No summary available.
ህዲር 13 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ዲሸን ባንክ አ.ማ ነ/ፈጅ የሺወርቅ ይመር ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዘነበ ድንቄሣ ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ አዋጅ ቁጥር 377/96 ‛ን“ መሰረት ያደረገ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በፋዳራለ መጀመያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በአመልካች ድርጅት ውስጥ ላይ በማገልገል ላይ እያለ በጋዜጣ ላይ አስተያየት ሰጥተሃል በሚል ሰበብ አመልካች ድርጅት ከታህሳስ 14 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ያላግባብ ከሥራ ያገዲቸው መሆኑን በመግለጽ ወደ ሥራ እንዱመለሱ የታህሳስ ወር ደመወዝ ከተለያዩ ወጪና ኪሳራዎችጋር እንዱከፈላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መከላከያ መልስም ተጠሪ በአመልካች ላይ ከባድ ጉዲት እያደረሱ በመሆኑ ጉዲዩ እስኪጣራ ድረስ ከስራ መታገዲቸውን ገልፆና እግደም በአግባቡ የተሰጠ መሆኑን ጠቅሶ እግደ ሉነሳ አይገባውም ላልሰሩበት ጊዜ ደመወዝ ሉከፈላቸው እንደማይገባ ገልጾ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዮን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም አመልካች ተጠሪን ከስራ ያገዲቸው በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 18 መሰረት ለማገድ የሚያበቁ ሕጋዊ ምክንያቶች በላለበት ሁኔታ መሆኑን ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የአዋጅ አንቀጽ 27(4) ድንጋጌ ሲታይም እግድ የሚፈቀደው በሕብረት ስምምነት ላይ በተመለከተው መሰረት መሆኑን ገልፆ ሕብረት ስምምነቱ በላለበት ሁኔታ ተጠሪን አመልካች ከሥራ ማገደ ሕገ ወጥ ነው በሚል ድምዲሜ ተጠሪን የታህሳስ ወር 2002 ዓ.ም ደመወዝ በመክፈል አመልካች ወደ ሥራ እንዱመለስ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ መጋቢት 06 ቀን 2002 ዓ.ም በጻፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(4) ድንጋጌ ጥፊት መኖሩን አሰሪው እስከሚያጣራ ድረስ ሰራተኛን ከስራ በማገድ ጉዲዩን ለማጣራት የሚችል መሆኑን ፈቃጅ በሆነ አገላለጽ ደንግጎ እያለ የሕብረት ስምምነት ከላለ ተፈጻሚነት የለውም በሚል የአመልካች እርምጃ ሕገ ወጥ ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታዘዙ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው መስከረም 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ነገረ ፈጅም ጥቅምት 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ተጠሪን ከስራ እና ደመወዝ ያገዲቸው ተጠሪ በድርጅቱ ላይ ጉዲት እያደረሱ ነው በሚል ጉዲዩን እስከሚያጣራ ድረስ ሲሆን ለእርምጃው ህጋዊነት በዋቢነት የሚጠቅሰውም አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27/(4) ስር የተመለከተውን መሆኑን ሲሆን የበታች ፍርድ ቤቶች የአመልካችን እርምጃ ሕገ ወጥ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሱት ሕብረት ስምምነት ሳይኖር በአዋጁ አንቀጽ 27(4) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈጻሚነት የለውም በሚል ምክንያት መሆኑን ነው። በመሆኑም በዚህ ችልት የሕግ ትርጉም የሚያስፈልገው ነጥብ የሕብረት ስምምነት የላለው አሰሪ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27(4) መሰረት የማገድ እርምጃ መውሰድ አይችልም ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች መወሰኑ ባግባቡ ነው? ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
