No summary available.
መስከረም 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልድ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የፉንጫአ ስኳር ፊብሪካ - ጠበቃ ፍቅሬ ሞያ ቀረቡ ተጠሪ፡- የፉንጫ ስኳር ፊብሪካ መ/ሰ/ማህበር - ነ/ፈጅ ኤልያስ አበበ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የአዋጅ ቁጥር 377/96“ን“ መሰረት አድርጏ የቀረበውን ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በቋሚ ቦርድ ሲሆን አመልካች የነበረው የአሁኑ ተጠሪ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 131 መሰረት መጋቢት 18 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም ከአሁኑ አመልካች ተወካዮች ጋር በሕብረት ስምምነት ላይ ድርድር ጀምሮ በዓመቱ ማለትም መጋቢት 24 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም መጨረሱን፣ ሆኖም የአሁኑ አመልካች የሕብረት ስምምነቱን የተደራደሩት ወኪልቹ ከውክልና ስልጣናቸው ውጪ ተደራድረዋል በሚል ምክንያት ሕብረት ስምምነቱን ልቀበል አልችልም በማለት መግለፁን በመዘርዘር ሕብረት ስምምነቱ ቀርቦ እንዱመዘገብና ሰራተኛውም በድርድሩ መሰረት የተገኙትን መብቶችና ጥቅማ ጥቅሞችን እንዱያገኝ እንዱወስንለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሣይ ነው። የአሁኑ አመልካች ለክሱ በሰጠው መልስም የአመልካች ወኪልች ከተሰጣቸው ስልጣናቸው ውጪ በተወሰኑት ነጥቦች ላይ መደራደራቸውንና የተወሰኑት ነጥቦችም በሕብረት ስምምነቱ የማይሸፈኑ መሆናቸው በመረጋገጡ አስፈላጊው ማሻሻያ እንዱደረግ ለአሁኑ ተጠሪ ምላሽ መስጠቱን በመግለጽ ክሱ ተቀባይነት የለውም ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ቋሚ ቦርድም በጉዲዩ ላይ የኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ የሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴር አስማሚ አስተያየቱን እንዱሰጥበት ከአደረገ በሁዋላ የአሁኑ አመልካች ያቀረበውን ክርክር ውድቅ በማድረግ ሕብረት ስምምነቱ ድርድሩ ያለቀለት ስለሆነ በሁለቱ ወገኖች ተፈርሞ አስፈላጊው ቅጂ በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 131 መሰረት ለመዝጋቢው አካል ተልኮ ይመዝገብ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ የአሁኑ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርብም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃው መጋቢት 23 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የአመልካች ተወካዮች በተወሰኑት ነጥቦች ላይ ከስልጣናቸው ውጪ የፈፀሙት ድርድር መሆኑን የአመልካች ማኔጅመንት አረጋግጦ እነዚህ ነጥቦች እንዱወጡ ያቀረበው ሐሣብ በተጠሪ ተቀባይነት ሣያገኝ ቀርቶ ክሱ ተቀባይነት ማግኘቱ ከውክልና ሕግ ድንጋጌዎችና ከሕብረት ስምምነት ድርድር ሐሣቦች ጋር በማይዛመድ መልኩ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም የአመልካችን መስሪያ ቤትን በመወከል ከተጠሪ ጋር የሕብረት