No summary available.
ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቶች፡- 1- የሮም ወርቅ ተስፊዬ በራስዋ እና ሞግዚት በሆነችላቸው ኤልሲ ተስፊዬ ፣ ፊሲል ተስፊዬ እና ደረጀ ተስፊዬ ፣ ወ/ሮ የሮም ወርቅ ቀረበች 2- አሸናፉ ተስፊዬ ቀረበ ተጠሪ፡- አሰግድ ሸነገለኝ አልቀረበም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ የቤት ሽያጭ ውልን መሰረት በማድረግ የተደረገውን ክርክር የሚመለከት ነው ክርክሩ በምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሽ የነበረው ተጠሪ ሲሆን፣ አመልካቾችን የከሰሰው ከእናታቸው ጋር በመሆን በውል የሸጡልኝን ቤት ያስረክቡኝ፣ የባለቤትነት መብቱንም በስሜ ያዛውሩልኝ በማለት ነው። ተጠሪዎች ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ በመሃከላችን የተደረገ ሕጋዊ ውል ስለላለ እንድንፈጽም አንገደድም በማለት ተከራክረዋል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ክርክሩን ከመረመረ በኋላ የተጠሪን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኖአል። ግራ ቀኝ ወገኖች ከውለ በፉት ወደ የነበሩበት እንዱመለሱም አዞአል። በልላ በኩል ደግሞ ተጠሪ ውሣኔውን በመቃወም ለኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን ፍ/ቤቱም ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ በመሻር አመልካቾች በውለ መሰረት ለመፈጸም ይገደዲለ በማለት ወስኖአል። የሰበር አቤቱታ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልትም ውሣኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት አቤቱታውን ሰርዞአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካቾች ሚያዝያ 7 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በጻፊት ማመልከቻ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሣኔ በሕግ ረገድ ያለው አግባብነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ ነው። በመሆኑም ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ክሱን በመጀመሪያ ደረጃ የሰማው ፍ/ቤት በሰጠው ውሣኔ እንደተመለከተው የሽያጭ ውለ ተደረገ የተባለው በ5/9/93 ዓ.ም ሆኖ ተጠሪ ክስ ያቀረበው ደግሞ በ27/9/99 ዓ.ም ነው። በክሱ እንደገለጸው ኤልሲ/ኤልሳቤት/ ፣ ፊሲል እና ደረጀ በወቅቱ አካለመጠን ያላደረሱ/ ክሱ ሲቀርብም/ በመሆናቸው የተወከለት በሞግዚታቸው በሮምወርቅ ተስፊዬ ነው። ተጠሪ የቤት ሽያጭ ውለን አደረግሁ የሚለው ከእነዚህም ህፃናት ጋር ጭምር ነው። ቤቱን ገዛሁ የሚለው በብር 200,000 እንደሆነ እና ውለ በተደረገበት ጊዜም ብር 57,285 ብቻ እንደከፈለ ቤቱን ግን እንዲልተረከበም በክሱ አመልክቶአል። ከላይ እንዲመለከትነው አመልካቾች በፍሬ ነገር ረገድ የተከራከሩት ከውለ ሕጋዊነት ጋር በማያያዝ ሲሆን፣ ክሱን የሰማው ፍ/ቤትም ውለ ተከሣሾችን /አመልካቾችን/ የማስገደድ ሃይል የለውም የሚል ምክንያት በመስጠት ነው ክሱን ሳይቀበል የቀረው ጉዲዩን በይግባኝ የሰማው ፍ/ቤት ደግሞ ውለ መደረጉ እስከ ታመነ ድረስ የማይፈጸምበት ምክንያት የለም ከሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል።
