No summary available.
ሚያዝያ 06 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- 1- አቶ ዲንኤል ጽጌ 2- ወ/ሮ ጽዮን ጽጌ ጠበቃቸው ቀረቡ ተጠሪዎች፡- ህፃን አሳለፈ ጽጌ ሞገዚት ኢ/ር ታምራት ብሩ ቀረቡ መዝገቡን ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የውርስ ሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ የድርሻ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ሟች አቶ ፅጌ ዘገኑ ሐምል ዐ7 ቀን 1998 ዓ/ም ለሕፃን አሳለፍ ፅጌ ያደረጉትን ኑዛዜ መሰረት በማድረግ የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጣቸው ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው ፍርድ ቤቱም የሕፃኗን የኑዛዜ ወራሽነት በማረጋገጥ ማስረጃ ከሰጠ በሁዋላ የአሁኑ አመልካቾች ይኸው የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ እንዱሰረዝላቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው። አመልካቾች ለስር ፍርድ ቤት ባቀረቡት መቃወሚያ የሟች አቶ ፅጌ ዘገኑ ልጆች ሁነው እያለ ሟች ባደረጉት ኑዛዜ አመልካቾች በህይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ስለአደረሱብኝ ከመጡ ለእያንዲንዲቸው ብር 5/ አምስት / እንዱሰጥ በማለት መግለፃቸው ከውርስ ንብረቱ ያለምክንያት የነቀሎቸው መሆኑን ዘርዝረው ለተጠሪ የተሰጠው የኑዛዜ ወራሽነት ተሰርዞ አመልካቾች የሟች ወራሾች ናቸው ተብል እንዱወሰንላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የስር ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የሟች ኑዛዜ አመልካቾችን ያለምክንያት ከውርስ የነቀለ ነው በሚል ምክንያት ለተጠሪ የሰጠውን የኑዛዜ ወራሽነት በማሻሻል አመልካቾችና ተጠሪ የሟችን ውርስ እኩል እንዱካፈለ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ባለመስማማት ይግባኙን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ ሟች ባደረጉት ኑዛዜ የአመልካቾችን ድርሻ ከማሳነስ ውጪ ከውርስ አልነቀሎቸውም በሚል ምክንያት የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ ሽሮ ኑዛዜው የጸና ነው በማለት ወስኗል። ከዚህም በሁዋላ አመልካቾች የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ጉዲዩ ተመርምሮ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካቾች ጠበቃ ሐምል 13 ቀን 2002 ዓ/ም በጻፊት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- ሟች ባደረጉት ኑዛዜ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾቻቸው ለሆኑት አመልካቾች ግምቱ ብር 6ዐዐ ሺህ በላይ ከሆነው ንብረታቸው ለእያንዲንዲቸው ብር 5/አምስት ብር / ብቻ እንዱሰጣቸው መናዘዛቸው አመልካቾችን በውጤት ከውርስ የነቀሎቸው መሆኑን የሚያሳይ ሁኖ እያለ የበታች ፍርድ ቤቶች የውርስ ንብረት ድርሻ አንሷል ከሚባል በስተቀር ከውርስ መነቀል አይደለም በማለት መወሰናቸው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938 እና 939 ድንጋጌዎችና ይዘትና መንፈስን ያላገናዘበ ነው፣ ይኸው እንኳ ቢታለፍ ጉዲዩ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1123 ድንጋጌ አንፃር መታየት ሲገባው መታለፈ ያላግባብ ነው በማለት ዘርዝረው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ እንዱሻሻል ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርመሮም ለሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል ተብል ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ህዲር 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ/ም በተጻፈ ማመልከቻ በይዘቱ በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ካቀረቡት ጋር ተመሳሳይ የሆነ መልሰ ሰጥተዋል። የአመልካቾች ጠበቃም ጥር 16 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፊት አንድ ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርነውም ሟች አቶ ጽጌ ዘገኑ ሐምል ዐ7 ቀን 1998 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ አመልካቾችን ነቅሎል አልነቀለም?፣ ውጤቱስ ምን ላሆን ይገባል?
የሚለት ነጥቦች በጭብጥነት ሉታዩ የሚገባቸው ሁነው አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች አቶ ፅጌ ዘገኑ ሐምል ዐ7 ቀን 1998 ዓ/ም ግልፅ ኑዛዜ የተው መሆኑን አመልካቾች የሟቹ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሾች/ ልጆች/ ፤ ተጠሪ ደግሞ የሟች ወንድም ልጅ መሆኑን ፣ ሟች ይኖራቸዋል ተብል የተጠቀሰው የንብረት ግምት ከብር 6ዐዐ ሺህ በላይ ሁኖ ለአመልካቾች ለእያንዲንዲቸው እንዱሰጣቸው የገለፁት ገንዘብ ብር 5/አምስት ብር / ብቻ መሆኑን ይህንን ለማድረግ በምክንያትነት የጠቀሱት ደግሞ በሕይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ስለፈጠሩብኝ የሚል መሆኑን ነው። የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ኑዛዜው ሕጋዊ ነው በማለት የወሰኑት ሟች ለአመልካቾች ድርሻቸውን ሰጥተዋል የድርሻ ማነስ ደግሞ የውርስ መነቀል ነው ልባል የሚችል አይደለም በሚል ምክንያት ነው።
No topics extracted.
በእርግጥ በኑዛዜው የሚከናወኑ ተግባሮች የኑዛዜ ስጦታ /legacy/ ወይም የክፍያ ደንብ / Rule of partition/ ሉሆኑ ይችላለ። በመርህ ደረጃ ደግሞ አንድ ሰው ከውርስ ሀብቱ መካከል አንድን ንብረት ለወራሾቹ መስጠቱ የኑዛዜ ስጦታ አያሰኘውም። ይልቁንም ይህ አይነት ኑዛዜ ሕጉ የሚቀበለው እንደ አንድ የክፍያ ደንብ ነው። በመሆኑም አንድ አውራሽ ለወራሹ አንድን ንብረት ቢናዘዝለት የኑዛዜው አፈፃፀም የስጦታ / legacy/አፈፃፀምን በመከተል ሳይሆን የክፍያ ደንብ /partition/ በመከተል የሚከናውን ይሆናል። ሆኖም በኑዛዜው ላይ የሚሰጠው ክፍያ መጠን በመገለፁ ብቻ ሁል ጊዜ የክፍያ ደንብ ነው ልባል የሚችል አይሆንም። በመሆኑም የተሰጠው የንብረት መጠን ከሟቹ የውርስ ንብረት ግምት ጋር ታይቶ ውጤቱም በዚሁ ረገድ መለየት ያለበት ጉዲይ ነው። በልላ አገላለፅ ሟች በኑዛዜው ላይ የሚያስፍረው የንብረት መጠን ከሟቹ የውርስ ንብረት መጠን ጋር እየታየ የመነቀል ጉዲይ ነው ወይስ የክፍያ ማነስ ነው? የሚለው ነጥብ የሚለይ ይሆናል።
በልላ በኩል አንድ ተናዛዥ/ ወላጅ/ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሹን ያለህጋዊና በቂ ምክንያት እንዱሁም በዝምታ ከውርስ ለመንቀል እንደማይችል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938 እና 939 ድንጋጌዎች ይዘት በግልፅ ያሳያል። ወላጅ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሹን ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት ወይም በዝምታ ከነቀለም ውጤቱ ምን ላሆን እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 915 ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች ጋር ተዲምሮ ሲታይ ምላሽ ይሰጣል። በዚህም መሰረት ከውርስ በዝምታ ወይም ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት የተነቀለ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ ሁነው የውርስ ንብረቱን ሉከፊፈለ የሚችለ መሆኑን ሕጉ ያስገነዝባል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤት ወደዚህ ድምዲሜ ከመድረሱ በፉት በወላጅ የተደረገ የኑዛዜ ስጦታ አይነቱ ጠቅላላ ወይም ልዩ ኑዛዜ ስጦታ መሆን ያለመሆኑን በቅድሚያ መለየት አለበት። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 912 ስር እንደተመለከተው የኑዛዜ ስጦታ ጠቅላላ ወይም ልዩ ኑዛዜ ስጦታ ላሆን ይችላል። ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ሲባልም ተናዛዡ ሀብቱን ጠቅላላ ወይም ከመላ ንብረቱ አንደን ክፍል በሙለ ሀብትነት ወይም በላጣ ርስትነት ለአንድ ወይም ለብዙ ሰዎች የሚያወርስበት የኑዛዜ ቃል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 912/1/ ድንጋጌ ያሳያል። የዚሁ ቁጥር ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ ማንኛውም ላላ የኑዛዜ ቃል ሁለ እንደ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ እንደሚቆጠር ይደነግጋል። እንደ ኑዛዜ ላይ የኑዛዜ ስጦታ መሆኑ የተረጋገጠ ደግሞ እንደውርስ እዲ ተቆጥሮ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1014 ድንጋጌ ቅደመ ተከተል መሰረት የሚከፈል ይሆናል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ሟች አቶ ፅጌ ዘገኑ ሀብታቸውን ሙለ በመለ ተጠሪ እንዱወርስ ለአመልካቾች ደግሞ ለእያንዲንዲቸው ብር 5/ አምስት/ የሰጡት መሆኑ ከኑዛዜው ሰነድ ይዘት ተረጋግጧል። ሆኖም ሟች አላቸው ተብል ከተገመተው የብር 6ዐዐ ሺህ ብር የውርስ ንብረት አንፃር ለአመልካቾች እያንዲንዲቸው ብር 5/አምስት ብር/ እንዱወስደ በማለት የተናዘዙት ሁኔታ ሲታይ እግምት ውስጥ የሚገባ ወይም የድርሻ ጥያቄ አነሰ የሚል ክርክር የሚያስነሳ ነው ልባል የሚችል ሳይሆን በውጤቱ የመነቀል ውጤትን ያስከተለ ነው ልባል የሚችል ነው። ሟች ለአመልካቾች ለእያንዲንዲቸው ብር 5/ አምስት / እንዱሰጥ በማለት የተናዘዙት ‛በሕይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ስለፈጠሩብኝ“ በሚል ምክንያት ነው። ሆኖም በሕይወቴ ላይ ከፍተኛ ችግር ስለፈጠሩብኝ የሚለው ሐረግ ዝርዝር ይዘቱ ግን በኑዛዜው ላይ አልተገለጸም። የዚህ ሐረግ አገላለፅ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938/2/ መሰረት እንደእውነት የሚወሰድ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከውርስ ለመንቀል የሚያስችል ሕጋዊ እና በቂ ምክንያት መሆኑን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938/3/ መሰረት መመልከቱ ተገቢ ነው። ከዚህም አንጻር በሕይወት ላይ ችግር መፍጠር የተለያየ ደረጃና መንገድ ያለው በመሆኑ ሟች አመልካቾችን በዚህ ምክንያት ብቻ መንቀለ ሕጋዊና በቂ ምክንያት ሁኖ አላገኘነውም።
ከላይ እንደተመለከተው ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በፍርማሉቲ ረገድ ፈራሽ ላሆን የሚችልበት ምክንያት የላለ ሲሆን ሟች አላቸው ከተባለው ጠቅላላ የውርስ ንብረት መጠን አንፃር ሲታይ ለአመልካቾች የተሰጠው የገንዘብ መጠን በውጤት ደረጃ አመልካቾችን ነቅሎል ከሚባል በስተቀር ድርሻቸውን አግኝተዋል ውጤቱም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1123 ላታይ የሚችል ነው ልባል የሚችል ሁኖ አላገኘነውም። በመሆኑም ከዚህ አንፃር ተናዛዡ ያደረጉት የኑዛዜ ስጦታ ሲታይ በውጤቱ አመልካቾችን ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት ከውርስ የነቀለ ሁኖ ዓይነቱ ልዩ የሆነ የኑዛዜ ስጦታ ሳይሆን ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ አይነት ነው። እንዱህ ከሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1014/ሰ/ ስር በተመለከተው መሰረት እንደውርስ እዲ ተቆጥሮ ለልዩ ኑዛዜ ተቀባዩ የሚከፈል ሣይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938 እና 939 እንዱሁም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 915 ድንጋጌዎች ታይቶ ተወላጅ ከውርስ ተነቅሎል፣ ከኑዛዜ ተቀባዩ ጋር እኩል ሉካፈል ይገባል የሚባልበት ነው። ስለሆነም ተጠሪ በፍ/ሕ/ቁጥር 915 መሰረት እንደጠቅላላ ኑዛዜ ወራሽ ተወስደው ከአመልካቾች ጋር እኩል ተካፊይ ናቸው ተብል ሉወሰን ሲገባው የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ከውርስ ንብረት ክፍያ ማነስ ጋር በማያያዝ የሰጡት ውሣኔ የኑዛዜውን ውጤት ሟች አላቸው ከተባለው ንብረት ግምት መጠን ጋር ባለማገናዘብ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 17 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 19 ቀን 2002 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 137/02 የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
ሟች አቶ ጽጌ ዘገኑ ሐምል ዐ7 ቀን 1998 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ በውጤቱ ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት አመልካቾችን የነቀለ በመሆኑ በአመልካቾች ላይ ተፈፃሚነት የለውም ብለናል፣ ኑዛዜው ተጠሪን በሟቹ ድርሻ ንብረት ላይ አንድ ወራሽ የሚያደርግ በመሆኑ አመልካቾች የሟችን ድርሻ ንብረት ከተጠሪ ጋር እኩል እንዱካፈለ ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።