ስምምነት ድርድር ያደረጉት ግለሰቦች በተሰጣቸው ሥልጣን መሰረት ስለመሆኑ መጣራት ያለበት ነው በሚል ምክንያት ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ መጥሪያ ተልኮለት ጠበቃው ቀርበው ሐምል 13 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ከተጠሪ ጋር የሕብረት ስምምነት ለማድረግ ግለሰቦችን በመወከል ድርድር ሲያካሂድ የቆየ ሲሆን ድርድሩ ተጠናቅቆ ጉዲዩን የአመልካች የማኔጅመንት አካል ሲመለከተው አመልካች የወከላቸው ግለሰቦች ድርድሩን ያካሄደት ከተሰጠቸው ሥልጣን ውጪ እና የህብረት ስምምነት በማይሸፍናቸው ጉዲዮች ሁኖ በማግኘቱ ይህንኑ ለተጠሪ እንዲሣወቁ እና ማሻሻያ እንዱደረግ ጥያቄ ማቅረቡን ነው። ተጠሪ የሚከራከረው ደግሞ ድርድሩ ላይ የተሣተፈት የአመልካች ወኪል ግለሰቦች ከስልጣናቸው ውጪ የሰሩት ነገር አለመኖሩንና በሕብረት ስምምነት የማይሸፈን የመብት ወይም የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ የለም በሚል ስለመሆኑም ተመልክተናል።
በመሰረቱ አዋጅ ቁጥር 377/96 ‛አንቀጽ“ 124 እስከ አንቀፅ 135 ድረስ የተመለከቱት ድንጋጌዎች ስለህብረት ስምምነት ትርጉም ስለህብረት ስምምነት ድርድር የህብረት ስምምነት ድርድር፣ የህብረት ስምምነት ድርድር ሥነ ሥርዓት፣ ስለህብረት ስምምነት አመዘጋገብ፣ የሕብረት ስምምነት የሚፀናበት ሁኔታ እና የሕብረት ስምምነት ተፈፃሚነት ወሰን ደንግጎ እናገኛለን። የአዋጁ አንቀፅ 124/2/ እና የአዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 3 ድንጋጌዎች ሲታዩ ተደራዲሪ ወገኖች በስራ ላይ ያለውን ህብረት ስምምነት የስራ ዘመኑ ከማለቁ ወይም ቀደም ብል ሕብረት ስምምነቱን እንዱሻሻል ወይም በልላ እንዱተካ መወሰን ያለባቸው መሆኑን የሚያስገነዝቡን ሲሆን በዚሁ መልክ በሚደረስበት ውሣኔ መሰረት ተደራዲሪዎች የህብረት ስምምነቱን ድርድር ተቀራርበው መስራት ያለባቸው መሆኑን አዋጅ ቁጥር 494/1998 አንቀጽ 3 በግልጽ ያሣያል። አዋጁ የሕብረት ስምምነት ድርድር ላደረግ የሚችልባቸውን ነጥቦችና ድርድሩን ለማድረግ የሚችለ ወገኖች እነማን እንደሆኑም በአንቀጽ 124/2/ እና 126 ስር ደንግጎ እናገኛለን። በመሆኑም ድርድሩ ስለስራ ሁኔታዎች ወይም ስለህብረት ስምምነት ወይም የሕብረት ስምምነትን ለማደስና ለማሻሻል በአሰሪዎችና በሰራተኞች ማህበር ወይም በሕጋዊ ወኪልቻቸው መካከል የሚደረግ ክርክር (NEGOTITON) ስለመሆኑ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ያሣያለ። ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች አስፈላጊነት ሲታይም የአሰሪና ሰራተኛ ወገኖች የመደራደርና ሕብረት ስምምነት የማድረግ መብታቸው በአግባቡና በቀና መንፈስ እንዱጠቀሙ ማስቻል ስለመሆኑ በአዋጁ ማሻሻያ ላይ የተደረገው የውይይት ሰነድ / ሀተታ ዘምክንያት/ ያሣያል። የሕብረት ስምምነት ከተፈረመ በሁዋላ የስምምነቱ አስፈላጊ ቅጅ በተዋዋይ ወገኖች አማካኝነት ለሰራተኛና ማህበራዊ ሚኒስቴር ለምዝገባ እንደሚላክ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 131 ስር ሰፍሯል። የአዋጁ አንቀጽ 133/2/ ድንጋጌ ሲታይም በህብረት ስምምነቱ በልላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር አንድ የሕብረት ስምምነት ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ የፀና እንደሚሆን ያስገነዝባል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የሕብረት ስምምነት ድርድር አመልካች ውክልና በሰጣቸው ወኪልችና በተጠሪ መካከል ስለመከናወኑ የተረጋገጠ ሲሆን አከራካሪው የሕግ ጥያቄ አመልካች ሰነደ በሕብረት ስምምነት ሉፀድቅ አይገባም በማለት ተቃውሞ አቅርቦ እያለ ወኪልቹ ስለፈረሙ ብቻ በሕግ ፉት የፀና ይሆን ዘንድ የድርድሩ ውጤት በሚመለከተው አካል እንዱመዘገብ ዲኝነት ሉያርፍበት የሚገባው ነው ወይ? የሚለው ነው።
ከላይ እንደተገለፀው የሕብረት ስምምነቱ እንዱመዘገብ የሚደረገው ከተፈረመ በሁዋላ ነው።
አመልካች በድርድሩ ወቅት የተሣተፈ ወኪልቹ ሰነደ ህብረት ስምምነት እንዱሆን ስምምነት የደረሱና የፈረሙ ስለመሆኑ ሣይክደ የወኪልቹን ተግባር የሕብረት ስምምነቱ በሚመለከተው አካል ከመመዝገቡ በፉት ተቃውሞታል። የሕብረት ስምምነት ድርድሩ በሕጋዊ ወኪልቹ እንዱከናወን ያደረገ አሰሪ በድርድሩ መሰረት የተደረሰን ስምምነት ለሚመለከተው አካል ቀርቦ ከመመዝገቡ በፉት ቢቃወመው ውጤቱ ምን ይሆናል? የሚለውን ጥያቄ አዋጅ ቁጥር 377/96“ም“ ሆነ የዚሁ አዋጅ ማሻሻያ የሆኑት አዋጅ ቁጥር 466/97 እና 494/98 ድንጋጌዎች ምላሽ አይሰጡም። ይሁን እንጂ አዋጅ ቁጥር 377/96 ድርድሩ በሕጋዊ ወኪልች የሚደረግበትን አግባብ የዘረጋ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕጉ ስለእንደራሴነት የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ጉዲዩን ማየቱ አግባብነት ያለው ይሆናል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 219ዐ ድንጋጌ በተለይ ሲታይም ከስልጣኑ ውጭ ወካይ የተወካይነት ተግባር ለማጽደቅ ወይም ለማፍረስ እንደሚችል ተመልክቷል።
በመሆኑም አመልካች ወኪልቹ በሕብረት ስምምነት ድርድር ላይ ክርክር ሲያደርጉ ቆይተው ሰነደ የሕብረት ስምምነት እንዱሆን በፊርማቸው ያረጋገጡበትን ሁኔታ ያልተቀበለው መሆኑን ምክንያቱን ገልጾ እንዱመዘገብ ፍላጎት የላለው መሆኑን መግለፁ ከመነሻውም ስምምነቱ ገና ወደሚመለከተው አካል ፉት ቀርቦ ያልፀደቀ ከመሆኑ በድርድር ደረጃ ያለ በመሆኑና በወካይነት ስልጣኑም የወኪልቹ ተግባር ሕጋዊ ግዳታ እንዲይጥልበት የማድረግ ሕጋዊ መብት ያለው በመሆኑ የሕብረት ስምምነቱን በፍርድ ኃይል እንዱያስመዘግብ የሚገደድበት የሕግ ምክንያት የለም። በሕጉ አግባብ የሕብረት ስምምነት የፀና ነው የሚባለው በተገቢው መንገድ በአሰሪው መፈረሙና የወኪልቹን ተግባር ማጽደቁ ሲረጋገጥ ነውና።
ተጠሪ ድርድሩ የበረሃ አበልን የማይመለከትና በአመልካች ተገቢ ባለሥልጣን ተፈርሞ እንዱመዘገብ የሚል ሃሣብ መጋቢት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የቀረበ ሁኖ እያለ የአመልካች ጠበቃ የሰበር አቤቱታ ማቅረባቸው ተገቢነት የለውም በሚል ያቀረበው ክርክር ሲታይም በሕጉ አግባብ አመልካች የሰበር አቤቱታውን የተወው መሆኑ እስካልተረጋገጠ እና ጉዲዩን አይተው ዲኝነት ባሣረፈት አካላት ፉትም ተጠሪ ይህንኑ ክርክር አቅርቦ ተቀባይነት ያገኘ ስለመሆኑ የሚያመለክት ሁኔታ በላለበት ይህ ችልት የሚቀበለው የክርክር ነጥብ ሁኖ አልተገኘም። በአጠቃላይ የአመልካች ተገቢ ባለሥልጣን ሰነደ የሕብረት ስምምነት እንዱሆን የበርሃ አበልን በተመለከተ የተቀመጠው ጉዲይ እንዱወጣ ሀሣብ አቅርቦ እያለ ሰነደ በወኪልቹ ተፈርሟል በሚል ምክንያት ብቻ በሚመለከተው አካል ፉት