No summary available.
ሐምል 29 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሪት ዝናሽ ዘውደ - ጠበቃ ሙለጌታ ወንድምአገኘሁ ቀረቡ።
ተጠሪ፡- የወ/ሮ መድኃኒት ካሳ ወራሽ - እነ ወ/ሮ ደብሪቱ ስዩም አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ሲሆን የአመልካች አባት አቶ ዘውደ አበበና የተጠሪዎች ልጅ እህት የሆኑት ወ/ሮ ሰናይት ስዩም በጋብቻ አብረው ሲኖሩ ወ/ሮ ሰናይት ስዩም ታህሳስ 25 ቀን 1995 ዓ/ም ከዚህ አለም በመለየታቸው ምክንያት ጋብቻው በሞት መፈረሱን ገልጸው ውርሱ ተጣርቶ እንዱቀርብላቸው ተጠሪ ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርበው ፍርድ ቤቱም አመልካችን አስቀርቦ አመልካች የይርጋ ክርክር ቢያነሱም ይኸው ታልፍ የውርስ ንብረቱ ተጣርቶ እንዱቀርብ የውርስ አጣሪ ሹሞ የውርስ አጣሪውም ሀብቱን አጣርቶ ለፍርድ ቤቱ ሪፕርቱን ሲያቀርብ ግራ ቀኙ አስተያየት እንዱሰጡበት ተደርጎ ፍርድ ቤቱ የውርስ አጣሪው በጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 08/16 የቤት ቁጥር 497 ግቢ ውስጥ ከዋናው ቤት ትይዩ የሚገኝ ሁለት ክፍል ቤቶችና አንድ ክፍል እቃ ቤት በአጠቃላይ ሶስት ክፍል ቤት የአመልካች የግል ቤት ነው በማለት የውርስ አጣሪ የደረሰበት መደምደሚያ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 መሰረት የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ ነው በማለት ውድቅ አድርጎ ዋናው ቤትና ሰርቪስ ቤቶች በሙለ የውርስ ሀብት ናቸው በማለት የውርስ አጣሪውን ሪፕርት አሻሽል አፅድቆታል። አመልካች የሰሩት ቤት ካለ ግምቱን ጠቅሰው ዲኝነት ከፍለው የመጠየቅ መብታቸው የተጠበቀ ነው በማለትም ትእዛዝ ሰጥቶበታል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ጸንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘትም የውርስ አጣሪው በ23/04/2002 ዓ.ም ያቀረቡት ሪፕርት በአግባቡ የቀረበ ሁኖ እያለ ፍርድ ቤቱ አከራካሪው ቤት የግል አይደለም ማለቱ ተገቢነት የለውም የሚል ነው።
አቤቱታቸው ተመርምሮም የውርስ አጣሪው ከሟች ሞት በኋላ የተሰራውን ሶስት ክፍል የአመልካች የግላቸው ነው በማለት ያቀረበው ሪፕርት በፍርድ ቤቶቹ ውድቅ የመደረጉን አግባብነት ለማጣራት ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ የተደረገ ሲሆን ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ በፅሁፍ ተከራክረዋል።
በበኩላችን ደግሞ የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት የውርስ ንብረት አጣሪውን ሪፕርት በሰርቪስ ቤቶችና በእቃ ቤት ላይ ተቀባይነት የለውም በማለት ውደቅ ያደረገው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን አንደመረመርነውም የውርስ አጣሪው ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ሪፕርት ቁጥሩ 497 በሆነው ዋና ቤት ከወ/ሮ ሰናይት ስዩም ሞት በሁዋላና ሁለት ክፍል ሰርቪስ ቤቶችና አንድ ክፍል እቃ ቤት