No summary available.
ሰኔ 27 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ አብርሀ የኋላሽት - ጠበቃ ፍሰሀ ሐጏስ - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ አበባ ዘመን - ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል።
ጉዲዩ የባልና ሚስት ክርክር ሲሆን በፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የተጀመረው በግራ ቀኙ የቀረበውን የንብረት ክፍፍል ጥያቄን በሚመለከት ነው። ለአሁኑ ቅሬታ መሰረት የሆነው በአመልካች ስም ያለው በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 19/20 የቤቱ ቁ. 708 የሆነ መኖሪያ ቤት ሲሆን ተጠሪ የጋራ ንብረታችን ነው በማለት የተከራከረች ሲሆን አመልካች በበኩለ በቀን 05- 11-80 ዓ.ም በስሜ የተመዘገበና የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ተሰጥቶት አሁን ያለውን ቤት ሰርቶ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የምኖርበት በመሆኑ ከተጠሪ ጋር ደግሞ በ1993 ዓ.ም በባህላዊ ጋብቻ የተገባን መሆኑና በዚህ ጋብቻ ውልም የጋራ ንብረት ያልተደረገና በድጋሚ ተደርገ የተባለው የጋብቻ ውል እኔ ታምሜ በአማኑኤል ሆስፑታል በነበርኩበት ወቅት በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። ተጠሪ በበኩሎ የተባለው ቤት ከጋብቻ በፉት 3 ክፍል ጭቃ ቤት የነበረ መሆኑ ከተጋባን በኋላ የኮርኒስ ስራ በር ቀለም እንዱሁም 1ዐ ቅጠል ቆርቆሮ ጨምረን በጋራ እድሣት ሰርተናል፣ አንድ መኝታ እና አንድ ሣልን ክፍል እንዱሁም አንድ 4x5 ክፍል ቤት ሰርተናል ፣ በኋላም በ1999 ዓ.ም በተደረገ የጋብቻ ውል የጋራ ንብረት ያደረግንና ይሄው የጋብቻ ውል በክብር መዝገብ ሹም ቀርቦ የተመዘገበ በመሆኑ የጋራ ንብረታችን ነው በማለት ተከራክሯል።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከላይ እንደተመለከተው ካከራከረ በኋላ ለዚህ ቅሬታ መነሻ የሆነውን ቤት እኩል ይካፈለ በማለት ወስኗል።
አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ይግባኝ የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቷል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ግራ ቀኙ የጽሁፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም የተነሱትን ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋግዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደተመረመረውም ለክርክሩ መነሻ የሆነው መኖሪያ ቤት የግራ ቀኙ የጋራ ንብረት ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ /ጭብጥ/ ተይዞ መፍትሓ ማግኘት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በዚሁ መሰረት በመጀመሪያ ደረጃ ለክርክሩ መነሻ የሆነው መኖሪያ ቤት ግራ ቀኙ ከመጋባታቸውም በፉት በአመልካች ስም ተመዝግቦ የሚገኝ መሆኑ አላከራከረም። በተመሣሣይም በግራ ቀኙ መካከል ቀድሞ የተደረገው የጋብቻው ውል ማለትም በቀን 18-12-1992 ዓ.ም የተደረገ ስለመኖሩና በዚህም የጋብቻ ውል የተመለከተው መኖሪያ ቤት የጋራ ንብረት ያልተደረገ መሆኑ አላከራከረም። በግራ ቀኙ አከራካሪ የሆነው ጉዲይ ታህሣስ 12 ቀን 1999 ዓ.