በመሰረቱ የቅጥር ውል ባይቋረጥም አሰሪውና ሰራተኛ ከግዳታዎቻቸው ለተወሰነ ጊዜ ነፃ የሚሆኑባቸው ሁኔታዎች ያለ ስለመሆኑ አዋጁ ቁጥር 377/96 ከአንቀጽ 17 እስከ 22 ድረስ የተደነገጉት ድንጋጌዎች ያሳያለ። የቅጥር ውል ሲታገድ ምክንያቶቹ የተለያዩ ሉሆኑ እንደሚችለ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎችና ከአንቀጽ 27(4) እና 184 ድንጋጌዎች መረዲት ይቻላል። ለአሁኑ ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው የእገዲ አይነት በአዋጁ አንቀጽ 27(4) ስር የተመለከተው ከዱስፔሉን ጋር ተያይዞ የሚፈፀምና የስራ ውልን ለማቋረጥ የሚያስችለ ጥፊቶችን ለማጣራት የሚደረግ እገዲ ነው።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት በአንቀጽ 27 ስር በተመለከቱት ምክንያቶች መሰረት የስራ ውለን ያለማስጠንቀቂያ እንዱቋረጥ ከመደረጉ በፉት ሰራተኛውን ለአንድ ወር ያህል ከስራ አግድ ማቆየት ስለሚቻልበት ሁኔታ በህብረት ስምምነት ሉወሰን ይችላል ተብል ተደንግጓል። የድንጋጌው ዓይነት ዓላማ አሰሪው በአስተዲደራዊ ሥልጣኑ ሰራተኛው ለሚፈጽመው ጉድለት ተገቢውን የዱሲፔሉን እርምጃ ለመውሰድ ይችል ዘንድ ሰራተኛው ፈፀመ የተባለውን የሥነ ምግባር ጉድለት በተገቢው መንገድ ለማጣራትና ለመመርመር እንዱችል ማድረግ ነው። ሕጉ ይህንን አላማ ለማሳካት ይቻል ዘንድ እገዲ ማድረግን የሚፈቅድ ሲሆን እገዲው የሚቆይበትን የጊዜ ገደብም ከአንድ ወር መብለጥ እንደላለበት ያስቀምጣል። ሕጉ አሰሪው እገዲውን ሲፈጽም ከድርጅቱ ሰራተኛ ማህበር (በህብረት ስምምነት መሰረት) ጋር በመስማማት ለመወሰን እንደሚችል ያሳያል። ሆኖም የህብረት ስምምነት የላለው ድርጅት ሰራተኛውን ቢያግድ እገዲው ሕገ ወጥ ሉባይ ሚችል ስለመሆኑ የድንጋጌው ይዘትና አቀራረጽ አያሳይም። የእገዲው አላማ በሰራተኛው ተፈፀመ የተባለውን የስነ ምግባር ጉድለት በተገቢው መንገድ ማጣራትና ለመመርመር አሰሪውን ለማስቻል ነው ከተባለ የሰራተኛ ማህበር የላለው (የሕብረት ስምምነት (የላለው) ድርጅት ሰራተኛው ፈፀመ ለተባለ ጉድለት እገዲ በማድረግ የዱስፔሉን ግድፈቱን ለማጣራት ወይም ለመመርመር እይችልም የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ድንጋጌው በይዘቱ ሲታይ ፈቃጅ እንጂ ክልከላ ያበጀ አይደለም። እገዲው የሚደረግበት አላማ ሲታይ እውነቱ በትክክል እንዱወጣ በሕጋዊ ምክንያት የስራ ውል እንዱቋረጥ ለማድረግ፣ ሰራተኛውም ለአሰሪው ታማኝ በመሆን አገልግልቱን እንዱሰጥ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንዱሁም የኢንደስትሪ ሰላምን ማስፈን ነው። ሕግ ሲተረጎምም ይህንን ግንዛቤ ውሰጥ ባስገባ መልኩ መሆን እንዲለበት ተቀባይነት ያላቸው የሕግ አተረጓጏም ደንቦች የሚያስገነዝቡን ሐቅ ነው። በልላ አገላለጽ ሕግ ሉተረጎም የሚገባው የሕጉን አላማ በሚያሳካ መልኩ ስለመሆኑ የሕግ አተረጓጏም መርሆዎች ያሳያለ። በመሆኑም አንድ የሕብረት ስምምነት የላለው አሰሪው ሰራተኛው የዱስፔሉን ጉድለት ፈጽሟል የሚልበትን ጉዲይ ለማጣራትና ለመመርመር ሰራተኛውን ከአንድ ወር ጊዜ ላልበለጠ ጊዜ ቢያግድ እርምጃው በአዋጅ ቁጥር 377/1996 አንቀጽ 27(4) የሚሸፈን አይደለም የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት የላለ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በዚህ ረገድ የሰጡት ውሳኔ መሰታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.