No summary available.
የሰበር ቀን 15/9/2003 ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ሜታ አቦ ቢራ አ/ማ ነገረ ፈጅ አቶ ሰለሞን ዘውዳ - ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ወ/መድህን ቢረዲ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
የአሁኑ ተጠሪ ለሥር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረበው ክስ በተከሳሽ ድርጅት /የአሁን አመልካች/ በዩቲሉቲ ክፍል ሃላፉ ሆኜ ስሰራ ቆይቼ ማያዝያ 26 ቀን 2001 ዓ.ም በሥር ላይ በደረሰብኝ አደገ በህክምና የተረጋገጠ 7% ጉዲት የደረሰብኝ ስሆን ተከሳሽ ክፍያ የፈፀመልኝ ካደረሰብኝ ጉዲት ባነሰ በመሆኑ ቀሪውን ገንዘብ ከነ ወለደ እንዱከፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የሥር ተከሳሽም በሰጠው መልስ ተከሳሽ በገባው የመድን ዋስትና መሰረት ለከሳሽ የሚገባውን የካሣ ገንዘብ ከፍሎል። ስለሆነም ቀሪ የሚከፈለው ካሣ የለም በማለት ተከራክሯል።
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በበኩለ ወደ ክሱ ጣልቃ በመግባት የተከራከረ ሲሆን የሥር ተከሳሽ በገባው የመድን ሽፊን መሰረት ክፍያ መፈፀሙን ገልጿል። የሥር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤትም በሰጠው ፍርድ ተከሳሽ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/2/ መሰረት ለከሣሽ ተገቢውን ካሣ የከፈለ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለውም ብሎል።
የሥር ከሣሽም በስር የመ/ደ/ፍ/ቤት ፍርድ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ያቀረቡ ሲሆን ለይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ያቀረበው የቅሬታ ነጥብይ መልስ ሰጪው ቀደም ሲለ ከከፈለኝ ገንዘብ ብር 7500 በተጨማሪ ብር 8649 ሉከፍለኝ ይገባል በማለት ያቀረብኩትን ክስ የሥር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ውድቅ ማድረጉ ያለአግባብ ነው የሚል ነው።
ከፍተኛ ፍ/ቤትም የመልስ ሰጪዎችን መልስ ከቀረበው የይግባኝ ቅሬታ ጋር ከመረመረ በኋላ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/1/ ድንጋጌ መሰረት ለሰራተኛ የሚከፈል የጉዲት ካሣ አሰሪው በገባበት የመድን ዋስትና ተፈፃሚ ይሆናል ተብል የተገለፀው የመንግስት ሰራተኞችን የሚመለከት መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በ1ኛ መልስ ሰጪ /የአሁን አመልካች/ እና 2ኛ መልስ ሰጪ /የኢት/መድን ድርጅት/ መካከል የተደረገው የመድን ሽፊን ውል ህግ ሆኖ የሚገዛው ሁለቱን ተዋዋይ ወገኖችን እንጂ ይግባኝ ባይ /ያሁን ተጠሪን/ የውለ ተገዢ ለማድረግ ሙለ በሙለ የሚያስገድድ አይደለም በማለት 1ኛ መልስ ሰጪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/3/ለ/ መሰረት ከደረሰው የአካል ጉዲት ጋር ተያይዞ ቀሪ የካሣ ክፍያ ብር 8649 የመክፈል ግዳታ አለበት በማለት ፈርዶል።
በሥር የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ፍርድ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል ሲል አመልካች ለዚህ ፍ/ቤት የሰበር አቤቱታ ያቀረበ ሲሆን በዋናነት የጠቀሳቸው የቅሬታ ነጥቦችም አመልካች የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን ተጠሪው ደግሞ የመንግስት ሰራተኛ ነው።
በመሆኑም አሰሪው ካሣ መክፈል ያለበት በአዋጅ አንቀጽ 109/1/ መሰረት አሰሪው በገባበት የመድን ዋስትና ወይም በመንግስት የጡረታ ህግ መሰረት ነው። በዚሁ መሰረትም አመልካች በገባው የመድን ዋስትና መሰረት ከሚገባው ካሣ በላይ ለተጠሪው ከፍሎል። ከፍተኛ ፍ/ቤት የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/3/ለ/ን ለውሣኔው መሰረት ያደረገ ሲሆን ይህ አንቀጽ ከ109/2/ ጋር ተያይዞ የሚታይ ነው። ምክንያቱም ድንጋጌው በጡረታ ህግ ላልተሸፈኑ ሰራተኞች አሰሪው በአንድጊዜ ስለሚከፍለው ካሣ ሲሆን ተጠሪ ግን የጡረታ ሽፊን ያለውና እንደማንኛውም ሰራተኛ ዕድሜው ለጡረታ ሲደርስ የጡረታ መብት የሚከበርለት ነው። ስለሆነም የስር የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲይ በተጠቀሰው ህግ አንቀጽ 109/3/ለ/ ሥር የሚሸፈን ነው በማለት ተጠሪው በተጨማሪነት እንዱከፈለው የጠየቀውን ገንዘብ አመልካች እንዱከፍል መወሰኑ ያለአግባብ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው የሚለ ናቸው።
ተጠሪው በበኩለ ለሰበር አቤቱታው በሰጠው መልስ አመልካች ለሰራተኛው የገባው የመድን ዋስትና የሚያስገኘው ጥቅም አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/3/ለ/ ለሰራተኛው የሚሰጠው ጥቅም ያነሰ ነው። የህብረት ስምምነቱም የካሣ ክፍያን አስመልክቶ ለሰራተኛው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ካስቀመጠው ያነሰ ጥቅም የሚሰጥ ከሆነ ተፈፃሚነት የለውም ተጠሪም እንዱከፍለኝ የጠየቅኩት የህብረት ስምምነቱ ያስቀረብኝን ጥቅም በመሆኑ የአመልካች ቅሬታ ህጋዊ መሰረት ያለው አይደለም ሲል የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሣኔ የህግ ስህተት ያልተፈፀመበት ነው ብሎል።
አመልካችም ለተጠሪ መልስ በማቅረብ ክርክሩን አጠናክሯል። የግራ ቀኙን ክርክር ከዚህ በላይ የቀረበ ሲሆን እኛም አመልካች በቀሪነት የሚፈለግበትን ገንዘብ የመክፈል ግዳታ አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን ጭብጥ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
ለተያዘውን ጭብጥ ምላሽ ለመስጠት ስለ ጉዲት ካሣ ክፍያ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109 የተደነገገውን መመልከት ተገቢነት ያለው ነው። የተጠቀሰው አዋጅ አንቀጽ 109/1/ የሚናገረው በመንግስት ድርጅቶች ሰራተኞች ላይ ለሚደርሰው ጉዲት ካሣ ስለሚከፈልበት ሁኔታ ሲሆን አከፊፈለም አሰሪው በገባበት የመድን ዋስትና ወይም በመንግስት የጡረታ ህግ መሰረት መሆኑን ይገልፃል። አንቀጽ 109/2/ ደግሞ ተፈፃሚ የሚሆነው በጡረታ ህግ ላልተሸፈኑ ሰራተኞች ሲሆን የጉዲት ካሣውም የሚከፈለው በጡረታ ህግ መሰረት ሳይሆን በአንድ ጊዜ ክፍያ ነው። የአንቀፁ ንዐስ ቁጥር 3 ደግሞ ከንዐስ ቁጥር 2 ጋር ተያያዥነት ያለው ሆኖ ስለ ጉዲት ካሣው መጠን ስላት የሚናገር ነው።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ አመልካች የመንግስት የልማት ድርጅት ሆኖ በደንብ ቁጥር 64/85 የተቋቋመ ሲሆን ተጠሪውም የመንግስት ሰራተኞች ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪው የደረሰበት ጉዲት 7% እንደመሆኑ መጠን መደበኛ ሥራውን እያከናወነ ያለና በጡረታ ህግ የተሸፈነና ዕድሜው ለጡረታ ሲደርስ የጡረታ አበል ጭምር የሚያገኝ መሆኑን አመልካች ያስረዲ ሲሆን ተጠሪው ግን ይህን በሚያስተባብል መልኩ ያቀረበው ክርክር የለም።
