No summary available.
ሰኔ 27 ቀን 2003 ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ጉልላት ወልዳ ጠበቃ ሰይፈ ረታ ቀረቡ ተጠሪ፡- የሸቀጦች ጅምላ ንግድና አስመጪ ድርጅት ነገረ ፈጅ ገ/ማርያም ዋዳሮ ቀረቡ መዝገቡን ተመርምሮ የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ሲሆን በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በአመልካች ከሣሽነት የተጀመረ ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ ከሣሽ በተከሣሽ ድርጅት በወር ብር 2847 እየተከፈላቸው ሲሰሩ ቆይተው ያላቸው የሥራ ውል በጡረታ ምክንያት ከሰኔ 01 ቀን 2001 ዓ.ም የተቋረጠ መሆኑን ገልፀው ከሥራ ከመገለላ ጋር ተያይዞ ሉከፈለኝ ከሚገባው የጥቅማ ጥቅም ክፍያ ብር 7ዐ51.49 ስላስቀሩብኝ ለዚህ ክስ ያወጣሁት ወጪና ኪሣራ ጋር እንዱከፍለኝ የሚል ነው።
ተከሣሽ ለቀረበው ክስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር መልስ የሰጡ ሲሆን ቀርቦ የነበረው የመጀመሪያ ደረጃ ተቃውሞ ከሣሽ ከሥራ የተሰናበቱበትና ክስ ያቀረቡበት ጊዜ መካከል ከ6 ወራት በላይ ያለፈ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ይሆናል የሚል ነው።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከላይ እንደተመለከተው ከካራከረ በኋላ ከሣሽ ከሥራ በጡረታ ከተገለለበት ቀን ሰኔ ዐ1 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ጀምሮ ክስ እስካቀረቡበት ጊዜ ሚያዚያ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም መካከል ያለው ጊዜ በአዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 162/4/ የተደነገገውን የይርጋ ዘመን ደንብ የሚፃረር በመሆኑ እና በወቅቱ የቀረበ ክስ ባለመሆኑ በይርጋ ውድቅ ይሆናል በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 337 መሰረት አፅንቶታል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን አመልካች ታህሣሥ 21 ቀን 2003 ዓ.ም በ2 ገፅ ጽፈው ያቀረቡት የቅሬታ ፍሬ ሃሣብ ተጠሪ ያለበትን የክፍያ ጥያቄ ጥቅምት 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈው ደብዲቤ ያመነ ሲሆን በአሁኑ አመልካች መተማመኛ ያልተደረገበትን ዕዲ ተቀናሽ በማድረግ ክፍያ የፈፀመው ደግሞ ጥቅምት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በመሆኑ ይርጋው የተቋረጠ መሆኑን እየተከራከርኩ ውድቅ መደረጉ ያለአግባብ ነው የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ የካቲት ቀን 2003 ዓ.ም በ2 ገፅ ፅፍ መልስ የሰጠ ሲሆን ፍሬ ሃሣቡ አመልካች ይርጋ ቀሪ ስለሚሆንበት አግባብ በሥር ፍርድ ቤት ያልተከራከረ በመሆኑ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አዱስ ክርክር ማቅረቡ ተቀባይነት የለውም የሚል ነው። የአመልካች የመልስ መልስ ቀርቧል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው ክርክር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የቀረቡትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል። እንደተመረመረውም የቀረበው የክፍያ ጥያቄ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ወይስ አይሆንም? የሚለው ጭብጥ ተይዞ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ አመልካች ለቀረበበት የይርጋ ተቃውሞ ይርጋው ሉቋረጥ ይገባል የሚለውን መከራከሪያ በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት አቅርቧል ወይስ አላቀረበም? የሚለውን ነጥብ መመልከት ተገቢ ነው።
