No summary available.
ሰኔ 16 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ዳኞች፡ ሐጏስ ወልዱ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡ ወ/ሮ አየለች ከበደ - ቀረበች ተጠሪ፡ በላቸው ዋለ ከጠበቃ ውብሰራ ሹመቴ ጋር - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዳዩ የጋብቻን በፍቺ መፍረስ ተከትል የተነሳ የንብረት ክፍፍል ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን አመልካች የጋራ ናቸው ያለቻቸውን ንብረቶች በመዘርዘር ድርሻዋን ትወስድ ዘንድ እንዲወሰንላት ጠይቃለች።
ተጠሪም በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ የሚክደውን በመካድ የሚያምነውን ደግሞ በማመን ክርክሩን አቅርቦአል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ የቀረበለትን ክርክር መርምሮ ተገቢ ነው ያለውን የንብረት ክፍፍል ውሳኔ ሰጥቶአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች በውሳኔው ባለመስማማትዋ ለፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባ ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶአል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ሚያዝያ 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዲታይ የተወሰነው በአዲስ አበባ ከተማ በጉለላ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መኖሪያ ቤት የባልና ሚስቱ የጋራ ሃብት ነው። የብልኬት ማምረቻና የገበያ ማዕከል እንዲሁም በሱልልታ ከተማ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ሥራዎች የግምቱን ግማሽ ለአመልካች ሰጥቶ ተጠሪ ያስቀረው በሚል የተሰጠውን ውሳኔ አግባብነት ለመመርመር ነው። በዚህ መሰረትም ግራቀኙ ወገኖች የተያዘውን ጭብጥ በሚመለከት ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ከሥር ጀምሮ በግራቀኝ ወገኖች የተደረገውን ክርክር እና የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ በዝርዝር ተመልክተናል። በሰበር ችልቱ እንዲመረመር ከተያዘው ጭብጥ እንደምናየው በግራ ቀኝ ወገኖች አከራካሪ ሆነው ከቀረቡት ነጥቦች አንደኛው የመኖሪያ ቤቱን የሚመለከት ነው። አመልካች ከሥር ጀምራ የተከራከረችው የመኖሪያ ቤቱን የሚመለከት ነው። አመልካች ከሥር ጀምራ የተከራከረችው ቤቱ በሞት ከተለየው ከቀድሞ ባለቤቴ ጋር በትዳር ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ የተሰራ የቀድሞ ባለቤቴ እና የኔ የጋራ ሃብት ነው። ባለቤቴ ከሞተ በኋላም በእኔ እና በልጆቻችን ስም ተመዝግቦና ካርታ ወጥቶለት ይዘነው ቆይተናል። በመሆኑም ተጠሪ በዚህ ቤት ላይ የጋራ ባለሃብት ነኝ ሉል አይችልም በማለት ነው። ተጠሪ ደግሞ በእርግጥ ቤቱ አመልካች እንደምትለው እሱ እና ተጠሪ ከመጋባታቸው በፊት የነበረ፣ በእስዋ እና በልጆችዋ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ስለመሆኑ አይክድም። ቤቱ የኔም የጋራ ሃብት ነው በማለት የሚከራከረው ከአመልካች ጋር ከተጋባን በኋላ ፈርሶ እንደ አዲስ ተሰርቶአል የሚል ምክንያት በመስጠት ነው። ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው ፍ/ቤትም ይህንኑ የተጠሪ ክርክር በመቀበል ነው ቤቱ የአመልካች እና የተጠሪ የጋራ ሃብት ነው ሲል የወሰነው።
በበኩላችን እንደምናየው ቤቱ የታደሰው አመልካች እና ከቀድሞ ባለቤትዋ የወለደቻቸው ልጆችዋ በጋራ በመሆን የእድሳት ፈቃድ ለሚሰጥ አስተዳደር /በጉለላ ክ/ከተማ የቀበላ 13/14 አስተዳደር ጽ/ቤት/ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት እንደሆነ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አረጋግጦአል። በእርግጥ በዚህ ጊዜ የአመልካች እና የተጠሪ ጋብቻ አልፈረሰም ነበር።
ተጠሪም ይህን መሰረት በማድረግ ነው እየተከራከረ ያለው። በቤቱ ላይ የተደረገው እድሳት አዲስ ቤትን እንደመሥራት የሚቆጠር በመሆኑ እና ይህ የሆነው ጋብቻው ፀንቶ በነበረበት ጊዜ ስለሆነ ቤቱ የጋራ ሀብቴ ነው በማለትም ነው ክርክርሩን ያሰማው።
