No summary available.
ኀዲር 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ስላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የውርስ ንብረት አጣሪ እንዱሾም አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ በይርጋ ታግዶል ተብል መወሰኑን በመቃወም ነው።
ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ ይዘት መረዲት እንደተቻለው የመልካቾች እና የተጠሪ አውራሽ ሟች ወ/ሮ በቀለች ደስታ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት በ1977 ዓ.ም ሆኖ አመልካቾች የውርስ ንብረት አጣሪ ተሹሞ በተጠሪ እጅ ያለ የውርስ ንብረት ተጣርቶ እንዱቀርብ ለፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡት መጋቢት 29 ቀን 2001 ዓ.ም በመሆኑ አቤቱታው ከ22 ዓመታት በኋላ የቀረበ ነው ስትል ተጠሪ ያቀረበችው መቃወሚያ የሥር ፍ/ቤት ተቀብል በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1677/1/ እና 1845 መሰረት የ10 ዓመት ጊዜ አልፍበታል ሲል አቤቱታውን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቷል። ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኙን ሰርዟል። በዚህ ሰበር ችልት አቤቱታ የቀረበው በዚሁ ላይ ነው።
አመልካቾች ያቀረቡት አቤቱታ ተመርምሮ ተጠሪ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረት ወደ ስማቸው ያዛወሩት በ1997 ዓ.ም ነው በማለት አመልካቾች ያቀረቡት ክርክር ይርጋ አቆጣጠርን በሚመለከት በሥር ፍ/ቤቶች ግምት ውስጥ ያለመግባቱን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ተጠሪዎች መልስ እንዱሰጡበት ታዟል።
ተጠሪ በጠበቃቸው አማካኝነት የሰጡት መልስ የውርስ ንብረት ይጣራልኝ ጥያቄ የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ሟች ከሞቱበት ጊዜ እንጂ ስመ ሐብቱ በተጠሪ ከተዛወረበት ጊዜ ላሆን እንማይገባ ገልፀው የስር ችልቱ የሰጠውን ውሳኔ መዝገብ በመጥቀስ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱፀና ጠይቀዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን በዚህ ሰበር ችልት እንዱመረመር ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደተቻለው አመልካቾችም ሆኑ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ በቀለች ደስታ ወራሾች መሆናቸው አላከራከረም። ሟች ወ/ሮ በቀለች ደስታ የሞቱት በ1977 ዓ.ም ስለመሆኑ ግራ ቀኙ የተማመኑበት ጉዲይ ነው። ይህ በእንዱህ ሆኖ ሳለ የሟች የውርስ ንብረት በተጠሪ ተይዟልና የውርስ ንብረት አጣሪ ይሾምልኝ ሲል አመልካቾች ሥር ፍ/ቤት አቤቱታ ያቀረቡት መጋቢት 29 ቀን 2001 ዓ.ም ስለመሆኑ የሥር ፍ/ቤት መዝገብ ያመለክታል።
እንግዱህ ግራ ቀኙ የሟች ወራሾች መሆናቸው እስከተረጋገጠ ድረስ የውርስ ንብረት በአንደኛው ወራሽ እጅ ነውና ውርስ አጣሪ ተሾሙ ይጣራልን የሚለውን ጥያቄ ማቅረብ የሚቻለው እስከመቼ ጊዜ ድረስ ነው? የሚለው ጉዲይ ምላሽ የሚያሻው ነው። በዚህ ረገድ ይህ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በተለያዩ የሰበር መዝገቦች የሰጠውን አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ማየት ተገቢ ይሆናል። ይህ የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በሰበር መ/ቁ. 17937 የሰጠው የሕግ ትርጉም እንደሚያስገነዝበው በወራሾች መካከል የሚነሳ የውርስ ንብረት ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1000/1/ በተደነገገው አግባብ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ ያለበት ሲሆን ወራሽ በሆነ እና ወራሽ ባልሆነ ተከራካሪ ወገን መካከል የሚቀርበው የውርስ ንብረት ጥያቄ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1677 እና 1745 መሰረት በአሥር /10/ ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ መብቱ በይርጋ እንደሚታገድ አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ተሰጥቷል። የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሚሰጠው የሕግ ትርጉም በተመሳሳይ ጉዲይ ላይ በፋዳራልም ሆነ በክልል ፍ/ቤቶች ተፈፃሚነት እንደሚኖረው አዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/4/ ድንጋጌ ያመለክታል። ስለሆነም በተያዘው ጉዲይ ተፈፃሚነት ያለው የይርጋ ጊዜ በሥር ፍ/ቤት የተጠቀሰው 10 ዓመት ጊዜ ሳይሆን 3 ዓመት ጊዜ ገደብ ብቻ ይሆናል ማለት ነው።
በልላ በኩል አመልካቾች አጥብቀው የተከራከሩት ተጠሪ ቤቱን እንድትጠቀም የተደረገው በግራ ቀኙ መካከል በተደረገ ስምምነት እና ተጠሪ ታላቅ እህታችን በመሆኗ በአዘኔታና በአክብሮት ስለሆነ ይርጋ ሉቆጠርብን አይገባም የሚል ነው። በዚህ ረገድ የፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 1853/1/ እንደሚያመለክተው በግራ ቀኙ መካከል ያለው ዝምድና ወይም ታዛዥነት፤ የመፍራት ወይም የማክበር ስሜት መኖር ሲታመን የይርጋ መቃወሚያ ቀጣይነት ሉያጣ እንደሚችል ያስገነዝባል።
በተያዘው ጉዲይ አመልካቾች ከተጠሪ ጋር በስምምነትና በአክብሮት ስሜት እንድትኖር ፈቅደናል ብልም ፍ/ቤቱን ሉያሳምን የሚችል ማስረጃ እንዲላቀረቡ የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ በግልጽ ያመላክታል።
ስለዚህም በዚህ ረገድ የቀረበው የአመልካቾች ክርክር ለመቀጠል አልተቻለም። ከዚህም ላላ የይርጋ ጊዜው ሉቆጠር የሚገባው ተጠሪዋ የቤቱን ስመ ሐብት ወደ ራሷ ካዛወረችበት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ላሆን ይገባል የሚል አማራጭ ክርክር በአመልካቾች በኩል ቀርቧል። በዚህ ረገድም ይህ ሰበር ችልት በሰበር መ/ቁ. 36975 በሰጠው ውሳኔ እንደተመለከተው የይርጋ ጊዜ አቆጣጠር ቤቱን በእጅ ካደረገበት ጊዜ እንጂ ስመ ሃብቱን በስሙ ካዞረበት /ካደረገበት/ ጊዜ ስላለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1000/1/ እንደቅድመ ሁኔታ እንዲልተቀመጠ ጠቅሷል። በዚህም አግባብ የአመልካቾች አቤቱታ ተቀባይነት የለውም። /እንዱሁም
ይመልከቱ።/ በአጠቅላይ የውርስ ንብረት አጣሪ ይሾምልኝ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1000/1/ መሰረት ሟች ከሞተበት ጊዜ ጀምሮ በ3 ዓመት ጊዜ ውስጥ ካልቀረበ ተቀባይነት ሉኖረው እንደማይገባ ይህ ሰበር ችልት በተለያዩ የሰበር ችልቱ መዝገቦች አስገዲጅ የሕግ ትርጉም መሰጠቱን ከተያዘው ጉዲይ ጋር በማገናዘብ የሥር ፍ/ቤት በአሥር ዓመት ይርጋ የአመልካቾች ጥያቄ ቀሪ ሆኗል የሚለው ምክንያት ከሰበር ችልቱ ትርጉም የሚጣጣም ባይሆንም በውጤት ደረጃ ግን የአመልካቾች ጥያቄ በ3 ዓመት ይርጋ ቀሪ መሆኑን ስለተረዲን ውሳኔውን በውጤቱ ተስማምተን አጽንተነዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 29647 ሰኔ 19 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 83973 ኀዲር 21 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በውጤቱ ብቻ በመስማማት አጽንተነዋል።
የአመልካቾች ጥያቄ በ3 ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል።
No topics extracted.