No summary available.
ሐምል 26 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ገረመው ሙሜቻ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አሰፈ ነበበ - ጠበቃ አልማዝ አሰፊ ቀረበች።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ክርክር የተጀመረው በአሁንዋ ተጠሪ ክስ አቅራቢነት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። አመልካችን የከሰሰችው በቤት ሰራተኛነት ተቀጥሬ በነበረበት ጊዜ አስገድድ ደፍሮኝ በማርገዜ ልጅ ወልጃለሁ። ልጅቷን አምኖ ሉቀበለኝ አልቻለም።
ስለዚህም የህፃን መታደል ወላጅ አባት መሆኑ ተረጋግጦ ይወሰንልኝ በማለት ነው። አመልካች በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ከሳሽ ክሱን የመሰረተችው ተደፈርኩ ካለችበት ጊዜ ከአሥር ዓመት በላይ ቆይታ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል። በኔ ቤት የቆየችው ለአንድ ወር ተኩል ያህል ከመሆኑም በላይ፣ በ85 ዓመት ዕድሜዬ ለመድፈር የአካልም ሆነ የሞራል ብቃትም የለኝም /አልነበረኝም/። ከሣሽ በእኔ ስለመደፈርዋ ማስረጃ የላትም በማለት ተከራክሮአል። ፍ/ቤቱም በዚህ መልክ የቀረበለትን ክርክርና ማስረጃ ከሰማ በኋላ አመልካች ህፃን መታደል አባት ነው በማለት ወስኖአል። በዚህ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም በበኩለ ክርክሩን የሰማ ሲሆን፣ በመጨረሻም ይግባኝ የተባለበትን ውሣኔ አፅንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ታህሣሥ 8 ቀን 2003 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል።
አቤቱታው በሰበር ችልቱ እንዱታይ የተደረገው የሥር ፍ/ቤቶች ወደ ውሳኔው ለመድረስ የተከተለት አካሄድ /የክርክር አመራር/ አግባብነት ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ አመልካች እና ተጠሪ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታው ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከሥር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር እና የተሰጡትን ውሣኔዎች ይዘት በዝርዝር ተመልክተናል። ተጠሪ ክስ ስትመሰርት ሰዎችን በምስክርነት የቆጠረች ሲሆን፣ የዱ.ኤን.ኤ /D.N.A/ ምርመራ እንዱደረግለትም ስለመጠየቅዋ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክር ከተደረገበት መዝገብ ጭምር ለማረጋገጥ ችለናል። አመልካችም በበኩለ ሰዎችን በመከላከያ ምስክርነት ቆጥሮ ማሰማቱን ተመልክተናል። ክሱን የሰማው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የግራ ቀኝ ወገኖችን ምስክሮች ከመስማት አልፍ የዱ.ኤን.ኤ /D.N.A/ ምርመራ እንዱደረግ አላዘዘም። በዚህ ረገድ የሰጠው ምክንያትም አመልካች የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ ማድረግ እንደማይችል እና እንደማይገደድ ገልጾ መልስ ሰጥቶአል የሚል እንደሆነ ከሰጠው ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። የአመልካች የሰበር አቤቱታ /ክርክር/ በዋነኛነት የተመሰረተውም በዚሁ ነጥብ ላይ ነው። ከሣሽ ተጠሪ ሆኜ ሳለ በአስረጂነት የጠቀሰችው የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ በኔ በተከሣሽ ወጪ ይደረግ መባለ ትክክል አይደለም በማለት ተከራክሮአል። ተጠሪ በበኩልዋ ለአቤቱታው በሰጠችው መልስ አባትነቱን በምስክር ያስረዲሁ ስለሆነ እና አቅምም ስለላለኝ የምርመራው ወጪ መሸፈን ያለበት አባት አይደለሁም የሚለው አመልካች ነው በማለት ተከራክራለች።
