No summary available.
ሰኔ 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ አሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የሚስትነት እና የወራሽነት ማረጋገጫ ይሰጠን በማለት የቀረበውን አቤቱታ /ጥያቄ/ የሚመለከት ነው። አቤቱታው የቀረበው በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት ለመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ፣ ፍ/ቤቱ ሟች /የ1ኛ አመልካች ባለቤት እና የላልቹ አመልካቶች አባት/ ከዘጠኝ አመት በፉት ወደኤርትራ ተመልሶ የኤርትራ ነዋሪ መሆኑን አረጋግጫለሁ /ተገንዝቤአለሁ/ በማለት አቤቱታውን ሣያስተናግድ ቀርቶአል። በዚህ ብይን ላይ አቤቱታ የቀረበላቸው የክልለ ከፍተኛ ፍ/ቤት እና ጠ/ፍ/ቤትም ብይኑ ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካቾችን ይግባኝ ሰርዘዋል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካቾች የካቲት 15 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በጻፊት ማመልከቻ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ጉዲዩን አቤቱታው ከቀረበበት ብይን እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል። በሰበር ችልቱ ሉመረመር ይገባል ተብል የተያዘው ጭብጥ ሟች የኤርትራ ነዋሪ ናቸው በማለት የአመልካቾች ጥያቄ ውድቅ የተደረገው በአግባቡ ነው ወይ? የሚለው ነው።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው ፍ/ቤት የሰጠው ብይን እንዲየነው የአመልካቾች ጥያቄ ማስረጃ ይሰጠን የሚል ነው ቢባልም ፤ የጠቀሱት ድንጋጌ /ህግ/ ግን በፍ/ብ/ህግ ቁ. 826/1/ የተመለከተው ነው። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው የአመልካቾች ኋላፉነት ከሟች ጋር ያላቸውን ግንኙነት /ዝምድና/ ተረጋግጦ ውርሱ እንዱከፈትላቸው መሆኑን ነው። በእርግጥም ሟች የሞተው ኤርትራ ውስጥ እንደሆነ በአቤቱታቸው ላይ ገልጸዋል። ፍ/ቤቱም ይህን መሰረት በማድረግ ብቻ ሟች ዋና መኖሪያው ስፍራ ኤርትራ ነው እሚል መደምደሚያ ላይ ደርሶአል። በበኩላችን እንደምናየው ግን ሟች ወደ ኤርትራ ሄድ ሣይመለስ እዛው በመሞቱ ብቻ ዋና መኖሪያው ስፍራ ኤርትራ ነው ወደሚለው ብቸኛ መደምደሚያ መድረሱ ትክክል አይደለም።
ከአመልካቾች አቤቱታ መገንዘብ እንደቻልነው ሟች በመደበኛነት ሲኖር የነበረው በሐረር ከተማ ውስጥ ከአመልካቾች /ሚስቱ እና ልጆቹ/ ጋር ነው። የኢትዮጵያ መንግስት ወታደር እንደነበር ፣ ከወታደርነት በጡረታ ከተገለለ በኋላም በመካኒክነት ስራ በግለ ተሰማርቶ ከቦታ ወደቦታ እየተዘዋወረ ሲሰራ እንደነበር ወደ ኤርትራ የሄደውም በዚሁ የመካኒክነት ስራ ለመስራት ሲሆን ፣ ጊዜውም በየካቲት ወር 1990 ዓ.ም እንደሆነ ፣ በኋላ ወደቤተሰቦቹ /ሐረር/ ሉመለስ ያልቻለው በግንቦት ወር 1990 ዓ.ም በተነሣው የድንበር ግጭት /ጦርነት/ ምክንያት መውጣት ባለመቻለ እንደሆነ ፣ ዜግነቱም ኢትዮጵያዊ እንደሆነ አመልካቾች ለዚህ ሰበር ችልት ገልጸዋል።
የስር ፍ/ቤቶች እነዚህን ሁኔታ እውነት ስለመሆን አለመሆናቸው ለማጣራት ስለመሞከራቸው በብይኑ አልተገለጸም።
ከላይ እንዲመለከትነው ለሰጡት ብይን ዋና መሰረት ያደረጉት ሟች ወደ ኤርትራ ከሄደ በኋላ ሣይመለስ እዛው ሞቶአል የሚለውን ፍሬ ነገር ብቻ እንደሆነም ነው ለማየት የቻልነው። ይህ አይነቱ አካሄድ እንዲለ ተቀባይነት ይኑረው ቢባል ለስራ ወይም ለተለያዩ ምክንያቶች ከአገራቸው ወጥተው ሣይመለሱ ሉሞቱ በሚችለት ኢትዮጵያውያን የውርስ አከፊፈት ጉዲይ ላይ ከፍተኛ ችግር ሉፈጠር እንደሚችል መገመቱ አይከብድም። በፍ/ብ/ህግ ቁ. 826/1/ የተመለከተው ድንጋጌ፤
በተለይም “…ዋና መኖሪያው ስፍራ…“ የሚለው ሐረግ መተርጏም ያለበትም ከዚህ አንጻር እየታየ ላሆን እንደሚገባ ልብ ልባል ይገባል። ይህን ታስቢ በማድረግ አቤቱታ የቀረበበት ብይን ስናየው ለጉዲዩ አወሣሰን አግባብነት ያላቸው ፍሬ ነገሮች በአግባቡ ሣይጣሩ የተሰጠ ሆኖ ነው ያገኘነው።
በዚህ ምክንያትም ብይኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የሐረር ህዝብ ክልላዊ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 33899 ህዲር 21 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ብይን፣ የሐረር ህዝብ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 07698 ጥር 16 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና በሐረር ህዝብ ክልላዊ መንግስት ጠ/ፍ/ቤት በመ.ቁ. 01792 ጥር 20 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
No topics extracted.
የሐረር ህዝብ ክልላዊ መንግስት የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካቾች ያቀረቡለትን አቤቱታ በተከፈተው መዝገብ ማሰማቱን እንዱቀጥል ፣ ይህ የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት ለጉዲዩ አወሳሰን አግባብነት ያላቸው ናቸው ያላቸዉን ሁኔታዎች እና ላልችም ፍ/ቤቱ አግባብነት አላቸው የሚላቸዉን ፍሬ ነገሮች እንዱያጣራ በመጨረሻም ፍሬ ነገሮችን አግባብነት ካለው ህግ ጋር በማገናዘብ ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥ ዘንድ ጉዲዩ ይመለስለት በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
343/1/ መሰረት ወስነናል።
እ.ከ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት