No summary available.
ሚያዚያ 18 ቀን 2003ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- አቶ ፈቃደ መክብብ ጠበቃቸው አቶ አምዳ አበበ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ዲንኤል ብሥራት ጠበቃቸው ወ/ሮ አበባ መንግስቱ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ለዚህ የሰበር ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት በስር አመልካች ወይም በአሁን ተጠሪ ዲንኤል ብሥራትና በስር ተጠሪ ሞገስ ብሥራት መዝገብ የሰጠው ውሳኔ ነው።
በሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት ያሁን ተጠሪ ባቀረበው አቤቱታ ሟች አባታችን አቶ ብሥራት ኪዲኑ ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ቦላ ምድብ የመ/ደ/ፍ/ቤት ከተጠሪ /ሞገስ ብሥራት/ ጋር ወራሽ ነኝ የሚል ግለሰብ እኔን ያሁን አመልካችን ወራሽ አይደለም በማለት ውሳኔ በማሰጠቱ አመልካች በይግባኝ የስር ፍ/ቤት ውሳኔን ሳይሽር ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ልጅነት አረጋግጬ ስቀርብ ከውርስ ልነቀል አይገባም በሚል መከራከር እንደሚችል ውሳኔ የሰጠ በመሆኑ የሟች ብሥራት ኪዲኑ ልጅ ስለመሆኔ ይረጋገጥልኝ ብሎል።
የስር ተጠሪ የነበረው አቶ ሞገስ ብሥራትም በሰጠው መልስ አመልካች ከሟች አቶ ብሥራት ኪዲኑ እና ከወ/ሮ ውድነሽ ይደግልኝ ህዲር 25 ቀን 1959ዓ.ም የተወለደ በአባትም በእናትም የምንገናኝ ወንድሜ ነው፣ ልጅነቱም እውነት ስለሆነ በጥያቄው መሰረት ቢረጋገጥለት ተቋውሞ የለኝም ብሎል።
የሥር አመልካችን አቤቱታና የተጠሪን መልስ የመረመረው የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤትም አመልካች ከሟች ብሥራት ኪዲኑ ስለመወለደ ተጠሪ ወይም የአመልካች ወንድም ያልተቃወመ በመሆኑ አመልካች የሟች ብሥራት ኪዲኑ ልጅ ነው በማለት በቤተሰብ ህግ ቁጥር 143 መሰረት ውሳኔ ሰጥቷል።
የስር የመ/ደ/ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ የአሁኑ የሰበር አመልካች ቅር በመሰኘት ለሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት በይግባኝ እንዱታረምለት ያቀረበ ቢሆንም ከፍተኛው ፍ/ቤቱ በ25/01/2003 ዓ.ም በዋለው ችልት መልስ ሰጪውን መጥራት ሳያስፈልግ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 337 መሰረት የይግባኙን መዝገብ በመዝጋት ይግባኝ ባዩን አሰናብቷል።
