No summary available.
ሕዲር 28 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ መድን ድርጅት - ነ/ፈጅ ማህላት ዓለሙ ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ ሰናይት መጫ (3 ሰዎች) - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል
**
ጉዲዩ በስራ ላይ ስለሚደርስ የሞት ጉዲትና የካሳ አከፊፈለን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪዎች በግልግል ጊዜ ቁጥር II ሣሉኒ ኮንስትራቶሪ ኤስ.ፑ.ኤ ላይ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- አቶ ሙላቱ ገብረ ማርያም በተከሳሽ ድርጅት ተቀጥሮ ሚያዚያ 07 ቀን 2001 ዓ.ም በዋሻ ውስጥ ስራ ላይ እያለ የኦክስጅን እጥረት ገጥሞት ከዋሻው ወደ ውጪ በባቡር ፈርጏ ሲወጣ ከፈርጏው ተንሸራቶ በመውደቅ በኩላሉቱና በጎን አጥንት መቀጥቀጥ አደጋ ደርሶበት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ገልፀው በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ካሳ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት እንዱከፈላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የስር ተከሳሽ ለክሱ በሰጠው መልስም ሟች በአደጋ ምክንያት ሕይወቱ ለማለፈ ከሳሾች ማስረጃ አለማቅረባቸውን በተቃራኒው ሟች እንደታመመ የፈፊ ጤና ጣቢያ በካርድ ቁጥር 760 የጻፈው ሪፈራል የሟች በሽታ ታይፍይድ እና የሽንት ቧንቧ ኤንፋክሽን የሚል ስለሆነ በስራ ላይ እንደደረሰ አደጋ ተወስድ ካሳ የሚከፈልበት ምክንያት የለም በማለት መልሱን ከሰጠ በሁዋላ ባለው የመድን ውል መሰረት የአሁኑ አመልካች ድርጅት ጣልቃ ገብቶ እንዱከራከርለት ጠይቋል። የአሁኑ አመልካችም ለስር ተከሳሽ ሰራተኞች የስራ ላይ ጉዲት የመድን ሽፊን የሰጡ መሆኑን በመግለጽ ሟች በስራ ላይ አደጋ አልደረሰበትም፣ የሞተው በወባና በታይፍይድ ስለሆነ በስራ ምክንያት የመጣ አደጋ ነው ልባል የሚችል ባለመሆኑ ካሳ የሚያስከፍል አይደለም በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የየም ልዩ ወረዲ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ የስር ተከሳሽን ለክሱ ኃላፉ በማድረግ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 110(2) እና 110(3) ድንጋጌዎች መሰረት የሞት ጉዲት ካሳ ለሟች ጥገኛ ለሆኑት ተጠሪዎች እንዱከፈል የአመልካች የኃላፉነት መጠንም በሰበር ተከሳሽ ጋር ባለው የመድን ውል መሰረት እንዱሆን እንዱሁም ክፍያው ለዘገየበት የሶስት ወር ደመወዝ እንዱከፈል ገልፆ ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለየም ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም፣ እንዱሁም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልትም ጉዲዩ የፋዳራል በመሆኑ በክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ላታይ የሚገባ አይደለም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ሰኔ 7 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶችን ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ሟች ሕይወቱ ያለፈው በስራ ላይ በመጣ አደጋ ሳይሆን በታይፍይድ በሽንት ቧንቧ ኢንፋክሽንና ወባ ስለመሆኑ የሕክምና ማስረጃ እየገለፀ የሰው ምስክሮች የሰጡት ቃል መሰረት ተደርጏ አደጋው በስራ ላይ የደረሰ ነው ተብል የሟች ጥገኞች ካሳ እንዱከፈላቸው መወሰኑ ከአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 97፣ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2005፣ 2011 እና 2012 ድንጋጌዎች ውጪ ነው በማለት ውሳኔው እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮም የሞት መንስኤው በስራ ላይ በመጣ ጉዲት ሳቢያ ነው? ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል ተብል ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጏላቸው ቀርበው መስከረም 27 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ስድስት ገጽ የአመልካችን ቅሬታ ነጥቦችም በመንቀፍ፣ የስር ፍ/ቤቶችን ውሳኔ ህጋዊነት በመዘርዘር መልሳቸውን የሰጡ ሲሆን አመልካችም ጥቅምት 07 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታውን በማጠናከር የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንጻር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። በዚህ ሰበር ችልት ምላሽ ያስፈልጋል ተብል የተያዘው ጭብጥ ሟች አቶ ሙላቱ ገ/ማሪያም የሞቱት በስራ ላይ በደረሰባቸው አደጋ ነው? ወይንስ በልላ ምክንያት? የሚለው ነው።
