No summary available.
ግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- የኦሮሚያ መንገድች ባለሥልጣን ነ/ፈጅ ሰላማዊት ኃይለ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ አቡ ጏበና ከጠበቃቸው ከአቶ ተካልኝ ነጋሣ ጋር ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በአሁኑ የሰበር ተጠሪ አቅራቢነት ለሥር ወረዲ ፍ/ቤት ነሐሴ 27 ቀን 1999 ዓ/ም የቀረበው ክስ በተከሣሽ /በአሁኑ አመልካች / መ/ቤት ከ1989 እስከ የካቲት 1999 ዓ/ም በተለያዩ የሥራ መደቦች በወር ብር 211ዐ ደመወዝ እየተከፈለኝ ከቆየሁ በኋላ ተከሣሹ ከሥራ ሲያስናበተኝ የአገልግልት ካሣ እና የዓመት ዕረፍት በገንዘብ ተለውጦ ብር 13,187.5ዐ ካሰበልኝ በኋላ ከዚሁ ገንዘብ ውስጥ ታክስ ብር 2,203.87 ከቀነሰ በኋላ በሥልጣኑ ለት/ቤት የከፈልኩት ነው በማለት ብር 6,792.57 ቆርጦብኝ ብር 4,191.04 ብቻ ከፍልኛል። የከፈለኝን ገንዘብም ቢሆን መክፈል ከሚገባው ጊዜ 2 ወር በማዘግየት የሚያዝያ ወር 1999 በመሆኑ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 337/96 በአንቀጽ 36 በተደነገገው መሰረት በ7 ቀን ውስጥ አልከፈለም።
የት/ቤት ክፍያም ቢሆን በህብረት ስምምነታችን አንቀጽ 25 ከ12ኛ ክፍል በላይ ለሆነ ትምህርት የት/ቤት ክፍያ ተከሣሽ መ/ቤት 5ዐ% እንደሚከፍል ተገልጿል። በመሆኑም ተከሣሽ መ/ቤት ያለ አግባብ የቆረጠብኝ ገንዘብና ክፍያ ባዘገየበት የ3 ወር ደመወዜን እንዱከፍለኝ ይወሰንበት የሚል ነው።
ተከሳሹም በነገረ ፈጁ አማካይነት በሰጠው መልስ ከሳሽ ለ11 ዓመት አገልግያለሁ የሚለው ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም ከሣሽ ከመስከረም 1 ቀን 1989 እስከ ሰኔ 3ዐ ቀን 1992 ድረስ የመንግስት ሰራተኞች አስተዲደር ሰራተኛ ነበር። የመንግስት ሰራተኛ ከሆነ ደግሞ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ 377/96 ጥቅማጥቅም ማግኘት አይችልም። ከሣሽ በተከሳሽ መ/ቤት የተቀጠረው ከሐምል 1 ቀን 1992 ጀምሮ ስለሆነ የአገልግልት ካሣ ማግኘት ያለበት ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ ነው። ከሣሽ በየጊዜው የትምህርት ቤት ክፍያ እየጠየቀ ተከሳሽ መ/ቤት ሲከፍል የቆየ በመሆኑ በመካከላችን ውል የለም ሲል ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም። ከዚህ በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/ለ/ ሥር የተጠቀሰውን ግዳታ አልተወጣም በማለት የከሣሽ ክስ ውድቅ እንዱደረግ ጠይቋል።
የሥር ወረዲ ፍ/ቤትም ዕዲን አንድ ሰራተኛ ከሚያገኘው የአገልግልት ካሣ ማቻቻል አይቻልም። ተከሣሽ አለኝ የሚለው መብት ካለ ህጉ በሚፈቅደው መሰረት መጠየቅ እንጂ ከደመወዙ ጋር ተያይዞ የሚገኝ ነገር ላይ ማቻቻያ ላደረግ አይገባም። ይህ ሆኖ ሣለ ተከሣሽ ከከሣሽ ደመወዝ መቁረጡ በፍትሀብሓር ህግ ቁጥር 1833 /11/ የተደነገገውን የሚፃረር ነው በማለት ተከሣሽ ከከሣሽ የቆረጠውን ገንዘብ ብር 6,792.57 ክፍያ ለዘገየበት የ3 ወር ደመወዝና ኪሣራ ብር 500 እንዱሁም የጠበቃ አበል 1ዐ% እንዱከፍል ወስኗል።
ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት በበኩለ ይግባኝ ባይ /የሥር ተከሣሽ/ የ11 ዓመት የአገልግልት ካሣ ለመልስ ሰጪው ከከፈለ በኋላ የ11 ዓመት አገልግልት በተከሣሽ መ/ቤት የለውም ሲል የተከራከረው ያለአግባብ ነው፤ ይግባኝ ባይ መልስ ሰጪውን ያስተማረ ቢሆንም ምን ያህል እንደሚያገለግል የተማረው መቼ እንደሆነና ግዳታውን ተወጥቷል የሚባለው መቼ ነው የሚለትን ነጥቦች ያላስረዲ በመሆኑ በሥር ፍ/ቤት ውሣኔ ላይ የሚነቀፍ ነገር የለም በሚል ውሣኔውን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/348/1/ መሰረት አጽንቷል።
የአሁኑ የሰበር አመልካች ለሥር የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ሲል በማመልከቱ የሥር ሰበር ሰሚው ችልትም የግራቀኙን ወገኖች ካከራከረ በኋላ ከአገልግልት ካሣ ክፍያ ውስጥ ለትምህርት የተከፈለውን በሚመለከት ተመላሽ የሚደረግ ስለመሆኑ ውል መኖር አለበት። ውል በላለበት አስተማርኩ በሚል ብቻ ከአገልግልት ካሣ ቆርጦ ማስቀረት ተቀባይነት የለውም። ክፍያ ለዘገየበት አመልካች ያመነውን ከፍል ያላመነውን ያልከፈለ ስለሆነ በክፈ ሀሳብ ተጠሪን ለመጉዲት አዘግይቷል ለማለት አይቻልም በማለት አመልካች ለተጠሪ የ3 ወር ደመወዝ መክፈል የለበትም ሲል የሥር ፍ/ቤት ውሣኔን በማሻሻል ወስኗል።
በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ቅር የተሰኘው የሰበር አመልካችም ለዚህ ችልት ባቀረበው ቅሬታ ተጠሪው ከመስከረም ዐ1 ቀን 1989 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ሰኔ ወር 1992 ዓ/ም ድረስ በአመልካች መ/ቤት ያገለገለው በአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረት ሳይሆን በመንግስት ሰራተኞች አስተዲደር ህግ በመሆኑ የሶስት ዓመት ከአሥር ወር የአገልግልት ክፍያ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ሉከፈለው አይገባም። ተጠሪው ሥራውን በገዛ ፈቃደ የለቀቀው የ2ኛ ዱግሪውን ትምህርት መንግስት እየከፈለ ትምህርቱን እንዲጠናቀቅ የሚፈለግበትን አገልግልት ሳይፈጽም በመሆኑ በተሻሻለው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/2/ መሰረትና አንቀጽ 39/ሸ/ የውል ግዳታ ስላለበት የሚከፈለው የአገልግልት ክፍያ የለም፣ ገንዘቡም ለመንግስት ተቆርጦ ገቢ መደረጉ ተገቢ ነው። ምንም ዓይነት ስምምነት ከአመልካች ጋር የለኝም በሚል ያቀረበው ክርክርም ቢሆን የህብረት ስምምነት አንቀጽ 26 በግልጽ የተቀመጠ በመሆኑ ባለመፈረሙ ብቻ ግዳታውን የሚያስቀርለት አይሆንም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሣኔ እስከአሻሽለው ድረስ የጠበቃ አበል 1ዐ% እና ኪሣራ ብር 5ዐዐ አሻሽል መወሰን አሉያም መሰረዝ ይገባው ነበር በማለት ከመስከረም 1 ቀን 1989 - ሰኔ 3ዐ ቀን 1992 ያለው የ3 ዓመት ከ1ዐ ወር የአገልግልት ካሣ አመልካች ለተጠሪው ይከፍላል የተባለው እንዱሰረዝ አመልካች ከተጠሪው የአገልግልት ካሣ ውስጥ ለትመህርት የከፈለውን ቆርጦ ማስቀረቱ ያለአግባብ ነው የተባለው ተሽሮ ገንዘቡ ለአመልካች ገቢ አንዱሆን እንዱወሰን፣ አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል የተወሰነበት የጠበቃ አበልና ኪሣራ እንዱሰረዝ ጠይቋል።
አመልካች ላቀረበው የሰበር ቅሬታ ተጠሪው በሰጠው መልስ ከመስከረም ወር 1989 ዓ/ም ጀምሮ ያለውን የአገልግልት ካሣ አስቦ የከፈለኝ ራሱ የአሁኑ አመልካች ስለሆነ ተጠሪ ክስ ከመሰረትኩበት በኋላ የአገልግልት ካሣው የተከፈለው በስህተት ነው ብልም ከመስከረም ዐ1 ቀን 1989 ዓ/ም ጀምሮ ሰራተኛ ስለመሆኔ በሥር ፍ/ቤት በቀረበው የፅሁፍ ማስረጃ ተረጋግጧል።
የህብረት ስምምነት አንቀጽ 26/2/ ከትምህርትና ሥልጠና ጋር በተያያዘ የውል ግዳታ መግባት እንደሚያስፈልግ ይናገራል። ተጠሪም የውል ግዳታ ገብቼ የፈረምኩት ሰነድ የለም። አመልካችም በማስረጃነት ያቀረበው ሰነድ የለም። አዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 39/1/ሸ/ ከሥልጠና ጋር በተያያዘ ለአሰሪው የውል ግዳታ ሳይኖርበት ሥራውን በገዛ ፈቃደ ሰራተኛው ሲለቅ የአገልግልት ካሣ እንደሚከፈለው ይደነግጋል። በመሆኑም የሰበር ተጠሪ ከአሰሪው መ/ቤት ጋር የገባሁት የትምህርት ውል ስለላለ የአገልግልት ካሣ ከማግኘት የሚከለክለኝ ነገር የለም። ስለሆነም በሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔ ላይ የተፈጸመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም በማለት ተከራክሯል።
የግራቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ እንደተገለፀው የቀረበ ሲሆን እኛም በሥር የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ ለተጠሪ ሉከፈለው ይገባል በሚል በተወሰነው ገንዘብ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ወይስ አልተፈፀመም የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለው በአገልግልት ካሣ፣ በጠበቃ አበል እና በኪሣራ ገንዘብ አከፊፈል ነው።
የአገልግልት ካሣን በሚመለከት ግራ ቀኙን የሚያከራክራቸው ጠቅላላ የአገልግልት ዘመን አቆጣጠርና የአግልግልት ካሣ ለተጠሪው ይገባል በማለት አመልካች ከወሰነው ገንዘብ ውስጥ አመልካች ለተጠሪው የትምህርት ቤት ክፍያ ፈጽሜአለሁ በማለት የቀነሰው ገንዘብ ነው።
ተጠሪው ከመስከረም 1989 እስከ የካቲት 1999 ዓ/ም ለአሥራ አንድ ዓመት በአመልካች መ/ቤት ማገልገለን በመጥቀስ ሲከራከር አመልካች ግን ተጠሪው ከ1989 መስከረም ወር ጀምሮ እስከ 1992 ሰኔ ወር ድረስ ተጠሪው በአዋጅ ቁጥር 377/96 የማይተዲደርና የመንግስት ሰራተኞች አስተዲደር ሰራተኛ ነበር በማለት ተከራክሯል። ከዚህ የተነሣም የ3 ዓመት ከ 1ዐ ወር የአገልግልት ካሣ አይገባውም ብሎል። ይሁን እንጂ ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደሚቻለው አመልካች መ/ቤት ቀደም ሲል በመንግስት ሰራተኞች አስተዲደር አዋጅ የሚተዲደር የነበረና ከዚያም በአዋጅ ቁ. 377/96 ማለትም ስለ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ በወጣው አዋጅ እንዱተዲደር መደረጉን ነው። ተጠሪም ቢሆን ቀደም ሲል በአመልካች መ/ቤት የመንግስት ሰራተኛ የነበረ ሲሆን አመልካች መ/ቤት በአዋጅ ቁጥር 377/96 እንዱተዲደር ሲደረግ ተጠሪውም በተመሳሳይ ሁኔታ በተጠቀሰው አዋጅ የሰራተኛን ትርጉም በማሟላት በአመልካች መ/ቤት ሲሰራ ቆይቷል። አመልካች መ/ቤትም ተጠሪው ለ11 ዓመት ያህል በአመልካች መ/ቤት ማገልገለን በማመን የ11 ዓመት የአገልግለት ካሣ በማስላት አጠቃላይ የሚከፈለው የአገልግልት ካሣ መጠን ከታወቀ በኋላ ለትምህርት ቤት የከፈለውን በመቀነሥ ለራሱ አስቀርቷል። ይሁን እንጂ አሰሪው ማለትም ያሁን አመልካች የተጠሪው የአገልግልት ዘመን 11 ዓመት መሆኑን ተቀብል ምን ያህል የካሣ መጠን እንደሚከፈለው ካረጋገጠ በኋላ በፍ/ቤት በተጠሪ ከሳሽነት ክስ ሲቀርብ የተጠሪውን ቀደም ሲል የመንግስት ሰራተኛ ነበር በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የአገልግልት ካሣ ማግኘት ያለበት ከሐምል 1992 ጀምሮ ነው በማለት ያቀረበው ክርክር ህጋዊ ውጤት ያለው ሆኖ አላገኘንም። ስለሆነም አመልካች ተጠሪን