No summary available.
የሰ/መ/ቁ. 459ዐ5 ጥቅምት ዐ3 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ሡልጣን አባተማም አመልካች፡- ሚስስ ሚላን ፑሲጂ ማልጂ ሚስስ ሲልቪ ፑሲጂ ጠበቃ የሽጥላ አስፊ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ ፍርድን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበትን አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪዎች ባቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ መነሻ ነው። የአሁኗ ተጠሪ ከሣሽ የነበሩ ሲሆን ተከሣሽ ሚስተር ጆርጅ ፓስልዱ ማልጂ ነበሩ። የአሁኑ ተጠሪዎች የአያታቸውን የማዲም ፓግሩሂ ፓስጂ ማልጂ ወራሾች መሆናቸው እንዱጣራላቸው ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ አቅርበው ውርስ አጣሪው ተሹሞ ውርስ ተጣርቶ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ ከመዘገበው በሁዋላ ይህንኑ በመያዝ የውርስ ሐብት ከፍፍል ድርሻ ይገባናል በማለት በስር ተከሣሽ ሚስተር ጆርጅ ፓስጂ ማልጂ ላይ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ አቅርበዋል። ክርክሩ ከተካሄደ በኋላም የውርስ ሐብቱን የአሁኑ ተጠሪዎች እና ሚስተር ጆርጅ እንዱካፈለት ውሣኔ ተሰጥቷል። የአሁኑ አመልካች የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ያቀረቡትም ከዚሁ የውርስ ሐብት ክፍፍል በኋላ ነው ። የአሁኑ አመልካች የመቃወሚያ አቤቱታ ይዘትም የሟች እናታችንና የሟች እህታችን ወራሾች በመሆናችን በተወላጅነት ከእናታችን፣ በተተኪነት ደግሞ የእህታችንን ድርሻ ስለሚገባን የተሰጠው የውርስ ሐብት ክፍፍል ውሣኔ መብታችን ስለሚነካ ፍርደ ሉታረም ይገባል የሚል ነው። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የአሁኑ አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ ለስር ከሣሾችና ተከሣሽ እንዱደርስ አድርጎ አቤቱታቸውን ከሰማ በሁዋላ ውርሱ የተጣራው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተሾመው የውርስ አጣሪ መሆኑን ይህ የውርስ ሪፕርት ደግሞ የአሁኑን አመልካችን የማያውቃቸው መሆኑን በመግለጽ የፍርድ መቃወሚያው ሪፕርቱን ለአፀደቀው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ከሚቀርብ በስተቀር የውርስ ሐብት ክፍፍል ውሣኔ ለሰጠው ፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ላቀርብ የሚችልበት አግባብ የለም በሚል ምክንያት የአመልካችን ጥያቄ ሣይቀበለው ቀርቷል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንን ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ግንቦት ዐ5 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የውርስ አጣሪ ሪፕርት አመልካችን ያላካተተ ከመሆኑም በላይ ከማስረጃነት አልፍ እንደፍርድ የማይቆጠር በመሆኑ ተቃውሞው ሪፕርቱን ለአፀደቀው ፍርድ ቤት ይቅረብ መባለ ያለአግባብ ሰለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው።
አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመታዘዙ የተጠሪዎች ጠበቃ ቀርበው ህዲር ዐ3 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ ሶስት ገጽ ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የአመልካች ጠበቃ በበኩላቸው ህዲር 29 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የመልስ መልሣቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። አንደመረመረውም የችልቱን ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ አመልካች መቃወሚያ ማቅረብ መደረጉ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ሁኖ አግኝቶታል።
