No summary available.
ግንቦት 15 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴአመልካች፡- ጊዬን ሆቴልች ድርጅት ነገረፈጅ እሱባለው ዋለልኝ ቀረቡተጠሪ፡- አቶ ስለሺ አምዳ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡትን የሰበር አቤቱታ አጣርቶ ለመወሰን ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው ተጠሪ አመልካች ህዲር 5 ቀን 2001 ዓ.ም አላግባብ ከሥራ አግድትና አሰናብቶት በፍርድ ቤት ውሣኔ ጥቅምት 20 ቀን 2002 ዓ.ም ወደሥራ የተመለሰ መሆኑን ገልፆ በጥቅምት ወር 2001 ዓ.ም የሰራሁበት የሃያ ቀን ደመወዝ የ2001 ዓ.ም የበጀት ዓመት ቦነስና የሰርቪስ ቻርጅ እንደዚሁም ከሀምላ 2001 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2002 ዓ.ም አስር ፏርሰንት የደመወዝ ጭማሪ እንዱከፍል ውሣኔ ይስጥልኝ በማለት አመልክቷል። አመልካች በተከሣሽነት ቀርቦ የሃያ ቀን የደመወዝ ክፍያ በይርጋ ይታገዲል።
ከሣሽ /ተጠሪ/ የ2001 ዓ.ም የበጀት ዓመት ቦነስ የሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ በህግም ሆነ በህብረት ስምምነቱ የማይገባቸው ክፍያ በመሆኑ ክሱ የህግ መሰረት የለውም በማለት ተከራክሯል። የሥር ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከመረመረ በኃላ አመልካች ትርፍ በተገኘበት 2001 ዓ.ም የበጀት ዓመት ስድስት ወር ያልሰሩ በመሆኑ ያቀረቡት የቦነስ ክፍያ ህግንም ሆነ በህብረት ስምምነቱን መሰረት ያደረገ አይደለም። የሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ ተከሣሽ /አመልካች/ ለከሣሽ /ተጠሪ/ የመክፈል ግዳታ የለበትም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ ተጠሪን አላግባብ ከሥራ ያባረረው አመልካች በመሆኑ አመልካች ተጠሪ የጠየቀውን የቦነስና ሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ የመክፈል ሃላፉነት አለበት በማለት ወስኗል።
አመልካች ነሐሴ 12 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ አስራአንድ ወራት እንዲልሰሩ ተረጋግጧል። ተጠሪ ባልሰሩበት ወቅት ለተገኘው ትርፍ የሚከፈለው የቦነስ ክፍያ የሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ እንድንከፍል ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የህብረት ስምምነቱን ግልፅ ድንጋጌ የሚጥስና የህግ መሰረት የላለው ነው። ስለሆነም በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩላቸው የካቲት 25 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ በትምህርት ዝግጅቴና በሥራ ልምድ ከላልች ሰራተኞች በተሻለ ሁኔታ ላይ ነበርኩኝ በ2001 ዓ.ም ያልሰራሁትና የሥራ አፈፃፀም ያልተሞላልኝ አመልካች ከህግ ውጭ ከሥራ ስላሰናበተኝ በመሆኑ ጥፊቱ የተጠሪ ሣይሆን የአመልካች ነው። ስለዚህ አመልካች በህብረት ስምምነቱ የተቀመጡ መስፈርቶችን እንዲላሟላ ከህግ ውጭ ከሥራ አሰናብቶኝ የቆየ በመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገቢና መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካች መጋቢት 19 ቀን 2003 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ ያደረጉት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ለተጠሪ የ2001 ዓ.ም የበጀት ዓመት ቦነስ የሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ እንዱከፍል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች የቦነስ ክፍያ የሚከፍለው የሥራ አፈፃፀሙ ተመዝኖ በአማካኝ ከሃምሳ ፏርሰንት በላይ መሆኑ ሲረጋገጥና ሰራተኛው በበጀት ዓመቱ ከስድስት ወር በላይ የሰራ መሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ በአስረኛው የህብረት ስምምነት በአንቀጽ 34/5/ለ እና አንቀጽ 356/ሐ/ ተደንግጓል።
