No summary available.
ሰኔ 17 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- እነ ተመስገን ገ/እየሱስ ጠበቃ ግርማ ዓለሙ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነ/ፈጅ ኮከብ ስለሺ ቀረበ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የቦነስ ክፍያ ጥያቄ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካቾች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡አመልካቾች የተጠሪ ድርጅት ሰራተኞች ሁነው ካገላገለ በሁዋላ በራሳቸው ፈቃድ ከባንኩ በቅርቡ የለቀቁ መሆኑን ፣ ተጠሪ በ2001 የበጀት አመት አትራፉ በመሆኑ በዚሁ የበጀት አመት ላገለገለ ሰራተኞች የሁለት ወር ደመወዝ ቦነስ የሰጠ ቢሆንም አመልካቾችን ግን ሕጋዊ ባልሆነ ምክንያት የከለከለ መሆኑን ገልጸው የአንድ ወር ደመወዛቸው በቦነስነት ፣ በሕብረት ስምምነቱ መሰረት ደግሞ የድጎማ ክፍያ እንዱከፈላቸው ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚሳይ ነው።
የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም አመልካቾች የቦነስ ክፍያው ያልተከፈላቸው ሕብረት ስምምነቱን መሰረት አድርጎ በወጣው መመሪያ ስር የተመለከቱት ሁኔታዎች ስለማያሟለ ነው በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆን ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ በ06/12/2001 ዓ/ም የወጣው የቦነስ አከፊፈል መመሪያ የተጠሪ ባንክ ሰራተኛ ማህበር ኘሮዝዲንት እና ምክትል ኘሬዝዲንት እንዱሁም የተጠሪ ባንክ ሰራተኛ ማህበር ጸሐፉን ጨምሮ የባንኩ የተለያዩ ክፍል ኃላፉዎች በተገኙበት ስምምነት የተደረሰበት መሆኑን እንደሚያስረዲ በማረጋገጥ በመመሪያው ሕጋዊነት ላይ የተነሣውን የአመልካቾች ክርክር ውድቅ ያደረገ ሲሆን የቦነስ ክፍያ ጥያቄውን ደግሞ በተጠቃሹ መመሪያ ቁጥር 2/ለ/4/ መሰረት አንድ ሰራተኛ ወይም የስራ መሪ ለቦነስ ክፍያው ብቁ የሚሆነው ይህ ቦነስ ክፍያ ተፈቅድ ክፍያ እስከተፈጸመበት እለት ድረስ ድርጅቱን በማንኛውም ምክንያት ከለቀቀ ወይም ለመልቀቅ ማመልከቻ ያላስገባ ሲሆን ብቻ መሆኑን ፣ በእድሜ ጣሪያ ምክንያት በጡረታ የተገለለ በመመሪያው ላይ የሰፈሩትን መስፈርቶች ያሟለ ከሆነ ክፍያ የሚከፈላቸው መሆኑን መደንገጉን በመመልከትና አመልካቾች ከስራ የተሰናበቱት በዕድሜ ጣሪያ ምክንያት በጡረታ ስለተገለለ ሳይሆን እያንዲንዲቸው አመልካቾች ከመመሪያው ተግባራዊነት በፉት ስራ ለመልቀቅ ባቀረቡት መልቀቂያ ማመልከቻ መሆኑን እንዱሁም የድጎማ ክፍያ በሕብረት ስምምነቱ መሰረት የሚከፈለውም በእድሜ ጣሪያ ከስራ ለተገለለ ሰራተኛ መሆኑን በማረጋገጥ የአመልካቾችን ክስ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሣኔ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ የአመልካቾችን መብት በሚያጣብብ መልኩ ያወጣው የቦነስና የድጎማ ክፍያ መመሪያና የህብረት ስምምነት ተቀባይነት ማግኘቱ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 134/2/ ድንጋጌ ጋር የማይሄድ ከመሆኑም በላይ የስር ፍርድ ቤቶች ውሣኔ የፋዳራል ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ለአመልካቾች