በመሰረቱ የፍ/ብ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌ የክርክሩ ተሣታፉ ያልሆነ ወገን አንድ በሕግ አግባብ የተሰጠ ፍርድ የሚቃወምበትን ሥርዓት የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። የአቤቱታው አቀራረብን በተመለከተም ሥነ ሥርዓት ሕጋችን በቁጥር 359 ደንግጓል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች መረዲት የሚቻለው የክርክሩ ተሣታፉ ያልሆነ ወገን መብቱን ወይም ጥቅሙን የሚነካ ፍርድ ከተሰጠ ፍርደ ከመፈፀሙ በፉት መቃወም የሚችል መሆኑንና ፍርድ ቤቱም የመቃወሚያ አቤቱታው በተገቢው ሥርዓትና በተገቢው ማስረጃ የተደገፈ ሁኖ ከአገኘው ቀድሞ የሰጠውን ፍርድ ማረም የሚችል መሆኑን ነው።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስ የአመልካች አቤቱታ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌን መሰረት አድርጎ የቀረበ መሆኑን ተቀባይነት ያለው መሆኑን ያለመሆኑን ከመመርመራችን በፉት በውርስ ሕጋችን ስለውርስ አጣሪ ስልጣን የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መመልከት ለጉዲዩ አወሳሰን አስፈላጊ ሁኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
ውርስ አጣሪ በሟች ንብረት ላይ መብት አለን የሚለትን ወገኖችን ወይም ወራሾችን የመወሰን፣ የሟች ኑዛዜ መኖር አለመኖሩን ማረጋገጥና በኑዛዜው ተጠቃሚዎችን የመለየት ውርሱን የማስተዲደር የውርሱን ተከፊይ ገንዘብ መሰብሰብና እዲዎችን መክፈል፣ የሟች ንብረት ማጣራትና ማፈላለግ እንዱሁም የኑዛዜ ስጦታዎችን የመክፈል ሥልጣን ያለው መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 944፣ 946 እና 956 ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 96ዐ ድንጋጌ ሲታይም የውርስ አጣሪው የማጣራቱን ተግባር ከአከናወነ በኋላ ሪፕርቱ ለወራሾችና ለፍርድ ቤት ማቅረብ እንዲለበት ያስገነዝባል። በዚሁ መሰረትም ተገቢው ክርክር ከተደረገ በኋላ የውርስ ማጣራቱ ተግባር ሲጠናቀቅ በአጣሪው ሪፕርት መሰረት ወራሾች የወራሽነት ምስክርነት ወረቀት /Certificate of Succession/ ከፍርድ ቤቱ እንደሚሰጥ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 996 ድንጋጌ ያሣያል። በመሆኑም የውርስ አጣሪ ስልጣኑና ተግባሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን የማጣራቱ ውጤትም እያንዲንደ ወራሽ ከውርሱ የሚደርሰውን ድርሻ ተለይቶ የወራሽነት የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑ በሕጉ በግልጽ ተመልክቷል። ድንጋጌዎቹ የሚያስገነዝቡት ውርሱ ተጣርቶ ለወራሽ የሚሰጥ የምስክር ወረቀት ወራሹ የምስክር ወረቀቱን መሰረት በማድረግ የውርስ ሀበት ክፍፍል መፈፀም፣ በወራሾች መካከል አለመግባባት ከአለ የክፍፍለን ጥያቄ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት የሚያቀርብ መሆኑን ነው።
በመሆኑም የውርስ አጣሪ ሪፕርት በፍርድ ቤት መጽደቅ በራሱ ፍርድ ሁኖ ለአፈፃፀም የሚቀርብ ሣይሆን እንደማስረጃ የሚያገለግል ነው። በመሆኑም ሪፕርቱ የማስረጃነት ዋጋ አለው ከተባለ ደግሞ የክፍፍለ ክርክር ሲቀርብ በማስረጃነቱ ላይ ክርክር ቢቀርብ ክርክሩ መቅረብ ያለበት በውርስ አጣሪና ሪፕርቱን በአፀደቀው ፍርድ ቤት ነው ተብል ውድቅ የሚሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች በውርስ ሐብት ድርሻ ያላቸው መሆኑንና የድርሻቸው መሰረትም ከሟች ጋር ያላቸው የመጀመሪያ ደረጃ እና የተተኪነት ወራሽነት መሆኑን ይህ ሁኖ እያለ በውርስ አጣሪ ሪፕርት ያልተካተተ መሆኑን ገልፀው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበው የክፍፍል ጥያቄ የተሰጠው ውሣኔ መብታቸውን ሉነካ የሚችል መሆኑን ጠቅሰው መብታቸው እንዱጠበቅ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአመልካች አቤቱታ አቀራረብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌን መሰረት ያደረገ ሲሆን የአመልካችን መብት ይነካል የተባለው እና ሉፈፀም የሚችል ፍርድ የተሰጠው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በመሆኑም አመልካች ከማስረጃነት ዋጋ ውጪ ላላ ዋጋ የላለውን የውርስ አጣሪ ሪፕርት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ሉቃወሙ ይገባል የሚባልበት አግባብ የለም። የውርስ አጣሪ ሪፕርት በፍርድ ቤት መጽደቁ ሪፕርቱን ሉፈፀም የሚችል ፍርድ የሚያደርገው አይደለም። በዚህም ምክንያት አመልካች ያቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ አቤቱታ ውድቅ የተደረገው የውርስ አጣሪ ኃላፉነትና ተግባር እንዱሁም የውርስ አጣሪ ሪፕርት በፍርድ ቤት መጽደቅና ውጤቱ ምን እንደሆነ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 ድንጋጌ መንፈስና ይዘት ጋር ባልተገናዘበ መልኩ ሁኖ ስለአገኘነው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተነዋል። በዚህ መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 26 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋደራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በመ/ መጋቢት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት መቃወሚያ ማቅረብ የሚችለት በውርስ ሐብት ክፍፍል ጥያቄ ላይ ውሣኔ ለሰጠው ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንጂ የውርስ አጣሪ ሪፕርቱን ለአፀደቀው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አይደለም ብለናል።
የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረቡትን አቤቱታ ተቀብልና የግራ ቀኙን ቀሪውን ሁለን ክርክር በመመርመር ጉዲዩን ተመልክቶ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 341/1/ መሰረት መልሰንለታል። ይፃፍ።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
ተ.ወ
ጥቅምት 5 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፣ ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድአመልካች፣ 1. አቶ ነስሩ ሰማን ቀረቡ 2. አቶ አብደራህማ ሰማን ቀረቡተጠሪ፣ ወ/ሮ ሙህሉሣ ኒጋኒ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና የፋዳራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልካች ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው በሥር ፍርድ ቤት አመልካች በአቶ ሰማን መሐመድ ላይ ባቀረቡት የክስ ማመልከቻ ጋብቻቸው በፍች የፈረሰ መሆኑን ገልፀው በኮልፋ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 የቤት ቁጥር 808 የጋራ ንብረት ስለሆነ እንዱያካፍለኝና ላልች ንብረቶችንም እንዱያካፍለኝ በማለት ክስ መሥርተዋል አመልካቾች ወላጅ አባታቸው አቶ ሰማን መሐመድ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ መሆኑን ገልፀው በክርክሩ ጣልቃ ገብተው ባቀረቡት ክርክር በኮልፋ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15/16 የቤት ቁጥር 808 አመልካቾች ሟች አባታችን ከመጋባታቸው በፉት የነበረ ስለሆነ የጋራ ንብረት አይደለም በማለት ተከራክረዋል። በሥር ፍርድ ቤት በተደረገው የቃል ክርክር የአመልካቾች ወላጅ አባትና ተጠሪ ከተጋቡ በኃላ ከዋናው ቤት ውጭ ያለት ሰርቪስ ቤቶችና ሽንት ቤቶች የተሰሩ መሆኑንና ዋናው ቤት ተጠሪ ከሟች ጋር ከመጋባታቸው በፉት 1949 ዓ.ም የተሰራ መሆኑን ምስክሮች ያረጋገጡ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በውሣኔው ካሰፈረ በኃላ 1949 ዓ.ም የተሰራ ቤት እስካሁን ይኖራል ተብል አይገመትም በማለት ደምደሟል በውሣኔው ማጠቃለያ በኮልፋ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 ቁጥር 808 ተመዝግቦ የሚገኘው ከዋናው ቤት ውጪ ያለ ሰርቪስ ቤቶችና ሽንት ቤቶች ተጠሪና የሟች የጋራ ንብረት ነው የቤቶቹን ግማሽ ተጠሪ ወስደው ግማሹን አመልካቾች ይካፈለት ካልተቻለ ዋናው ቤት በመሀንዱስ ተገምቶ ከተሸጠ በኃላ ይከፊፈለ በማለት ወስኗል።
