No summary available.
መስከረም 24 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው ዓልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሰኒያ ሼኀ ተማም - የቀረበ የለም ተጠሪ፡-
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ አንድ ወንድ ከሁለት ሴቶች ጋር ጋብቻ ፈጽሞ ሲኖር ከቆየ በሁዋላ ከአንደኛዋ ጋር በፍቺ ሲለያይ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ የሚስተናገድበትን አግባብ የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ በአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ላይ በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዲ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ መነሻ ነው። 1ኛ ተጠሪ በ2ኛ ተጠሪ ላይ የመሰረቱት ክስ ይዘት ባጭሩ ሲታይ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ሲኖሩ በእንሲኖ ከተማ ውስጥ አንድ ክፍል ቆርቆሮ ቤት ማፍራታቸውንና የገጠር መሬት አራት ጥማድ የነበራቸው መሆኑን ገልፀው እነዚህን ንብረቶች 2ኛ ተጠሪ እንዱያካፍላቸው ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስም 1ኛ ተጠሪ ጋር የተጋቡት በ1988 ዓ.ም ሆኖ እስከ 199ዐ ዓ.ም ድረስ ቆይታ መሄዶንና በ1994 ዓ.ም ላላ ጋብቻ አለኝ በማለቷ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ፈጽማ የነበረችው ጋብቻ እንዱፈርስ መወሰኑን በጋራ ያፈሩት ንብረት አለመኖሩን ንብረቶቹ የተፈሩት ከአሁኗ አመልካች ጋር መሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ከዚህም በኋላ የአሁኗ አመልካች ወደ ክርክሩ በጣልቃ ገብነት ለመግባት ማመልከቻ አቅርበውና የስር ፍርድ ቤት ፈቅድላቸው ባቀረቡት ክርክር ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ሕጋዊ ጋብቻ ፈጽመው ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ንብረቶች ያፈሩት አመልካች እንጂ የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ያለመሆናቸውን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩ በዚህ መልኩ የቀረበለት ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመስማት ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የገጠር መሬትን በተመለከተ የጋራ ባለይዞታዎች የአሁኗ አመልካችና 2ኛ ተጠሪ መሆናቸውን የቆርቆሮ ቤቱን በተመለከተ ግን የጋራ ባለሀብቶች ተጠሪዎች ስለሆኑ እኩል ሉካፈለ የሚገባቸው መሆኑን ገልፆ ወስኗል። በዚሁ የቆርቆሮ ቤቱን በተመለከተ በተሰጠው የውሣኔ ክፍል አመልካች ቅር በመሰኘት በየደረጃው ላለት ፍ/ቤቶች ይግባኝና የሰበር አቤቱታ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ባለመስማማት ለማስለወጥ ነው።
አመልካች የካቲት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ሕጋዊ ጋብቻ በ198ዐ ዓ.ም በመመስረት አከራካሪውን ቤት ስለማፍራታቸው ማስረጃ አቅርበውና አረጋግጠው ባለበት ሁኔታ ንብረቱ የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ነው ተብል መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሣይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም የአመልካችና 2ኛ ተጠሪ ጋብቻ ፀንቶ ባለበት ጊዜ በእንሲኖ ከተማ ውስጥ ያለው ቤት የተሰራ መሆኑን የሚያመለክት ማስረጃ እንዲለ የስር ፍርድ ቤት ውሣኔ ያሣያል ስለሆነም ቤቱ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ መካከል ጋብቻ ፀንቶ እያለ የተሰራ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ ንብረቱ የተጠሪዎች የጋራ ንብረት ነው ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር መጋቢት 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው የአሁኗ አመልካችና የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ሕጋዊ ጋብቻ በ198ዐ ዓ.ም መሥርተው እስካሁንም አንድ ላይ ያለ መሆኑን የአሁኑ 2ኛ ተጠሪ ከአሁኗ 1ኛ ተጠሪ ጋር በ1988 ዓ.ም ጋብቻ መሥርተው እስከ 199ዐ ዓ.ም ድረስ ከኖሩ በኋላ 1ኛ ተጠሪ ጥለው በመሄድ በልላ ቦታ ቆይተው በ1994 ዓ.ም የፍቺ ጥያቄ አቅርበው መለያየታቸውን በእንሴኖ ከተማ ውስጥ ይገኛል በተባለው ቦታ ቀድሞውንም የሳር ቤት የነበረና ይህ ቤት ፈርሶ 2ኛ ተጠሪና አመልካች አንድ ላይ ሁነው ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት መስራታቸው በማስረጃ መረጋገጡን የስር ፍርድ ቤት አመልካች ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረት አይገባቸውም በማለት ሉወስን የቻለው ቤቱ የተሰራበትን ቦታ የያዙበትን መንገድና መቼ እንደያዙ እንዱሁም 1ኛ ተጠሪ በንብረቱ ላይ መብት የላላቸው መሆኑን አላስረደም፣ ንብረቱ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የጋራ ስለማድረጋቸውም የሚያሣይና በፍርድ ቤት የተመዘገበ የፅሐፍ ማስረጃ አላቀረቡም በሚል ምክንያት መሆኑን ነው።
No topics extracted.