ተጠሪ ከሣሽ እንደመሆንዋ እንደ ክሱ ያስረደልኛል ያለቻቸውን ምስክሮች እና የሕክምና ማስረጃ በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 223 በተደነገገው መሰረት በዝርዝር ስለማቅረቧ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክር ከተደረገበት መዝገብ ተመልክተናል። የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የሰማው ምስክሮችን ብቻ እንደሆነም ተገንዝበናል። ተጠሪ ከማስረጃዎችዋ አንደ የዱ.ኤን.ኤ /D.N.A/ ምርመራ እንደሆነ በማስረጃ ዝርዝር መግለጫዋ ገልፃ ሳለ ፍ/ቤቱ ግን በዚህ ረገድ የተጠየቀውን ማስረጃ አልሰማም። ማስረጃውን ያልሰማበትን ሕጋዊ ምክንያት ያለው ስለመሆኑም አልገለፀም። ምክንያት ያደረገው አመልካች /በወቅቱ ተከሣሽ/ የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለሁም ወይም አልገደድም ብልአል የሚል ነው። ክርክር የተደረገበት መዝገብ አስቀርበን እንዲያነው ፍ/ቤቱ የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ እንዱደረግ ወይም የምርመራው ውጤት ይቀርብለት ዘንድ የሰጠውን ትዕዛዝ አላገኘንም። አመልካች ለክሱ የሰጠው መልስ እንዲየነው ደግሞ በራሴ ገንዘብ /ወጪ/ የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ ለማድረግ አልገደድም የሚል ግልጽ የመከራከሪያ ነጥብ ያለው ነው። አመልካች ይህን የመከራከሪያ ነጥብ ሉያነሳ የቻለው ተጠሪ የዱ.ኤን.ኤ /D.N.A/ ምርመራው በተከሣሽ /በአሁኑ አመልካች/ ወጪ ይደረግልኝ በማለት በማስረጃ ዝርዝር መግለጫዋ ላይ በመግለጽዋ /በመጠየቅዋ/ እንደሆነም ከመዝገቡ ተመልክተናል። ፍ/ቤቱ አመልካች የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ ለማድረግ ፈቃደኛ አይደለም ወደሚለው መደምደሚያ የደረሰውም ከዚህ በመነሳት ይመስላል። ይሁን እንጂ ይህ ዓይነቱ አካሄድ የፍሬ ነገርም ሆነ የሕግ መሰረት ያለው አይደለም።
No topics extracted.
ከላይ እንዲመለከትነው ተጠሪ ከሣሽ እንደመሆንዋ እንደ ክስ አቀራረብዋ የሚያስረዲላትን ማስረጃ አቅርባ የማሰማት ግዳታ /ሸክም/ አለባት። የዱ.ኤን.ኤ /የህክምና ማስረጃ/ እንደ ላልቹ ማስረጃዎች አንደ የተጠሪ ማስረጃ ሆኖ በመቆጠሩ ማስረጃው ቀርቦ ይሰማ ዘንድ የማድረግ ግዳታ የተጠሪ እንጂ ማስረጃውን በመከላከያነት ያልቆጠረው የአመልካች ግዳታ ላሆን አይችልም፤
አይገባምም። ከሣሽ የሆነው ወገን የከሣሽነት ቃለን በመስጠት መመሥረት የሚገባውን ጭብጥና ያቀረበውን ክስ የሚደግፍለትን ማስረጃ እንደሚያቀርብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 259/1/ መመልከቱን መገንዘቡም ተገቢ ነው። የሕክምና ማስረጃው የተቆጠረው በኔ ቢሆንም፤ መቅረብ ያለበት በአመልካች ወጪ ነው የሚለው የተጠሪ ክርክር ሲታይ ከመሰረታዊ የማስረጃ ሕግ መርህ የወጣ እና ከሳሽ እንደሚያቀርብ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 259/1/ የተቀመጠውን ድንጋጌ የሚቃረን በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። በልላም በኩል የዱ.ኤን.ኤ ምርመራ የሕክምና ዘዳን /ሳይንሳዊ/ መሰረት በማድረግ የሚከናወን በመሆኑ የአስረጂነት ዋጋው ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው። ፍ/ቤቱም በሂደቱ መጨረሻ እውነት ላይ መድረስ ሲገባው ማስረጃውን ሳይሰማ የሚያልፍበት በቂ ምክንያት የለም። ከዚህ የተነሣም የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ወደ ውሳኔ ያመራው የክርክሩ እና የማስረጃ አሰማም ሂደቱን በሕጉ አግባብ ሳያጠናቅቅ ነው ለማለት ችለናል። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ተመሣሣይ መንገድ በመከተል ውሳኔውን ከማፅናት አልፍ ማስረጃውን አልሰማም።
በመሆኑም አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በክርክር አመራር እና ማስረጃ አቀባበል ረገድ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ችለናል። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።