No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 12 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሀመድ አመልካች፡- ወ/ሮ አስመረት ነጋሲ በይን አቶ ግርማቸው ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ጽጌረዲ ስዩም ከነጠበቃቸው ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
በዚህ መዝገብ ለሰበር ለቀረበው ጉዲይ መነሻ ሆኖ የተገኘው ሟች አቶ ወልደማርያም ወልደጋብር ሐምል 29 ቀን 1996 ዓ.ም በፍታብሄር ሕግ ቁጥር 881 መሰረት አድርገዋል የተባለው ግልጽ ኑዛዜ እንዱፀድቅ ተደርጏ በዚሁ በፍትሐብሄር ሕጉ ቁጥር 996(1) መሰረት የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ ይሰጠኝ በሚል ቀርቦ የነበረ ጥያቄ ነው።
ሟች ኑዛዜውን አድርገዋል የተባለው ለአሁኗ አመልካች ሲሆን የአሁኗ አመልካችም የኑዛዜ ይጽደቅልኝ ጥያቄውን ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበው ፍ/ቤቱ በኑዛዜው ሰነድ በምስክርነት ፈርመዋል የተባለት ምስክሮች ቀርበው እንዱሰሙ ካደረገ በኋላ ምስክሮቹ በአቤቱታው መሰረት አስረድተዋል የኑዛዜው የሰነድ ማስረጃም ቀርቧል። ስለዚህ ኑዛዜው ፀድቋል አመልካችም የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸው ተረጋግጧል የሚል ውሣኔ ሰጥቷል።
ከዚህ በኋላ የአሁኗ ተጠሪ ወ/ሮ ጽጌረዲ ስዩም በዝምድና የዘር ሐረግ የሟች ወራሽ እኔ ነኝ፤ አመልካች ሟች ኑዛዜ አድርገውልኛል ያለት ሀሰት ነው የቀረበው የሟች ኑዛዜ አይደለም በኑዛዜው ላይ የሰፈረው ፊርማ የሟች አይደለም በሚል በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ በማቅረባቸው የኑዛዜው ጉዲይ እንደገና እንዱንቀሳቀስ ተደርጓል። ፍ/ቤቱ በኑዛዜው ጉዲይ ላይ ሁለቱን ወገኖች ካከራከረ በኋላ በመቃወሚያ አቅራቢ በኩል በኑዛዜው ሰነድ ላይ የሰፈረው ፊርማ የሟች አይደለም ተብል ስለተካደ በሰነደ ላይ በጣት አሻራ የተፈረመው የሟች መሆን አለመሆኑ በፍረንሲክ ምርመራ ተጣርቶ ውጤቱ ይቅረብ ብል አዞ የቴክኒክ ባለሙያው ፊርማውን ከላልች ፊርማዎች ጋር ለማመሳከር አልተቻለም የሚል መልስ በመስጠቱ ላላ የሰማው ማስረጃ ሣይኖር ወደ ውሣኔ መስጠት አምርቷል። በሰጠው ውሣኔም መቃወሚያ አቅራቢዋ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የሟች አይደለም ቢለም የሟች ፊርማ ስላለመሆኑ ለማስረዲት አልቻለም በሚል ምክንያት አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 360(2) መሰረት አጽድቆታል። በዚሁ ውሣኔው መቃወሚያ አቅራቢዋ የአሁኗ ተጠሪም የሟች ህጋዊ ወራሽ መሆኔ ይረጋገጥልኝ ብለው ያቀረቡትን ጥያቄም አብሮ በማየት የሟች ወራሽ ናቸው ብሎል።
በአሁኗ ተጠሪ የይግባኝ አቤቱታ መነሻ ጉዲዩ ቀርቦለት የተመለከተው የከተማ ነክ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትም መርምሮ ይግባኙ አያስቀርብም ብልታል።