የአገልግልት ዘመን በሁለት በመክፈል ካሣ ሉከፈለው የሚገባ ው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 መተዲደር ከጀመረበት ጊዜ ነው በማለት ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍ/ቤት ያልተቀበለው በአግባቡ ነው። በመሆኑም ተጠሪው 11 ዓመት አገልግልት አለው ተብል በዚሁ መጠን የ11 ዓመት የአገልግልት ካሣ ሉከፈለው አይገባም በማለት አመልካች ያቀረበውን ክርክር የሥር ፍ/ቤት ውድቅ በማድረጉ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለም። ከዚህ ከካሣ አከፊፈል ጋር ተያይዞ የሚነሣው አመልካች ለተጠሪው የሚገባውን የካሣ መጠን በስላት ካረጋገጠ በኋላ የተጠሪው 2ኛ ዱግሪ ሲማር አመልካች የት/ቤት ክፍያ ከፍሎል በማለት ብር 6,792.57 ከካሣው ገንዘብ መቁረጡ ነው።፡ አመልካች ለት/ቤት የከፈለውን ገንዘብ የቀነሰው ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ በአመልካች መ/ቤት ማገልገል ሲገባው ግዳታውን አልተወጣም። ስለሆነም አመልካች ለት/ቤት ያወጣውን ወጪ ከተጠሪው ለመቀበል በአዋጅ ቁጥር 494/98 አንቀጽ 2/2/ሸ/ መሰረት መብት አለው ምክንያቱም በአመልካችና ተጠሪ መካከል የውል ግዳታ አለ የሚል ነው። የውል ግዳታውም ሉመሰረት የቻለው ተጠሪው የትምህርት ቤት ክፍያ እንዱከፍልለት በየጊዜው እየጠየቀ አመልካችም ይከፍልለት ነበር በማለት ነው። ሆኖም ከአመልካች አለ የሚለውን የውል ግዳታ ተጠሪው የፈረምኩት ሰነድ የለም በማለት ይከራከራል።
እዚህ ላይ ምላሽ ማግኘት ያለበት ነጥብ በአመልካችና በተጠሪው መካከል የትምህርት ቤት ክፍያን በሚመለከት ውል አለ ወይስ የለም? የሚለውን ነጥብ ሳይሆን አመልካች ለተጠሪው ከሚገባው የአገልግልት ካሣ የትምህርት ቤት ክፍያ ቆርጦ ማስቀረት ይችላል ወይስ አይችልም?
የሚለውን ነጥብ ነው።
ከዚህ በላይ ከፍ ተብል እንደተገለፀው አመልካችና ተጠሪ የሚተዲደሩት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ሲሆን የግራ ቀኙን ተከራካሪዎች በአዋጁ የተቀመጡትን መብትና ግዳታ ማክበር ይጠበቅባቸዋል ። በአዋጁ ከተጠቀሱት መብቶች አንደ የሥራ ውል ሲቋረጥ ሰራተኛው ደመወዙንና ከደመወዙ ጋር የተያያዙትን ክፍያዎችን በህጉ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖም ክፍያው አከራካሪ ሆኖ ከተገኘ የሕጉን አካሄድ መከተል የግድ ይላል። በዚህ በተያዘው ጉዲይ የመንግስት ግብር ተቀንሶ ተጠሪው የአገልግልት ካሣ ማግኘት ያለበት ብር 10,983.63 መሆኑን ሲገልጽ ይኸንኑ የገንዘብ መጠን አመልካችም ትክክል መሆኑን ያምናል። ይሁን እንጂ የት/ቤት ክፍያ ብር 6,792.57 መቀነሱ አግባብ ነው ይላል። በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 የደመወዝ ቅነሣን በሚመለከት በአንቀጽ 59 የተደነገገ ሲሆን ይኸው አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ /1/ ደመወዝ የሚቀነሰው በህግ በህብረት ስምምነት ወይም በሥራ ደንብ በተወሰነው ወይም በፍ/ቤት ትዕዛዝ መሰረት ካልሆነ ወይም ሰራተኛው በጽሁፍ ካልተስማማ አሰሪው ከሰራተኛው መቀነሥ እንደማይችል ወይም በዕዲ ሉይዝ ወይም ሉያቻችል እንደማይችል ተደንግጓል። የአገልግልት ካሣም ቢሆን ለዕዲ የሚያዝ ወይም የሚቀነሥ ከሆነም በተጠቀሰው የህግ አንቀጽ መሰረት መቀነስ ወይም ሉያዝ ከሚችል ውጪ አሰሪ በራሱ ውሣኔ ሉቀንስ ሉይዝ ወይም ለዕዲ እንዱቻቻል ማድረግ አይችልም።
