No summary available.
ሰኔ 29 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የውርስ ክርክር ሲሆን የተጀመረው በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የአሁን አመልካቾች ባቀረቡት ክስ ነው። ቀርቦ የነበረው ክስ አውራሻችን ሟች ወ/ሮ ሙለሸዋ ወ/መስቀል ከሟች አቶ አበበ ተክለ ግር ጋር ጋብቻ ፈጽመው በቦላ ክ/ከተማ ቀበላ 14/15 የቤት ቁጥር 1654 እና የተለያዩ የቤት ዕቃዎችን በጋራ አፍርተዋል። ተከሣሽ የሟች አውራሻችንን ንብረት ይዘው እየተጠቀሙ ሲሆን እንዱለቁ ቢጠየቁ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው በህግ ተገደው ንብረቱን እንዱያካፍለን ወይም ንብረቱ ተሽጦ የድርሻችን ክፍያ እንዱፈጸምልን የሚል ነበር።
ተከሣሽ /የአሁን ተጠሪ/ በሰጡት መልስ የተጠቀሰው ቤት የባልና ሚስት ስለመሆኑ ማስረጃ አላቀረቡም እና ቤቱም በተከሣሽ ስም የተመዘገበ በመሆኑ የመክሰስ መብት የላቸውም፤ አውራሻቸው ከሞቱ ከመጋቢት 04/1990 ጀምሮ ከ1ዐ ዓመት በኋላ የቀረበ ክስ በመሆኑ በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ተከራክሯል።
የፋ/ ከፍተኛ ፍ/ቤት ከላይ እንደተመለከተው ካከራከረ በኋላ የመክሰስ መብት የላቸውም በማለት የተነሣውን ተቃውሞ ውድቅ በማድረግ ቢያልፈውም ይርጋን በተመለከተ ግን ተቀባይነት ያለው ተቃውሞ መሆኑን በመግለጽ የቀረበውን ክስ በዚሁ በይርጋ ውድቅ አድርጏታል።
አመልካቾች በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለፋ/ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ካከራከረ በኋላ የሥር ፍ/ቤቱን ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት አጽንቶታል።
አሁን የቀረበው ቅሬታ በዚሁ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ሲሆን ነሐሴ 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በ4 ገጽ በተጻፈ አቤቱታ ፍሬ ሃሣብ አመልካቾች የወራሽነት ማስረጃቸውን ከያዙ በጥቂት ወራት ውስጥ ያቀረቡት ክስ በመሆኑ ተጠሪ ተሰጠኝ የምትለው በስጦታ በመሆኑ የተደረገው ደግሞ መጋቢት 04 ቀን 1993 ዓ.ም በመሆኑ የይርጋ ጊዜ ከዚህ ጀምሮ ሲቆጠር 1ዐ ዓመት ያልሞላው በመሆኑ እና ተጠሪም በይዞታቸው ስር አደረጉ እንኳ ቢባል ከዚሁ ጊዜ ጀምሮ በመሆኑ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ላሆን አይገባም የሚል ነው። ጉዲዩ ያስቀርባል በመባለ ተጠሪ ህዲር 27 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም በ2 ገጽ የተጻፈ የመልሣቸዉ ፍሬ ሃሣብ የአመልካቾች አውራሽ ከሞቱ ከ1ዐ ዓመት በኋላ የቀረበ ክስ በመሆኑ በይርጋ ውድቅ ይሆናል። የስጦታው ውል ለውርስ ጥያቄ የይርጋ መቁጠሪያ መነሻ ጊዜ ላሆን አይችልም እና ወራሽነታቸውን ያረጋገጡበት ቀንም እንደ ይርጋ መቁጠሪያ መነሻ ሉያገለግል ስለማይችል የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም በማለት ተክረክሯል። የአመልካቾች የመልስ መልስ ቀርቧል። በግራቀኙ መካከል የነበረው የክርክር ሂደት ከላይ የተመለከተው ሲሆን ችልቱም መዝገቡን ከተነሱት ክርክሮች ከተያዘው ጭብጥና አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮታል። እንደመረመረውም ፡አመልካቾች ያቀረቡት የውርስ ክስ በይርጋ ቀሪ ይሆናል ወይስ አይሆንም የሚለው ጭብጥ ተይዞ እልባት ማግኘት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በዚሁ መሰረት የአመልካቾች አውራሽ የሞቱት መጋቢት 04 ቀን 1990 ዓ.ም እንደሆነ፣ አመልካቾች ወራሽነታቸውን ያረጋገጡት በ2ዐዐዐ ዓ.ም ውስጥ እንደሆነና ክስ ያቀረቡት ደግሞ መጋቢት 22 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም እንደሆነ አላከራከረም።
