No summary available.
ቀን 16/9/2003 ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ወልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ አሞኘስ ገብሬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- በአቃቂ መለዋወጫ ዕቃዎች የእጅ መሥሪያዎች አ/ማ የሰራተኞች የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/የግ/ማህበር - ነገረ ፈጅ አዲነ አረጋ ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ ከአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ጋር ተያያዥነት ያለው ሲሆን በበታች ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ከሳሽ ስትሆን ተጠሪ ደግሞ ተከሳሽ ነበር። ጉዲዩ የተጀመረው በፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን ከሳሽ በአሰሪ መስሪያ ቤቷ ላይ ባቀረበችው ክስ ተከሳሽ መስሪያ ቤቷ ባቀረበው ተቃውሞ ከሳሽ የስራ መሪ እንጅ ሰራተኛ አይደለም። የከሳሽና ተከሳሽ ክርክር መዲኘት ያለበት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ሳይሆን የራሱ የሆነ ሕግ ስለአለ በአዋጅ ቁ. 147/91 እና 402/96 መሰረት መሆን አለበት በማለት ተከራክሯል።
በእነዚህ በቀረቡት መቃወሚያዎች ላይ ፍርድ ቤቱ ካከራከረ በኋላ ከሳሽ የስራ መሪ ናቸው በማለት የቀረበውን ተቃውሞ በተመለከተ ከሳሽ የሂሳብ ሰራተኛ ባለሙያ እንጂ ለአሰሪ መስሪያ ቤት የምታቀርበው የውሣኔ ሃሳብ ባለመኖሩ ተቀባይነት የለውም በማለት ሲወስን ሁለተኛውን የተቃውሞ ነጥብ /ተፈፃሚነት ያለውን ህግ በተመለከተ/ እንደዚህ አይነት የህብረት ሥራ ማህበራት ተቋም ሂደታቸው የሚመራው በአዋጅ ቁ. 147/91 አንቀጽ 49/3/ እና 52 እና አዋጅ ቁ. 402/96 አንቀጽ 8 መሰረት መሆኑን በማብራራት አለመግባባቶች ሲከሰቱ መጀመሪያ በእርቅ፣ በእርቅ ካልተቻለ ደግሞ በሽምግልና ዲኝነት መታየት እንዲለበትና እነዚህ አካላት በሚወስኑት ውሣኔ ላይ ቅሬታ ካለ ወደ ሚመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ እንደሚችለ ስለሚደነግግ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት የስረ ነገር ስልጣን የለውም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበች ሲሆን ጉዲዩን ለሽማግላዎች አስፈላጊውን መመሪያ በመስጠት እንዱያዩት እንዲዘዘና መዝገቡን እንደዘጋ ከመዝገቡ መረዲት ተችሎል።
የአሁኑ ይግባኝ ላቀርብ የቻለው በከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሲሆን በ18/12/2002 ዓ.ም የተፃፈ የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ በተጠሪ መስሪያ ቤት ውስጥ ተቀጥሬ ስሰራ የቆየሁ ሲሆን ተጠሪ ሰኔ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ የስራ ውላን አቋርጦ ከስራ ስላሰናበተኝ የተቋረጠብኝ ጥቅም ተጠብቆ ወደ ስራዬ እንድመለስ ትዕዛዝ እንዱሰጠኝ የበታች ፍርድ ቤት ብጠይቅም ጉዲዩ መታየት ያለበት በእርቅ ወይም በሽምግልና ዲኛ ነው በማለት መዝገቡን ዘግተውብኛል። ስለሆነም በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው ግንኙነት የስራ ውል እንደመሆኑ መጠን በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መታየት ሲገባው በመጀመሪያ በእርቅ ይሄም ካልተቻለ በሽምግልና መታየት አለበተ በማለት መዝገቡ መዘጋቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤት በህጉ አግባብ ዲኝነት እንዱያዩልን ውሣኔ እንዱሰጥልኝ የሚል ነው።
ተጠሪ ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥ በመታዘዙ በተወካያቸው አማካኝነት በ27/382003 ዓ.ም በ2 ገጽ ጽፈው ባቀረቡት መልስ የበታች ፍርድ ቤት ይሄ ጉዲይ በህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ 147/91 መታየት አለበት በማለት የሰጡት ውሣኔ ምንም ዓይነት መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ የቀረበው ቅሬታ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል።