በመሆኑም የሥር ፍ/ቤት የሰበር አመልካች ቆርጦ ያስቀረው የአገልግልት ካሣ ገንዘብ ለተጠሪ እንዱመልስ በሰጠው ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት አላገኘንም።
ላላው አመልካች እንደመሰረታዊ የህግ ስህተት የጠቀሰው የጠበቃ አበል 1ዐ% አመልካች ለተጠሪ እንዱከፍል መወሰኑ ነው። በዚህ ነጥብ ላይ አመልካች ተጠሪው ክርክር ያካሄደው በግለ ስለመሆኑ አልተከራከረም። ነገር ግን 1ዐ% ለጠበቃው አበል መወሰኑ አለአግባብ መሆኑን ገልጾ ተከራከሯል። ጠበቃው ሙያዊ አገልግልት መስጠቱ እስካልተካደ ድረስ ደግሞ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 57/1992 አንቀጽ 42 በተደነገገው መሰረት ተገቢና ሚዛናዊ የሆነ የአገልግልት ክፍያ ማግኘት ይኖርበታል። ተገቢና ሚዛናዊ ክፍያ ነው የሚባለው ደግሞ በተጠቀሰው የህግ ቁጥር ከንዐስ ቁጥር 1-8 የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች መሰረት በማድረግ የተወሰነ ሆኖ ሲገኝ ነው።
አመልካች ግን የሥር ፍ/ቤት 1ዐ% የጠበቃ አበል ሲወስን በደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 42 ሥር የተዘረዘሩ መመዘኛዎች የተጣሱ ስለመሆናቸው ያቀረበው የህግ ክርክር የለም። ይህ ችልትም የቀረበውን የጠበቃ አበል ቅሬታ ከተጠቀሰው ደንብ ቁጥር 57/92 አንቀጽ 42 እና ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 462ና 463 ድንጋጌ ጋር እንዲገናዘበው በደንቡ የዘረዘሩት መመዘኛዎች የተጣሱ ስለመሆናቸው አመላካች የሚሆን ነገር አላገኘም። በመሆኑም በጠበቃ አበል አወሣሰን ላይ በሥር ፍ/ቤት ውሣኔ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ሥህተት የለም።
አመልካች ያቀረበው ላላው ክርክር የሥር ሰበር ሰሚ ችልት የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ በማሻሻል እስከወሰነ ድረስ የብር 500 /አምስት መቶ / ኪሣራ መቀነስ ወይም መሰረዝ ነበረበት የሚል ሲሆን ይህ ችልት ተጠሪ በክርክር ወቅት ከብር 500(አምስት መቶ) ያላነሰ ኪሣራ እንደሚደርስበት ያምናል። የኪሣራው መጠን ከዚህ ከተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ያንሣል ቢባል እንኳል የአመልካችን ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙን በጎላ መልኩ የሚጉዲ አይደለም። በልላ በኩል የሥር ሰበር ሰሚ ችልት የሥር ፍ/ቤቶችን ውሣኔ አሻሽል በመወሰኑ ብቻ ኪሣራ መቀነሥ አለበት ወይም ሙለ በሙለ መሰረዝ አለበት ለማለት ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም ። በመሆኑም የሥር ሰበር ሰሚው ችልት የሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔን አሻሽል ሲወስን ኪሣራውን ግን በማጽናቱ የተጣሰ ህግ የለም። ስለሆነም በኪሣራ አወሣሰን ረገድም የሥር ፍ/ቤት የፈፀመው መሰረታዊ የህግ ስህተት አላገኘንም።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በቀን 14/10/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል፣ በውሳኔው የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የለም ተብሎል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ።
ከዚህ በፉት በዚህ ጉዲይ ተሰጥቶ የነበረው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ ይሁን ።፡
No topics extracted.