No summary available.
መጋቢት 8 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አሉ መሐመድ አመልካች፡- የኦሮሚያ መንገድች ባለሥልጣን ተጠሪ፡- አቶ ግርማ ወዮሳ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው ሰራተኛው የአሁኑ ተጠሪ የተቀጠረበትን የአሰሪውን ሥራ በመሥራት ላይ እያለ ድንጋይ ወድቆበት ሁለት የእግሮቹ ጣቶች ተቆርጠው ዘላቂ የአካል ጉዲት ደርሶበታል ተብል በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 109(3) መሰረት ካሣ ብር 57,442.66 እንዱከፈለው በሚል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 80(3) መሰረት የቀረበ ነው።
የጉዲት ካሣውን ክስና ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ አይቶ ውሣኔውን የሰጠው የግራር ጃርሶ ወረዲ ፍ/ቤት ሲሆን ቀጥልም የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ጉዲዩ በይግባኝ ቀርቦለት ክርክሩን ከሰማ በኋላ መርምሮ በሰጠው ውሣኔ ወረዲው ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት አጽንቶታል። በመጨረሻም የአሁኑ አመልካች ሰራተኛው ዘላቂ የአካል ጉዲት ደርሶበታል ተብል ካሣ እንዱከፈለው ተብል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታውን አቅርቦ የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም በጉዲዩ ላይ ግራቀኙን ካከራከረ በኋላ መርምሮ በሰጠው ውሣኔ በወረዲው ፍ/ቤትም ሆነ በዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት ሉያፀናው ችሎል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ በዚህ ምክንያት የቀረበ ሲሆን የአመልካች ነገረ ፈጅ በ13/1/2003 ዓ.ም ጽፈው ባቀረቡት የሰበር ማመልከቻ የካሣውን ጉዲይ በየደረጃው ያዩት የክልለ ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል።
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ ተብል በመወሰኑ ማመልከቻው ለአሁኑ ተጠሪ ተልኮ ቀርቦ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጓል። በዚህም መሰረት ተጠሪ በ23/5/2003 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካች በእኔ ላይ ጉዲት ስለመድረሱ እያየና በህክምና ማስረጃም ተረጋግጦ እያለ ሉከፈለኝ የሚገባውን ካሣ እንዲይከፈል ለማድረግ ለሰበር ችልት አቤቱታ ማቅረቡ ተቀባይነት ሉሰጠው አይገባም፣ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም፣ ኪሣራ ተቆርጦልኝ መዝገቡ ሉዘጋ ይገባል በማለት ተከራክሯል። የአመልካች ነገረ ፈጅም በተጠሪው በኩል በቀረበው መልስ ላይ በጽሐፍ የመልስ መልስ ሰጥቶበታል። የአመልካች ነገረ ፈጅ አጥብቆ የሚከራከረው የቀረበው የሕክምና ማስረጃ በአሁኑ ተጠሪ አካል ላይ ስለደረሰው ጉዲት መጠን የሚያረጋግጥ ስላልሆነ ቋሚ ሙለ የአካል ጉዲት ደርሶበታል ተብል ካሣ ሉወሰንለት አይገባም፤ የጉዲቱ መጠን ባልተገለፀበት ሁኔታ ካሣ እንዱከፈለው መወሰን ስለማይቻል እንደገና ወደ ሆስፑታል ተልኮ የጉዲቱ መጠን ተገልጾ መቅረብ አለበት በማለት ነው።