በበኩላችን እንደምንገነዘበው በጉዲዩ ላይ ትክክለኛ ውሣኔ ለመስጠት ይቻል ዘንድ ሉያዝ የሚገባው ጭብጥ በውለ መደረግ አለመደረግ ወይም በመታመን አለመታመን ላይ የሚመሰረት ሳይሆን፣ ውለ ሉያስከትለው በሚችለው ሕጋዊ ውጤት ላይ የሚመሰረት ነው አመልካቾች እንደውለ እንዱፈጽሙ በፍርድ ሉገደደ የሚችለት ውለ በሕጉ አግባብ ውጤት ላሰጥ የሚችል ነው ለማለት የሚቻል ከሆነ ነው ። ደጋግመን እንዲመለከትነው አመልካቾች ውለ በሕግ ረገድ ውጤት ሉኖረው አይገባም በማለት ተከራክረዋል። ውለ ተደረገ በተባለበት ጊዜ ኤልሲ /ኤልሳቤት/ ፣ ፊሲል እና ደረጀ እንደቅደም ተከተላቸው የ12 ፣ የ14፣ እና የ1ዐ ዓመት ህፃናት እንደነበሩ ተጠሪው ለሰበር አቤቱታው በሰጠው መልስ ጭምር ተረጋግጦአል። ይህም ማለት የቤት ሽያጭ ውለ የተደረገው በሞግዚታቸው አማካይነት ነው ማለት ነው ቤቱ የሁለም አመልካቾች የጋራ ሃብት በመሆኑ ሉሸጥ ወይም ለሶስተኛ ወገን ሉተላለፍ የሚችለው የሁለም አመልካቾች የጋራ ስምምነት ሲኖር እንደሆነ በፍ/ብ/ሕግ ቁ 1226 ተደንግጎአል። ለዚህም ነው ተጠሪ አመልካቾች አንድ ላይ በመሆን ቤቱን ሸጠዉልኛል በማለት ክስ የመሰረተው ይሁንና ከጋራ ባለሃብቶቹ ከፉልች ለአካለ መጠን ያላደረሱ ህፃናት በመሆናቸው /ውለ ተደረገ በተባለበት ጊዜ/ እና ውለ ሕጋዊ ውጤት የለውም የሚል ክርክርም ስለተነሳ ሕጉ ለአካለ መጠን ያላደረሱ ልጆችን /ህፃናት/ ንብረት አጠባበቅ በሚመለከት ያደረገውን ጥበቃ በዝርዝር ማየቱ ተገቢ ይሆናል።
ክርክር የተነሳው በኦሮሚያ ብ/ክ/መ/በመሆኑ የተሰማውም በክልለ ፍ/ቤቶች ነው።
የኦሮሚያ ብ/ክ/መ/የራሱ የሆነ የቤተሰብ ሕግ በአዋጅ ቁ 69/1995 /በአዋጅ ቁ 83 /1996 የተሻሻለው / አውጥቶአል። ይህ የቤተሰብ ሕግ አካለ መጠን ስላላደረሱ ሰዎችን በሚመለከት በአዋጅ ምዕራፍ አሥራ ሁለት ሥር ዝርዝር ድንጋጌዎችን አካቶአል። አካለ መጠን ያላደረሰውን ሰው አሳዲሪ እና ሞግዚት ሥልጣን በሚመለከትም በክፍል ሶስት ሥር የተቀመጡ ድንጋጌዎችን ሲኖሩ ከእነዚህም መካከል ለተያዘው ክርክር አወሳሰን ተገቢነት ያለው በአንቀጽ 294 የተመለከተው እንደሆነ ለመገንዘብ ችለናል። በዚህ ድንጋጌ እንደተቀመጠው ሞግዚቱ መሸጥ የሚችለው አካለ መጠን ያላደረሰውን ሰው ንብረት የሆኑ የሚንቀሳቀሱ ግዙፍ ንብረቶችን አክሲዮኖችንና የገንዘብ ሰነድችን ነው። ሞግዚቱ አካለ መጠን ያለደረሰውን ሰው ንብረት የሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ እንደሚችል በዚህ ድንጋጌ አልተመለከተም። ይልቁንም ሕጉ የመረጠው /የተከተለው/ ሞግዚቱ ሉሸጣቸው የሚችላቸውን ንብረቶች በግልጽ አስቀምጦ /ደንግጎ / ማለፍ ነው ሕጉ ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ደግሞ በተቃራኒው አስተሳሰብ ሲታይ ሞግዚቱ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለመሸጥ በሕጉ በቀጥታ ያልተፈቀደለት መሆኑን ነው። የተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግም እንደዚሁ በአንቀጽ 277/1/ ተመሣሣይ ድንጋጌ አስቀምጦአል።
እንደምንመለከተው ሕጉ አካለመጠን ላላደረሱ ሰዎች ልዩ ጥበቃ ይኖር ዘንድ ግልጽ ድንጋጌዎችን በቤተሰብ ሕጉ አካቶአል። እንኳንስ አካለመጠን ባላደረሰው ሞግዚት የተደረገው ቀርቶ በራሱ አካለ መጠን ባላደረሰው ሰው ወይም ልጅ የተደረገው ውልም ፈራሽ እንደሆነ በኦሮሚያ ቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 316 እንደዚሁም በተሻሻለው የፋዳራል መንግስት የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 299 ተደንግጎአል። እነዚህን ድንጋጌዎችን ቀደም ሲል ከተቀጠቀሱት ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን ስናየው በዚህ መዝገብ ለቀረበው ክስ መነሻ የሆነው የቤት ሽያጭ ውል በሕጉ ረገድ ተፈጻሚነት ያለው ነው ለማለት አይቻልም። የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት እና የጠ/ፍ/ቤቱ ሰበር ችልት የደረሱበት መደምደሚያ ከዚህ አንፃር ሲታይ ሕጉን በአግባቡ በመተርጎም የተደረሰ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም። ከዚህ የተነሣም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ብለናል።
ው ሣ ኔ
No topics extracted.