No summary available.
ሐምል 12 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሤ አመልካች፡- ወ/ሮ ገዛችን ገብሩ - ከጠበቃቸው ከአቶ ተክለ አብ ስዩም ጋር ቀረቡ።
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ዓለምነሽ በየነ - አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ተሰጥቷል።
ለዚህ ሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ክስ የተጀመረው በሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን የአሁኗ የሰበር ተጠሪ ከሳሽ አመልካች ደግሞ 2ኛ ተከሳሽ ነበሩ። የክሱ ፍሬ ቃልም ከሟች አቶ ፀጋዬ ተክለሃይማኖት ጋር ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ እንደ ባልና ሚስት አብረን ለአምስት ዓመታት ስንኖር ህፃን ገሉላ ፀጋዬ የተባለችውን ልጅ የወለድን ሲሆን በጋራ ከሟች ጋር የነበረንን ኮድ 3.03110 የሆነውን የጭነት መኪና የሟች ሚስት ነኝ የሚለት 2ኛ ተከሳሽ ይዘው ስለሚገኙ ድርሻዬን እንዱያካፍለኝ ይወሰንልኝ የሚል ነው።
የሥር 2ኛ ተከሣሽም /ያሁኗ አመልካች/ በክሱ በሰጡት መልስ ከሳሽ ከሟች ጋር እንኳን ለአምስት ዓመታት ቀርቶ ለወራት እንኳን እንደ ባልና ሚስት አልኖሩም። ከሳሽ ለመካፈል የጠየቁትን መኪና እኔና ባለቤቴ የነበረንን ኮድ 3.50133 የሆነውን አይሱዙ መኪና ሸጠን የገዛነው በመሆኑ ከሳሽን የሚመለከት አይሆንም በማለት ተከራክረዋል።
የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤትም ከሳሽ በማስረጃነት ያቀረቡትን በመ/ ሰኔ 09 ቀን 2000 ዓ/ም የተሰጠውን ውሳኔ ከመረመረ በኋላ በዚህ በማስረጃነት በቀረበው ውሳኔ ከሳሽ ከ1991 ዓ.ም እስከ 1996 ዓ.ም ድረስ ከሳሽና ሟች ፀጋዬ ተክለሀይማኖት በተከራዩት ቤት እንደ ባልና ሚስት ሲኖሩ እንደነበር ሆኖም ግን ጋብቻ ይፈጽሙ አይፈጽሙ እንደማያውቁ ምስክሮች ያስረደ ስለሆነና ከሳሽ የጋራ ሀብት ነው በሚል የጠየቁት ኮድ 3.03110 የሆነው መኪና የተገዛው ጥቅምት 21 ቀን 1993 ዓ/ም መሆኑን የአዱስ አበባ ከተማ ትራንስፕርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በማረጋገጡ መኪናው ከሳሽና ሟች እንደ ባልና ሚስት አብረው በነበሩበት ጊዜ የተገዛ ነው በማለት በመኪናው ከሳሽ እና 2ቱም የሥር ተከሳሾች እያንዲንዲቸው 1/3ኛ ድርሻ አላቸው ብሎል።
በዚህ በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሥር 2ኛ ተከሳሽ ይግባኝ ለሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ከፍተኛው ፍ/ቤትም በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት መልስ ሰጪዋን መጥራት ሳያስፈልግ የይግባኙን መዝገብ በመዝጋት ይግባኝ ባይዋን አሰናብቷል።
የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚሁ በሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ ሲሆን በዋናነት አመልካች ያቀረቡት ቅሬታም ተጠሪዋ ክርክር ባስነሳው መኪና መብት ሳይኖራቸው የአመልካች ድርሻ ከመኪናው 1/3 ብቻ እንዱሆን መወሰኑ ያለአግባብ ነው የሚል ነው።
ተጠሪዋ በበኩላቸው በሰጡት መልስ ከሟች ፀጋዬ ተክለሃይማኖት ጋር እንደ ባልና ሚስት በኖሩበት ወቅት አከራካሪው መኪና የተገዛ መሆኑን በማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ አመልካች ባቀረቡት ክርክር ተጠሪዋ ከመኪናው መብት የላቸውም ሲለ የተከራከሩት የህግ መሰረት የለውም ብለዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ የተገለፀ ሲሆን እኛም ተጠሪዋና ሟች ፀጋዬ ተክለሃይማኖት እንደ ባልና ሚስት ኖረዋል? ወይስ አልኖሩም? የሚለው ጭብጥ በሥር ፍ/ቤት በአግባቡ ተረጋግጧል? ወይስ አልተረጋገጠም የሚለውን ነጥብ ይዘን ክርክሩን እንደሚከተለው መርምረናል።
በሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የአሁኗ የሰበር ተጠሪ ከሟች ፀጋዬ ተክለሃይማኖት ጋር እንደ ባልና ሚስት ሲኖሩ እንደነበር በመግለጽ የጋራ ሀብት ነው የሚለት የጭነት መኪና ድርሻቸው እንዱሰጥ ሲጠይቁ አመልካች ባቀረቡት መልስ ካነሷቸው ነጥቦች አንደና ዋናው ከሳሽ /ያሁን ተጠሪ/ ከሟች ጋር እንደ ባልና ሚስት አልኖሩም ሲለ ተከራክረዋል። በዚህ መልኩ ክርክር እስከቀረበ ድረስ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተቀበለው የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤትም ሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች የተለያዩበትን ጭብጥ በመያዝ የግራ ቀኙን ተከራካሪዎች ማስረጃ ሰምቶ ውሳኔ መስጠት ሲገባው በመቃወም አመልካች /የአሁኗ አመልካች/ እና በመቃወም ተጠሪ /ያሁኗ ተጠሪ/ በመዝገብ የአሁኗ ተጠሪ የሟች ፀጋዬ ተክለሃይማኖት ሚስት ናቸው ተብል በ11/10/96 ዓ.ም የተሰጠ ውሳኔ እንዱሰረዝ ክርክር ባቀረቡበት ወቅት የቀረቡት ምስክሮች የአሁኗ ተጠሪና ሟች እንደ ባልና ሚስት ሲኖሩ እንደነበር አረጋግጠዋል በማለት በመ/ ለተያዘው ጉዲይ ውሳኔ ለማሰጠት የቀረቡትን ማስረጃዎች በዚህ መዝገብ /60691/ በተያዘው ጉዲይ አግባብነት እንዲላቸው በመቁጠር ፍ/ቤቱ የምስክሮቹን ቃል ለውሣኔው መሰት ማድረጉ ተገቢ ሆኖ አላገኘንም። ይኸውም በመ/ የክርክሩ ጭብጥ የአሁኗ ተጠሪ የሟች ፀጋዬ ተክለሃይማኖት ሚስት ናቸው ወይስ አይደለም የሚለው ከተረጋገጠ በኋላ ሚስት አለመሆናቸው ተረጋግጦ በ11/10/96 ዓ/ም በዋለው ችልት ተጠሪዋ ሚስት ናቸው ተብል የተሰጠ ውሣኔ እንዱሰረዝ የተደረገበት ሲሆን በዚህ መዝገብ በተያዘው ጉዲይ ግን ክሱ የቀረበው ከሟች ጋር እንደ ባልና ሚስት በመኖራችን የጋራ ሀብት የሆነው መኪና ተካፍል ድርሻ ይሰጠኝ በሚል ነው።
No topics extracted.
ስለሆነም የሥር ፍ/ቤቶች ተጠሪዋ ላቀረቡት ክስ አግባብነት የላለውን በመ/ የተሰጠውን የምስክርነት ቃል መሰረት በማድረግ በተጠሪና በሟች ፀጋዬ ተክለሃይማኖት መካከል እንደ ባልና ሚስት የመኖር ሁኔታ መኖር አለመኖሩን በተሻሻለው የፋዳራል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 መሰረት ተገቢውን ማጣሪያ ሳያደርጉ ተጠሪዋ ከመኪናው 1/3ኛውን ድርሻ ያግኙ ሲለ የወሰኑት መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ያለበት ነው፡
የሥር የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 22/8/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ፍርድ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የሥር የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመ/ በቀን 29/10/2002 ዓ/ም በዋለው ችልት የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
በተጠሪዋና በሟች ፀጋዬ ተክለሃይማኖት መካከል እንደ ባልና ሚስት የመኖር ሁኔታ የነበረ መሆኑንና አለመሆኑን የግራ ቀኙን ማስረጃዎች የሥር የፋ/መ/ደ/ፍ/ቤት ከሰማ በኋላ ለቀረበው የጋራ ሀብት ክፍፍል ጥያቄ በተሻሻለው የፋ/የቤተሰብ ሕግ መሰረት ተገቢውን እንዱወስን ክርክሩን በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሣራ አመልካችና ተጠሪ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
መዝገቡን ዘግተናል። ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።