የጉዲዩ አመጣጥና የክርክሩ ይዘት ከዚህ በላይ እንደተመለከተው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን አግባብነት ካላቸው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሯል።
እንደመረመረውም በአሁኑ አመልካችና በተጠሪው መካከል የአሰሪና ሰራተኛ የሥራ ውል ግንኙነት መኖሩና ሰራተኛው የአሁኑ ተጠሪ በአሰሪው የተቀጠረበትን ሥራ በማከናወን ላይ እያለ ጉዲት የደረሰበት መሆኑ የሚያከራክር አይደለም። የሚያከራክር ሆኖ የተገኘው የአካል ጉዲት መጠን ደረጃው የሚመደበው በጊዜያዊ የአካል ጉዲት ነው ወይንስ ዘላቂ ከፉል የአካል ጉዲት ወይንም ደግሞ በዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት መሆን አለመሆኑ እና የካሣው መጠን እንዳት ይወሰናል የሚለው ነው።
በሰራተኛው /በአሁኑ ተጠሪ/ ላይ ጉዲት የደረሰው በየትኛው አካለ ላይ ነው? በቀረበው የሕክምና ማስረጃስ የተረጋገጠው ምንድነው? የሚለውን በተመለከተ፡ተተርጉሞ ከዚህ መዝገብ ጋር ተያይዞ በቀረበው የግራር ጃርሶ ወረዲ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ ተጽፍ የሚገኘው እና ቀጥል ጉዲዩን በይግባኝ ያየው የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በውሣኔ ላይ የገለፀው ፍሬ ነገርም ሆነ የማስረጃ ሁኔታ የተምታታ ከመሆኑም በላይ በዚህ መዝገብ በነበረው የክርክር ሂደት ሰራተኛው የአሁኑ ተጠሪ በግንባር በችልት ተገኝቶ ስለደረሰበት የአካል ጉዲት ተጠይቆ ከገለፀውና ካሣየው ጋር የማይገናኙ ነገሮች ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። የግራር ጃርሶ ወረዲ ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ ላይ የአሁኑ ተጠሪ ባቀረበው የክስ ማመልከቻ ላይ የፃፈው ነው ብል ያሰፈረው በእግሩ ላይ ድንጋይ ወድቆበት እግሩ የተሰበረና ሲሰራ የነበረውን ግንበኝነት ለመሥራት የማያስችለው ዘላቂ የአካል ጉዲት የደረሰበት ስለመሆኑ የሚገልጽ ሲሆን የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ደግሞ በውሣኔው ላይ በክሱ የተገለፀ ነው ብል የፃፈው ለድልድይ የሚሆን ድንጋይ እየጠረበ እያለ ድንጋይ ወድቆበት ሁለት የእግር ጣቶቹ ተቆርጠው እግሩም ተሰብሯል የሚል ነው። የግራር ጃርሶ ወረዲ ፍ/ቤትም በውሣኔው ላይ የፍቼ ሆስፑታል የሃኪሞች ቦርድ የፃፈው የህክምና ማስረጃ በአሁኑ ተጠሪ ላይ ጉዲት የደረሰበት በእግር ጣቱ ላይ ስለመሆኑ የሚያስረዲ ነው በሚል መንገድ ገልጾታል። ሆኖም ከሣሹ የአሁኑ ተጠሪ በአካል ቀርቦ ሲጠየቅ የተቆረጡት የእግር ጣቶቹ ሣይሆኑ የግራ እጁ ሁለት ጣቶች እንደሆኑ አሣይቷል። ሲታይም የግራ እጅ ሁለት የመሀል ጣቶች ተጏምደዋል። እግሬም ተሰብሯል ብሎል። በእርግጥ የአሁኑ ተጠሪ ለወረዲው ፍ/ቤት የቀረበው የፍቼ ሆስፑታል የሀኪሞች ቦርድ የሰጠው የሕክምና ማስረጃ ነው በማለት ከመዝገቡ ጋር እንዱያያዝ አድርጏት የተገኘው በእንግሉዘኛ የተፃፈው ሲታይ፡- ………. Patient Girma Weysswa Boru …… …. X-ray showing fracture of the femur, and amputation of tip of two fingers from left hand for which reason referred to Tukur Anbassa Hospital.
But he developed mal union and shortening of the high and difficulty in using his leg as previously.
Thus the board decided the above named patient can’t work as carpainter.
