No summary available.
ኀዲር ዐ1 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም.
ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ከፍያለው በቀለ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወጣት ሶፉያን አብደልቃድር - ቀረበ።
መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፤ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ አካለ መጠን ያላደረሰን ልጅ ንብረት በሞግዚትነት ሲያስተዲድሩ የነበሩት ወላጆች በሽያጭ ለላላ ሦስተኛ ወገን ባስተላለፈ ጊዜ አካለ መጠን ባልደረሰው ልጅ ላይ ይኸው ተግባር የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው? የሚለውን የሕግ ክርክር የሚመለከት ነው።
የነገሩ መነሻ የአሁን አመልካች ከተጠሪ ወላጆች የማይንቀሳቀስ ንብረት ቤት በውል ገዝቻለሁ፤ ውል ሉፀድቅልኝ ይገባል የሚል አቤቱታ አቅርቦ፣ ከሻጮች ጋር ከተከራከረ በኋላ እንደ ጥያቄው ምላሽ የሚሰጥ ውሣኔ አግኝቷል።
ከዚህ በኋላ የአሁን ተጠሪ የተሸጠው ንብረት ስመሃብትነት በእኔ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ነው በተሸጠበት ጊዜ በወላጆቼ የሞግዚትነት ሥልጣን ሥር የምተዲደር አካለ መጠን ያልደረስኩ ልጅ ነበርኩ። ወላጆቼ የሽያጭ ተግባሩን ለመፈፀም የሚያስችል ከሕግ የመነጨ መብት የላቸውም።
በዚህ በሕግ ረገድ ተቀባይነት በላለው ተግባር መነሻ እኔ በላለሁበት ገዢና ሻጭ ናቸው ተብል በተነሣው ክርክር የሽያጭ ውል ይጽደቅ በሚል የተሰጠው ውሣኔ መብቴን ስለሚነካ ውሣኔው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 36ዐ መሰረት ሉሰረዝ ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 358 መሰረት ፍርደን ለፈረደው ፍ/ቤት እራሱን በቻለ መዝገብ አቤቱታ አቅርቧል።
ከዚህ ቀደም በአሁን አመልካችና በተጠሪ ወላጆች መካከል የተነሣውን ክርክር ተመልክቶ ውሣኔ የሰጠው የክልለ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በዚህ ነጥብ ላይ አመልካችና ተጠሪን ካከራከረ በኋላ በአሁን ተጠሪ ከላይ በተገለፀው አኳኋን የቀረበውን ክርክር መሰረት በማድረግ ከዚህ ቀደም በልላ መዝገብና የሽያጭ ውል ይጸድቃል በማለት የሰጠው ውሣኔ ውጤት እንደማይኖረው አድርጎ ሰርዞ ወስኗል።
በዚህ መነሻ በተሰጠው ውሣኔ ሁለቱም ወገኖች በየደረጃው ባለ ፍ/ቤቶች ሲከራከሩ ከቆዩ በኋላ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተጠሪ የአቤቱታ አቀራረብ የተፈፀመው ሥነ ሥርዓታዊ ጉድለት መሰረታዊ ሆኖ በሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ በመሰረዝ የሰጠውን ዲኝነት ለማስለወጥ የሚያበቃ አይደለም።
አካለ መጠን ያልደረሰውን ልጅ የማይንቀሳቀስ ንብረት በሞግዚትነት ሥልጣን ወላጆቹ በማናቸውም መንገድ ቢሆን ለማስተለለፍ ሥልጣን ያላቸው ስለመሆኑ በክልለ ሕግ አልተደነገገም፤
ስለሆነም በዚህ ረገድ የወረዲው ፍ/ቤት እና ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛ ፍ/ቤት ሻጮች ለገዢው የሽያጭ ውል ሉያፀድቅ ይገባል በሚል አስቀድሞ ተሰጥቶ የነበረው ውሣኔ ተሰርዟል ሲለ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት አይደለም የሚለውን ጠቅሶ የክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት የአቤቱታ አቀራረብ ሥርዓት መጓደልን ምክንያት በማድረግ የሰጠውን ውሣኔ በመሻር ወስኗል።
በዚህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር በየደረጃው ባለት የሥር ፍ/ቤቶች በየፉናቸው አቅርበውት ከነበረው የተለየ አይደለም።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን፣ እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው ተመልክተናል።
በዚህ ጉዲይ ለክርክሩ መነሻ በሆነው የሽያጭ ውል ላይ ተሽጧል የተባለው የማይንቀሳቀስ ንብረት /ቤት/ ስመ ሃብትነቱ በአሁን ተጠሪ ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝ አከራካሪ የሆነ ጉዲይ አይደለም የአሁን አመልካች አጠንክሮ ከሚከራከርበት ነጥብ አንደ ምንም እንኳ ስመ ሃብትነቱ በተጠሪ ስም ተመዝግቦ ይገኝ እንጂ በተሸጠበት ጊዜ ተጠሪ ንብረት ለማፍራት በሚችልበት የዕድሜ ክልል ስላልነበረ ንብረቱንም በውርስ አግኝቻለሁ ስለማይል ሀብትነቱ የሻጮች በመሆኑ በፈፀሙት ሕጋዊ ተግባር ሉገደደ ይገባል የሚለው ነው። ሆኖም የተሸጠው ንብረት ባለቤት ማን ነው? የሚል እንደ አሁኑ ያለ ጥያቄ በተነሣ ጊዜ አከራካሪ ከሆነው ንብረት ዓይነት አንፃር የንብረት ምዝገባን መሰረት በማድረግ ሕጉ ምላሽ የሚሰጥበት በመሆኑ በአመልካች በኩል በፍሬ ነገር ላይ ተመርኩዞ የቀረበው ክርክር ሕጋዊ መሰረት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
ንብረቱን በግዢ አግኝቼ ለ14 ዓመታት በእጄ አድርጌ ከቆየሁ በኋላ በተጠሪ በኩል የቀረበው ክርክር ተቀባይነት የለውም በሚል ጊዜን መነሻ በማድርግ የቀረበውን ክርክር በሚመልከት ገዝቻለሁ ካለ በኋላ እንደጠቀሰው ለዓመታት ያሕል በእጁ ይዞ የቆየ ስለመሆኑ በሥር ፍ/ቤቶች በተሰጡት ውሣኔዎች ላይ ያልተረጋገጠ የፍሬ ነገር ክርክር ከመሆኑም በላይ ለዚህ የሰበር ጉዲይ መነሻ የሆነው አንድ ተከራካሪ መሆን ይገባው የነበረ ሰው የክርክር ተካፊይ ሳይሆን የተሰጠው ውሣኔ መብቴን ይነካል ብል በቀረበ ጊዜ አቤቱታው መቼ መቅረብ አለበት ለሚለው የጊዜ ማሟያ እንደ ውሣኔው የሚፈፀም እና ያለመፈፀም ጉዲይ ብቻ በመሆኑ ክርክሩ ለጉዲዩ አግባብነት ያለው አይደለም።
No topics extracted.
