No summary available.
የካቲት 22 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ መልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገብረሥላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዩጵያ ብሓራዊ ባንክ ሰራተኛ ማህበር - አቤነዘር በወንጌል ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስትር የሕግ ተወካይ አቶ ፈቃደ ደጀኔ ቀረቡ።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረበ ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ተቋቁሞና ሕጋዊ ዕውቅና እና ሕልውና አግኝቶ የኖረ ማህበር መሆኑን ገልፆ ከታህሣሥ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ጀምሮ የብሓራዊ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 377/96 እንደማይተዲደርና በልዩ ሕግ የሚታዲደር መሆኑ በሕግ የተደነገገ በመሆኑ ማሕበሩ እንዱፈርስ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክቷል። አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ዓላማዬን ማሣካት አልቻልኩም ብል የመፍረስ ጥያቄ ማቅረብ የማሕበሩ እንጂ የከሳሽ (ተጠሪ) መብት አይደለም ማሕበሩ የሚፈርስበት ምክንያት የለም የሚል ክርክር አቅርቧል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ ሰራተኛው ከአዋጅ ቁጥር 377/96 ውጭ በተለየ ደንብ መታዲደሩ ማሕበሩን ለማፍረስ ያማያስችል አይደለም በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የብሓራዊ ባንክ ሰራተኞች በደንብ ቁጥር 157/2ዐዐ1 የሚተዲደሩ መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 3/1/ሰ/ የሚሸፈኑ ባለመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት ማሕበሩ ሉፈርስ አይገባም ሲል የሰጠው ውሣኔ ተገቢ አይደለም በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሽሮ አመልካች ማሕበር እንዱፈርስ ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካች ግንቦት 2 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ማሕበሩ ለሰላሣ ሦስት ዓመት ያሕል ዕውቅና አግኝቶ የሰራተኛውን መብትና ጥቅም ሲያስጠብቅ የኖረ ነው። ሰራተኛው በደንብ ቁጥር 157/2ዐዐ1 የሚተዲደር መሆኑ ማህበሩ ያለውንና ቀደም ሲል የነበረውን ህልውና ለማስጣት የሚቻል አይደለም። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 12ዐ ድንጋጌና የአገሪቱን ሕገ መንግስት አንቀፅ 31 እንደዚሁም ዓለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት በኩል ያፀደቁትን ስምምነቶች በተለይም ቁጥር 87 እና ቁጥር 98 የሚጥስና መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። ስለሆነም በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ታሕሣሥ 7 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር መልስ የብሓራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁ. 591/2ዐዐዐ የባንኩን ሰራተኞችና የአስተዲደር አካላትን በተመለከተ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ እንድያወጣ ሥልጣን ይሰጣል። በዚህ መሰረት ደንብ ቁጥር 157/2ዐዐ1 ወጥቶ ሥራ ላይ ውሎል። የባንኩ ሰራተኞች በዚህ ልዩ ሕግ የሚተዲደሩና በአዋጅ ቁጥር 377/96 የማይተዲደሩ በመሆናቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 ንዐስ አንቀጽ 2/ሰ/ መሰረት በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ያቋቋመው አመልካች ሕልውና ኖሮት ተግባሩን ሉያከናውን አይችልም ። አመልካች የአዋጅ ቁ/ 377/96 አንቀፅ 12ዐን በመጥቀስ ያቀረበው አቤቱታ ከተያዘው ክርክር ጋር አግባብነት ያለው አይደለም። በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 31 እና ዓለም አቀፍ የሰራተኞች ድርጅት ስምምነቶች ቁጥር 87 እና ቁጥር 98ን በመጥቀስ ያቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት ያለው አይደለም። በልዩ ሕግ የሚተዲደሩ እንደ ፕሉስ ዐቃቢያነ ሕግ ዳኞች የመንግስት ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የተደራጀ ማሕበር እንደማይኖራቸው ሁለ አመልካች የተለየ የሚሆንበት ምክንያት የላለ በመሆኑ የአመልካችን የሰበር አቤቱታ ውድቅ በማድረግ እንዱያስናብተን በማለት መልስ ሰጥቷል። በሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች እንዱፈርስ ተጠሪ ያቀረበው ጥያቄና ይግባኝ ሰሚው ችልት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም ? የሚለው ጭብጥ መመርመር ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 31 ማንኛውም ሰው ለማንኛውም ዓላማ የመደራጀት መብት እንዲለው የተደነገገ መሆኑን ገልፆ በተጠሪ የተመዘገበውን የምስክር ወረቀት የተሰጠው የብሓራዊ ባንክ ሰራተኛ ማሕበር የሚፈርስበት ሕጎዊ ምክንያት የለም የሚል ክርክር አቅርቧል።
እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ አመልካች በሕገመንግስቱ አንቀፅ 31 እና ላልች የሕግ ማዕቀፍችን መሰረት በማድረግ እንደተቋቁሙት ላልች የሙያ ማሕበራት የሚቆጠር ነው ወይስ አይደለም?
