No summary available.
ህዲር 14 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ የቻይና መንገድና ድልድይ ሥራ ድርጅትተጠሪ፣ ግርማ ቡሽራ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ መካከል የተነሳውን የሥራ ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ሲሆን፣ በአመልካች ላይ ክስ የመሰረተው የሥራ ውላን ያለአግባብ አቋርጦብኛል በማለት ነው። በዚህ መሰረትም የተለያዩ ክፍያዎችን እንዱከፍለው እንዱወሰንለት ጠይቆአል አመልካች ደግሞ ለክሱ በሰጠው መልስ ተጠሪ እራሱ ሥራውን ትቶ ሄደ እንጂ እኔ አላባረርኩትም ሥራውን ትቶ የሄደው በብድር የወሰደውን ገንዘብ ላለመክፈል ነው በማለት ተከራክሯል ክሱን የሰማው የባህር ዲር ወረዲ ፍ/ቤት የአመልካችን ክርክር አልተቀበለም። የሥራ ውለ የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በማለትም አመልካች የተጠየቀውን ክፍያ ለተጠሪ ይከፍል ዘንድ ወስኖአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም በወረዲው ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ ያፀና ሲሆን በመጨረሻ የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤትም ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት አቤቱታውን ሰርዞአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሰኔ 22 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ ስህተቱ ይታረምለት ዘንድ ጠይቆአል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው በአመልካች እና በተጠሪ መካከል የነበረውን የሥራ ውል የተቋረጠው ከሕግ ውጪ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? በሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ግራቀኙ ወገኖች ጭብጡን መሰረት በማድረግ ያሰሙት ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር እና ከተሰሙት ውሣኔዎች ይዘት መገንዘብ እንዲቻልነው ተጠሪ ውለ የተቋረጠው ከሕግ አግባብ ውጪ ነው በማለት ሲከራከር፤ ተጠሪ ደግሞ በኔ በኩል ተጠሪን አላሰናበትኩም ሥራውን ትቶ የሄደው እራሱ ነው ይህን ያደረገውም በብድር የወሰደውን ብር 2000 አጠቃል ላለመክፈል ለመሸሽ በማሰብ ነው በማለት ተከራክሮአል ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው ፍ/ቤትም በእርግጥ ተጠሪ በአሰሪው ድርጅት የበላይ ሃላፉ ወይም ሰራተኛን የማሰናበት /የሥራ ውል እንዱቋረጥ የመወሰን/ ሥልጣን ባለው ሃላፉ ስለመሰናበቱ ወይም ሥራውን እንዱለቅ ስለመደረጉ አላረጋገጠም በውሣኔው እንዲመለከተው አመልካች ይሰራው በነበረው የአስፕልት መንገድ አካባቢ ተጠሪ እና አንድ ቻይናዊ ሲጣለ አይተናል የሚለ መንገደኞች የሰጡትን ምስክርነት ብቻ በመያዝ ነው ወደውሣኔው ያመራው ይህ ማለት ግን ተጠሪ በድርጅቱ ከሥራው ስለመሰናበቱ ያመለክታል ማለት አይደለም ከፍ ሲል እንዲመለከትነው አመልካች እኔ ተጠሪን አላሰናበትኩም በማለት እስከተከራከረ ድረስ በእርግጥ በአመልካች ስለመሰናበቱ ተጠሪ የማስረዲት ግዳታ ነበረበት። እንደምንመለከተው ግን ተጠሪ የማስረዲት ሸክሙን /ግዳታውን/ አልተወጣም በልላ አነጋገር በእርግጥ በአመልካች ኃላፉዎች የሥራ ውለ የተቋረጠበት ስለመሆኑ ሉያስረዲለት የሚችል ማስረጃ ከነጭራሹ አላቀረበም። ከዚህ የተነሳም የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ የሕግ መሰረት ያለው ነው ለማለት አይቻልም። የሕግ መሰረት የላለው ውሣኔ ደግሞ ትክክለኛ ውሣኔ ልባል ስለማይችል አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የባህርዲር ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት በመ. መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. ግንቦት 16 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና በአማራ ብ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ ሰኔ 11 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
ተጠሪ የሥራ ውለ ከሕግ ውጪ ተቋርጦአል በማለት የጠየቃቸው ክፍያዎች ሉከፈለት አይገባም ብለናል።
ግራቀኙ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
ም.አ
ታህሣሥ 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ አቶ ንጉስ ሐደሽ አልቀረቡምተጠሪዎች፣ የመቀላ ዩንቨርሲቲ የተማሪዎች ዱን አልቀረቡም መዝገቡ ለዛሬ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መዝገቡን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የግራቀኙን ከሥራ ቅጥር የመነጨን ክርክር የሚገዛው የትኛው ህግ ነው የሚለውን ለይቶ ዲኝነት ለመስጠት ሲባል የቀረበ ነው።
የአሁን አመልካች በተጠሪ ጽ/ቤት በሻሂ ማሽን ሰራተኝነት በደመወዝ ተቀጥሮ ሲሰራ የቆየ ለመሆኑ እና በመጨረሻም ተጠሪ በሰጠው ምክንያት ከሥራ የተሰናበተ ለመሆኑ ተጠሪ የካደው ጉዲይ አይደለም።
በዚህ መነሻ በተጠሪ በኩል የተፈፀመው የሥራ ስንብት የአሰሪና ሰራተኛ ህግ ከደነገገው ውጭ ስለሆነ ልዩ ልዩ ክፍያ ይገባኛል በማለት የአሁን አመልካች ለቀረበው ክስ የአሁን ተጠሪ በሥር ፍ/ቤት በጥሪው መሰረት የበኩለን መልስ ለማቅረብ አልቻልም በሚል ምክንያት ክሱ የቀረበለት የወረዲ ፍ/ቤት የአሁን አመልካችን የክስ አቤቱታ እና እንደ አቤቱታው ለማስረዲት ያቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ ተመልክቶ በግራቀኙ መካከል የሥራ ቅጥር ግንኙነት እንዲለ እና ከዚህ የቅጥር ግንኙነት የተነሳው ክርክር የሚዲኘው በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት መሆኑን ገልፆ ሰራተኛው ለቀጣሪው ከሰጠው የአገልግልት ዘመን አንፃር ሉሰጠው የሚገባው የአንድ ወር የማስጠንቀቂያ ጊዜ ብቻ ሆኖ አልተገኘም የማስጠንቀቂያ አሰጣጥ ሥርዓቱ የተሟላ ሆኖ አልተገኘም ስለሆነም ከአዋጅ አንቀጽ 35/1/ለ/ አንፃር ሲታይ ስንብቱ ህግ ከደነገገው ውጭ ሆኖ ተገኝቷል በማለት ልዩ ልዩ ክፍያ እንዱከፈለው ወስኗል።
በዚህ ውሣኔ ላይ የአሁን ተጠሪ በቀረበው የይግባኝ አቤቱታ መነሻ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ግራቀኙን አከራክሯል።
ዋነኛ የይግባኝ አቤቱታውም የመቀላ ዩኒቨርሲቲ የሚተዲደረው በአዋጅ ቁጥር 515/99 እና በደንብ ቁጥር 61/99 መሰረት በመሆኑ ዩኒቨርቲው ተከራካሪ የሆነበትን ይህን መሰል ጉዲይ በሚተዲደርበት አዋጅ መሰረት እንጂ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ የሚገዛ አይደለም የሚለው ይገኝበታል።
ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤትም የአሁን ተጠሪ እንደሚለው ጉዲዩ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ የሚዲኝ አለመሆኑን የሥር ፍ/ቤት ተገናዝቦ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 9 እና 231/1/ለ/ መሰረት መዝገቡን መዝጋት ነበረበት በሚል ምክንያት ተችቶ የሥር ፍ/ቤትን ውሣኔ ሽሮታል። በዚህ ውሣኔ ቅር ተሰኝቶ ለክልለ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚው ችልት የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አለማግኘቱን ገልፆ ለዚህ የሰበር ጉዲይ ምክንያት የሆነውን የሰበር አቤቱታ የአሁን አመልካች አቅርቧል።