በእነዚህ ውሣኔዎች መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል ተብል አቤቱታ የቀረበለት የአዱስ አበባ ከተማ ነክ ሰበር ችልት ደግሞ በጉዲዩ ላይ ግራቀኙን አከራክሮ በመጨረሻም መርምሮ ኑዛዜው ይጽደቅልኝ ብለው ያቀረቡት የአሁኗ አመልካች በኑዛዜው ላይ ያለው የሟች ፊርማ ስለተካደ የሟች ፊርማ ስለመሆኑ በሕጉ የማስረዲት ሸክም አለባቸው። ነገር ግን አመልካች የሟች ፊርማ ስለመሆኑ ለማስረዲት ያሰሙት ማስረጃም ሆነ ለማሰማት ያዘጋጁት ምስክር የለም፣ ስለዚህ የሟች ፊርማ ስለመሆኑ ስላላስረደ የሟች የኑዛዜ ወራሽ መሆን አለብኝ በሚል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም። ይኼው ሣይረጋገጥ ወ/ሮ አስመረት ነጋሲ የሟች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው ተብል በሥር ፍ/ቤት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.348(1) መሰረት ተሽሯል የሚል ውሣኔ ሰጥቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም በከተማ ነክ ሰበር ችልት የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በሚል ምክንያት በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 80(3/ሀ) መሰረት የቀረበ ነው።
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ይታይ በመባለ ማመልከቻው ለአሁኗ ተጠሪ ተልኮላቸው እንዱቀርቡ ተደርጏ የግራ ቀኙ ጠበቆች በተገኙበት ክርክሩ ተሰምቷል።
የአመልካች ጠበቃ አመልካች በኑዛዜው ሰነድ ላይ ያለው የጣት አሻራ ፊርማ የሟች ስለመሆኑ አስቀድመው ምስክሮች አቅርበው በማረጋገጥ ውሣኔ ተሰጥቷቸዋል። የአሁኗ ተጠሪ መቃወሚያ ካቀረቡ በኋላም ቢሆን በሰነደ ላይ ያለው የጣት አሻራ የሟች ስለመሆኑ በምርመራ ይጣራ ተብል ሲላክ ቀለም የበዛበት ስለሆነ ከላልች ፊርማዎች ጋር ማመሳከር አይቻልም ተብል ተመለሰ እንጂ የሟች ፊርማ አይደለም አልተባለም፣ ስለዚህ ተጠሪዋ የሟች ፊርማ አይደለም ካለ የማስረዲት ሸክሙ የተጠሪዋ እንጅ የአመልካች ላሆን አይችልም የሚል ክርክር ያቀረቡ ሲሆን የተጠሪዋ ጠበቃ ደግሞ በቀረበው መቃወሚያ መነሻ በሰነደ ላይ ያለው ፊርማ የሟች መሆን አለመሆኑ በፍረንሲክ ምርመራ ተጣርቶ እንዱቀርብ ታዞ ተልኮ ቀለም የበዛበት በመሆኑ የሟች ፊርማ ስለመሆኑ ለማረጋገጥ አይቻልም ተብል ስለተመለሰ በተጠሪዋ በኩል የሟች ፊርማ ስላለመሆኑ አስረድተናል የሚል መልስ ሰጥተዋል።
ይህ ችልትም ጉዲዩን መርምሯል።
በኑዛዜው ሰነድ ላይ ያለው የጣት ምልክት ፊርማ የሟች ስለመሆኑ ወይም ስላለመሆኑ የማስረዲት ሸክም ያለበት የትኛው ተከራካሪ ወገን ነው በሚል የተነሣውን ክርክር በተመለከተ በኑዛዜው የሰፈረውን ቃልና ኑዛዜው መኖሩን ማስረዲት ያለበት በዚሁ ኑዛዜ ተጠቃሚ ነኝ የሚለው ሰው መሆኑን የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 896 ያስረዲል።
የአስረጂውን አይነት በሚመለከት በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 897(1) ላይ እንደተመለከተው በግልጽ ወይም በተናዛዡ ጽሐፍ የተደረገ ኑዛዜ ስለመኖሩ የሚረጋገጠው የኑዛዜውን ጽሐፍ ዋናውን በማቅረብ ወይም ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ዘንድ ወይም በፍርድ ቤት መዝገብ ቤት ሹም ትክክለኛ ሆኖ በተመሰከረ አንድ ግልባጭ በማቅረብ ነው።