የሚለው ነጥብ ነው።
የሰራተኛ ማህበር የማቋቋም መብት በህገመንግስቱ አንቀፅ 31 ከተደነገገው በተለየ ሁኔታ በህገመንግስቱ አንቀፅ 42 ንዐስ አንቀፅ 1/ሀ/ የፊብሪካና የአገልግልት ሰራተኞች ገበሬዎች የእርሻ ሰራተኞች ላልች የገጠር ሰራተኞች ከተወሰነ ደረጃ በታች ያለና የሥራ ጠባያቸው የሚፈቅድላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሥራና የኢኮኖሚውን ሁኔታ ለማሻሻል በማህበር የመደራጀት መብት አላቸው ይህ መብት የሰራተኛ ማሕበራትን ላልች ማሕበራትን በማደራጀት ከአሰሪዎችና ጥቅማቸውን ከሚነኩ ላልች ድርጅቶች ጋር የመደራደር መብት ያካትታል በማለት ይደነግጋል። በህገመንግስቱ አንቀፅ 42 ንዐስ አንቀፅ 1/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት የሚቋቋም የሰራተኛ ማህበር በህገመንግስቱ አንቀፅ 31 እና በላልች የህግ ማዕቀፍች ከሚቋቋሙ ማህበራት በአደረጃጀቱ በዓላማውና በተግባሩ የሚለይበት ሁኔታ እንዲለ በህገመንግስቱ አንቀፅ 42 ንዐስ አንቀፅ 1/ለ/ እና በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 42 የንዐስ አንቀፅ 2 እና ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ የሰራተኛ ማሕበር የሚመዘገበበትና የምስክር ወረቀት የሚያገኝበት መንገድ ላልች ማሕበራት ከሚመዘገቡበትና ዕውቅና ከሚያገኙበት የተለየ መሆኑን ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 118 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል። "የሰራተኛ ማህበር“ በህገ መንግስቱ አንቀጽ 42 መሰረት የመመሥረት መብት ያላቸው "ሰራተኞች" ሲሆኑ ማንኛውም ሰው ዓላማውን እደግፊለሁ በሚል ምክንያት የአንድ ሰራተኛ መሕበር አባል መሆን አይችልም ።
የሰራተኛ ማሕበር የመመስረት የሰራተኛ ማሕበር አባል መሆንና የመሣተፍ መብት ያላቸው "ሰራተኞች" ብቻ መሆናቸውን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 113 ንዐስ አንቀጽ 1 በግልጽ ተደንግጓል። የሰራተኛ ማሕበር ማለት ሰራተኞች በአንድነት ሆነው የሚያቋቁሙት ማህበር እንደሆነ በአዋጁ አንቀጽ 113 ንዐስ አንቀጽ 2/ሀ/ ተደንግጓል።
"ሰራተኛ ' ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ 4 በተመለከተው መሰረት ከአሰሪ ጋር በቅጥር ላይ የተመሰረተ ግንኝነት ያለው ግለሰብ ነው በማለት አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 2/4/ ትርጓሜ ሰጥቶታል። ስለሆነም በአንድ ተቋም ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች የሰራተኛ ማህበር ለማቋቋም የሚችለት ወይም ቀደም ሲል በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ አቋቁመውት የነበረው ማህበር ህጋዊ ህልውና ኖሮት በሰራተኛ ማህበርነቱ ሉቀጥል የሚችለው የተቋሙ ሰራተኞችና የማህበሩ አባላት በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና በህገመንግስቱ አንቀጽ 42 መሰረት የሰራተኛ ማህበር የማደራጀት መብት ያላቸውና "ሰራተኛ ' የሚለውን ትርጓሜ የሚያሟለ ሁነው ሲገኙ እንደሆነ ከላይ በዝርዝር ከገለፅናቸው ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል።
