሪ ይሰጠኝ ጥያቄ የሕግ መሰረት የለውም ብለናል። በዚህ መሰረትም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.
ግንቦት 30 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቶአል።
No topics extracted.