እንዱህ አይነቱን ኑዛዜ አድርጓል የተባለው ሰው ህጋዊ ወራሽ መሆኑ የታወቀ ሰው በኑዛዜው ላይ የሚያቀርበውን የተቃውሞ ክርክር በተመለከተም በፍትሐብሄር ሕግ አንቀጽ 1677(1) ላይ ግዳታዎቹ ከውል የተገኙ ባይሆኑም ስለውልች በጠቅላላው የተመለከቱት ደንቦች በማሟያነት ይፈፀሙባቸዋል ተብል በተደነገገው መሰረት ስለውል ጉዲይ ማስረጃዎች በሚመለከተው ምዕራፍ ሥር የሚገኘው የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 2007(2) ለኑዛዜም ጉዲይ ስለሚያገለግል ወራሹ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ ወይም ጽሐፍ የአውራሹ ስለመሆኑ አላውቅም ማለቱ ብቻ ይበቃል።
ፊርማው ወይም ጽሕፈቱ የሱ ነው የተባለው ሰው ስለመሆን አለመሆኑ ለማረጋገጥ ደግሞ ዳኞች እንዱመረመር ሉያዙ እንደሚችለ የፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 208 ላይ ተገልጿል።
በዚህም ጉዲይ የአሁኗ አመልካች ሟቹ አቶ ወልደማርያም ወልደጋብር ሐምል 29 ቀን 1996 ዓ.ም ያደረጉልኝ ግልጽ ኑዛዜ አለ ብለው የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን እንዱረጋገጥ የኑዛዜውን ጽሐፍ በማስረጃነት አቅርበዋል። የአሁኗ አመልካች በመጀመሪያ የኑዛዜውን ጽሁፍ ብቻ ሣይሆን ኑዛዜው ሲደረግ በምስክርነት ተገኝተው በኑዛዜው ላይ ፈርመዋል የተባለትን አራት ምስክሮች ጭምር ፍ/ቤት በማቅረብ አስመስክረዋል። ፍ/ቤቱም ማስረጃውን መርምሮ ኑዛዜው በሕጉ መሰረት የተደረገ ነው በማለት በጥያቄአቸው መሰረት በማጽደቅ የአሁኗ አመልካች የሟች የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ውሣኔ ሰጥቷል።
ከዚህ ውሳኔ በኋላ የአሁኗ ተጠሪ በዝምድና የዘር ሐረግ የሟች ህጋዊ ወራሽ እኔ ነኝ፣ አመልካች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው ተብል የተወሰነው የወራሽነት መብቴን የሚያሳጣ ነው፣ ሟች አድርገዋል የተባለው ኑዛዜ ሀሰት ነው፣ ፊርማው የሟች አይደለም በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ በማቅረብ እንደገና በኑዛዜው ጉዲይ ላይ ክርክሩ በሚሰማበት ጊዜ የአሁኗ ተጠሪ የሟችን ኑዛዜ የመቃወም መብት የላቸውም ህጋዊ ወራሽ አይደለም በሚል የተነሣ ክርክር የላለና ህጋዊ ወራሽ ነኝ ብለው ባቀረቡት መሰረት እንዱቀጥል የተደረገ ስለሆነ ከፍሲል እንደተገለፀው በመቃወም አመልካችዋ የአሁኗ ተጠሪ በኑዛዜው ሰነድ ላይ የሰፈረው የጣት ምልክት ፊርማ የአውራሼ የሟች ስለመሆኑ አላውቅም ማለታቸው ብቻ በሕጉ በቂ ይሆናል። ተጠሪዋ ግን ከዚህ አልፈው በኑዛዜው ሰነድ ላይ ያለው ፊርማ የሟች አይደለም በማለት በግልጽ በመካድ ተከራክረዋል።
የአዱስ አበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኑዛዜው ሰነድ ላይ የሰፈረው የጣት ምልክት ፊርማ የሟች መሆን አለመሆኑን አረጋግጦ ለመወሰን እንዱቻል በፍረንሲክ ምርመራ እንዱጣራ ያዘዘ ቢሆንም የተላከለት የቴክኒክ ምርመራ ክፍል በኑዛዜው ሰነድ ላይ ያለው የጣት ምልክት ፊርማ ቀለም የበዛበት ስለሆነ ከላልች ማመሳከሪያዎች ጋር በማመሳከር ለመመርመር አይቻልም ብል መልሶታል።