ቀርቦ እንዱመዘገብ የተደረገው ያላግባብ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ ስለአገኘን ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በኢትዮጵያ ፋዳራላዊ ዱሞክራሲያዊ ሪፐብላክ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዲይ ሚኒስቴር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዲይ ወሣኝ ቦርድ በመ/ቁጥር 383/ቀወ1/2ዐዐ1 ጥር 27 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 9ዐዐ31 መጋቢት 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በትእዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች ወኪልቹ ያደረጉትን ድርድር ያለመቀበል ሥልጣን ያለው በመሆኑ በተገቢው ባለስልጣን ያልተፈረመ ሰነድ የሕብረት ስምምነት ሁኖ እንዱመዘገብ እንዱያስደርግ የሚገደድበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸን ይቻለ ብለናል።
ተ.ወ
ህዲር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ አቶ አየለ አበበ ቀረቡተጠሪ፣ የፉንፉኔ የደን ድርጅት ነገረፈጅ ጋንገና ገብረሚካኤል ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው በዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሣሽ አመልካች ተከሣሽ በመሆን ተከራክረዋል።
ተጠሪ አመልካች የድርጅቱ ንብረት ዱ 7 ኤች ተብል በሚጠራው ድዘር ላይ ጉዲት በማድረሱ ብር 227,594.18 ካሣ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ አመልካች ማሽኑን ለሥራ ከማንቀሳቀሱ በፉት ቅባት ዘይትና ውሃ ማየት የነበረበት ቢሆንም ይህንን ሳይፈትሽ በመንዲት እንዱሰባበር በማድረጉ ለጥገና ብር 227,594.18 /ሁለት መቶ ሃያ ሰባት ሺ አምስት መቶ ዘጠና አራት ብር ከአስራ ስምንት/ ሣንቲም ወጭ አድርገናል። ስለዚህ አመልካችና የአመልካች ወኪል ይህንን ገንዘብ እንዱከፍለ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። አመልካች ማሽኑ የተሰበረው በእኔ ችልታና ሙያ ሉፈተሹ የሚችለ የሞተር ቅባት ዘይትና ውሃ ሣልፈትሽ ስለነዲሁት አይደለም። ማሽኑ የተሰበረው በቴክኒክ ባለሙያ ስላትና ክትትል ላደረግበት የሚገባው የመጨረሻ ክፍልች /Final Drive/ በደረሰበት ጉድለት ነው። የፊይናል ድራይቨ ዘይት መፈተሽና መፍታት የእኔ ሥራ ድርሻ አይደለም በማለት መልስ ሰጥቷል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኃላ ሬይስ ኢንጀነሪንግ የሰጠውን ሙያዊ አስተያየት በመመርመር ለማሸኑ ብልሽት አመልካች ፊይናል ደራይቨ ዘይት ሣይፈትሽ በመንዲቱ ነው በማለት አመልካች ብር 227,594.18 /ሁለት መቶ ሃያ ሰባት ሺ አምስት መቶ ዘጠና አራት ብር ከአስራ ስምንት ሣንቲም/ የመክፈል ሃላፉነት አለበት በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ያቀረበ ቢሆንም በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካች የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ያቀረቡ ሲሆን የክልለ ሰበር ችልት አቤቱታቸውን አልተቀበላቸውም።