የቦነስ ክፍያው አይገባቸውም ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል በጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ በተደረገለት ጥሪ መሰረት በመቅረብ የሰበር ችልቱ አስገዲጅ ውሣኔ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑና የተጠሪዎች ጥያቄ ውደቅ የተደረገው ባግባቡ መሆኑን ጠቅሶ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ ሉፀና ይገባል ሲል ተከራክሯል። አመልካቾችም የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
በክርክሩ ሂደት አመልካቾች በተጠሪ ድርጅት ተቀጥረው ሲያገለግለ ቆይተው እድሜያቸው የጡረታ ጣሪያ ሳይደርስ በገዛ ፈቃዲቸው ስራውን የለቀቁ ፣ ተጠሪ መስሪያ ቤትም የቦነስና የድጎማ ክፍያ ለአመልካቾች አይገባም በማለት የሚከራከረው ሕብረት ስምምነቱንና ይህንኑ መሰረት አድርጎ የወጣውን መመሪያ በመመርኮዝ መሆኑን ነው። አመልካቾች የሕብረት ስምምነቱ ህጋዊነት ተፈፃሚነት ላይ በስር ፍርድ ቤት ያቀረቡት ክርክር የታለፈው ሕብረት ስምምነቱ የወጣው ሥርአቱን ተከትል እና የሚመለከታቸውን አካላት በማሳተፍ ስምምነት ተደርሶበት መሆነና በሕብረት ስምምነቱ ላይም የቦነስ አከፊፈል መመሪያና ማውጣት እንደሚቻል ፣ ሰራተኛ ስራ ሲለቅ ድጎማ የሚከፈልበት አግባብ በሕብረት ስምምነቱ መመልከቱ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጦ ሲሆን በዚህ የሰበር ክርክር ደረጃም አመልካቾች የሚከራከሩት የህብረት ስምምነቱ የተሻለ መብት የማይጠብቅ በመሆኑ ተፈፃሚነት ሉኖረው አይገባም በማለት ነው።
በመሰረቱ በተመሣሣይ ጉዲይ በሕግ ከተደነገገው ይልቅ የሕብረት ስምምነቱ ለሰራተኞች የበለጠ ጥቅም የሚያስገኝ ሆኖ ሲገኝ ስምምነቱ ተፈፃሚ እንደሚሆን በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 134/2/ ሥር ተደንግጓል። ለጉዲዮቹ የተደነገገው ሕግ ለሰራተኞቹ የበለጠ ጥቅም የሚሰጥ ከሆነ ግን ሕጉ በስራ ላይ ሉውል የሚገባ መሆኑን ይኸው ድንጋጌ በኃይለ ቃል አስቀምጧል። በመሆኑም ህብረት ስምምነቱ ተፈጻሚነት የሚኖረው ከአሰሪና ሰራተኛ ሕግ የተሻለ ሁኖ ሲገኝ ሲሆን ከሕጉ ተቃራኒ ወይም ያነሰ ጥቅም የሚያስገኝ ሁኖ ከተገኘ ደግሞ ስራ ላይ የማይውል መሆኑን ከድንጋጌው መንፈስ ፣ ይዘትና ቅርፅ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው። በተያዘው ጉዲይ የአመልካቾች ጥያቄ የቦነስና የድጎማ ጥያቄ ነው። አንድ ሰራተኛ ቦነስ ወይም ድጎማ ሉያገኝ የሚገባው ከአሰሪው ጋር በሚኖረው ስምምነት እንጂ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት ለሰራተኛው አሰሪው በአሰሪነቱ የግድ እንዱከፍል ተለይቶ የተቀመጠ ጉዲይ አለመሆኑን ከአዋጁ አንቀጽ 4፣ 12፣ 13፣ አና 53 ድንጋጌዎች ቅርጽ ፣ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በመሆኑም አመልካቾች የሕብረት ስምምነቱ ከአሰሪና ሰራተኛ ሕግ የተሻለ ጥቅም የማይጠብቅ በመሆኑ ተፈፃሚነት ሉኖረው አይችልም በማለት ያቀረቡት ክርክር በአሰሪና ሰራተኛ ሕግ የተጠበቀ መብት ባለመሆኑ አግባብነት ያለው ክርክር ሁኖ አላገኘነውም። ስለሆነም ለጉዲዩ ሕብረት ስምምነቱ ተፈጻሚ የማይሆንበት ምክንያት የለም። ሕብረት ስምምነቱ ተፈፃሚነት ይኖረዋል ከተባለ ደግሞ የቦነስ ክፍያ ጥያቄ የሚፈፀምበት አግባብ በመመሪያ ሉወጣ እንደሚችል በህብረት ስምምነቱ የተመለከተ ሁኖ ይህንኑ መሰረት አድርጎ ተጠሪ ነሐሴ 06 ቀን 2ዐዐ1 ዓ/ም መመሪያ አውጥቶ ስራ ላይ አውሎል። በዚህ መመሪያ ተራ ቁጥር 4 ላይ ከስራ በጡረታ የተገለለና ላልች መስፈርቶችን የሚያሟለ ቦነስን እንደሚያገኙ ተመልክቷል። በዚሁ በመመሪያው ተራ ቀጥር 4 የቦነስ ክፍያ ተፈቅድ እስከ ተፈጸመበት እለት ድረስ በማንኛውም ምክንያት ከሰራ ሰራተኛው ከለቀቀ ወይም ለመልቀቅ ማመልከቻ ያላስገባ ሲሆን ብቻ ቦነሱ እንደሚከፈል መመልከቱን የስር ፍርድ ቤት አረጋግጧል። አመልካቾች ይህንኑ የመመሪያውን ይዘት ትክክል አይደለም በማለት ያቀረቡት ክርክር የላለ ሲሆን አመልካቾች ስራቸውን ለመልቀቅ ማመልከቻውን ያስገቡትና ከስራ የተሰናበቱት መመሪያው ነሐሴ 06 ቀን 2001 ዓ/ም ከመውጣቱ በፉት መሆኑን ፍሬ ነገርን የማጣራትና ማስረጃን የመመዘን ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ጉዲይ ነው። የድጎማ ክፍያን በተመለከተ ደግሞ የሕብረት ስምምነቱ በአንቀፅ 34/1/ እና /4/ መሰረት ሉከፈል የሚችለው ሰራተኛው በእድሜ ብቁነት በጡረታ ከስራ ሲገለል መሆኑን የተረጋገጠ ጉዲይ ነው። በመሆኑም አመልካቾች በእድሜ ብቁነት ሳይሆን በገዛ ፈቃዲቸው ስራቸውን የለቀቁ መሆኑ ከተረጋገጠ እና ሕብረት ስምምነቱም ሆነ የቦነስ ክፍያ መመሪያው የሚከለክሎቸው መሆኑ ግልፅ ነው። አመልካቶች አጥብቀው የሚከራከሩት የሰበር ችልት በመ/ የሰጠው የሕግ ትርጉም ለጉዲዩ አግባብነትና ተፈጻሚነት አለው በማለት ነው። በእርግጥ አንድ ሰራተኛ በበጀት አመቱ ለሚገኘው ትርፍ አስተዋጽኦ ማድረጉ እስከተረጋገጠ ድረስ ስራውን ቢለቅም ቦነሱ ሉከፈለው እንደሚገባ ሰበር ችልቱ በተጠቃሹ መዝገብ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። ይሁን እንጂ በዚህ መዝገብ የተረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ ከሰ/መ/ ከተረጋገጠው ፍሬ ጉዲይ ጋር ሙለ ሙለ ተመሳሳይነት አለው ለማለት የሚቻል አይደለም። ቦነስ ከአሰሪው ለሰራተኛው የሚሰጥ ጉርሻ /የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 53/2/ሐ/ ይመለከቷል/ እንደመሆኑ መጠን አከፊፈለን በተመለከተ ተጠሪ ሥርዓቱን ዘርግቷል። በዚህ ስርዓት መሰረት ደግሞ አመልካቾች የቦነሱና የድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን ሁኔታዎችን የሚያሟለ መሆኑ በሚገባ ተረጋግጧል። በመሆኑም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካቾች ክርክርም ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ሲጠቃለልም አመልካቾች የቦነስና የድጎማ ክፍያ አይገባቸውም ተብል መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም መሰረት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 17 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ ጥር 17 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካቾች የቦነስና የድጎማ ክፍያ አይገባቸውም ተብል የተወሰነው ባግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መ/ቤት ይመለስ።
No topics extracted.