አመልካችም በ20/4/2003 ዓ.ም በ2 ገጽ ባቀረቡት የመልስ መልስ ቅሬታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆኑ እኛም የቀረበውን ቅሬታ የበታች ፍርድ ቤት ከሰጡት ውሣኔ ከተያዘው ጭብጥና ጉዲዩ ከሚመለከተቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማያያዝ ጉዲዩን መርምረናል። እንደመረመርነውም የአመልካች የስራ ውል በመቋረጡ ምክንያት ክስ መቅረብ ያለበት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 396/96 ነው ወይስ በህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁ. 147/91 ነው የሚለው ጭብጥ ተይዞ መፍትሄ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በዚሁ መሰረት ጉዲዩን ስንዲስሰው በእርግጥ በአዋጅ 147/91 አንቀጽ 49 ስር አለመግባባቶች ሲኖሩ እንዳት ሉፈቱ እንደሚገባቸው ይደነግጋል። ይሄውም በመጀመሪያ ደረጃ በእርቅ መታየት እንዲለበት በእርቅ ካልተቻለ ደግሞ በሽምግልና ታይቶ በዚህ አካል በሚሰጠው ውሣኔ ቅሬታ ያለው አካል በይግባኝ ወደሚመለከተው ከፍተኛ ፍርድ ቤት በይግባኝ መሄድ እንደሚቻል ይዲነግጋል።
ሆኖም ምን አይነት ጉዲዮች ናቸው በእንደዚህ አይነት ሂደት መታየት ያለባቸው የሚለውን በምናይበት ጊዜ በዚሁ አንቀጽ መግቢያ ላይ እንደተመለከተው ለሽምግልና ዲኝነት የሚቀርቡት ጉዲዮች በዝርዝር ስለአንድ ማህበር አቋም ስለስራው አካሄድ ወይም ስለስራው አፈፃፀም እንደሆነ ተመልክቷል። የዚሁ አንቀጽ መግቢያ የእንግሉዝኛ ትርጉም ‛The arbitrators shall have the power to hear disputes not settled by arbitration regarding the organization, management or operation of a society…“ ይላል። የዚህን አንቀጽ አቀራረጽ ስናይ አጠቃላይ የህብረት ስራ ማህበሩን እንቅስቃሴ ወይም ህልውና የሚመለከቱ በተለይም አደረጃጀቱን አመራሩና የስራ እንቅስቃሴን መሰረት ያደረገ አለመግባባት እንጅ ማህበሩ እንደማንኛውም ህጋዊ ሰውነት እንዲለው ተቋም ሉቀጥራቸውና ሉያሰራቸው ወይም በስሩ የሚተዲደሩትን ሰራተኞች በዚሁ የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ለመምራት ያሰበ ስለመሆኑ የሚያመለከት ነገር የለም። የአንቀፁን መንደርደሪያ ከላይ ለማመልከት እንደተሞከረው ከአሰራተኞቹ ጋር ሉፈጠር የሚችለውን የስራ ክርክር ሂደት ከላይ በተጠቀሰው የሙግት አመራር ስርዓት ለማስኬድ የህግ አውጪው ሃሳብ ስለመሆኑ የሚያሳይ ነገር የለም።
የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ቁ. 147/91 አጠቃላይ ትኩረት ተመሳሳይ ፍላጏት ባላቸው ሰዎች መካከል በፈቃደኘነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የህብረት ስራ ማህበራትን በመፍጠር ገንዘብን፣ እውቀትን፣ ንብረትንና ጉልበትን በማስተባበር ቁጠባንና እርስ በርስ መደጋገፍ የሚጏለብትበትና የሚመራበትን የህግ ማዕቀፍ መፍጠር እንደሆነ ከዚሁ አዋጅ መግቢያ መረዲት ይቻላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአዋጁ አንቀጽ 4/1-9/ የተዘረዘሩትን ዓላማዎች ስንመለከት የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍልች ለየብቻቸው ሆነው ሉከብዲቸው የሚችለውን ጉዲይ በመተባበር ሉደርሱባቸው የሚችለበትን የአደረጃጀት ማዕቀፍ ከመዘርጋት አኳያ እንጅ እንደማንኛውም የህግ ሰውነት ያለው ተቋም አሰሪ የሚሆንላቸውን ሰራተኞች በዚህ አዋጅ መሰረት ሉፈጠሩ የሚችለትን አለመግባባቶች ለማስኬድ የታሰበ ስለመሆኑ የሚያሳይ አይደለም።
