No summary available.
ሰኔ 14 ቀን 2ዐዐ3ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ ጥሩወርቅ ለማ ተጠሪ፡- ታፈሰ ተሰማ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጋብቻን ፍቺ መፍረስ ተከትል የተደረገውን የንብረት ክፍፍል ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በሃዋሣ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት ሲሆን ፣ ፍ/ቤቱ በሁለቱ ተከራካሪ ወገኖች የቀረበለትን ክርክር ከተመለከተ በኋላ የንብረት ክፍፍለ በዕጣ እንዱሆን በማዘዝ አከፊፍልአል በወጣው ዕጣ መሰረት ለአመልካች የደረሰው ቤት ለተጠሪ ከደረሰው ቤት በዋጋ የሚበልጥ ነው በማለትም አመልካች ብር 31,585.65 ለተጠሪ ትክፈል ብልአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካች በውሣኔው ባለመስማማት ለሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርባ የነበረ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱ ይግባኝ የተባለበት ውሣኔ ጉድለት የለበትም በማለት ይግባኙን ሰርዞአል። በመጨረሻም አመልካች ለደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቤቱታ በማቅረብዋ በዚህ ደረጃም ክርክሩ የተሰማ ሲሆን ፣ ችልቱ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠውን ውሣኔ አፅንቶአል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ጥቅምት 23 ቀን 2003 ዓ.ም በጻፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው የንብረት ክፍፍለ የተመራው በሕጉ አግባብ ነው ወይ? የሚለው ጭብጥ ላይ ነው። በመሆኑም ግራ ቀኝ ወገኖች ጭብጡን መሰረት በማድረግ ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
እንደምንመለከተው ለክፍፍል የቀረቡት ንብረቶች በፍቺ የተለያዩት ባልና ሚስት /ተከራካሪዎች/ የጋራ ሃብት ናቸው። ከዚህ ደግሞ በቅድሚያ መገንዘብ የሚቻለው ሁለቱም በሃብቶቹ ላይ እኩል የሆነ መብት ያላቸው መሆኑን ነው። በመብት ረገድ አንደኛው ከላላኛው አያንስም ወይም አይበልጥም ከተባለ ደግሞ የክፍፍለ ሥርዓትም ይህንኑ መሰረት በማድረግ ነው መከናወን ያለበት። የእኩልነት መርሁ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 35/1/ እና/2/ የተቀመጠ ሲሆን ፣ ቀጥለው በወጡት የፋዳራል እና የክልል ቤተሰብ ሕጎችም እንደዚሁ በግልጽ ተቀምጦአል። በያዝነው ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነት ያለው የቤተሰብ ሕግ ‛የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 75/1996 “ ሲሆን የባልና ሚስት የጋራ ሃብት ለሁለቱም እኩል እንደሚከፊፈል በአንቀጽ 101/1/ ደንግጎአል። በእርግጥ ባልና ሚስቱ ሃብታቸውን በስምምነት ለመከፊፈል ከፈለጉና ከቻለ ሕጉ ይህን ስምምነታቸውን እንደሚያከብርላቸውም ተመልክቶአል። ቀጥል የሚነሳው ጥያቄ በስምምነት መከፊፈል ካልቻለ/ካልፈለጉ / የክፍፍለ ሥርዓት እንዳት ሉከናወን ይችላል? የሚለው ነው።
ከፍ ሲል የተጠቀሰው የቤተሰብ ሕግ የክፍፍል ሥርዓቶቹን በቅደም ተከተል በዝርዝር አስቀምጦአል /በአንቀጽ 1ዐ2/2/ እና በአንቀጽ 1ዐ3/1/ በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው ለክርክሩ መነሻ የሆኑት ንብረቶች በአይነት ሉከፊፈለ የሚችለ ናቸው አልተባለም። ችግሩ የተፈጠረው በአይነትም ለመከፊፈል ሁለቱም ወገኖች ስምምነት ላይ ባለመድረሳቸው ነው። አመልካች እስከዚህ ሰበር ችልት ድረስ እየተከራከረች ያለችው በእጣ ደርሶሻል የተባልኩት ከስምምነቴ ውጪ ነው።
በዕጣ የደረሰኝ ነው የተባለውን ንብረት ብወስድ እጎዲለሁ። ተጠሪ አልተጎዲሽም የሚል ከሆነ ለኔ ደርሶአል የተባለውን ንብረት ብር 31,585.65 በመክፈል ጠቅልል ይውሰድ ፤ እኔ ደግሞ ለእሱ የደረሰውን ልውሰድ በማለት ሲሆን፣ ተጠሪ ግን በዚህ አይስማማም ። እየተከራከረ ያለው አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ ሉፀና ይገባል በማለት ነው። ከዚህም በግልጽ መገንዘብ የሚቻለው በንብረት ክፍፍለ ግራ ቀኝ ወገኖች አለመስማማታቸውን ነው። እጣ እንዱወጣ ያዘዘውም ፍ/ቤቱ /በራሱ አነሳሽነት / እንጂ ተከራካሪ ወገኖቹ ክፍፍለ በዕጣ ይሁን ብለው ስለተስማሙ እንዲልሆነም ከተሰጡት ውሣኔዎች ይዘት ጭምር ለመገንዘብ ችለናል።
ፍ/ቤቱ ወደ ዕጣ አማራጭ የሄደው ግራ ቀኝ ወገኖች በስምምነት ለመከፊፈል ባለመቻላቸው እና ንብረቱም በአይነት የማይከፊፈል በመሆኑ እንደሆነ የደቡብ ብ/ብ/ህ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሰጠው ውሣኔ ተመልክቶአል።
በንብረቱ ክፍፍል ረገድ ችግር ሲያጋጥም ማለትም ንብረቱ ለክፍፍል የማያመች ወይም ለማከፊፈል የማይቻል ሆኖ የተገኘ እንደሆነና ባልና ሚስቱን ንብረቱ ከሁለቱ ለአንዲቸው እንዱሰጥ ለማስማማት ሳይቻል የቀረ እንደሆነ ንብረቱ ተሸጦ የተገኘውን እንዱከፊፈል እንደሚደረግ በቤተሰብ ሕጉ አንቀጽ 1ዐ3/1/ ግልጽ ባለሁኔታ ተመልክቶአል። ይህ ድንጋጌ ንብረቱ በዕጣ የሚከፊፈልበትን የክፍፍል ሥርዓት በአማራጭ አላስቀመጠም። ሕጉ ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ደግሞ ከሕጉ በመውጣት ውሣኔ መስጠት የሚቻልበት አግባብ የለም። ሕጉ እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሰው /አንቀጽ 103 / ቀደም ሲል የተመለከትነውን የእኩልነት መርህን ግንዛቤ ውስጥ በማግባት እንደሆነም ልብ ልባል ይገባል። በመሆኑም የንብረቱ ክፍፍል በዕጣ እንዱሆን በማለት የተሰጠው ውሣኔ በሕጉ አተረጓጎም ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል። በዚህ መሰረትም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የሃዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መደበኛ ችልት በመ. በ28/10/2002 ዓ.ም የሰጠው ብይን ፣ የሃዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. በ8/11/2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ እና በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክ/መ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሰበር መ. በ27-1-2003 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች እና ተጠሪ ንብረቱን መከፊፈል ያለባቸው በቤተሰብ ሕጉ በተዘረጋው የክፍፍል ሥርዓት መሰረት ነው ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.