አመልካቾች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራቀኙን ክርክር ከሰማ በኃላ የሥር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል። አመልካቾች ለሰበር ባቀረቡት አቤቱታ በኮልፋ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 ቁጥር 808 የሟች አባታችን የግል ንብረት ነው። ተጠሪ በዋናው ቤት ላይ ድርሻ አላቸው ሣይባል ዋናው ቤት በመሀንዱስ ተገምቶ እንዱሸጥ በማለት የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው እኔ ሟች አቶ ሰማን መሐመድና ወ/ሮ መህድያ መሐመድ ያፈሩትን ንብረት በማመን ተከራክሬለሁ የሰርቪስ ቤቶቹ እኔና አቶ ሰማን መሐመድ በጋብቻ ባለንበት ጊዜ የተሰሩ ስለሆነ የጋራ ንብረቴ ናቸው በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካቾች የመልስ መልስ በፅሐፍ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው በኮልፋ ቀራንዬ ቀበላ 16 ቁጥሩ 808 የሆነው ዋናው ቤት ሟች ሰማን መሐመድ ተጠሪን ከማግባታቸው በፉት የተሰራ መሆኑን ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት ባቀረቡት የቃል ክርክር ያመኑ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በውሣኔው የተመዘገበ ሲሆን የቤት ቁጥር 808 የሆነው ዋናው ቤት ተጠሪ ከሟች አቶ ሰማን መሐመድ ጋር ከመጋባታቸው በፉት የተሰራ መሆኑ በምስክሮች ተረጋግጧል። ስለሆነም በኮልፋ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 የሚገኘው የቤት ቁጥር 808 ዋናው ቤት የተጠሪ የጋራ ንብረት አይደለም። በልላ በኩል ተጠሪ ሟች ጋር ጋብቻ ከመሰረቱ በኃላ ሰርቪስ ቤቶችና ሽንት ቤት የተሰራ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል። ስለሆነም በኮልፋ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ የቤት ቁጥር 808 ይዞታ ሥር የተሰሩት ሰርቪስ ቤቶች እና ሽንት ቤት የአመልካችና የተጠሪ የጋራ ንብረት ናቸው የበታች ፍርድ ቤቶች የተጠሪ የጋራ ንብረቶች ሰርቪስ ቤቶቹና ሽንት ቤቱ መሆኑን ካረጋገጡ በኃላ የኮልፋ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 የሚገኘው 808 ዋናው ቤት በመሀንዱስ ተገምቶ እንዱሸጥና በሟች ወራሾችና ለተጠሪ እንዱከፊፈል በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበትና የተሻሻለውን የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ የሚጥስ ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
በኮልፋ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 ቁጥሩ 808 የሆነው ዋናው ቤት የተጠሪ የጋራ ንብረት አይደለም ብለናል።
በኮልፋ ቀራንዬ ክፍለ ከተማ ቀበላ 16 ቁጥሩ 808 ከሆነው ዋና ቤት ውጭ የተሰሩ ሰርቪስ ቤቶችና ሽንት ቤት የተጠሪና የሟች አቶ ሰማን መሐመድ የጋራ ንብረት ነው በማለት ወስነናል።
የሟች አቶ ሰማን መሐመድ ወራሾችና ተጠሪ ከዋናው ቤት ውጭ ያለትን ሰርቪስ ቤቶችና ሽንት ቤት በአይነት ይከፊፈለ። ሰርቪስ ቤቶቹንና ሽንት ቤቶቹን በአይነት ለመከፊፈል የማይቻል ከሆነ ሰርቪስ ቤቶቹና ሽንት ቤቱ በሀራጅ ተሽጦ ግማሹ ለተጠሪ ቀሪውን ደግሞ የሟች ወራሾች ይውሰደ።
በዚህ ፍርድ ቤት የወጣውን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻቻለ። ይኸ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።