በሚል የሚነበብ ሲሆን ይህም ተጠሪው ቀርቦ የደረሰብኝ ጉዲት ነው ብል ያሣየውን የሚደግፍ ሆኖ ተገኝቷል።
ላላው የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በውሣኔው ላይ የጥቁር አንበሳ ሆስፑታል የሕክምና ቦርድ ጽፎል ብል የጠቀሰው የሕክምና ማስረጃ በሚመለከት ተጠሪው ተጠይቆ ጥቁር አንበሳ ሆስፑታል ሂድ አለመታከሙን ስላረጋገጠ ፍ/ቤቱ ከየት አምጥቶ በውሣኔው ላይ ሉጽፈው እንደቻለ ለመረዲት አልተቻለም። የአሁኑ ተጠሪ ጥቁር አንበሳ ሆስፑታል ሄጄ አልታከምኩም እያለ በውሣኔው ላይ ጥቁር አንበሳ ሆስፑታል ሄድ የታከመበት ማስረጃ እንዱቀርብ ተደርጏ የህክምና ቦርድ በተጠሪ ላይ የደረሰው ጉዲት ዘላቂነት ያለው በፉት ሲሰራ የነበረውን የአናጺነት ሥራ ለመሥራት እንደማይችል አረጋግጧል ተብል የተፃፈውን ለመቀበል አይቻልም።
ሰራተኛው የአሁኑ ተጠሪ የተቀጠረበትን የአሰሪውን ሥራ በመሥራት ላይ ሳለ ጉዲት የደረሰበት ሆኖ ከተገኘ አሰሪው የአሁኑ አመልካች በአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 96(1) ድንጋጌ መሰረት ኃላፉነት አለበት።
በሰራተኛው /በአሁኑ ተጠሪ/ ላይ የደረሰው የአካል ጉዲት መጠን በተመለከተም፡የአዋጁ አንቀጽ 99(1) ‛የአካል ጉዲት“ ማለት የመሥራት ችልታ መቀነስን ወይም ማጣትን በሚያስከትል ሁኔታ በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዲት እንደሆነ የሚያስረዲ ነው።
በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ ‛2“ ሥር በሥራ ላይ የደረሰ የአካል ጉዲት ውጤቶች፡-
የአዋጁ አንቀጽ 100 ‛ጊዜያዊ የአካል ጉዲት“ የሚለውን ሰራተኛው ሥራውን ለተወሰነ ጊዜ በሙለ ወይም በከፉል ለማከናወን እንዲይችል የሚያደርገው የአካል ጉዲት እንደሆነ የሚገልጽ ሲሆን አንቀጽ 101 ደግሞ ዘላቂ ከፉል ወይም ሙለ የአካል ጉዲት የሚባለው እንዳት እንደሆነ የሚያብራራ ነው። በዚህ የሕጉ ትርጓሜ መሰረት ዘላቂ ከፉል የአካል ጉዲት ማለት ጉዲት የደረሰበትን ሰራተኛን የመሥራት ችልታ የሚቀንስ የማይድን በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዲት ነው።
ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ማለት ደግሞ ጉዲት የደረሰበትን ሰራተኛ ማናቸውንም ደመወዝ የሚያስገኝ ሥራ ለመሥራት የሚከለክለው የማይድን በሥራ ላይ የሚደርስ ጉዲት ነው።
በዚህ ጉዲይ በሰራተኛው ላይ የደረሰው የአካል ጉዲት ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት የሚለውን የሚያሟላ መሆን አለመሆኑ ከዚሁ ከአዋጅ አንቀጽ 101(2) አንፃር ሲመረመር የፍቼ ሆስፑታል የሕክምና ቦርድ የሰጠው የሕክምና ማስረጃ በአሁኑ ተጠሪ ላይ የደረሰው የአካል ጉዲት ማናቸውንም ደመወዝ የሚያስገኝ ሥራ ለመሥራት የሚከለክለው የማይድን የአካል ጉዲት ስለመሆኑ የሚያሳይ ባለመሆኑ በሕጉ ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ልባል የሚችል አይደለም። ተጠሪው የፍቼ ሆስፑታል የህክምና ቦርድ በፃፈው የሕክምናው ማሥረጃ ላይ ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፑታል ሂድ እንዱታይ ባለው መሰረት ሣይሄድ መቅረቱን ራሱ ያረጋገጠ ሲሆን አመልካች ተጠሪው እንደገና በልላ ሆስፑታል ታይቶ የጉዲቱ መጠን ተረጋግጦ እንዱቀርብ የጠየቀውንም ከሰጠው መልስ እንደሚታየው የሚስማማበት ሣይሆን ባለው ታይቶ እንዱወሰን የሚጠይቅ በመሆኑ የደረሰበት የአካል ጉዲት ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ስለ መሆኑ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ነው ተብል ካሣ ሉከፈለኝ ይገባል በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም።
አሁን ባለው ሁኔታም ሲታይ በተጠሪው ላይ የደረሰው ጉዲት በሕጉ ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት የሚባል ሆኖ ባይገኝም የአካል ጉዲት የደረሰበት መሆኑ ተረጋግጧል። በሕክምናው ማስረጃም የደረሰበት የአካል ጉዲት ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረበትን ሥራ ለመሥራት እንደማያስችለው ተገልጿል።
አመልካችም በክርክሩ ላይ ተጠሪ ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረበትን ሥራ ተመልሶ መሥራት ይችላል አላለም። አመልካች በሰራተኛው ላይ የደረሰው ጉዲት ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር ካሣ ሉከፈለው አይገባም በማለት የሚያቀርበው ክርክር በሕጉ ተቀባይነት የሚሰጠው አይደለም።
የአዋጁ አንቀጽ 109(3)(ለ) በሰራተኛው ላይ የደረሰው ጉዲት ከዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት መጠን በታች ሆኖ ከተገኘ በዚሁ አንቀጽ ንዐስ አንቀጽ 3(ሀ) ክፍያ መሰረት ሆኖ ከአካል ጉድለት ደረጃው ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ክፍያ እንደሚሰጠው የሚደነግግ ነው።
በአሁኑ ተጠሪም ላይ የደረሰው ጉዲት ከዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት መጠን በታች ነው ለማለት ስለተቻለ በዚሁ ድንጋጌ መሰረት ተመጣጣኝ የሆነ የጉዲት ካሣ እንዱያገኝ መወሰን ይኖርበታል። ሕጉ እንዱህ አይነት ሁኔታ ሲያጋጥም የካሣውን መጠን በርትዕ መሰረት አይቶ መወሰን ስለሚፈቅድ በዚሁ መሰረት በማመዛዘን ታይቶ የአሁኑ አመልካች ለሰራተኛው ለአሁኑ ተጠሪ (ሃያ አራት ሺህ) ካሣ ሉከፍለው ይገባል በማለት ተወስኗል። የሥር ፍ/ቤቶች በአሁኑ ተጠሪ ላይ የደረሰውን ጉዲት በአዋጅ አንቀጽ 109(3)(ለ) መሰረት አይተው የካሣውን መጠን መወሰን ሲገባቸው የደረሰበት ጉዲት ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት መሆኑ ሣይረጋገጥ የደረሰበት ጉዲት ዘላቂ ሙለ የአካል ጉዲት ነው በማለት በአዋጅ አንቀጽ 109(3)(ሀ) መሰረት የአመት ደመወዙ በአምስት ተባዝቶ ካሣ እንዱከፈለው በሚል የሰጡት ውሣኔም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ በ10/01/2003 የሰጠው ውሣኔ፣ የኦሮሚያ ሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ በ30/09/2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የግራር ጃርሶ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ በ16/06/2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሻሽል አሰሪው የአሁኑ አመልካች ለሰራተኛው /ለአሁኑ ተጠሪ/ የጉዲት ካሣ (ሃያ አራት ሺህ) እንዱከፍለው ተወስኗል።
በዚህ መዝገብ በተደረገው የሰበር ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
በዚህ መዝገብ የተሰጠው ፍርድ ትክክለኛ ግልባጭ ይተላለፍ።
በዚህ መዝገብ በ26/01/2003 ዓ.ም በግራር ጃርሶ ወረዲ ፍ/ቤት የተከፈተው አፈፃፀም እንዲይቀጥል ተብል የተሰጠው የዕግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ይፃፍ መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.