የሰበር ቅሬታው ይዘትም የሥር ወረዲ ፍ/ቤት ጉዲዩን የወሰነው የአሁን ተጠሪ በላለበት ስለሆነ ይህ ተጠሪ በዚያው ጉዲይ ተከራካሪ ለመሆን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 78 መሰረት በክርክሩ እንዱገባ ካልተደረገ በቀር በቀጥታ የይግባኝ አቤቱታ የማቅረብ መብት የለውም ይህን ክርክር ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አላየውም እኔን የቀጠረኝ የመቀላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዱን ጽ/ቤት ሲሆን የተቀጠርኩትም ለሻሂ ክብብ በሻሂ ማሽን ሰራተኛነት ነው የምሰራበት ክበብ በእራሱ ገቢና በጀት የሚተዲደር በተማሪዎች ዱን ጽ/ቤት ቁጥጥር የሚንቀሳቀስ በመሆኑ በቀጥታ በአዋጅ ቁጥር 515/99 ሆነ በደንብ ቁጥር 6199 የሚገዛ የሚሸፈን አይደለም የሚለውን በግራቀኙ መካከል ለተነሳው የህግ ጥያቄ መነሻና አንኳር የሆነውን ክርክር አቅርቧል።
በዚህ የሰበር አቤቱታ ላይ የአሁን ተጠሪ ቀርቦ የበኩለን ክርክር ማቅረብ ይችል ዘንድ መጥሪያ ተልኮለት መጥሪያው የደረሰው ለመሆኑ በእራሱ ማህተም ካረጋገጠ በኃላ እንደ ጥሪው የመደመጥ መብቱን ሉጠቀም አልቻለም። በመሆኑም የአሁን አመልካች በተጠሪ በኩል የተጠቀሱት አዋጆች ለግራቀኛችን የቅጥር ሁኔታ ተፈፃሚነት የላቸውም በማለት ለቀረበው ክርክር በተጠሪ በኩል ላቀርብ የሚችል ማስተባበያ ካለ በአከራካሪ ነጥብነቱ ለይቶ ተገቢውን ዲኝነት መስጠት አልተቻለም የተለየ ማስተባበያ እስካልቀረበ ድረስም አመልካች እንዲለው እንዱያገለግል የተቀጠረበት የሻሂ ክበብ በእራሱ ገቢና በጀት የሚተዲደር ከሆነ ከዚህ መሰል ቁጥር የመነጨን ክርክር ተጠሪ የጠቀሳቸው ህጎች የማይገዙ ይልቁንም ክፍተቱ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ የሚሸፈን ሆኖ አግኝተነዋል። ስለሆነም በመቀላ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ስለተገኘ ወይም ለዩኒቨርሲቲው የህ/ሰብ ክፍል አገልግልት ስለሰጠ ብቻ በደፈናው በሲቪል ሰራተኛ አስተዲደር ህግ ይገዛል ለማለት የሚያበቃ አለመሆኑ እየታወቀ ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት የግራቀኙ ጉዲይ በአሰሪና ሰራተኛ ህግ የሚገዛ አይደለም በዚህም ሳቢያ የወረዲው ፍ/ቤት ጉዲዩን ተመልክቶ ዲኝነት ለመስጠት ሥልጣን የለውም በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ 7229 በ19/6/2001 ዓ.ም የሰጠው ፍርድ እና የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰ/መ/ በ30/7/2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ከሥራ ቅጥር የመነጨውን የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ሥልጣን ባለው የወረዲ ፍ/ቤት ታይቶ ዲኝነት የተሰጠበት ስለሆነ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በይግባኝ ሰሚነቱ ስልጣን የመ/ቁጥር 7229 አንቀሳቅሶ በልላው ጉዲይ ላይ ተገቢውን ዲኝነት ይሰጠበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት መልሰናል። ግልባጩ ይድረሰው።
አመልካች ለዚህ ክርክር ያወጣውን ወጭ በእራሱ ይሸፍን ብለናል። መዝገቡን ዘግተናል።
No topics extracted.