የአመልካቾች አውራሽ በሞቱበት ጊዜ ስራ ላይ የነበረው የቤተሰብ ህግ በፍትሐብሕር ህግ አንቀጽ 683 እስከ 689 ጋብቻ ከተጋቢዎቹ በአንደ መሞት ሉፈርስ እንደሚችልና መብት አለን ባዮች የድርሻቸውን መጠየቅ እንደሚችለ ይደነግጋል። ሆኖም እስከ መቼ ድረስ መጠየቅ እንደሚገባቸው ስለማያመለክት ክርክሩም ደግሞ በወራሾች መካከል ባለመሆኑ በፍ/ብሓር ህግ ኡንቀጽ 1677/1/ እና 1845 መሰረት በ1ዐ ዓመት ይርጋ መታየት እንዲለበት ከዚህ በፉት በመዝ.ቁ. 17937 እና ላልች በርካታ መዛግብት ላይ የህግ ትርጉም ተሰጥቶበታል።
ጊዜው መቆጠር ያለበት አውራሻችን ነው የተባለው ሰው ከሞተበትና ጋብቻውም በዚያው ምክንያት ከላይ እንደተመለከተው ከፈረሰበት ጊዜ ጀምሮ መሆን እንዲለበት ከላይ የተመለከተው የቤተሰብ ህግ ድንጋጌዎች እና የይርጋ ዘመን አቆጣጠርን የተመለከቱ የህግ ድንጋጌዎች ያስረዲለ።
No topics extracted.
በተጨማሪም የይርጋ ዘመን አቆጣጠርን የሚመለከቱ ድንጋጌዎች ከመቼ መቆጠር እንደሚጀምሩ በምንመለከትበት ጊዜ በአንደኛው ተጋቢ መሞት ምክንያት ከፈረሰ ጋብቻ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡ የጋራ ንብረት ክፍፍል ጥያቄ ጋብቻው በሞት ከፈረሰበት ዕለት ጀምሮ መሆን እንዲለበት ከመውረስ መብት አኳያ ሲታይም በፍ/ብ/ህግ ቁ. 826/1/ መሰረት ውርሱ የሚከፈተው የአመልካቾች አውራሽ በሞቱበት ቦታና ቀን እንደሆነ ስለሚደነግግ እና የይርጋ ዘመን መቀጠር የሚጀምረው በፍ/ብ/ህግ ቁ. 5 እና 1846 መሰረት መሆን እንዲለበት ስለሚደነግግ የይርጋው ዘመን መቆጠር ያለበት የአመልካቾች አውራሽ ከሞቱበት ቀን ጀምሮ መሆኑን ያስገነዝባል። ምክነያቱም የአመልካቾች መብት ሉበስል ወይም መጠየቅ ይችላለ የሚባለው ወይም ንብረቱ በዕጅ ይገኛል የተባለው ሰው የማስረከብ ግዳታ አለበት የሚባለው አውራሻቸው ከሞቱበት ቀን ጀምሮ ስለሚሆን ነው።
በዚሁ መሰረት የአመልካቾች አውራሽ ከሞቱ ከ1ዐ ዓመታት በኋላ የቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች መወሰናቸው መሰረታዊ የህግ ስህተት የላለበት ከመሆኑም በላይ አመልካቾች የይርጋው ዘመን መቆጠር ያለበት ወራሽነታችንን ካረጋገጥንበት ቀን ጀምሮ ነው ወይም ደግሞ ለተጠሪ ስጦታ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች የህግ መሰረት የላቸውም ብለናል።
በመሆኑም ቀጥል የተመለከተውን ውሣኔ ሰጥተናል።
ው ሣ ኔ
የፋ/ጠ/ፍ/ቤት በመዝ/ቁ. 50871 ግንቦት 25 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በዋለው ችልት እና የፋ/ከፍ/ፍ/ቤት በመዝ/ቁ. 65579 በቀን 16-2-2002 ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጡት ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ጸንቷል።
አመልካቾች ያቀረቡት የውርስ ክስ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ በአግባቡ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት በግራቀኙ ለደረሰው ወጪና ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻለ ብለናል።
ከፋ/ከፍ/ፍ/ቤት የመጣው የመ/ቁ. 65579 ወደ መጣበት ይመለስ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።