No summary available.
የካቲት 21 ቀን 2003 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ በዛብህ እሸቴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ሳሉኒ ኮንስትራክሽን - ጠበቃ አቶ አሥራኤል ተክለ ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ በግራ ቀኙ መካከል የተነሣውን የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ተቀብል በማስተናገድ የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት የትኛው ነው? የሚለውን አስመልክቶ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ለመለየት ሲባል የቀረበ ነው።
የአሁን አመልካች አሰሪዬ የአሁን ተጠሪ ያለአግባብ ከሥራ ያሰናበተኝ ስለሆነ ወደ ሥራ ይመልሰኝ ይህ ካልሆነ ያለአግባብ በመሰናበቴ ምክንያት ልዩ ልዩ ክፍያዎችን ይፈፅምልኝ በማለት ባቀረቡት ክስ በማስረጃነት የቀረቡት ግራ ቀኙ ያደረጉትን የሥራ ቅጥር ውል ነው።
የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ከዚህ የቅጥር ውል በመነሳት የሥራ ቅጥር ውለ የተደረገው በተባበሩት አረብ ኤምሬት የአሰሪና ሰራተኛ ሕግ መሰረት ነው። የሥራ ቦታውም በዚሁ ሀገር በሚገኘው የተጠሪ ቅርንጫፍ መ/ቤት መሆኑ ተረጋጋጧል። ይህም ከሆነ ጉዲዩ በዓለም አቀፍ የግል ሕግ መሰረት ታይቶ ሉወሰን እንደሚገባ አስረጂ ነው። በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 11/2/ መሰረት ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት እንጂ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባለመሆኑ ሥልጣን የለኝም በማለት አመልካችን አሰናብቷል።
የአሁን አመልካች የቅጥር ውል የፈፀምኩት ኢትዮጵያ ከሚገኘው የተከሳሽ መ/ቤት ጋር ነው፤ ይህ አልታየልኝም በማለት ክርክር በማቅረቡ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ክርክሩን እንደ አዱስ የቀረበ መሆኑን ተገንዝቦ ለትክክለኛ ፍትህ አሰጣጥ እንዱረዲ ለዚሁ ክርክሩ ማስረጃ እንዱያቀርብ ቀጠሮ ቢሰጠውም ይህንኑ መፈፀም አለመቻለን አይቶ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ አፅንቶታል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበው ክርክርም በሥር ፍ/ቤት አንስቶ ከተከራከረበት በይዘቱ የተለየ አይደለም።
አመልካች የሥራ ቅጥር ውል የተፈፀመው ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኘው ቅርንጫፍ መ/ቤት ጋር ነው የሚለውን ክርክር በሥር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ለማረጋገጥ የተሳነው መሆኑ የተገለፀ ስለሆነና የዚሁ ክርክር ይዘት በማስረጃ ሉረጋገጥ የሚችልን ፍሬ ነገር ጉዲይ የሚመለከት በመሆኑ በሰበር ደረጃ ላታይ የሚችል ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል ግራ ቀኙ ያደረጉት የሥራ ቅጥር ውል ጋር በተያያዘ ክርክር ቢነሳ ጉዲዩን የሚገዛው የተባበሩት አረብ ኢምሬት ሀገር ሕግ ስለመሆኑና የሥራ ቦታውም በዚሁ አገር ውስጥ ለመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይ ነው።
ይህም ከሆነ ክርክሩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ መሆኑ ብቻ ሳይሆን በግራ ቀኙ መካከል ክርክር ቢነሳ በየትኛው ሀገር ሕግ ታይቶ ዲኝነት ማግኘት የሚገባው ስለመሆኑና የሥራ ቦታውስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሳይሆን በውጭ ሀገር መሆኑን ሁለ ጠቅሰው በውል ለይተው አስቀምጠውታል።
ይህም ከሆነ ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ያላቸው ፍ/ቤቶች የየትኛው ሀገር ነው? ጉዲዩስ የሚታው በየትኛው ሀገር ሕግ ነው የሚለትን ጥያቄዎች ስለሚያስነሳ ይህን መሰል የሕግ ጥያቄ ያካተተ ጉዲይ ደግሞ በዓለም አቀፍ የግል ሕግ መሰረት ታይቶ የሚዲኝ ነው።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤቶች ለማቋቋም በወጣው ሕግ አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 11/2/ መሰረት በክርክሩ ውስጥ የተካተተው የገንዘብ መጠን ይብዛም ይነስም ክርክሩ የዓለም አቀፍ የግል ሕግን የሚመለከት ሆኖ ከተገኘ ከጉዲዩ ዓይነት አንፃር ብቻ በማየት ጉዲዩ ለመጀመሪያ ጊዜ አይቶ ለመወሰን ሥልጣን ያለው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ለመሆኑ ተደንግጓል።
የሥር ፍ/ቤትም የክርክሩን ባህሪ በማየት በዚሁ ሕግ መሰረት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን የሚያስችለው የሥረ ነገር ሥልጣን የለውም። ጉዲዩ መታየት ያለበት በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው በማለት የሰጡት ትርጉም በአግባቡ የተሰጠ እንጂ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩል የሥር ፍ/ቤቶች ጉዲዩ ላታይ የሚገባው በየትኛው ደረጃ በሚገኘው ፍ/ቤት ነው? የሚለውን ለይተው ዲኝነት ሰጡበት እንጂ የኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ጉዲዩን ለማየት የሚያስችላቸው ሥልጣን የላቸውም ከሚል ትርጉም ላይ አልደረሱም። ዲኝነት በዚህ አኳኋን የተሰጠ መሆኑ እየታወቀ የአሁን ተጠሪ ጉዲዩ በኢትዮጵያ ፍ/ቤቶች ላታይ የሚችል አይደለም የሚለው የሰበር ክርክሩ ሥርዓቱን ጠብቆ ያልቀረበ ከመሆኑም በላይ እንደ ሥርዓቱ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ዲኘነት ለማሳረም ቀርቧል እንኳ ቢባል ክርክሩ ሕጋዊ መሰረት ያለው አይደለም።
በዚህ ሁለ ምክንያት በግራ ቀኙ መካከል የተነሣውን የሥራ ክርክር ለመዲኘት ሥልጣን ያለው የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው በሚል በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አልተገኘም። በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80/3/ መሰረት እንዱሁም በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 መሰረት በሰበር ሉተረጎም የሚገባው የመጨረሻ ፍርድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው በዚህም መሰረት የሚከተለውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን የሥረ-ነገር ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት በየትኛው ደረጃ የሚገኘው የፋዳራል ፍ/ቤት ነው የሚለውን አስመልክቶ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተለ በኮ/መ/ቁ. 45888 ታህሣስ 12 ቀን 2002 ዓ.ም. እና በኮ/መ/ቁ. 87855 ሐምል 13 ቀን 2002 ዓ.ም. የሰጡት ብይን እና ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
አመልካች ጉዲዩ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቀርቦ ላታይ ይገባል በማለት ያቀረበው የሰበር ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም ይህ የሰበር ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.