መሰራቱን በምስክሮች ቃል መረጋገጡን የገለፁ ሲሆን ይህ ድምዲሜ በበታች ፍርድ ቤቶች ቤቶቹን የአመልካች የግል አያደርጋቸውም ተብል ውሳኔ የተሰጠው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 1195 መሰረት ከአስተዲደር አካል የተሰጠ የባለሀብትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አልቀረበም፣ ባለሀብትነቱ በሰው ማስረጃ ሉረጋገጥ የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት ነው።
በመሰረቱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 956 እንደተደነገገው የአጣሪው ሥራ ሟቹ አንድ ኑዛዜ ትቶ እንደሆነ መፈለግና በመጨረሻም ውርሱ የሚደርሳቸው ሰዎች እነማን እንደሆኑ ማረጋገጥ፣ የውርሱን ሃብት ማስተዲደር፣ መክፈያቸው የደረሰውን የውርስ እዲዎች መክፈል እና ሟቹ ኑዛዜ ያደረገባቸውን ስጦታዎች መክፈልና የኑዛዜውን ቃል ለመፈፀም ማንኛቸውም ላልች አስፈላጊ ጥንቃቄዎች ማድረግ ነው። እነዚህ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በሚያከናውንበት ጊዜ ደግሞ በኑዛዜው የውርስ ንብረት መሆናቸውን ጠቅሶ የክፍፍል ስርዓትም የተቀመጠላቸውና ወራሾች በሙለ የተስማሙባቸው ንብረቶችና መክፈያቸው የደረሰው የውርስ እዲዎች ሲኖሩ በወራሾቹ ስምምነት መሰረት ንብረቶቹን ሉያከፊፍልና እዲዎችንም ሉከፍል ይችላል። በኑዛዜው ላይ በተጠቀሱትና ባልተጠቀሱት ንብረቶች የውርስ ሃብት መሆን ያለመሆን ላይ ወራሾቹ ያልተስማሙና ክርክር ያነሱ ከሆነ የአጣሪውሥራና ኃላፉነት ወራሾች የተስማሙባቸውን ንብረቶች የውርስ ሃብት መሆናቸውን መመዝገብ፣ ወራሾች ያልተስማሙባቸው ንብረቶችና እዲዎች ካለ ደግሞ ማስረጃ በመስማት ማስረጃው ምን እንደሚያስረዲ ሪፕርቱ ላይ በማስፈር እንዱያጣራ ላዘዘው ፍ/ቤት ማቅረብ እንጂ ንብረት አጣሪው ይህ ንብረት የውርስ ሐብት አይደለም የሚለ ወራሾች ቢኖሩም ማስረጃ በመስማት የውርስ ሃብት መሆኑን ስለተገነዘብኩኝ ንብረቱ የውርስ ሃብት ነው በማለት ወስኛለሁ ወይም ደግሞ ማስረጃውን እንደተመለከትኩት ንብረቱ የውርስ ሐብት ያለመሆኑን ስላረጋገጥኩኝ የውርስ ሐብት አይደለም ወይም የእገላ የግል ንብረት ነው በማለት ወስኛለሁ ለማለት የሚያስችለው ሥልጣን የለውም።
በዚህ ጉዲይ የውርስ አጣሪው ያደረጉትን የማጣራት ሥራ ስንመለከተው ወራሾቹ የውርስ ሐብት ናቸው በሚለዋቸው ዋና ቤት እና በሰርቪስ ቤቶች ላይ ገና ከጅምሩ አንስቶ ያልተስማሙና ክርክር ያነሱ በመሆኑ አጣሪው ማስረጃ መስማታቸው በአግባቡ ነው። ሆኖም አጣሪው በወራሾች መካከል የተደረገው ክርክር እንደነበረ፣ የኑዛዜ ወራሾችና የሕግ ወራሾች እነማን እንደሆኑ፣ የግራ ቀኙ ማስረጃ ምን እንደሚመስል፣ እንዱሁም ወራሾች የተማመኑባቸውና ያልተማመኑባቸው የውርስ ንብረቶችና እዲዎቹ ምን ምን እንደሆኑ በመዘርዘር ሪፕርት ማዘጋጀት ሲኖርባቸው ከዚህ አልፈው ወራሾችን አከራከረው ማስረጃ ከሰሙ በኋላ ክርክሩንና ማስረጃውን ከሕግ ጋር በማገናዘብ ይህ ንብረት የአመልካች እንጂ የሟች የወ/ሮ ሰናይት ስዩምና የሟች ዘውደ አበባ የጋራ ንብረት አይደለም በማለት መወሰናቸው ከተሰጣቸው የውርስ አጣሪነት ሥልጣን በላይ በመሄድ መደበኛ ፍ/ቤት በሚያከናውነው የዲኝነት ሥራ ውስጥ መግባት መሆኑንና ይህም ተገቢ ያለመሆኑን ተገንዝበናል። ውርስ አጣሪው