No summary available.
የሰ/መ/ቁ/62370 ታህሣስ 26 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ኃይል ኮርፕሬሽን - የቀረበ የለም ተጠሪዎች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የሥራ ውል ማቋረጥን የሚመለከት ነው። ተጠሪዎች ሥር ፍ/ቤት ከሣሽ ነበሩ። የሥር ፍ/ቤት አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የነበረውን የሥራ ውል ከሕግ አግባብ ውጪ አቋርጧል በሚል ወደ ሥራ እንዱመልሳቸው ወስኗል። ከፍተኛው ፍ/ቤት ይህንኑ አጽንቷል።
አመልካች ለዚህ ሰበር ችልት ያቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ አመልካች የ6 ወር ደመወዝ ከፍል ተጠሪዎችን ወደ ሥራ ይመለስ ተብል መወሰኑ በአግባቡ ስለመሆኑ ለመመርመር ተብል ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡ ተደርጓል።
ተጠሪዎች ታህሣስ 1 ቀን 2003 ዓ.ም. የተጻፈ መልስ አቅርበዋል። ተጠሪዎች በሰጡት መልስ በአመልካች በተያዘው የፔሮጀክት ሥራ ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያየ ቦታና የሥራ መደብ ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልፀው የሥራ ውል ማደስ አስፈላጊ ነው ከተባለም ይሰሩ ከነበሩበት ሙያ ጋር በሚጣጣም መልኩ ባለመቅረቡ እንጂ ውል ለማደስ ፈቃደኛ መሆናቸውን ዘርዝረው በዚህም ምክንያት የሥራ ውል ማቋረጥ ከሕግ ውጭ ነው ተብል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ፍርድ በአግባቡ ነው በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች አቤቱታውን ከጠናክሮ የመልስ መልስ ሰጥቷል። የጉዲዩ አመጣጥ በአጭሩ ከላይ የተመለከተው ነው። እኛም ጉዲዩን ከተያዘው ጭብጥ አንፃርና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዲት የተቻለው አመልካች ከተጠሪዎች ጋር የነበረውን የሥራ ውል ለማቋረጥ ምክንያት ያደረገው ተጠሪዎች የውል እድሳት ውል ለመፈረም አልፈቀደም አዱስ የውል ሁኔታን አቅርበዋል በሚል ነው።
በሥር ፍ/ቤት ውሣኔ እንደተረጋገጠው ተጠሪዎች በአመልካች በተያዘው የፔሮጀክት ሥራ ውስጥ በነዲጅ ቀጅነትና በብየዲ ሥራ ላይ ይሰሩ እንደነበር እና የሥራ ውል ሉታደስ የሚገባ ከሆነም በዚሁ አግባብ እንጂ ጫኝ እና አውራጅ በሚለው የሥራ መደብ መሆን የለበትም የሚል ነው።
አመልካች አጥብቆ የሚከራከረው ተጠሪዎች ለውል እድሳት ያቀረቡት ሁኔታ ቀድሞ አልነበረም ተጠሪዎች የተቀጠሩት በዩኒቨርሳል ኤላክትሪፉኬሽን አክሰስ ፔሮጀክት ውስጥ የተወሰነ ሥራ ለመሥራት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 10/1/ሀ መሰረት ነው።
በመሰረቱ የሥራ ውል ባህሪ የሚወሰነው በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 9 እና 10 በተደነገገው አግባብ መሆኑ እሙን ነው። አሰሪው የሥራ ውል በአዋጅ አንቀጽ 10 ሥር በተደነገገው አግባብ የተፈፀመ መሆኑን ማስረዲት ይጠበቅበታል። ይህንን ማስረዲት ከቻለ ደግሞ የሥራ ውል ታደሰም አልታደሰ ሥራው ሲያልቅ ወይም ጊዜው ሲያበቃ የሥራ ውል ሉቋረጥ እንደሚችል አዋጁ በግልፅ ደንግጓል።
በተያያዘው ጉዲይ አመልካች ተጠሪዎች የተቀጠሩበት የፔሮጀክት ሥራ ተጠናቋል የሚል ክርክር በአመልካች በኩል አልቀረበም። ስለሆነም የፔሮጀክት ሥራው አሁንም ቀጥል ያለ ስለመሆኑ መረዲት አዲጋች አይደለም። ስለዚህም ተጠሪዎች የተቀጠሩበት ሥራ አመልካች እንደሚለው በአንቀጽ 10/1/ሀ ሥር የሚሸፈን ነው እንኳ ቢባል የፔሮጀክቱ ሥራ ተጠናቋል። እስካልተባለ ጊዜ ድረስ የሥራ ውል አድሰዋል ወይም አላደሱም አሉያም ለማደስ ፈቃደኛ አልሆኑም በሚል ምክንያት ብቻ የሥራ ውልን ለማቋረጥ የሚቻልበት ሁኔታ በሕጉ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ስለሆነም አመልካች ያቀረበውን መከራከሪያ ነጥብ ውድቅ በማድረግ የሥር ፍ/ቤት የደረሰበት ድምዲሜ በሕግ ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚባልበት ምክንያት አልተገኘም።
ስለዚህም ውሣኔው ባለበት እንዱፀና ብለናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 25 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ30/02/2003 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ መዝገብ ላይ ህዲር 17 ቀን 2003 ትዕዛዝ ተሰጥቶ የነበረው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይጻፍ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.