ከዚህም አንፃር እንደ ውል ይጽደቅልኝ ብል ካስወሰነ በኋላ እንደ ውለ ያልፈፀመ ስለመሆኑም ገልፆ አልተከራከረም ስለሆነም ክርክሩ ተቀባይነት የለውም።
ላላውና ከሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ ጋር በተያያዘ የተነሣው ጉዲይ የአሁን ተጠሪ ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነውን አቤቱታ ወይም መዝገብ ያልከፈተበት አግባብነት ነው። ለአቤቱታው መሰረት አድርጎ ያቀረበው የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌ እንደሚያስረዲውና የነገሩ አመጣጥ እንደሚያስገነዝበው የተጠሪ የአቤቱታ አቀራረብ እኔ የክርክር ተካፊይ ባልሆንኩበት ተሰጠ የተባለውን ውሣኔ በያዘው መዝገብ ላይ በመቅረቡ የተዘጋውን መዝገብ እንዲይንቀሳቀስ ማድረግ ሲገባው እራሱን የቻለ አዱስ መዝገብ ማስከፈቱ እንደ ሥርዓት አነጋገር ግድፈት የተፈፀመበት ሆኖ ቢገኝም መብቱን ለማስከበር አንኳር የሆኑ ማሟያ ምክንያቶች ተሟልተው እስከተገኙ ድረስ በየትኛው መዝገብ ክርክሩ መካሄድ ነበረበት የሚለው ጥያቄ መሰረታዊ የሕግ ጉዲይ ሆኖ የጉዲዩን ውጤት ለማስለወጥ የሚያበቃ የሥነ ሥርዓት ግድፈት ስለመሆኑ በዚህ ረገድ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመ መሆኑን አያሳይም።
የሞግዚትነትን የሥልጣን ውልን በሚመለከት የተነሣው ጉዲይ የሥር ፍ/ቤቶች ትርጉም የሰጡበት አንድ የሕግ ክርክር እንደሆነ ከመዝገቡ ግልባጭ ተገንዝበናል። በሥር ፍ/ቤቶች በተሰጠው የሕግ ትርጉም ላይ እንደተተቸው የሞግዚቶች ንብረትን ወደ ሦስተኛ ወገን የማስተላለፍ ሥልጣን አካለ መጠን ካልደረሰው ልጅ የሚንቀሳቀስ ንብረት ጋር የተያያዘ እንጂ የማይንቀሳቀስን ንብረት በማናቸውም መንገድ ቢሆን ወደ ሦስተኛ ወገን ለማስተላለፍ የሚያስችል ሥልጣን የላላቸው ስለመሆኑ ይኸው ለጉዲዩ አግባብነት ያለው የክልለ ሕግ ግልባጭ ንባብ አስረጂ ነው። ይህንኑ በሕግ የተገደበ ሥልጣን ተላልፈው ንብረት ባስተላለፈ ጊዜ ንብረቱ የተላለፈለት ወገን ሉኖረው የሚችለው ማስተካከያ ምን እንደሆነ በሕጉ ላይ አልተመለከተም። ጥበቃው አካለ መጠን ላልደረሰው ልጅ ከመሆኑ በቀር ከዚህ የተለየ ውጤት ለገዢው የተደረገ ጥበቃ ስለመኖሩ በሕጉ ላይ አልተመለከተም። ስለሆነም ሻጮች በልላቸው ሥልጣን የፈፀሙት ተግባር መሆኑን መነሻ በማድረግ ሻጮች የሽያጭ ውለን ሉያፀድቁ ይገባል፣ በውጤት ደረጃ ስመሃብትነት ሉያዛውሩ ይገባል በሚል ተሰጥቶ የነበረውን ውሣኔ ከላይ በዝርዝር በተመለከቱት ምክንያቶች ውጤት እንዲይኖረው በማድረግ የተሰጠው ውሣኔ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ
348/1/ የፀና ሲሆን በተቃራኒው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 71141 የሰጠው ብይን ተሽሯል።
ይህ የሰበር ክርክር ላስከተለው ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ፤ መዝገቡ ተዘግቷል።