በኑዛዜው ጽሐፍ ላይ ያለው ፊርማ ቀለም የበዛበት በመሆኑ ምክንያት የሟች ፊርማ ነው አይደለም የሚለው በፍረንሲክ ምርመራ ሉረጋገጥ ባልቻለበት ሁኔታ የኑዛዜው ተጠቃሚ ነኝ የሚለት የአሁኗ አመልካች የተጣለባቸውን የማስረዲት ሸክም አልተወጡም የሚል መደምደሚያ ላይ ለመድረስ አይቻልም። አመልካች የአሁኗ ተጠሪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ በማንሣት ከመቅረባቸው በፉት በኑዛዜው ላይ ተገኝተው ፈርመዋል የተባለትን አራት ምስክሮች ጭምር በማስረጃነት ቆጥረው ቀርበው እንዱሰሙ አድርገው የነበረ ሲሆን ተጠሪዋ መቃወሚያውን ካቀረቡ በኋላ ግን ምስክሮቹ እንደገና ቀርበው እንዱመሰክሩ ሣይደረግ ታልፎል። የከተማ ነክ ሰበር ሰሚ ችልት በቀረበው የኑዛዜ ሰነድ ላይ ያለው የጣት ምልክት ፊርማ የሟች አይደለም ተብል የተረጋገጠበት መንገድ ሣይኖር እና በኑዛዜው ላይ ያለት አራት ምስክሮች መቃወሚያው ከቀረበ በኋላ እንደገና ቀርበው እንዱመሰክሩ ሣይደረግ የአሁኗ አመልካች የማስረዲት ግዳታቸውን አልተወጡም ያለው ተቀባይነት ሉኖረው አይችልም። የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኑዛዜው ሰነድ ላይ ያለው የሟች ፊርማ ነው የተባለው ቀለም ስለበዛበት በፍረንሲክ ምርመራ ለማጣራት አይቻልም ተብል ሲመለስ ፊርማው የሟች ስላለመሆኑ ማስረዲት ያለባቸው የሟች ወራሽ ነኝ ብለው መቃወሚያ ያቀረቡት የአሁኗ ተጠሪ ናቸው ያለውም ትክክል አይደለም።
በፍትሐብሄር ህግ ቁጥር 881 መሰረት ግልጽ ኑዛዜ ተደርጓል ተብል በቀረበው የኑዛዜው ጽሐፍ ላይ ተናዛዡ በጣት ምልክት ፈርመዋል የተባለው በቀለም መብዛትም ሆነ ቆይቶ በመደብዘዙ ምክንያት በፍረንሲክ ተመርምሮ ሉረጋገጥ የሚችል አይደለም የሚባል ሆኖ ከተገኘ ምን ላደረግ ይችላል? ሟች ኑዛዜውን ሲያደርጉ በምስክርነት ተገኝተው በኑዛዜው ሰነድ ላይ ፈርመዋል የተባለት አራት ምስክሮች በማስረጃነት በቀረበው የኑዛዜ ሰነድ መሰረት ስለኑዛዜው መደረግ እና ሟች በኑዛዜው ሰነድ ላይ በጣት ምልክት ፈርመዋል ተብል በቀረበው መሰረት ስለመፈረማቸው ለማስረዲት ይችላለ አይችለም? የሚለው ሲመረመር በሕጉ በኩል የሚከለክል ነገር የለም። የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሰበር ችልት በውሣኔው ላይ የአሁኗ አመልካች ስለኑዛዜው ጉዲይ ለማስረዲት ያሰሙትና ለማሰማትም ያዘጋጁት ምስክር እንደላለ አድርጏ ይግለጽ እንጂ አመልካች ከመጀመሪያው የኑዛዜ ይጽደቅልኝ ጥያቄውን ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲያቀርቡ በኑዛዜው ሰነድ ላይ ፈርመዋል የተባለትን አራት ምስክሮች ቆጥረው ቀርበው እንዱሰሙ ማድረጋቸውን የመጀመሪያው የፍ/ቤቱ ውሣኔ ያስረዲል። የአሁኗ ተጠሪ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት መቃወሚያ አቅርበው የኑዛዜው ጉዲይ እንደገና ተንቀሳቅሶ ክርክሩ በሚደረግበት ጊዜ በኑዛዜው ላይ ነበሩ የተባለት ምስክሮች ቀርበው እንዱሰሙ መደረግ ሲገባው ፍ/ቤቱ አልፍታል። የተቆጠሩት ምስክሮች በመጀመሪያ ያልነበሩት የአሁኗ ተጠሪ ባለበት እንደገና ቀርበው እንዱሰሙ ማድረጉ የፍ/ቤቱ የሥራ ድርሻ ስለሆነ የተከራካሪዋ የአሁኗ አመልካች ጉድለት ተደርጏ የሚታይ አይደለም።