አመልካች መስከረም 4 ቀን 2000 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የተበላሸው የድዘር ክፍል /ፊይናል ድራይቭ/ በኦፔሬተር በቀላለ የማይፈታና ሰርቪስ የማይደረግ መሆኑ ከሬስ ኢንጅነሪንግ የተላከው ባለሙያ በማረጋገጡ ወደ ሥራዬ ተመልሼ እየሰራሁ እገኛለሁ። በወንጀልም ተከሣሼ በነፃ ተሰናብቻለሁ የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች ማስረጃ ሣይመረምርና ስህተቱ የእኔ አለመሆኑን ሳያገናዝብ አለአግባብ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በሥራ ክርክር ችልት የሰጠው ውሣኔም ሆነ በወንጀል ችልት የሰጠው ውሣኔ የጉዲት ካሣ ከመጠየቅ የሚገድበን አይደለም። ማሸኑ የተበላሸው በአመልካች ጥፊት መሆኑን አስረድተናል የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት በቃል ክርክር መልስ ሰጥቷል። ከዚህ በኃላ ህዲር 14 ቀን 2003 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰበር ችልቱ ባቀረባቸው ጥያቄዎች አመልካችና ተጠሪ በቃል ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር በፅሐፍና በቃል የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል መዝገቡን እንደመረመርነው የተጠሪ ንብረት የሆነው ዱ. 7 ኤች ተብል የሚታወቀው ድዘር ላይ ጉዲት ያደረሰው አመልካች በሥራው ሂደት ማድረግ የሚገባውን ጥንቃቄ ሣያደርግ ድዘሩን በማንቀሳቀሱ ነው በማለት የሚያቀርበው ክርክር የህግ መሰረትና ድጋፍ አለው? ወይስ የለውም? የሚለው ጭብጥ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። አመልካች የድዘሩ ኦፔሬተር መሆኑና የአመልካች የሥራ ድርሻና ሃላፉነት ማሽኑን ኦፔሬት በማድረግ መስራት የሚገባውን ሥራ መሥራት መሆኑ በግራቀኙ የታመነ ጉዲይ ነው።
የአንድ የድዘር ኦፔሬተር ጠቅላላ የሥራ ሃላፉነት የሞተር የመሪ ዘይትና ላልች በቀላለ ሉፈተሹ የሚችለ የድዘሩን አካላት ድዘሩን ከማንቀሳቀሱ በፉት መፈተሽና የተጓደለ ነገር ቢኖር እንዱሟላ ማድረግ እንደሆነ በአመልካችና በተጠሪ በኩል ከቀረበው ክርክርና ማስረጃ ለመገንዘብ ችለናል።
አሁን ድዘሩን ለብልሽት የዲረገውና ተጠሪውን ለጥገና ከፍተኛ ወጭ ያስወጣው /ፊይናል ድራይቭ/ የሚባለው የማሽኑ ክፍል እንደሆነ ይህንን ክፍል ለመፈተሽ የተለየ መፍቻና የተለየ ሥልጣና የሚያስፈልግ መሆኑን አንድ የድዘር ኦፔሬተር የፊይናል ድራይቭ ልዩ መፍቻ ከተሰጠው ፊይናል ድራይቭ እንዳት እንደሚፈታና እንደሚፈተሽ ሥልጠና ከተሰጠውና ይኸው በሥራ መዘርዝሩ በግልፅ ከተካተተ ፊይናል ድራይቭ ዘይት መፍታት የሚችል መሆኑና የመፈትሸም ግዳታ እንዲለበት በማብራራት ሬስ ኢንጅነሪንግ በፅሐፍ የሰጠውን መግለጫ እንድያብራራ የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ አስቀርቦ የሙያ ምስክርነታቸውን የሰማቸው የሬስ ኢንጅነሪንግ ባለሙያ በሰጡት ምስክርነት ያረጋገጡ መሆኑን የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሀምላ 9 ቀን 2000 ዓ.ም በሰጠው ውሣኔ ገልፆል።