ም ተደረገ የተባለው የጋብቻ ውል ሲሆን የተጠሪ ክርክር በዚህ ጋብቻ ውል መሰረት በአዱስ ከተማ ክ/ከተማ ቀበላ 19/20 የቤት ቁጥሩ 7ዐ8 የሆነ ቤት የጋራ ንብረት እንዱሆን ተስማምተናል የሚል ሲሆን በአመልካች በኩል የቀረበው ክርክር ደግሞ ከላይ በድጋሚ ተደረገ የተባለውን የጋብቻ ውል የማያውቁ መሆናቸውን ፣ በወቅቱ የአዕምሮ በሽተኛ ሆኖ አማኑኤል ሆስፑታል ሲታከም የነበረ መሆኑን ፣ ተጠሪ ራሷ አዘጋጅታ ያቀረበችው በመሆኑ ተቀባይነት የለውም በማለት ተከራክሯል። በዚህ ነጥብ ላይ የተነሳውን የግራ ቀኙን ክርክር አግባብነት ካላቸው ከፋዳራል የቤተሰብ ህግ ጋር ስንመረምር በእርግጥ የተሻሻለው የፍደራል የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/1992 አንቀጽ 47/1-3/ ስንመለከት ቀድሞ የተደረገውን የጋብቻ ውል ማሻሻል እንደሚቻል የሚደነግግ ሲሆን ለፍ/ቤት ቀርቦ የተደረገው የጋብቻ ውል መሻሻል የቤተሰብን ጥቅም የማይጏዲ ከሆነ ሉጸድቅ እንደሚችል ይደነግጋል። ይሄ የተሻሻለው የጋብቻ ውል ለፍ/ቤት ቀርቦ ማጽደቅ ውጤቱ ምን ላሆን እንደሚችል በዚህ አንቀጽ ስር መልስ የሚሰጥ ባይሆንም በዚህ አዋጅ አንቀጽ 73 ጋር አያይዘን ስንተረጉም ፍ/ቤት ካላጸደቀው በስተቀር ተቀባይነት የለውም የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል። በዚሁ መሰረት ወደ ያዝነው ጉዲይ ስንመለስ ከላይ የተመለከተው በግራ ቀኙ መካከል በድጋሚ ተደርገ የተባለው የጋብቻ ውል በክብር መዝግብ ሹም ፉት ቀርቦ የተመዘገበ ስለመሆኑ በፍሬ ነገር ረገድ የተረጋገጠ ቢሆንም ከላይ በተመለከተው አግባብ ለፍ/ቤት ቀርቦ የጸደቀ ስለመሆኑ ተጠሪ ያስረዲች ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
በልላ በኩል ታህሣስ 12 ቀን 1999 ዓ.ም በድጋሚ ተደርገ የተባለው የጋብቻ ውል ከላይ በተመለከተው ምክንያት ሉጸና አይችልም ቢባልም በተጠሪ በኩል ተነስቶ የነበረው ላላው ክርክር መኖሪያ ቤቱ በተጠሪ ስም የነበረና ሶስት ክፍል ጭቃ ቤት የነበረበት መሆኑን ሆኖም ከተጋቡ በኋላ ለዚሁ ቀድሞ ለነበሩት ክፍልች አጠቃላይ እድሣት ያደረጉ ከመሆኑም በላይ በተጨማሪ ከሶስት የማያንሱ ክፍልችን ጨምሮ የሰሩ መሆናቸዉን የተከራከሩ ሲሆን አመልካች ደግሞ ውጪ አገር ሆኖ በላከው ገንዘብ እንደተሰሩ ተከራክሯል። በዚህ ነጥብ ላይ ግራ ቀኙ የሚያነሷቸው ክርክሮች ባላቸው ማስረጃ ተጣርተው ያልተወሰነ በመሆኑ እና የግራ ቀኙ በመኖሪያ ቤቱ ላይ ያላቸው መብት ተገቢው መጣራት ከተደረገ በኋላ መወሰን ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በመሆኑም ግራ ቀኙ ሲጋቡ የተጠቀሰው መኖሪያ ቤት የሚገኝበት አጠቃላይ ይዘት እንዳት እንደነበር ፣ አብሮ ባለበት ጊዜ የተደረገው መሻሻል ምን ያህል እንደሆነ እና ክሱ ሲቀርብ የመኖሪያ ቤቱ አጠቃላይ ይዘት በግራ ቀኙ ማስረጃ ተጣርቶ በቤቱ ላይ የግራ ቀኙ መብት ምን ይሆናል?
የሚለውን የበታች ፍ/ቤቶች መወሰን ሲገባቸው ማለፊቸው መሰረታዊ የሆነ የሙግት አካሄድ መርሆቹን የተከተለ ባለመሆኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚሁ መሰረት የሚከተለውን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ከ/ፍ/ቤት በመዝ/ቁ. 92430 ነሐሴ 13 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት በመዝ/ቁ. 155334 በቀን 29-7-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት በአዱስ አበባ ከተማ አዱስ ከተማ ክፍለ ከተማ ቀበላ 19/20 የቤት ቁ. 708ን በተመለከተ የተሰጠው የውሣኔ ክፍል በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የፋ/የመ/ደ/ፍ/ቤት ከላይ በፍርድ ሐተታው በተመለከተው መሰረት የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማት ተገቢውን ውሣኔ እንዱሰጥበት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰናል፤
ይጻፍ።
No topics extracted.