እንደምናየው ቤቱ የአመልካች እና የተጠሪ ጋብቻ ከመመሥረቱ በፊት የነበረ ነው።
ከዚህም ላላ የቤቱ ባለሃብቶች አመልካች እና ከሟች የተወለዱ ልጆችዋ እንደሆኑ ተረጋግጦ ከሚመለከተው የመንግሥት አስተዳደር ክፍል ማስረጃ የተሰጠ ስለመሆኑ ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው ፍ/ቤት አረጋግጦአል። እነዚህ የቤቱ የጋራ ባለሃብቶች ቤቱን እንዲያድሱ እንዲፈቀድላቸው ቀበላውን በጋራ የጠየቁትም የተረጋገጠላቸውን የባለሃብትነት መብታቸውን መሰረት በማድረግ ነው። በመሆኑም ቤቱ የታደሰው የአመልካች እና የተጠሪ ጋብቻ ፀንቶ በነበረበት ጊዜ ስለሆነ ብቻ የአመልካች እና የተጠሪ የጋራ ሃብት /በጋብቻ ጊዜ የተፈራ/ ነው ለማለት የሚቻልበት የሕግ አግባብ የለም። ባልና ሚስት ጋብቻቸውን በሚፈጽሙበት ጊዜ በየግል የነበሯቸው ንብረቶች የግል ንብረቶች ሆነው እንደሚቀሩ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 57 መመልከቱንም እዚህ ላይ ማንሳቱም ተገቢ ይሆናል። በልላ በኩል ደግሞ ተጋቢዎች ጋብቻቸው ንብረታቸውን በተመለከተ ስለሚያስከትለው ውጤት በውል መወሰን እንደሚችለ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 42/1/ የተደነገገ ቢሆንም፣ አመልካች እና ተጠሪ ግን በዚህ ድንጋጌ መሰረት ያደረጉት ውል ስለላለ አመልካች ቤቱን የተጠሪም የጋራ ንብረት እንዲሆን ፈቅዳለች የሚባልበት አግባብ የለም። ስለዚህም ቤቱ የኔም የጋራ ሃብት ነው በማለት ተጠሪ ያቀረበው ክርክር እና የሥር ፍ/ቤቶችም ይህን ክርክር በመቀበል የሰጡት ውሳኔ የሕግም ሆነ የፍሬ ነገር መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘነውም።
በመቀጠል በሁለተኛ ደረጃ የተመለከትነው የቡልኬት ማምረቻና ሱፐር ማርኬት/ የገበያ ማዕከል/ እንዲሁም በሱለልታ ከተማ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን በሚመለከት የተነሳውን ክርክር ነው። በዚህ ረገድ የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ እንዳየነው መሰረት ያደረገው ንብረቶቹ የአመልካች እና የተጠሪ የጋራ ሃብት አይደለም የሚል አይደለም።
ንብረቶቹ የጋራ ሃብት አንደሆኑ ፍ/ቤቱ አረጋግጦአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ የንብረቶቹን ግምት ግማሽ ለአመልካች በመስጠት ያስቀራቸው በማለት ወስኖአል። አመልካች የተቃወመችው ይህን ውሳኔ ነው። ንብረቶቹ የጋራችን እስከሆኑ ድረስ መካፈል ያለብን እኩልነታችን ተጠብቆ ነው በማለትም ነው የተከራከረችው ተጠሪም ቢሆን ንብረቶቹ የጋራ አይደለም የሚል መከራከሪያ የለውም። ክርክሩ አመልካችም በጉለላ ክፍለ ከተማ የሚገኘውን ቤት ለኔ ድርሻዬን ግምት ከፍላ እንድታስቀር ስለተወሰነላት ይህንኑ ለማቻቻል ተብል የተደረገ ነው የሚል ነው።
ቀደም ሲል እንደተገለጸው በጉለላ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መኖሪያ ቤት የአመልካች እና የልጆችዋ ብቻ በመሆኑ ተጠሪ የዚህ ቤት እኩል ድርሻ አለኝ የሚልበት አግባብ የለም።
በመሆኑም በላልች ንብረቶች የተሰጠው ውሳኔ ከመኖሪያ ቤቱ ጋር የሚያያዝበት ሁኔታ እንዳለ በማድረግ ተጠሪ ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት አይኖረውም። እዚህ ላይ በአግባቡ መታየት ያለበት ጉዳይ ላልቹ ንብረቶች የአመልካች እና የተጠሪ የጋራ ሃብት መሆናቸው ከተረጋገጠ ክፍፍለ መፈጸም ያለበት በምን አይነት ሁኔታ ነው የሚለው ነው። ባልና ሚስት በጋራ ያፈሩአቸው የጋራ ሃብቶች መከፋፈል ያለባቸው በእኩልነት መርህ ላይ በመመሥረት እንደሆነ በኢ.ፍ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 35/2/ እና በተሻሻለው የቤተሰብ አንቀጽ 9ዐ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል። የእኩልነት መርህ መጠበቅ አለበት ከተባለ ደግሞ አንዱ ከላላው ያነሰ ወይም የበለጠ አይወስድም ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። በያዝነው ጉዳይ እንደምናየው የባልና ሚስቱ የጋራ ሃብቶች ናቸው የተባለት የቡልኬት ማምረቻ እና የገበያ ማዕከል እንዲሁም በሱለልታ ከተማ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ስራዎች በባለቤትነት /በተግባር/ እንዲረከብ ወይም እንዲወስድ የተባለው ተጠሪ ነው። የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ተቀባይነት ይኑረው ከተባለ አመልካች ልታገኝ የምትችለው የንብረቶቹ ግምት/ገንዘብ/ ግማሽ ብቻ ነው። አመልካች ግን አልተስማማችም። ገንዘቡን የምትወስደው በፍርድ ስለተገደደች እንጂ ፈቅዳ አይደለም ማለት ነው ተጠሪ ንብረቱን መውሰድ አለብኝ እንደሚለው ሁለ አመልካችም የንብረቱን ግምት ግማሽ በገንዘብ ተለውጦ እንድትወስድ አልገደድም የማለት ከእኩልነት መርህ የሚነሳውን ክርክርዋ ከሕግ አግባብ ውጪ እንዳለመቀበልም ነው የሚቆጠረው። በእኛ እምነት እና ግንዛቤ የንብረት ክፍፍለ መከናወን ያለበት ሕጉ ባስቀመጠው የእኩልነት መርህ እና በቤተሰብ ሕጉ በተመለከተው የክፍፍል ሥርዓት መሰረት ነው።
ከፍ ሲል እንደተመለከትነው አመልካች እና ተጠሪ ንብረቶቹን በስምምነት ሉከፋፈለ አልቻለም። ከዚህ የተነሣም ሕጉ ወደአስቀመጠው የክፍፍል ሥርዓት መሄዱ የግድ ነው።
በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 91 እንደተመለከተው ሃብቱን በአይነት መከፋፈል የሚቻል ከሆነ ከንኡስ አንቀጽ /1/ እስከ ንኡስ አንቀጽ /3/ በተቀመጡት ድንጋጌዎች መሰረት እንዲፈጸም የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል። በዚህ ሁኔታ ለማከፋፈል የማይቻል ከሆነ ደግሞ ቀጥል ባለው አንቀጽ 92 መሰረት ንብረቱን በመሸጥ ከሺያጩ የተገኘውን ገንዘብ እንዲከፋፈለ ማድረግ ነው። በያዝነው ጉዳይ የሥር ፍ/ቤቶች የንብረት ክፍፍለ በዚህ ሥርዓት መሰረት እንዲፈጸም አላደረጉም። በመሆኑም ውሳኔው በሕጉ አተገባበር /አተረጓጏም/ ረገድ መሰረታዊ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
በመጨረሻም ያየነው በጉለላ ክፍለ ከተማ የሚገኘው መኖሪያ ቤት ሲታደስ እኔም ገንዘብ አዋጥቻለሁ የሚለው የተጠሪ ክርክር በምን አግባብ ላታይ ይገባል የሚለው ነው። የሥር ፍ/ቤቶች ቤቱ የአመልካች እና የተጠሪ የጋራ ሃብት ነው ብለው በመደምደማቸው ላላውን አማራጭ አላዩም። በበኩላችን እንደተገነዘብነው ቤቱ የአመልካች እና የልጆችዋ የጋራ ሃብት ነው ቢባልም፤ ሲታደስ በጥቅም ላይ ከዋለው የእድሳት ወጪ/ገንዘብ/ ውስጥ ግማሹ የአመልካች መሆኑ የሚታመን ሲሆን ይው ገንዘብ የአመልካች የግል ስለመሆኑ እስካልተረጋገጠ ድረስ ከተጠሪ ጋራ የጋራ ሃብት ነው ተብል የሕግ ግምት የሚወስድበት ነው። በመሆኑም ተጠሪ ያለው መብት አመልካች ለእድሳት ካወጣችው ወጪ ግማሽ ገንዘብ ውስጥ ግማሹን ማለትም የቤቱን መቶ ፐርሰንት ሃያ አምስት ከመቶ /ፐርሰንት/ መውሰድ ነው። ይህ መጠን ደግሞ በሥር ፍ/ቤት ሉረጋገጥ የሚገባው ነው። ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/544ዐ6 ነሐሴ 23 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፍድራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ.728ዐ5 ሚያዝያ 8 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሻሽለዋል።
በጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 13/14 ውስጥ የሚገኘው ቁጥሩ 1ዐዐ5 በሆነው የመኖሪያ ቤት ላይ ተጠሪ የጋራ ባለሃብትነት መብት የለውም ብለናል።
የቡልኬት ማምረቻው እና የገበያ ማእከለ /ሱፐርማርኬት/ እንዲሁም በሱለልታ ከተማ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ሥራዎች/የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሰጠው ውሳኔ በተራ ቁጥር 6 የተመለከቱት/ በአይነት ለማከፋፈል የሚቻል ከሆነ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 91 መሰረት ክፍፍለ እንዲፈጸም፤ በዚህ መሰረት ማከፋፈል ካልተቻለ ደግሞ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 92 በተደነገገው መሰረት ተሸጠው አመልካች እና ተጠሪ ገንዘቡን እኩል እንዲካፈለ በማለት ወስነናል።
ተጠሪ ለቤቱ እድሳት ከወጣው ወጪ ውስጥ ሉያገኝ /ሉመለስለት/ የሚገባው መጠን ምን ያህል እንደሆነ የፍድራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንዲወስን በዚህ ነጥብ ብቻ ጉዳዩን መልሰንለታል።
በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣ ወጪና ኪሣራን በተመለከተ ግራቀኝ ወገኖች ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.