ስለሆነም የአመልካችና የተጠሪው ክርክር መወሰን ያለበት የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደጠቀሰው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/3/ለ/ ሳይሆን በአንቀጽ 109/1/ መሰረት ነው።
በዚህ በተጠቀሰው አንቀጽ ማለትም 109/1/ መሰረት አንድ የመንግስት ድርጅት በሰራተኛው ላይ ለደረሰው ጉዲት ካሣ የሚከፍለው በገባበት የመድን ዋስትና ወይም በመንግስት የጡረታ ህግ ሲሆን ይህ ሉቀየር የሚችለው አሰሪውና ሰራተኛው በህብረት ስምምነታቸው በተቃራኒ ተስማምተው እንደሆነ ብቻ ነው። ሆኖም በህብረት ስምምነት በተቃራኒ የተወሰነ ወይም የተደረገ ስምምነት ስለመኖር በሥር ፍ/ቤት በአስረጂነት የቀረበ ነገር የለም።
አመልካችም የጉዲት ካሣውን ገንዘብ የከፈለው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/1/ መሰረት ለተጠሪው በገባለት የመድን ዋስትና ሲሆን የዋስትና ሽፊኑም ብር 7500 በመሆኑና ይህንኑ ገንዘብ ለተጠሪው መክፈለን ገልጿል። በአንቀፁ የጉዲት ካሣው አሰሪው በገባበት የመድን ዋስትና ላሆን እንደሚችል ከተደነገገው በተጨማሪ በአመልካች እና በሜታ አቦ ቢራ አክስዮን ማህበር መሰረታዊ የሰራተኞች ማህበር መካከል በ2000 ዓ.ም በተደረገው የህብረት ስምምነት አንቀጽ 32 ድርጅቱ /አመልካች/ ለማንኛውም ሰራተኛ በሥራውና ከሥራው ውጪ ለሚደርስበት አደጋ የሕይወት መድን ዋስትና ይገባለታል የተባለ ሲሆን ለአካል ጉዲትና የሕይወት መድን ዋስትና ድርጅቱና ሰራተኛው በጋራ በሚያዋጡት አረቦን ዓመታዊ የህይወት ዋስትና እንደሚገባለት አንቀፁ ይናገራል።
በመሆኑም አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 እና በ2000 ዓ.ም በተደረገው የህብረት ስምምነት መሰረት ለሰራተኞች /ተጠሪን ጨምሮ/ የመድን ዋስትና ገብቶላቸው ተጠሪውም ዓመታዊ አረቦን ማዋጣቱን እያወቀ ለደረሰበት ጉዲት አመልካች ለተጠሪው በገባለት የመድን ሽፊን መሰረት የከፈለውን የጉዲት ካሣ አንሶኛል በማለት ያቀረበውን ክርክር የሥር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት መርምሮ የጉዲት ካሣ በአግባቡ ተከፍሎል በማለት የወሰነውን የሥር የፋ/ከ/ፍ/ቤት ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 109/ለ/ በመጥቀስ ቀሪ ገንዘብ አመልካች ለተጠሪ ይክፈል ሲል የወሰነው መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የሥር የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 99288 በቀን 02/05/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የሥር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ. 16634 በቀን 03/02/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል። ውሣኔውም የህግ ስህተት የላለበት ነው ብለናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ የተዘጋ ስለሆነ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.