ከዚህ በተጨማሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 ተቋቁሞ በተጠሪ ተመዝግቦና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶት የተደረጀና ሕጋዊ ህልውናውን ይዞ የሚቆይ የሰራተኛ ማህበር ከላልች ማህበሮች የተለየና "ሰራተኞች'ን ብቻ በአባልነት የያዘ መሆን እንደሚገባው ስለ ሰራተኛ ማህበር አመሰራረት በሚደነግገው አንቀፅ 114፣ ስለሰራተኛ ማሕበር ተግባር ከሚደነግገው አንቀፅ 115 ስለ ማሕበራት ምዝገባና ሕጋዊ ሕልውና ከሚደነግገው አንቀፅ 118 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይቻላል። ስለሆነም የሰራተኛ ማሕበር የመመስረት መብት በአዋጅ ቁጥር 377/96 "ሰራተኛ ' የሚለውን ትርጉም የሚያሟለ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚተዲደሩ ሰራተኞች መብት ብቻ መሆኑን ከሕገመንግስቱ አንቀፅ 42 ንዐስ አንቀፅ 3 እና ከአሥሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ዝርዝር ድንጋጌዎች ለመረዲት ይቻላል።
አመልካች አባላቱ በአዋጅ ቁ. 377/96 በሚተዲደሩበት ጊዜና ከዚህ የሕግ ማዕቀፍ በፉት በነበረው አዋጅ ቁጥር 42/68 መሰረት ተደራጅቶ የነበረ መሆኑ ከክርክሩ ለመገንዘብ ችለናል።በአዋጅ ቁጥር 42/1968 እና በአዋጅ ቁጥር 377/96 አባላቱ "ሰራተኛ' የሚለውን የሕግ ትርጓሜን በሚያሟለበት ወቅት የተደራጀ የሰራተኛ ማሕበር ተቋሙ የሚተዲደርበት የሕግ ማዕቀፍ ከተቀየረና አባላቱ "ሰራተኛ' የሚለውን የሕግ ትርጉም የማያሟለበት ሁኔታ ከተፈጠረ "በሰራተኛ ማህበርነቱ' ተሰጥቶት የነበረው ምዝገባና እውቅና እንዱሁም የምስክር ወረቀት ለሚመለከተው ክፍል እንዱመልስ ተጠሪን ከመጠየቅ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 12ዐ ድንጋጌዎች የሚከለክል አይደለም። የአዋጁ አንቀፅ 12ዐ በባህሪው የአመልካች ክርክር (Indicative) የህግ ድንጋጌ እንጂ ‛Exhaustive“ አሳሪ ወይም አሟጣጭ የህግ ድንጋጌ አይደለም።
ስለሆነም አባላቱ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ጥር 377/96 በሚተዲደሩበትና ሰራተኛ የሚለውን ትርጓሜ በሚያሟለበት ወቅት በሰራተኛ ማህበርነት ተመዝግቦና ከተጠሪ የምስክር ወረቀት ወስድ በህገመንግስቱ አንቀፅ 42 እና በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አንቀጽ 115 የተመለከቱትን ተግባራት ሲፈፅም የቆየው አመልካች የተቋሙ ሰራተኞች በደንብ ቁጥር 157/2ዐዐ1 መተዲደር ከጀመሩበትና "ሰራተኞች' የሚለውን ትርጓሜ የሚያሟለ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 3 ንዐስ አንቀጽ 2(ሰ) ከተዘረዘሩት መካከል የሚመደቡ በመሆናቸው ከተጠሪ የተደረገለትን ምዝገባና የምስክር ወረቀት ይዞ በሰራተኛ ማሕበርነት የሚቀጥልበት ምክንያት የለም። ስለሆነም ተጠሪ አመልካችን በአዋጅ ቁጥር377/96 በአንቀጽ 118 ንዐስ አንቀጽ 3 መሰረት በመመዝገብ የሰጠው የምስክር ወረቀት እንዱሰረዝለት ማመልከቱ ተገቢና ሕጋዊ መሰረት ያለው ሲሆን የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትም የተጠሪን ጥያቄ በመቀበል የሰጠው ውሣኔ የህገመንግስቱን አንቀፅ 42 ድንጋጌዎችና በአዋጅ ቁጥር 377/96 ከላይ የተገለፁትን አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች መሰረት ያደረገ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የላለበት ነው በማለት ወስነናል፡
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.