አዘጋጅተው ያቀረቡት ሪፕርት ውሳኔም ጭምር ያዘለ በመሆኑ ሪፕርቱ በቀረበለት ፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከላይ በተመለከተው ሁኔታ በውርስ አጣሪ ውሳኔ መሰጠት እንደማይገባ ሉገለፅና ሂደቱ ሕጋዊ አይደለም ተብል ውድቅ መደረግ ሲገባው መታለፈ ያላግባብ ሁኖ አግኝተነዋል። የባለቤነት ክርክር በውርስ ማጣራት ሂደት ከተነሳ ጉዲዩ መታየት ያለበትና እልባት ሉያገኝ የሚገባው በመደበኛው ፍርድ ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ መሰረት ተገቢው ጭብጥ ተይዞ የግራ ቀኙ ማስረጃዎች ተሰምተው ላሆን ይገባል። ፍርድ ቤት የባለሀብትነት ክርክር ሲቀርብ ሉያረጋግጥ የሚገባው ደግሞ ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎችን ሁለ ሰምቶና ተገቢውን የማስረጃ ምዘና መርህ ተከትል ነው።
በመሰረቱ የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለቤትነት ምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው የዚሁ ንብረት ባለሃብት ሁኖ እንደሚቆጠር የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195(1) ድንጋጌ ያሳያል። የዚህ ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የሚያሳየው የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለሃብትነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው የንብረቱ ባለሃብት እንደሆነ ሕጉ ግምት የሚወስድ መሆኑን ነው። ይህ የሕጉ ግምት ሉስተባበል የሚችል ስለመሆኑም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1196 ድንጋጌ ያሳያል። በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 ስር የተመለከተው የሕጉ ግምት ባለሃብትነት በልላ መንገድ የማይረጋገጥ አይደለም በሚል የተቀመጠ አይደለም። በዚህ መሰረትም አንድ ንብረት በአንድ ሰው ስም ስለመመዝገቡ በአስተዲደር መስሪያ ቤት ታውቆለት የባለሃብትነት የምስክር ወረቀት ከተሰጠውና ይኸው ምስክር ወረቀት የተገኘበትን መንገድ ሕጋዊ አለመሆኑን ክርክር ከቀረበ ፍርድ ቤቱ ንብረቱ በማን እንደተፈራ፣ የምስክር ወረቀት በተሰጠው ሰው ስም እንዳት ሉመዘገብ እንደቻለ ከተገቢው አካል የቤቱ ማህደር ቀርቦ ወይም ላልች ማስረጃዎች ቀርበው እንዱታዩ የቀረበውን ክርክር በመመልከትና ጉዲዩን በማስረጃ በማንጠር ወደ እውነት የሚደርስበት ይሆናል እንጂ ስመ ሀብቱ የተመዘገበው ሰው የንብረቱ ባለሃብት ነው ወይም ስመ ሀብቱ ካልተመዘገበ አንድ ሰው የንብረት ባለቤት ላሆን አይችልም፣ ወይም በሰው ማስረጃ ሉያስረዲ አይችልም በሚል ደምድሞ ከወዱሁ ክርክሩን ወይም ክሱን ውድቅ የሚያድርግበት አይደለም። በመሆኑም አመልካች ቤቱን ራሳቸው ያፈሩት ስለመሆኑና በግራ ቀኙ ማስረጃዎቻቸው ሳይነጥርና ተገቢውን የማስረጃ ምዘና መርህ በመከተል ሳይመዘኑ ከአስተዲደር አካል የተሰጠ የምስክር ወረቀት የለም ተብል የሰው ምስክሮች ቃል ከወዱሁ ውድቅ የተደረገው የአመልካችን የክርክር ይዘት ባለገናዘበና ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195 እና 1196 