በተጨማሪ መነሳት ያለበት ጉዲይ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የስራ ክርክርን በተመለከተ የተለየ ህግ በመሆኑና በህብረት ስራ ማህበራት ውስጥ ያለ ሰራተኞች በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ሉተዲደሩ አይገባም ልባል የሚችልበት አጋጣሚ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 3/2/ /ሰ/ መሰረት የሚተዲደሩበት የራሳቸው ዝርዝር ህግ ወጥቶላቸው ቢሆን ኖሮ ነበር። ከዚህ አኳያም የወጣ ነገር የለም። እንደማንኛውም ሕጋዊ ሰውነት እንዲለው ተቋም ሰራተኛ ሉቀጥርና ሉያስተዲድር የሚችል ተቋም መሆናቸው ቢታመንም ባላቸው የስራ ግንኙነት ምክንያት ወይም የስራ ውል መሰረት ያደረገ አለመግባባት ሲፈጠር የሚመራበት የተለየ ህግ በላለበት ሁኔታ፣ የህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ተፈፃሚነት ይኖረዋል ቢባል እንኳ የትኛውን ህግ መሰረት ያደርጋል? ሰራተኛው ከሚያነሳው የመብት ጥያቄ አኳያ የሚሰጠው መፍትሓ (remedy) ምንድነው? የሚለው ጥያቄ በአዋጁ መልስ አላገኘም። በልላ በኩል በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የሚነሱትን የስራ ውል ተያያዥ ክርክሮችን ለምሳላ የሥራ ስንብት፣ የካሳ አከፊፈል እና የመሳሰለትን ጥያቄዎች የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መፍትሓ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ሕግ አውጪው ጉዲዩን በአዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት ተፈፃሚ እንዱሆን ያሰበ መሆኑን ያመለክታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በግልጽ የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ተፈፃሚነት የለውም ባልተባለበት ሁኔታ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ አይመራም መባለ ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። በመሆኑም በህብረት ስራ ማህበራት አዋጅ ውስጥ እየተጠቀሰ ያለው የቅሬታ አፈታት ስርዓት ከላይ በተመለከተው ምክንያት ለላላ ዓላማ የተቀመጠ በመሆኑ ተፈፃሚነት ያለው አዋጅ ቁ. 377/96 ይሆናል ብለናል። የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ በአንድ ወጥ በሆነ የህግ ማዕቀፍ ለማስተዲደር መሰረታዊ የሆነ የህግ አውጭው ሐሳብ እንደሆነ ከወጣው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ መግቢያ ንባብ ከመረዲታችን በላይ በህብረት ስራ ማህበራት ውስጥ ላለት ሰራተኞች የተለየ ህግ ማስፈለጉን በግልጽ ባልተደነገገበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤቶች የወሰደት አቋም አግባብነት ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤትም ሆነ የፋ/ከ/ፍ/ቤት ይሄንን ሳያገናዝቡ ጉዲዩን ለማየት ስልጣን የለንም በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለው ሆኖ አግኝተነዋል። በመሆኑም ቀጥል ያለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 44428 በ21/5/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠው ብይንና የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመዝ.ቁ. 90023 ሐምል 29 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ጉዲዩ መታየት ያለበት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ. 377/96 መሰረት በመሆኑ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ጉዲዩን ለማየት ስልጣን አለው ብለናል። የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የቀረበውን ክስ ግራ ቀኙን አከራክሮ ተገቢውን ፍርድ እንዱሰጥ በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ህግ ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰናል።
በዚህ ችልት ለደረሰው ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል ወደ መዝገብ ቤት መልሰናል።
No topics extracted.