No summary available.
ኀዲር 03 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አንበሳ ጫማ አ/ማህበር -የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ወ/ሮ እትሁን አያላው - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96“ን“ መሰረት አድርጏ የቀረበ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በምእራብ አማራ አሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሳኝ ቦርድ በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- ከአመልካች ጋር የግል ስራ ክርክር ሲያደርጉ ከቆዩ በሁዋላ የፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ.ም በ
የቅጥር ውለ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ነው በማለት ውሳኔ ከሰጠ በሁዋላ ታህሣሥ 16 ቀን 2002 ዓ.ም በቁጥር 11/መ/485/2-3 በተፃፈ ደብዲቤ ከባህር ዲር ሽያጭ መደብር ወደ ሃዋሳ ሽያጭ መደብር ያለበቂ ምክንያት ያዛወራቸው መሆኑን በመግለጽ ዝውውሩ እንዱሰረዝላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም ክሱ የግል የስራ ክርክር በመሆኑ በቋሚ ቦርድ ላታይ የማይገባው መሆኑን በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት አንስቶ የተከራከሩ ሲሆን ፍሬ ጉዲዩን በተመለከተ ግን ድርጅቱ ዝውውሩን ለማድረግ የወሰነው ድርጅቱ ያለበት ቦታ ለኢንቨስትመንት የተሰጠ በመሆኑ በህብረት ስምምነቱ መሰረት መሆኑን ገልፆ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል በማለት ተከራክሯል። ጉዲዩ የቀረበለት ቋሚ ቦርድም ጉዲዩን መርምሮ ዝውውሩ በህብረት ስምምነቱ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች ውጪ የተፈፀመ መሆኑን በማረጋገጥ ዝውውሩ ተገቢ አይደለም በማለት ሰርዞታል። ይህ ውሳኔ በየደረጃው ባለት የክልለ ፍርድ ቤቶችም ተቀባይነት አግኝቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ድርጅት ወኪል መጋቢት 20 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ቦርደ ጉዲዩን አይቶ ለመወሰን አይችልም፣ዝውውሩም የተከናወነው በሕብረት ስምምነቱ መሰረት ነው የሚለ ምክንያቶችን በመዘርዘር ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የተጠሪ ዝውውር ሕገ ወጥ ነው ተብል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏአል። በዚህም መሰረት ተጠሪ ቀርበው የፁሁፍ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ በአመልካች ላይ የግል የስራ ክርክር አቅርበው በዚህ ሰበር ችልት ተጠሪ ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠረች ሰራተኛ ነች ተብል ውሳኔ ጥቅምት 25 ቀን 2005 ዓ.ም ተሰጥቶ አመልካች ድርጅት ታህሣሥ 16 ቀን 2002 ዓ.ም ዝውውሩን መፈፀሙን፣ ዝውውሩን ለመፈፀም አመልካች በምክንያትነት የጠቀሰው ድርጅቱ ያለበት ቦታ ለኢንቨስትመንት በመፈለጉ ቦታውን እንዱለቅ ከሚመለከተው አካል ትእዛዝ የደረሰው መሆኑን፣ሆኖም ዝውውሩ በሁለም ሰራተኛ የተከናወነ ሳይሆን በተጠሪ ላይ ብቻ መሆኑን ነው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ቋሚ ቦርድም ዝውውሩ በህብረት ስምምነቱ ላይ በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረት የተደረገ ሳይሆን ከሕጋዊ ምክንያቶች ውጪ መከናወኑን በፍሬ ነገር ደረጃ ማረጋገጡን ከቦርደ ውሳኔ ይዘት ተገንዝበናል። በመሆኑም ፍሬ ነገርን ለማጣራትና ማስረጃን ለመመዘን ስልጣን ያላቸው ቦርድና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መደበኛ ችልት ዝውውሩ በህብረት ስምምነቱ ከተመለከቱት ምክንያቶች ውጪ ስለመፈፀሙ በፍሬ ነገር ደረጃ የተስማሙበት ከሆነ ሉነሳ የሚችለው ጥያቄ የፍሬ ነገር ወይም የማስረጃ ምዘና እንጂ የሕግ ትርጉም ጥያቄ አይደለም። ፍሬ ነገርና ማጣራት ወይም ማስረጃን መመዘን ደግሞ የዚህ ሰበር ችልት ሥልጣን አለመሆኑን ከኢ.ፋ.ዱ.ሪ ፏብሉክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80(3(ሀ) እና ከአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። በመሆኑም ዝውውሩ ሕገ ወጥ ነው የተባለው ተጠሪ ከአመልካች ላይ የነበራቸው ክስና ከዚህ በሁዋላ የተከናወኑትን ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፤ማስረጃዎቹም ተመዝነው በመሆኑ የመሰረታዊ የሕግ ስህተት መመዘኛን የማያሟላ እና በዚህ ችልት ላታይ የሚችል ሁኖ አላገኘውም። በዚህም ምክንያት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩን ወስነናል።
በጉዲዩ ላይ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 06880 መጋቢት 14 ቀን 2002 ዓ.ም የቦርደን ውሳኔ በማጽናት የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.