እንዱሁም በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 40(1) እና (2) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ውጪ ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት አከራካሪውን ቤት የሰራው ማን ነው? የሚለው ጭብጥ ተይዞ በዚህ ረገድ የሚቀርቡት የግራ ቀኙ ማስረጃዎች በፍርድ ቤት ፉት ቀርበው ተሰምተው ምስክሮቹ የሚሰጡት ቃል ከንብረት ባለቤትነት መብት ሕግጋት ጋር ተዛምድ ውሳኔ መሰጠት ሲገባው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባለሀብትነት ሉረጋገጥ የሚገባው በአስተዲደር አካል በሚሰጥ የምስክር ወረቀት ነው በሚለው ነጥብ ላይ ብቻ በማተኮር የሰጠው ውሳኔ አመልካች ንብረቱን ያፈሩት ስለመሆኑ ለማረጋገጥ ያቀረቡትን ክርክርና ማስረጃ ከፍ ብለን ከጠቀስናቸው የፍትሐብሕር ድንጋጌዎችና የህገ መንግስት ድንጋጌዎች ጋር ያላገናዘበ ነው። አመልካች የቤቶችን ግምት ጠቅሰው ዲኝነት ከፍለው በልላ መዝገብ ይጠይቁ ተብል መወሰኑም የፍትሐ ብሓር ስነ ሥርዓት ሕግ መሰረታዊ አላማ ጋር አብሮ የማይሄድ መሆኑን ተገንዝበናል። እንዱሁም ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1195(1) ድንጋጌ የማይንቀሳቀስ ንብረት የባለሀብትነት የምስክር ወረቀት የተሰጠው ሰው የንብረቱ ባለሀብት እንደሆነ ሕጉ ግምት ይወሰዲል ከማለት ውጪ ማንኛውም የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በልላ መንገድ አይረጋገጥም የማይል ስለመሆኑ በሰ/መ/ ጥቅምት 18 ቀን 2001 ዓ/ም በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2(1) መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በአጠቃላይ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል።
በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ/ም በጉለላ ክፍለ ከተማ በቀበላ 08/16 ክልል ውስጥ በሚገኝ የቤት ቁጥር 497 ግቢ ውስጥ ከዋናው ቤት ትይዩ የሚገኝ ሁለት ክፍል ሰርቪስ ቤቶች እና አንድ ክፍል እቃ ቤት በአጠቃላይ ሶስት ክፍል ቤቶች የውርስ ሀብት ናቸው ተብል ተወስኖ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 05 ቀን 2003 ዓ/ም የጸናው የውሳኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1)መሰረት ተሽሯል።
በጉለላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 08/16 የቤት ቁጥር 497 ግቢ ውስጥ ከዋናው ቤት ትይዩ የሚገኝ ሁለት ክፍል ሰርቪስ ቤቶች እና አንድ ክፍል እቃ ቤት በአጠቃላይ ሶስት ክፍል ቤቶች በማን እንደተሰሩና ሕጋዊ ባለሀብት ማን እንደሆነ የግራ ቀኙን ማስረጃዎችን የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ በሆነው ቀጥል ተገቢውን ውሳኔ ላሰጥበት ይገባል በማለት ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰናል። ይጻፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.