በመሰረቱ አንድ ከሣሽ ክስ ሉመሰርት የሚገባው ለክሱ ምክንያት በሆነው ንብረት ላይ መብት ወይም ጥቅም ያለው ስለመሆኑ በማረጋገጥ ስለመሆኑ ከፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 33 ድንጋጌ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ለክሱ ምክንያት በሆነው ነገር ላይ ከሣሹ መብት ወይም ጥቅም ያለው መሆኑን የማስረዲት ግዳታ የከሣሽ እንጂ የተከሣሽ ላሆን አይገባም።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት መብት የላቸውም ተብል በበታች ፍርድ ቤቶች የተወሰነው 1ኛ ተጠሪ በቤቱ ላይ መብት የላላቸው ስለመሆኑ በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ ምስክሮች አልተመሰከረም በሚል ነው። የሥር ፍርድ ቤት ቤቱ የተሰራው አመልካችና 2ኛ ተጠሪ በጋብቻ ፀንተው በነበሩበት ጊዜ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ደረጃ ያረጋገጠው ጉዲይ ሲሆን የአመልካችን ክርክር ውድቅ ሉያደርግ የቻለው ቦታው በምን መልኩ እንደተያዘና መቼ እንደተያዘ እንዱሁም ቤቱ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር የጋራ ስለመደረጉ በፍርድ ቤት የተመዘገበ ማስረጃ አላቀረቡም በሚል ነው። ይሁን እንጂ ባድ ቦታ ባለቤትነቱ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝቦች ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገመንግሥትና በላልች አግባብነት ባላቸው ሕጎች የተረጋገጠ ሲሆን አንድ ሰው በሕጉ ጥበቃ የሚደረግለት በሕጉ አግባብ የተሰጠው የባለይዞታነት መብቱ ነው። ይህ የሚሆነው በተገቢው መንገድ ባለይዞትነቱን ሲያረጋግጥ ነው። በተያዘው ጉዲይ 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ጋብቻ የነበራቸው ስለመሆኑ በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠ ሲሆን አከራካሪው ንብረት ግን በአመልካችና በ2ኛ ተጠሪ የተሰራ እንጂ በ1ኛ ተጠሪና በ2ኛ ተጠሪ የተሰራ ስለመሆኑ አልተረጋገጠም። ይልቁንም 1ኛ ተጠሪ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ጋብቻ የነበራቸው ቢሆንም ጋብቻቸውን በ199ዐ ዓ.ም ትተው መሄዲቸውና አከራካሪው ቤትም በዚሁ ወቅት ስለመሰራቱ መረጋገጡን የስር ፍርድ ቤት የውሣኔ ግልባጭ ያሣያል። 1ኛ ተጠሪ ጋብቻቸውን በተገቢው መንገድ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር ያፈረሱት በ1994 ዓ.ም ቢሆንም ለአከራካሪው ቤት መሰራት ግን ያደረጉት አስተዋጽኦ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም። በእርግጥ ጋብቻው በሕጉ አግባብ ሣይፈርስ የተፈራ ንብረት የባልና ሚስት የጋራ ስለመሆኑ ሕጉ ግምት የሚወስድበት ነጥብ ነው። ሆኖም ጋብቻው በተገቢው መንገድ ሣይፈርስ ጋብቻውን ትቶ የሄደ ተጋቢ ጋብቻውን ትቶ በሄደበት ወቅት ላላው ተጋቢ ያፈራውን ንብረት የጋብቻ ውጤት ነው በማለት የክፍያ ጥያቄ ሲያቀርብ ንብረቱ በዚህ ሁኔታ የተፈራ ስለመሆኑ የተረጋገጠ የሆነ እንደሆነ ጋብቻውን ትቶ የሄደ ተጋቢ ንብረቱ የጋራ ነው የሚለውን የሕግ ግምት ተጠቃሚ ላሆን አይገባም። ለንብረቱ መፈራት ምክንያት የሆነው ተጋቢ የንብረቱ የግል ባለሀብት ይሆናል እንጂ ምንም አስተዋጽኦ ያላደረገ ተጋቢ እንዱካፈል ማድረግ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 4ዐ/1/ስር የተቀመጠውን የንብረት ባለቤትነት መብት የሚጥስና የሕግ መሰረት የላለው ነው። የቤተሰብ ሕጉ በጋብቻ ጊዜ የተፈራ ንብረት የጋራ ነው የሚል ሕጋዊ ግምት የወሰደውም ተጋቢዎች ለንብረቱ መፈራት የየራሣቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ታሣቢ በማድረግ ነው ተብልም ይገመታል። ይህ ግምት ግን በተቃራኒ ማስረጃ የማይስተባበልበት ምክንያት የለም። በመሆኑም ምንም እንኳ ጋብቻው በሕጉ አግባብ ሣይፈርስ አንደኛው ተጋቢ ጋብቻውን ትቶ በሄደበት ወቅት ቀሪው ተጋቢ ላላ ሰው አግብቶ ንብረቱን ማፍራቱ በሚገባ እስከተረጋገጠ ድረስ ጋብቻውን ትቶ የሄደ ተጋቢ በልላ ጊዜ በመምጣት በላለበት የተፈራውን ንብረት ልካፍል በማለት የሚያቀርበው ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ ስለንብረት ማፍራት መብት የተደረገውን ጥበቃ እና በቤተሰብ ሕጉም ስለባልና ሚስት የጋራ ንብረት የተዘረዘረትን ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መሰረት ያደረገ ነው ልባል የሚችል አይደለም። በዚህም ምክንያት የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች አከራካሪውን ንብረት ከ2ኛ ተጠሪ ጋር በጋራ ያፈሩት ሁኖ እያለ ድርሻ የላቸውም የተባለው ያላግባብ በመሆኑ በዚህ ረገድ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የበታች ፍርድ ቤቶች በእንሴኖ ከተማ ውስጥ የሚገኘው ቆርቆሮ ቤት እኩል ሉካፈለ የሚገባቸው ተጠሪዎች ናቸው በማለት የሰጡት የውሣኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ ከ2ኛ ተጠሪ ጋር እኩል መብት ያላቸው አመልካች እንጂ የአሁኗ 1ኛ ተጠሪ /ወ/ሮ በላይነሽ ማተቦ/ አይደለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
ተ.ወ የማየነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት