No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ኤላክትሪክ ሀይል ኮርፕሬሽን አልቀረበም ተጠሪ፡- አቶ ጌትነት መኮንን ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የኦሮሚያ ክልል የጅማ ወረዲ ፍርድ ቤትና የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በሰበር ተጣርቶ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። የክርክሩ መነሻ ተጠሪ አመልካች አላግባብ ከሥራ አሰናብቶኛል ወደ ሥራ እንዱመልስ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ያቀረበው ክስ ነው።
አመልካች ተጠሪ የመብራት ቢል ሰብሳቢ ሆኖ ሲሰራ ብር 11,177.01 /አስራ አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ ሰባት ብር ከዜሮ አንድ ሣንቲም/ ለግል ጥቅሙ ያዋለ መሆኑ በኦዱተር ተረጋግጧል በማለት መልስ ሰጥቷል። ተጠሪ በበኩለ አመልካች ጥፊቱ መፈፀሙን በአወቀ በሰላሣ ቀን ውስጥ ከሥራ አላሰናበተኝም። ስለዚህ በአዋጅ ቁጥር 277/96 አንቀፅ 37/3 በመተላለፍ የፈፀመው የሥራ ስንብት ህገወጥ ነው በማለት ተከራክሯል። የወረዲው ፍርድ ቤት ተጠሪ ከላይ የተገለፀው ገንዘብ ዋጋ ያላቸውን ቢልች ወስድ ለግል ጥቅሙ ያዋለ መሆኑ ከህዲር 21 ቀን 2002 ዓ.ም እስከ ህዲር 29 ቀን 2ዐዐ2 በተደረገው የኦዱት ምርመራ ተረጋግጧል። አመልካች ከሥራ የተሰናበተው ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ደብዲቤ ነው። ስለዚህ ስንብቱ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ 3 የሚጥስ በመሆኑ ህገ ወጥ ነው በማለት አመልካች የተጠሪን የስድስት ወር ደመወዝ ከፍል ወደ ሥራ እንዱመልሰው ወስኗል። አመልካች ይግባኝ ለጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቦ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት በማድረግ ይግባኙን ሰርዞታል።
አመልካች ጥር 9 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ 11,177.01 ብር ቢል ለግል ጥቅም ያዋለ መሆኑን ኦዱተሮች ሪፕርት ያደረጉት ታህሣሥ 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ነው አመልካች ተጠሪን በማገድ በህብረት ስምምነቱ መሰረት የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ካደረገ በኋላ ተጠሪ ከሥራ እንዱሰናበት የካቲት 4 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ተወስኗል። የሥር ፍርድ ቤት ደብዲቤው ውጭ የሆነበትንና ተጠሪ የወሰደበትን ጊዜ ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም በማየት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ ጥር 4 ቀን 2003ዓ.ም በተፃፈ መልስ ከሥራ ለማሰናበት የፃፈው ደብዲቤ ወጭ የሆነው ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም መሆኑን በሰበር ማመልከቻው አምኗል። አመልካች በእኔ በፃፈልኝ የስንብት ደብዲቤ የኦዲተሮች ሪፕርት የደረሰው ታህሣሥ 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም መሆኑና ከሥራ ያገደኝ ጥር 25 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም መሆኑንና ከሥራ ያሰናበተኝ ሚያዚያ 1 ቀን 2002 መሆኑን በግልፅ ካሰፈረ በኋላ ዕውነታውን የሚሸፊፍን የሰበር አቤቱታ ማቅረቡ ተገቢ አይደለም በማለት መልስ ሰጥቷል አመልካች የመልስ መልስ እንዱያቀርብ በተቀጠረበት ቀነ ቀጠሮ ባለመቅረቡ የመልስ መልስ የማቅረብ መብቱ ታልፎል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪን ወደ ሥራ እንዱመልስ የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ በስህተት በተደራቢነት ከተሰጠው የደንበኞች የሑሳብ መሰብሰቢያ ቢል ለግል ጥቅሙ በማዋል ብር 11,177.01 ሣንቲም ያጎደለ መሆኑ በኦዱት ማስረጃ ተረጋግጧል። አመልካች ተጠሪ ይህንን ጥፊት ያጠፊ መሆኑ በኦዱተሮች ሪፕርት የተደረገለት በህዲር ወር መጨረሻ እንደሆነ ፍሬ ጉዲይ የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ሥልጣን ባለው በወረዲው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች ለተጠሪ የፃፈው የስራ ስንብት ደብዲቤ ወጭ የሆነው ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም መሆኑ በሥር ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። አመልካች ተጠሪ እንዱሰናበት የተወሰነው የካቲት 4 ቀን 2002 ዓ.ም ነው። ደብዲቤው ወጭ ሣይሆን የቀረው የተጠሪን መምጣት ስንጠብቅ ነው በማለት በሰበር አቤቱታው የገለፀ ቢሆንም አመልካች ለተጠሪ የሥራ ስንብት ደብዲቤ ወጭ አድርጎ የሰጠው ሚያዚያ 1 ቀን 2002 ዓ.ም እንደሆነ በበታች ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። ስለሆነም አመልካች የተጠሪን ጥፊት ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሰላሣ ቀን ውስጥ የሥራ ውለን ለማቋረጥ የሥራ ስንብት ደብዲቤ ያልፃፈ በመሆኑ የአመልካች እርምጃ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ 3 በተደነገገው የይርጋ የጊዜ ገደብ ይታገዲል በማለት የወረዲውን የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት በመሆኑ በዚህ በኩል አመልካች ያቀረበውን የሰበር አቤቱታ አልተቀበልነውም።
የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሰናበተው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 27 ንዐስ አንቀፅ 3 የተደነገገው የይርጋ የጊዜ ገደብ ካለፈ በኋላ በመሆኑ ህገወጥ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው። ሆኖም የበታች ፍርድ ቤቶች የተጠሪ የሥራ ስንብት ህገወጥ ነው የሚባል ከሆነ ተጠሪ ወደ ሥራ ቢመለስ መልካም የሥራ ግኑኝነት ስለማይኖረን በአማራጭ በአዋጅ ቁጥር 43 ንዐስ አንቀፅ 3 መሰረት የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍለውት ተጠሪ እንዱሰናበት ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበውን አማራጭ የዲኝነት ጥያቄ ማለፊቸው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለው ነጥብ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች በህግ በተደነገገው የጊዜ ገደብ የሥራ ውለን ባለማቋረጡ እንጅ ተጠሪ ከባድ የዕምነት ማጉደል ተግባር የፈፀመ መሆኑ በአመልካች ኦዱተሮች ተረጋግጧል።
አመልካች የደንበኞች ቢልና ክፍያ ሰብሳቢ የነበረ መሆኑ አመልካችና ተጠሪ ካደረጉት ክርክር ተረድተናል። ተጠሪ ሲሰራበት የነበረው የሥራ መደብ ከፍተኛ የሆነ ዕምነት የሚጠይቅ ነው። ስለሆነም ከዚህ በኋላ ተጠሪ ወደ ሥራ ቢመለስ በአመልካችና በተጠሪ መካከል የመተማመን መንፈስ እና የመልካም የሥራ ግኑኝነት ይኖራቸዋል ብል ለመደምደም የማይቻል በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች በአማራጭ ያቀረበውን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም የወረዲው ፍርድ ቤትና የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡትን ውሣኔ በማሻሻል አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 43 ንዐስ አንቀፅ 3 በሚደነግገው መሰረት ለተጠሪ ካሣ ከፍል እንዱያሰናብተውና ክፍያውም በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 43 ንዐስ አንቀፅ 4 መሰረት ታስቦ እንዱከፍለው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል የጅማ ወረዲ ፍርድ ቤትና የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
ተጠሪ ወደ ሥራ ቢመለስ ከአመልካች ጋር መልካም የሥራ ግኑኝነት ሉኖረው የማይችል በመሆኑ አመልካች ለተጠሪ ካሣ ከፍል እንዱያሰናብተው በማለት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 43/4/ መሰረት ወስነናል። የክፍያው መጠን የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀፅ 43/4/ መሰረት ተደርጎ ሉሰላ ይገባዋል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.