ሰበር ችልቱ ይህንን ከመዝገቡ ተመልክቶ በመቃወሚያው የክርክር ሂደት ሣይሰሙ የታለፈትን የአሁኗን አመልካች አራት ምስክሮች የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እንደገና ምስክሮቹን ሰምቶ በኑዛዜው ጉዲይ ላይ ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት መመለስ ሲገባው አመልካች ያሰሙትና ለማሰማት ያዘጋጁት ምስክር ስለላለ ክርክራቸው ተቀባይነት የለውም በማለት የወሰነው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። ስለሆነም የሚከተለው ተወስኗል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ሰበር ችልት በመ/ የካቲት 2 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ተሽሮ በኑዛዜው ሰነድ ላይ ፈርመዋል የተባለት አራት ምስክሮች ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች ባለበት ቀርበው በጽሐፍ ማስረጃነት በቀረበው የኑዛዜ ሰነድ ላይ በተገለፀው መሰረት ስለኑዛዜው መደረግ እና በኑዛዜው ሰነድ ላይ ሟች በጣት ምልክት ፈርመዋል ስለተባለው ተጠይቀው የሚሰጡት ምስክርነት ከተሰማ በኋላ በጉዲዩ ላይ ተገቢውን እንዱወሰን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት ተመልሷል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ፍ/ቤት በዚህ ውሣኔ መሰረት እንዱፈጽም ታዟል። ይተላለፍ።
በዚህ መዝገብ በተደረገው ክርክር የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት፡ የሰ/መ/ ጥር 10 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ሐጏስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ስላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ አቶ ገብረሉባኖስ ረዲ ጠበቃ ከበደ መንገሻ ቀረበተጠሪ፣ ወ/ሮ አዜብ አሰፊ ጠበቃ አዱሱ ሽባባው ቀረበ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ የቀረበው አባትነትን ስለማስረዲት ዲኝነት በተጠየቀ ጊዜ አባትነትን የማስረዲት ጉዲይ እና የውሣኔ አሰጣጥ አስመልክቶ በግራቀኙ ጉዲይ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ መነሻ በማድረግ ተገቢውን ትርጉም ለመስጠት ሲባል ነው።
የጉዲዩም መነሻ እንደሚከተለው ነው። ከዚህ ጉዲይ ጋር ተያያዥነት ባለው በሰበር መ/ ጥር 10 ቀን 2003 ዓ.ም በተሰጠው የሰበር ውሣኔ ላይ እንደተገለፀው የአሁን ተጠሪ ከሟች አቶ መዝሙር አፈወርቅ ጋር በጋብቻ እየኖሩ እያለ ህፃን ሜሮን እንደተወለደች ገልፀው አባቷ አቶ መዝሙር አፈወርቅ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ስለሆነም የህፃን ሜሮን ወራሽነት ይረጋገጥልኝ በማለት ለአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ህፃን ሜሮን የሟች አቶ መዝሙር አፈወርቅ ወራሽ ናት በሚል ከተወሰነ በኃላ የአሁን አመልካች ይህቺ ህፃን የተወለችው ከአሁን ተጠሪ ጋር በትዲር እያለ መሆኑን የጋብቻውን ዘመን እና ህፃኗ የተወለደችበትን ቀን በመጥቀስ ካስረደ በኃላ አባት እኔ ሆኜ እያለ ሟች አቶ መዝሙር አፈወርቅ አባት እንደሆኑ ተደርጎ የተሰጠው ውሣኔ የእኔን መብት ይነካል ይሰረዝልኝ በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሰረት ጥያቄ አቅርበው ይኸው ጉዲይ እስከ ከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ደርሶ የህፃን ሜሮን አባት ማን ነው? የሚለውን የልጅነት ጉዲይ ያስነሳ ክርክር ሆኖ በመገኘቱ ይህ ዓይነት ጉዲይ በፋዳራል ፍ/ቤቶች ስልጣን ሥር የሚወድቅ እንጂ የአ/አበባ ፍ/ቤቶች ተመልክተው ለመዲኘት ሥልጣን የላቸውም ስለሆነም የህፃን ሜሮን አባት ማን ነው? የሚለው ሥልጣን ባለው የፋዳራል ፍ/ቤት ተወስኖ እስከሚታወቅ ድረስ ህፃን ሜሮን የአባቷ የአቶ መዝገሙር አፈወርቅ ወራሽ ናት በሚል ቀደም ሲል በአ/አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሰጥቶት የነበረውን የውሣኔ ክፍል ለጊዜው አግድ ግራቀኙን አሰናብቷቸዋል።
ይህም የሰበር አቤቱታ የቀረበበት ፍርድ ምክንያት የሆነው በዚህ መሰረት የሜሮን አባት ማን ነው? የሚለው አከራካሪ ነጥብ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ታይቶ ዲኝነት እንዱሰጥበት የአሁን አመልካች አቶ ገ/ሉባኖስ ረዲ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የአቤቱታቸውም ይዘት ከተጠሪ ጋር ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ በፍቺ እስከተለያየንበት እስከ 1994 ድረስ በጋብቻ ላይ እያለን ከወልድናቸው ላልች ልጆች በተጨማሪ ህፃን ሜሮን ገ/ሉባኖስን ግንቦት 13 ቀን 1989 ዓ.ም ተወልዲለች ተጠሪ ከእኔ ጋር በጋብቻ ተሳስራ እየኖረች እያለ ይህቺ ህፃን ተወልዲ እያለ ተጠሪ ይህንን በመካድ ከሟች ከአቶ መዝሙር አፈወርቅ ጋር ከጥር 28 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ በጋብቻ እያለ ሜሮን ከአቶ መዝሙር አፈወርቅ እንደተወለደች አድርገው የወራሽነት ማስረጃ ለማግኘት ጥረት ማድረጋቸውን ስለተረዲሁ የእኔ አባትነት በፍርድ ይረጋገጥልኝ የሚል ነው።
ተጠሪም የህፃን ሜሮን አባት ሟች አቶ መዝሙር እንጂ አመልካች እንዲልሆነ በሚያስረዲ አኳኋን ክደው በመከራከራቸው ክሱ የቀረበለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ ጥር 14 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት አመልካች በክስ አቤቱታቸው የገለፁት ሜሮን የተወለደችው ከተጠሪ ጋር በጋብቻ ተሳስረው በሚኖሩበት ጊዜ ነው በጋብቻ ጊዜ ለተወለደ ህፃን አባቱ በጋብቻው ያለው ሰው እንደሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 126 ላይ የህግ ግምት ተቀምጧል። በዚህ የህግ ግምት አመልካች የሜሮን አባት ናቸው ይህንን የህግ ግምት ተጠሪ እናቲቱ አባቷ ላላ ሰው ነው በማለት ውድቅ ማድረግ አይችለም በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 143 በፍርድ ቤት ውሣኔ አባትነት የሚታወቀው የልጅ አባት ያልታወቀ ወይም አባቱ ልጁን የካደው እንደሆነ ነው አመልካችም ሜሮን ልጄ አይደለችም ብለው የመካድ ክስ አላቀረቡም በሕግ ግምት ደግሞ አመልካች የሜሮን አባት ናቸው ስለሆነም የሜሮን አባት የታወቀ በመሆኑ አባቷ ለታወቀ ሰው ልጅነቷ በፍርድ ቀርቦ የሚረጋግጥበት አግባብ የለም ክሱ ለፍርድ የሚቀርብ አይደለም በማለት የፍርድ ሐተታ አስፍሮ የአመልካች አቤቱታ ለፍርድ የሚቀርብ ባለመሆኑ የክስ አቤቱታው ተሰርዟል በማለት ተወስኗል።
ይህም ፍርድ በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ስህተት የላለበት መሆኑ ተገልፆ የአሁን አመልካች የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነትን ሳያገኝ በመቅረቱ ይህ የሰበር ጉዲይ ላቀርብ ችሎል።
የሰበር አቤቱታው ፍሬ ቃልም የህፃን ሜሮን አባት ማን ነው? የሚለው ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ሉረጋገጥ ካልቻለ እንዳት ፍትህ ማግኘት ይቻላል? የሚለውን የሚያብራራ ነው።
እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል እንደመረመርነውም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ግራቀኙን ያከራከረው ጉዲይ በፍርድ ሉያልቅ የሚገባው አይደለም ከሚል መደምደሚያ ሉደርስ የቻለው በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 በአንቀጽ 126 እና 143 የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ይዘትና ትርጉም አዛብቶ በመተርጎሙ የተነሳ እንደሆነ ተገንዝበናል ይኸውም አባትነት የሚረጋገጥባቸው ሶስት መንገድች ያለ ሲሆን እነዚህም መንገድች በቀደም ተከተል ተደንግገዋል። በቅድሚያ የተቀመጠው ጋብቻ መኖርንና ክርክር የተነሳበት ህፃን በዚህ ጋብቻ ጊዜ የመወለድን ሁለት መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች መነሻ በማድረግ የልጅ አባት ወይም አባቷ ባል የሆነው ሰው ይሆናል የሚል ግምት ህጉ የወሰደበት ነው ይህ የህግ ግምት ነው ይህ የህግ ግምት መረጋገጥ በሚገባቸው ፍሬነገሮች ላይ የተመሰረተ ነው እነዚህን ፍሬ ነገሮች ማረጋገጥ የቻለ ወገን ላላ የተለየ ማስረጃ ማቅረብ ሳይጠበቅበት ህግ በእራሱ ግምት የወሰደለት መሆኑን የሚያሳይ ነው።
የህግ ግምት ህግ አውጭው ከተለያዩ መነሻ ሀሳቦች በመነሳት ህጉ የሚገመተው ነገር እንደማስረጃ ሆኖ እንዱያገለግል ያስቀመጠው እንጂ በህጉ የተቀመጠው ግምት ያለ ፍርድ ቤት ዕውቅና በእራሱ ተፈፃሚ እንዱሆን አይደለም የህግ ግምት እንደማስረጃ ከሚወሰደት እንደ ሰነድ፣ የሰው ምስክርነት ቃል፣ የእምነት ቃል ገላጭ ማስረጃ ወዘተ ሆኖ ሉያገለግለ ከሚችለት የማስረጃ ዓይነቶች የሚመደብ እንጂ በእራሱ እንደፍርድ ሉቆጠር የሚችል አይደለም።
የህግ ግምት ተጠቃሚ የሆነው ወገን በቅድሚያ በህጉ ግምት መነሻ የሆኑትን መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች የማረጋገጥ ግዳታ አለበት። ከላላው ወገን ተከራካሪ መብት አንፃር እነዚህን መሰረታዊ ፍሬ ነገሮች ማረጋገጡና አለመረጋገጡ ክርክሩን በሚያየው ፍ/ቤት ዲኝነት የሚያስፈልገው ነው አረጋግጦ የህግ ግምት በማስረጃነት እንዱያለግለው ወይም እንዱጠቅመው ከማድረግ ደረጃ እንኳ ቢደርስ እንደ ግምቱ ዓይነት ሁኔታ ሉስተባበል የሚችል ከሆነም ላላው ተከራካሪ ወገን በተራው እነዚያ የህግ ግምት መነሻ የሆኑት ፍሬነገሮች ያልተሟለ ያልተረጋገጡ መሆኑን በፍ/ቤት በማስረዲት የህጉን ግምት የማፈረስ መብት አለው ይህ ሁለ ተግባር በክርክር ሂደት በፍርድ ቤት ሉረጋገጥ የሚችል የዲኝነት ሥራን የሚጠይቅ ጉዲይ መሆኑ እየታወቀ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአሁን አመልካች በክስ አቤቱታው