ምንም እንኳን በሥራና አሰሪ ክርክር ችልት የተሰጠ ውሣኔ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5/1/ መሰረት የአሰሪውን የፍታብሓር ክስ የማቅረብ መብት የማይገደብ ቢሆንም የአሰሪና ሰራተኛ ክርክር ችልት ውሣኔ ለፍታብሓር ክርክር በማስረጃነት አንዲይቀርብ የሚከለክል ግልፅ የህግ ድንጋጌ የላለ በመሆኑ ውሣኔውን ሰራተኛው በአሰሪው የቀረበበትን ክስ ለመከላከል በማስረጃነት ቢያቀርበው በህግ ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ነው። የፍታብሓር ክሱን የሚያየው ፍ/ቤት ይህንን ማስረጃ ተቀብል የመመዘን ግዳታና ሃላፉነት አለበት።
በያዝነው ጉዲይ ሬስ ኢንጅነሪንግ በፅሐፍ የሰጠው ሙያዊ አስተያየት ጥቅልና ግልፅነት የጎደለው በመሆኑ የሬስ ኢንጅነሪግ ባለሙያ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አሰሪና ሰራተኛ ይግባኝ ሰሚ ችልት በማጣሪያ ምስክርነት ቀርበው አንድ ኦፔሬተር ‛ፊይናል ደራይቨ“ የተባለው የድዘር ክፍል በመፍታት ዘይት ያለው ወይም የላለው መሆኑን ለመፈተሽ የሚችለው ሶስት መሰረታዊ ሁኔታዎች መሟላታቸው ሲረጋገጥ መሆኑን አሰረድቷል። ሶስቱ መሰረታዊ ሁኔታዎችም ፊይናል ድራይቭ ለመፍታትና ለመግጠም የሚያስችል ልዩ ስልጠና ለሰራተኛው በአሰሪው የተሰጠ ሲሆን ፊይናል ደራይቨ ለመፍታት የሚያስችል ልዩ መፍቻ ለሰራተኛው የተሰጠ መሆኑ ሲረጋገጥና በሰራተኛው የሥራ መዘርዝር ፊይናል ደራይቨ የመፍታትና የመፈተሽ ሃላፉነት የኦፔሬተሩ መሆኑ በግልፅ ተፅፍ የተሰጠው መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የፊናል ደራይቨ መፈተሽ የሞተር ዘይት የራዱያተር ውሃና የሀይድሮሉክ ዘይትና የትራንስሚሽን ዘይት እንደመፈተሽ አመልካች ሉፈፅመው የሚገባው ሥራ ነው በማለት የተከራከረ ቢሆንም ተጠሪ አመልካች የድዘሩን ፊይናል ደራይቨ ለመፈተሽ የሚያስፈልገውን ልዩ ሥልጣና የሰጠ መሆኑንና ይህንን የድዘሩን ክፍል ለመፍታት የሚያስችል ልዩ መፍቻ ተጠሪ ለአመልካች የሰጠው ስለመሆኑ በማስረጃ ሣይረጋገጥ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለጉዲቱ ሃላፉ ነው በማለት የወሰነ መሆኑን ለመገንዘብ ችለናል።
በልላ በኩል ተጠሪ ለአመልካች ፊይናል ደራይቨ ለመፍታትና ለመፈተሽ አስፈላጊ የሆነውን ልዩ ሥልጠና ያልሰጠና ይህንን የማሸን ክፍል ለመፍታት የሚያስችለው ልዩ መፍቻ ያልሰጠው መሆኑ የአሰሪና ሰራተኛ ክርክሩን በይግባኝ ሰምቶ በወሰነው ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ስለሆነም ተጠሪ አመልካችን ለጉዲቱ በኃላፉነት ለመጠየቅ በመጀመሪያ ማሟላት ያለባቸው ሶስት ሁኔታዎች መሞላታቸውን ሣያረጋግጥ አመልካች የድዘሩን ፊይናል ድራይቨ ዘይት ሣይፈትሹ ማሽኑን አንቀሣቅሰዋል በማለት የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚና ሰበር ችልት ማፀናታቸው አሰሪው ግዳታና ሃላፉነቱን በአግባቡ የተወጣ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ የማያስገባና በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 12 ንዐስ አንቀጽ /1/ሀ የተደነገገውን የሚጥስ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልትና ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች በተጠሪ ድዘር ላይ ለደረሰው ጉዲት በሃላፉነት አይጠየቅም በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡት ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
No topics extracted.