የሰርቪስ ቻርጅ የሚከፈለውም በወቅቱ ሥራ ላይ ለነበሩና አገልግልት ለሰጡ ሰራተኞች እንደሆነ በህብረት ስምምነቱ አንቀጽ 28/4/ የተመለከተ ሲሆን የደመወዝ ጭማሪ የሚደረገው የሰራተኛው የሥራ አፈፃፀም ከተመዘነ በኃላ እንደሆነ ለመገንዘብ ችለናል። አንድ ሰራተኛ አሰሪው ጥቅም እንዱሰጠው ለመጠየቅ የሚችለው በአሰሪውና በሰራተኛው መካከል የሥራ ውል የህብረት ስምምነቱን ወይም የአሰሪና ሰራተኛ ህግን መሰረት በማድረግ ነው። በአመልካችና በተጠሪ መካከል የተደረገው የሥራ ውል አመልካች ተጠሪን አላግባብ ከሥራ ያገደ ወይም ያሰናበተ መሆኑ ተረጋግጦ በፍርድ ሲወሰን ተጠሪ ባልሰራበት የበጀት ዓመት የሚከፈል የቦነስ ክፍያ የሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ የሚከፍል ስለመሆኑ እንደማይገልፅ ግራቀኙ በሰበርና በሥር ፍርድ ቤት ካደረጉት ክርክር ለመገንዘብ ችለናል። አመልካች ተጠሪን ከሥራ ሲያግደውና ሲያሰናብተው ሥራ ላይ የነበረው አስረኛው የህብረት ስምምነት ተጠሪ ከሥራ ታግድ ወይም ከሥራ ተሰናበቶ በነበረበት ጊዜ የተገኘ የቦነስ ክፍያ የሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ አመልካች እንዱከፍል የማያስግድደው መሆኑን ከላይ ከጠቀስናቸው የህብረት ስምምነቱ ድንጋጌዎች ይዘት ተገንዝብናል።
አሰሪው አላግባብ ከሥራ የተሰናበተ መሆኑ ተረጋግጦ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2 መሰረት ወደ ሥራው እንዱመለስ የተወሰነለት ሰራተኛ በመጀመሪያ ደረጃ የሥራ ክርክር ችልት ከስድስት ወር ያልበለጠ ውዝፍ ደመወዝ እንዱከፈለው ፍርድ ቤቱ የሚወሰንለት መሆኑንና በይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ወደ ሥራ የመመለስ ውሣኔው ከፀና ከአንድ ዓመት ያልበለጠ ውዝፍ ደመወዝ እንደከፈለው ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት እንደሚወሰንለት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43 ንዐስ አንቀጽ 5 ተደንግጓል። ደመወዝ ማለት አንድ ሰራተኛ በሥራ ውለ መሰረት ለሚያከናውነው ሥራ የሚከፈለው መደበኛ ክፍያ ማለት እንደሆነ በአዋጅ አንቀጽ 53 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል። ከዚህ በተጨማሪ ከአሰሪው የሚሰጥ ጉርሻ /ቦነስ/ እንደ ደመወዝ ክፍያ የማይቆጠር መሆኑ በአዋጁ አንቀጽ 53 ንዐስ አንቀጽ 2/ሐ/ በግልፅ ተደንግጓል። ከላይ ከተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎች አመልካች ተጠሪን አላግባብ ከሥራ አሰናብቶ በመገኘቱ ተጠሪን ወደ ሥራ እንዱመልስ የአሰሪና ሰራተኛ የመጀመሪያ ደረጃ የሥራ ክርክር ችልትና የይግባኝ ችልት ሲወስኑ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 45 ንዐስ አንቀጽ 5 መሰረት እስከ ስድስት ወር ወይም እስከ አንድ ዓመት የሚደርስ ውዝፍ ደመወዝ እንዱከፍል ከሚወሰን በስተቀር ተጠሪ ባልሰራበት ዓመት ለላልች ሰራተኞች የተከፈለው ቦነስ የሰርቪስ ቻርጅና የደመወዝ ጭማሪ እንዱከፍል ለመወሰን የሚያስችል የህግ መሰረት የለም።
ስለሆነም የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ተጠሪን ከህግ ውጭ አሰናብቶት በፍርድ ቤት ውሣኔ የተመለሰ በመሆኑ ባልሰራበት ዓመት የተገኘው ትርፍ ለሰራተኞች የተከፈለውን የቦነስ ክፍያ የደመወዝ ጭማሪና የሰርቪስ ቻርጅ ለተጠሪ እንዱከፍል የሰጠው ውሣኔ የአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 43 ንዐስ አንቀጽ 5 እና አንቀጽ 53 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀጽ 2/ሐ/ የሚጥስና የህብረት ስምምነቱን መሰረት ያላደረገ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፍደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
No topics extracted.