በመሰረቱ በስራ ላይ የሚደርስ ጉዲት ማለት በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ (Occupational injury) ወይም በስራ ምክንያት የሚመጣ በሽታ (occupational disease) እንደሆነ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 95(2) ስር በግልጽ ተመልክቷል። የአዋጅ አንቀጽ 97 ደግሞ በስራ ላይ የሚደርስ አደጋ ማለት ማንኛውም ሰራተኛ ሥራውን በማከናወን ላይ ሳለ ወይም ከሥራው ጋር ግንኙነት ባለው ሁኔታ ከራሱ ውጭ በሆነ ምክንያት ወይም ስራውን ለማከናወን ባደረገው ጥረት ምክንያት በአካለ ወይም በአካለ ማንኛውም ክፍል ተፈጥሮአዊ እንቅስቃሴ ላይ በድንገት ጉዲት በሚደርስበት ጊዜ እንደሆነ ትርጉም ተሰጥቶበታል። በዚሁ ድንጋጌ መሰረት የካሳ ክፍያ ጥያቄ የሚያቀርበው ወገን ጉዲቱ የደረሰው በአንቀጽ 97 በተመለከተው አኳኋን በስራ ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት መሆኑንና እንደዚሁም በድርጊቱና በውጤቱ መካከል ቅርብና ቀጥተኛ የሆነ የምክንያትና የውጤት ግንኙነት መኖሩን (Proximate cause and effect relationship) ማስረዲት እንደሚጠበቅበት ይታመናል። በልላ በኩል የአሰሪው ኃላፉነት በጥፊት ላይ ያልተመሰረተ (strict) ስለሆነ ካሣ ጠያቂው ወገን ጉዲት የደረሰበት መሆኑን ማሳየት ብቻ እንጂ ከዚህ አልፍ የጉዲት አድራሹን ወይንም የአሰሪውን የአእምሮ ሁኔታ (State of Mind) ማስረዲት እንደማይጠበቅበት በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 96 ስር ከተመለከተው ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የምንችለው ጉዲይ ነው።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስ ሟች ሙላት ገ/ማሪያም በስር ተከሳሽ ድርጅት ተቀጥሮ ሚያዚያ 07 ቀን 2001 ዓ.ም በዋሻ ውስጥ ስራ ላይ እያለ የኦክስጅን እጥረት ገጥሞት ከዋሻው ወደ ውጭ በባቡር ፈርጎ ሲወጣ ከፍርጎው ተንሸራቶ በመውደቅ አደጋ ደርሶበት ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱን ተጠሪዎች ገልፀው በስራ ላይ የደረሰ አደጋ ካሳ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሰረት እንዱከፈላቸው ዲኝነት የጠየቁ ሲሆን አመልካች ለጉዲቱ ኃላፉነት የለብኝም የሚለው ሟች በስራ ላይ በደረሰ አደጋ መክንያት ሕይወቱ ለማለፈ ተጠሪዎች ማስረጃ አለማቅረባቸውን በተቃራኒው ሟች እንደታመመ የፈፊ ጤና ጣቢያ በካርድ ቁጥር 760 የጻፈው ሪፈራል የሟች በሽታ ታይፍይድ፣ ወባ እና የሽንት ቧንቧ ኤንፋክሽን የሚል ስለሆነ በስራ ላይ እንደደረሰ አደጋ የሚቆጠር አይደለም በሚል ምክንያት ነው። የስር ፍርድ ቤት የተጠሪዎችን ምስክሮችን አቅርቦ የሰማ ሲሆን የተጠሪዎች ምስክሮች በክሱ በተገለፀው መሰረት መመስከራቸውን ፍሬ ነገር የማጣራትና ማስረጃ የመመዘን ስልጣን ያላቸው የበታች ፍ/ቤቶች የተቀበለት ጉዲይ ነው። አመልካች ይኸው የተጠሪዎች ምስክሮች ቃል ውድቅ ላደረግ ይገባል የሚለው የሕክምና ማስረጃው ከሚገልፀው ይዘት ውጪ ነው በማለትና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2005፣ 2011 እና 2012 ድንጋጌዎችን በዋቢነት በመጥቀስ ነው። ይሁን እንጂ ሟች ጉዲቱ ደረሰ ከተባለበት ጊዜ ጀምሮ በሕክምና ሲረዲ የቆየ መሆኑ የተረጋገጠ ሲሆን የሕክምናው ማስረጃ በሟች ላይ ምርመራ በተደረገበት ወቅት ታዩ የተባለ ሁለም ምልክቶች ከመነሻ የተከሰቱና ለሞቱ ምክንያት መሆናቸውን የሚገልጽ አይደለም። የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በግልጽ የሚያሳየው ደግሞ በተጠሪዎች በኩል የቀረቡት የሰው ምስክሮች ከመነሻው የነበረውን ሁኔታና በሟች ላይ የደረሰውን ጉዲት ገልፀው ለሞቱ ምክንያት የሆነው ነገር የተከሰተው ሟች በስራ ላይ እንዲለ ስለመሞቱ ማስረዲታቸውን በመቀበል የህክምና ማስረጃው ደግሞ የተጠሪዎችን ምስክሮች ቃል ሉያስተባብል አለመቻለን በመግለጽ በጉዲዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎች መመዘናቸውን ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች የቀረቡትን ማስረጃዎች በማመዛዘን ውሳኔ የሰጡ ሲሆን የሕክምና ማስረጃው ይዘት ሲታይም ተጠሪዎች በሟች ላይ በደረሰው አደጋ የኩላሉት መቀጥቀጥ የደረሰ መሆኑን የገለጹትን የህክምና ማስረጃ ሟች የሽንት ቧንቧ ኢንፋክሽን ደርሶበት የነበረ መሆኑ የሚገልጽ ከመሆኑ አንፃር ሲታይ የሕክምናው ማስረጃ በይዘቱ ከሰው ምስክሮች ቃል ሙለ በሙለ የተለየ ነው ለማለትም የሚያስችል አይደለም። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የግራ ቀኙን ማስረጃ በመመዘን አደጋው በስራ ቦታ ላይ የደረሰ ስለመሆኑ የደመደመ በመሆኑ ክብደቱ ለሕክምና ማስረጃ የግድ መሰጠት አለበት ልባል የሚገባው ሁኖ አልተገኘም። በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ፍሬ ነገርን የጣራና ማስረጃዎቹን የመዘነ ከሆነ ይኸው ተገቢ መሆን ያለመሆኑ መሰረት ተደርጏ ጉዲዩ በዚህ ሰበር ችልት የሚታይበት አግባብ የላለ መሆኑን በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 80(3(ሀ)) እና ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ሟች በስራ ቦታ ላይ በደረሰው አደጋ መሞታቸውን በሕጉ አግባብ መረጋገጡን መሰረት አድርጏ የተሰጠ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.