No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 13 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ወ/ሮ ሙለ ደምሴ - ጠበቃ ከበደ ወርቁ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ሸራተን አዱስ - ጠበቃ ግርማ ሀይላ - ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በስር ፍርድ ቤት አመልካች ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ በምግብ ዝግጅት የስራ መደብ ተቀጥረው የሰሩ መሆናቸውን ገልጸው ተጠሪ የስራ ውለ ለተወሰነ ጊዜ የተደረገ ነው በማለት ለላልች ሰራተኞች የሚሰጠውን ጥቅማጥቅም የማግኘት መብት ነፍጏኛል።
ስለሆነም ከመስከረም ወር 2002 ዓ.ም ጀምሮ የቲፔ ክፍያ ቦነስ የሁለት ወር ደመወዝ የደመወዝ ጭማሪ አስር ፏርሰንት በየዓመቱ የስድስት ወር ፔሮቪደንት ፈንድ እንዱከፍል ይወሰንልኝ። ከዚህ በተጨማሪ ተከሣሽ የመድን ሽፊን እንዱሰጠኝ የህክምና ወጭ እንዱሸፍንልኝ የደመወዝ መክፈያ ጊዜ ከላልች ሰራተኞች ጋር እንዱያስተካክልልኝና የስራ የምስከር ወረቀት እንዱሰጠኝ ይወስንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪ በስር ፍርድ ቤት በተከሣሽነት ቀርቦ ከሣሽ /አመልካች/ ከዚህ በፉት ክስ አቅርበው የቲፔና ዓመታዊ የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገ በመሆኑ በድጋሚ የቀረበችው ክስ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5 መሰረት ተቀባይነት የላለው ነው። ከሣሽ ላልቹን ጥያቄያቸውን ከዚህ በፉት ካቀረቡት ክስ ጋር ዘርዝረው ያላቀረቡ በመሆኑ አሁን ማቅረባቸው የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 216 የሚጥስ ነው። ከሣሽ የጠየቋቸው ጥቅማጥቅሞች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች ነው። ከሣሽ ለተወሰነ የስራ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኛ በመሆናቸው ያቀረቡት የጥቅማጥቅም ጥያቄ ተገቢነት የለውም በማለት ተከራክሯል።
የስር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ አመልካች ቲፔ እንዱከፈላቸው በመዝገብ ጠይቀው ጥያቄያቸው ውድቅ የተደረገ በመሆኑ በዚህ መዝገብ ክስ መልሰው መጠየቃቸው በፍርድ የመጨረሻ ውሣኔ ባገኘ ጉዲይ ያቀረቡት ስለሆነ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5 የሚታገድ ነው። እንደዚሁም በመዝገብ አመልካች /ከሣሽ/ አስር ፏርሰንት የደመወዝ ጭማሪና የህክምና ክፍያ አልጠየቁም። ከሣሽ የሰርቪስ ቻርጅ በቀጣይነት እንዱከፈላቸው ነው ክስ ያቀረቡት ስለሆነም ከሣሽ ክሣቸውን ነጥለው ያቀረቡ ስለሆነ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 216 ቀሪ ነው በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
በልላ በኩል የስር ፍርድ ቤት የአመልካች የስራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ነው ተጠሪ የሁለት ወር ቦነስ ሉከፍል ይገባል። የመድን ሽፊንና የደመወዝ መክፈያ ጊዜ ይስተካከልኝ ጥያቄ ግልጽነት የጏደለው ነው። ተጠሪ የስራ ምስክር ወረቀት ይሰጣት በማለት ወስኗል።
አመልካች በስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ይግባኙን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካች መጋቢት 2 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ የሰበር አቤቱታ የስር ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል ያለው የስራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የስራ ውል መሆኑን ከወሰነ በኋላ አመልካች ያቀረቡትን የመብትና የጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ለጉዲዩ አግባብነት የላላቸው የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 5 እና አንቀጽ 216 በመጥቀስ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት ስለሆነም ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሰራተኞች የከፈላቸውን መብቶችና ጥቅማጥቅሞች እንዱያከብር ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩለ ግንቦት 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተጻፈ መልስ አመልካች በሶስት መዝገቦች ማለትም በመዝገብ በመዝገብ እና ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ውሣኔ በተሰጠበት የመዝገብ የተለየዩ ጥያቄዎችን አቅርበው በፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገ በመሆኑ አሁን የሚያቀርቡት ክርክር የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5 የሚቃረን ነው በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች ሰኔ 6 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከስር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለጸው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ያቀረቧቸውን የጥቅማጥቅምና የመብት ጥያቄዎች የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5 እና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 216 በመጥቀስ ውድቅ ማድረጋቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለባቸው ሆነው አግኝተነዋል።
አመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የስራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የስራ ውል መሆኑን በስር ፍርድ ቤት ተወስኗል። ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የስራ ውል ላይ የተመሰረተ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት በህግ አግባብ እስከሚቋረጥ ድረስ ቀጣይነት ያለው ግንኙነት እንደሚሆን የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ልዩ ባህሪ የስራን ውል መነሻ በማድረግ ሉቀርቡ ከሚችለት የመብት ጥያቄዎችና እነዚህ የመብት ጥያቄዎች ላይ ተፈጻሚነትና ገዥነት ካለው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ለመረዲት ይቻላል። ማንኛውም አሰሪ በስራ ውለ ከተስማማባቸው ልዩ ግዳታዎች በተጨማሪ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ 377/96 አንቀጽ 12 የተዘረዘሩት በህግ የተጣለበት ግዳታዎች እንዲለበት ከህጉ ድንጋጌ ለመረዲት ይቻላል። ለሰራተኛው ደመወዙንና ላልች ክፍያዎችን በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ወይም በህብረት ስምምነት መሰረት የመክፈል ግዳታ አሰሪው እንዲለበት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 2 ተደንግጓል።
ይኸም የሚያሣየው ሰራተኛው አሰሪው በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ህግ መሰረት ሉከፍለው የሚገባውና ያልከፈለው ክፍያ መኖሩን ወይም በህብረት ስምምነቱ መሰረት ሉከፍለው የሚገባው ክፍያና ሉያከብርለት የሚገባው መብት እንዲለ በተረዲ ጊዜ አሰሪውን የመጠየቅ መብት ያለው መሆኑን ነው። የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነት ካለው ቀጣይነትና ዘላቂነት አንጻር ስንመለከት ሰራተኛው በአንድ ወቅት ሉጠበቅልኝ ወይም ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ያቀረበው የመብት ወይም የክፍያ ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ በልላ ጊዜ መብቱን ወይም ክፍያውን ለመጠየቅ የሚያስችለውን የስራ ውል የህግ ድንጋጌ ወይም የህብረት ስምምነት ዋቢ በማድረግ እንዲይጠይቅ የሚገድበው አይደለም።
ከዚህ አንጻር ተጠሪ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5 በመጥቀስ ያቀረቡት ክርክር ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህ በተጨማሪ ሰራተኛው በአንድ ወቅት ክስ ሲያቀርብ ክፍያዉን ለመጠየቅ የሚያስችለው የስራ ውል፣ የህግ ድንጋጌ ወይም የህብረት ስምምነት ባለመኖሩ ያልጠየቀውን ክፍያ ወይም የመብት ጥያቄ በልላ ጊዜ እንዱከፈለው ከመጠየቅ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 216 ይገድበዋል የሚል መደምደሚያና ትርጉም ላይ መድረስ የአሰሪና ሰራተኛ ግንኙነትን እና የስራ ውል አስመልክቶ የሚነሱ የመብት ጥያቄዎችና ክርክሮች ከላልች ጉዲይ ከሚደረጉ ክርክሮች አንፃር ያላቸውን ውስብስብና ልዩ ባህሪ ያላገናዘበና የአሰራና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ዓላማና ግብ የማያሳካ የህግ አተረጓጏም ነው። ከዚህ አንጻር ስንመለከተው የስር ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ ለተደረጉ የስራ ውል ላላቸው ሰራተኞች የሚያከብራቸውን መብቶችና የሚጠብቃቸዉን ጥቅማጥቅሞች ተጠሪ እንዱያከብርላቸው ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች ከፉልቹን የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5 እና የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 216 በመጥቀስ ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህ ላይ ከተገለጸው በተጨማሪ አመልካች ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ እና በመዝገብ ክስ አቅርበው ከተጠሪ ጋር የተከራከሩበት መሰረታዊ ጭብጥ ለዚህ ክርክር መነሻ ከሆነውና ለስር ፍርድ ቤት በመዝገብ ካቀረቡት ክርክርና ጥያቄ በባህሪውም ሆነ በይዘቱ የተለየ ሆኖ አግኝተነዋል። በተለይም አመልካችና ተጠሪ በመዝገብ የተከራከሩት አመልካች ከተጠሪ ጋር ያለውን የስራ ውል መቋረጥና ከስራ መሰናበቱ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው መሰረታዊ ጭብጥ ላይ ሆኖ እያለ ይህንን መዝገብ በመጥቀስ አመልካች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠርኩ ሰራተኛ ስለሆንኩ ለቋሚ ሰራተኞች የሚከበረው መብትና የሚከፈላቸው የጥቅማጥቅም ጥያቄ ለእኔም ይከፈለኝ በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ የስር ፍርድ ቤት ውድቅ ማድረጉ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪ ለላልች ላልተወሰነ ጊዜ ለተቀጠሩ ሰራተኞች የሚያሟላውን መብትና የሚከፍላቸውን የጥቅማጥቅም ክፍያዎች ለእኔም እንዱያከብር ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 5/1/ እና አንቀጽ 216 በመጥቀስ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሻሽሎል።
አመልካች ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኛ ስለሆኑ ተጠሪ የሁለት ወር ደመወዝ እንዱከፍል በማለት የስር ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጡት የውሣኔ ክፍል ጸንቷል።
በድርጅቱን የህብረት ስምምነትና ደንብ መሰረት ተጠሪ ላልተወሰኑ ጊዜ ለተቀጠሩ ሰራተኞች የሚያከብረውን መብትና የሚከፍለውን የጥቅማጥቅም ክፍያ ለአመልካች ሉያከብርላትና ሉከፍላት ይገባል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሣቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.