የገለፃቸው ፍሬ ነገሮች እንዲለ እውነት አድርጎ በመያዝ እና በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 126 እንደተነገረው የህፃን ሜሮን አባትነት በህግ ግምት ተረጋግጧል ላላ የፍርድ ቤት ተጨማሪ ሥራ የሚያስፈልገው አይደለም ከሚለው መደምደሚያ የደረሰው ከላይ በዝርዝር እንዲሰፈረው የህግ ግምት የሚቋቋምበትንና የህግ ግምት እንደማስረጃ ሉወሰድ የሚችል መሆኑን ካለማገናዘብ በስህተት መተርጉሙን የሚያሳይ በመሆኑ በአተረጓጏም ረገድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ በፈፀመው ስህተት መነሻነትም ለተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 143 ተፈፃሚነት ውስጥም በስህተት እንዱተረጎም አድርጎታል /አብቅቶታል/።
አባትነት በፍርድ ሉነገር የሚችልበት ሁኔታ በአንቀጽ 143 ሲቀመጥ በቅድሚያ አባትነት ከህግ ግምት የሚመነጭ በህግ ግምት የሚረጋገጥ ከሆነ በዚህ አኳኋን በጋብቻ ጊዜ የመወለድ ሁኔታ ካለ በአንቀጽ 126 በተመለከተው በህግ ግምት የሚረጋገጥ እንጅ አንቀጽ 143 ሥራ ላይ የማይውል መሆኑን እንዱሁም የጋብቻ ግንኙነት ወይም በህግ የታወቀ ግንኙነት ሳይኖር የተወለደን ልጅ አንድ ሰው አባት ነኝ በሚል በፅሐፍ ያወቀ እንደሆነ በዚሁ ሥርዓት አባትነትን ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን ከላይ በተቀመጡት ሁኔታዎች በማይሸፈኑት በቁጥር 143 የተዘረዘሩት ምክንያቶች ባጋጠሙ ጊዜ እንደ ሶስተኛ የአባትነት ማረጋገጫ መንገድ አባትነት በፍርድ የሚነገርበትን አግባብ የደነገገ በመሆኑ የአሁን አመልካች አባትነቴ በአንቀጽ 126 መሰረት ታይቶ ይረጋገጥልኝ በማለት ያቀረቡትን የዲኝነት ጥያቄ ልክ በአንቀጽ 143 አባትነት በፍርድ ይረጋገጥልኝ በማለት እንደቀረብ የዲኝነት ጥያቄ አድርጎ መተርጎሙ ከመጀመሪያው ስህተት የመነጨ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈፀመ የህግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
በዚህ ሁለ ምክንያት የግራቀኙ ክርክር በፍርድ ሉያልቅ የሚገባው በየፉናቸው ያቀረቡት የህግና የፍሬ ነገር ክርክር በየተራቸው በሚያቀርቡት የማስረጃ አግባብነት ጥንካሬ ታይቶ ፍርድ ሉያርፍበት የሚችል ሆኖ እያለ በተሳሳተ የህግ ትርጓሜ መነሻ ጉዲዩ በፍርድ ሉያልቅ የሚገባው ሆኖ አልተገኘም በማለት የሰጠው ፍርድ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት እና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት እንደቅደም ተከተለ በኮ/መ/ በ14/5/2002 ዓ.ም የተሰጠው ፍርድ እና በመ/ በ18/6/2002 የተሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በግራቀኙ መካከል የተነሳውን ክርክር በፍርድ ሉያልቅ የሚገባው ስለሆነ በፍርድ ሀተታው እንደተገለፀው በጉዲዩ ላይ ግራቀኙን አከራክሮን ተገቢውን ዲኝነት ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 341 መሰረት ጉዲዩን መልሰናል።
ግራቀኙ እዚህ ሰበር ድረስ ክርክር ለማድረግ የበቁበት የሥር ፍ/ቤቶች በፈፀሙት የህግ ስህተት ሳቢያ በመሆኑ ግራቀኙ የየራሳቸውን ወጭና ኪሣራ ይቻለ።
No topics extracted.