ከዚህ አኳያ አመልካች ይርጋውን ሉያቋርጥ ይችላል ብል የሚከራከረውን በተጠሪ የተፃፈ ደብዲቤ ከክሱ ጋር አያይዞ ያቀረበ በመሆኑ ፣ ከዚያ በመቀጠል የይርጋ ተቃውሞ በተጠሪ ሲቀርብበት ተጠሪ ያለበትን ክፍያ በማረጋገጥ የፃፈው ደብዲቤ ይርጋን ያቋርጣል በማለት የተከራከረ መሆኑን ችልቱ ተረድቷል። ይሄ ከሆነ ደግሞ አመልካች ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ በተመለከተው ፍርድ ቤት ያላቀረበውን ክርክር እያቀረበ ነው የሚባል አይደለም። ይልቁንም በበታች ፍርድ ቤት ሲያነሣው የነበረ እና ፍርድ ቤቱ ሣይመለከተው ያለፈው መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑ በሰበር ሰሚ ደረጃ የተነሣ አዱስ ክርክር ነው በማለት ተጠሪ ያቀረበውን ክርክር አልተቀበልነውም።
በልላ በኩል የአመልካችን ክርክር አግባብነት ስንመለከት በእርግጥ በአዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 162/4/ መሰረት ከሥራ ውለ መቋረጥ ጋር ተያይዞ ሉከፈለኝ የሚገባ ክፍያ አለኝ በማለት የሚቀርበው ክስ በ6 ወር ይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ይደነግጋል። ተጠሪም እየተከራከረ ያለው አመልካች በጡረታ የተገለለበት ጊዜ እና ክስ ያቀረበበት ጊዜ መካከል ያለው ጊዜ ከ6 ወራት በላይ ሆኖአል የሚል ነው። ይሄንን የይርጋ ተቃውሞ በተመለከተ አመልካች ከበታች ፍርድ ቤት ጀምሮ እስከ ሰበር ሰሚ ችልት ድረስ እየተከራከረ ያለው ተጠሪ በፃፈው ደብዲቤ የይርጋ ዘመኑ ይቋረጣል በሚል ነው። ይሄንን በተመለከተ ጥቅምት 3ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተጠሪ ተፃፈ በማለት የተነሳው ነጥብ ስለመፃፍ ግራ ቀኙን አላከራከረም። በዚህም ደብዲቤ ለአመልካች የሚከፈል ክፍያ እንዲለና ሆኖም የሚቀናነሱ ክፍያዎች በዚሁ ደብዲቤ የተገለፁ መሆኑን ችልቱ ተረድቷል። ይሄ ከሆነ ደግሞ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 164/3/ መሰረት ይርጋን ለማቋረጥ ከሚችለት ምክንያቶች አንደ በመሆኑ ይርጋው በዚሁ ደብዲቤ ይቋረጣል ብለናል። ይርጋ ዘመን ከተቋረጠ ደግሞ አዱስ የይርጋ ዘመን መቆጠር የሚጀምር ስለመሆኑ ስለዚሁ የሚደነግግ የፍ/ብ/ሕግ አንቀጽ 1852/1/ ሥር የተደነገገ በመሆኑ ከጥቅምት 26 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ጀምሮ ጊዜውን ስንቆጥር ክስ እስከቀረበበት ሚያዚያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም ድረስ 6 ወራት ያላለፈው በመሆኑ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆን አይደለም ብለናል።
በዚሁ መሰረት ጉዲዩን በመጀመሪያ ያየው የፋ/የመ/ደ/ፍርድ ቤት ከላይ እንደተመለከተው መወሰን ሲገባው የቀረበው ክስ በይርጋ ውድቅ ነው በማለት መወሰኑና የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትም ይሄንን ሣያስተካክል ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ብለናል።
በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመዝ/ በቀን 02/03/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመዝ. በቀን 07/10/2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሮአል።
የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ስለማይሆን በፍሬ ጉዲይ ተገቢውን ማጣራት ከተደረገ በኋላ የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰናል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ግራ ቀኙ ላይ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ከፋ/የመ/ደ/ፍቤት የመጣው የመዝ.ቁ . 33762 ወደ መጣበት ይመለስ ብለናል።
No topics extracted.