የሰበር አመልካችም በስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ጥቅምት 22ቀን 2003ዓ.ም የተጻፈ ቅሬታ አቅርቧል። በሰበር አቤቱታ የተጠቀሱት ዋና ዋና የቅሬታ ነጥቦችም፡ሟች አጏቴ አቶ ብሥራት ኪዲኑ በሕይወት ዘመናቸው ያደረግኩላቸውን ውለታ በመግለጽ በቦላ ክ/ከተማ ቀበላ 04/06/07 ክልል የሚገኘውን ቁጥሩ 288 የሆነውን የግል መኖሪያ ቤታቸውን በታህሳስ 15 ቀን 1994ዓ.ም በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት 4 ምስክሮችን ይዞ በመቅረብ የተናዘዙልኝ በመሆኑ ይህንኑ መሰረተ በማድረግ የኑዛዜ ወራሽነቴን በቦላ የመ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁ 373/2000 እንዱረጋገጥ ያደረግኩ ሲሆን ያሁኑ ተጠሪና አቶ ሞገስ ብሥራት ኑዛዜውን ተቃውመው የሟች ኑዛዜ በፍረንሲክ ላብራቶሪ ተመርምሮ የሟች ፊርማ መሆኑ በመረጋገጡ ጉዲዩን በይግባኝ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት ወራሽነቴን በማጽናት ውሳኔ ሰጥቷል። ከዚህ ውሳኔ በኋላ ተጠሪው እንደገና ሳያገኝ አቶ ሞገስ ብሥራት የተባለውን በተጠሪነት መዝግቦ በቀጥታ አቤቱታ በማቅረቡ የሥር መ/ደ/ፍ/ቤትም አመልካቹን የሟች ልጅ ነው ሲል ውሳኔ በመሰጠቱ ያሁን አመልካችም በዚሁ ውሳኔ መቃወሚያ ባቀረብም የሥር ፍ/ቤት በቤተሰብ ህግ አንቀጽ 177/1-3/ መሰረት የመቃወም መብት የለህም ማለቱ የህግ ስህተት ነው፣ በሥር ፍ/ቤት በተጠሪነት የተመዘገበው አቶ ሞገስ ብሥራት በቦላ ምድብ የመ/ደ/ፍ/ቤትም ሆነ በይግባኝ፣ ሰሚው ፍ/ቤት የተከራከረኝ ሲሆን እንደ ህጉ ዓላማ ከሆነ በተጠሪነት መመዝገብና መጠራት የሚገባኝ እኔ ያሁኑ አመልካች ነበርኩ። ይህ ታልፍ ከዚህ በላይ በስም የተጠቀሰውን ግለሰብ ተጠሪ ማድረጉ የህግ ስህተት ነው፣ የሚለ ሲሆኑ ተጠሪው የሟች ብሥራት ኪዲኑና የወ/ሮ ውድነሽ ይደግልኝ ልጅ ሳይሆን የአቶ መኮንን በላይና የወ/ሮ ሰማያት ይደግልኝ በመሆኑ ተጠሪው ፍ/ቤቱን ሳያስፈቅድና ፍ/ቤቱም ሳይፈቅድለት ከሟች የተወለደ ልጅ ነው በሚል የተሰጠ ውሳኔ ይሻርልኝ ሲል ጠይቋል።
ለቀረበው የሰበር ቅሬታ ተጠሪው በሰጠው መልስ፡- አባትነትን መቃወም ለማንም የተለቀቀ ሳይሆን ለቅርብ የቤተሰብ አባላት የተሰጠ መብት ነው። አመልካች የሟች ወንድም በመሆኑ በቤተሰብ ህግ አንቀጽ 177/1-3/ ሥር ከተመደቡት የዘር እርከን ውስጥ አይሸፈንም። ተጠሪን የሟች ብሥራት ኪዲኑ ልጅ አይደለም በማለት የሚከራከረውም ሟች ንብረታቸውን በኑዛዜ ሰጥተውኛል በሚል ሲሆን በቤተሰብ ህግ አንቀጽ 177/3/ ከጥቅም ግጭት የተነሳ አባትነትን ለመቃወም ከተገለጹት ወራሽና ወኪል አንደ በመሆኑ ክርክሩ ተቀባይነት የለውም። ሟች አቶ ብሥራት ኪዲኑ ለአመልካች በኑዛዜ ንብረታቸውን የሰጡ መሆኑንና ይህንኑ ተጠሪና ወንድሜ ተቃውመን ኑዛዜው የሟች ነው በሚል በመረጋገጡ አሁን ለዚህ ችልት ከቀረበው የልጅነት ጥያቄ ጋር የሚያናኝ ነገር የለም። በማለት የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ላይ የተፈፀመ መሰረታዊ የህግ ስህተት ባለመኖሩ ይጽናልኝ ሲል ጠይቋል።
ተጠሪው ላቀረበው መልስ አመልካች ባቀረበው የመልስ መልስ የተጠሪው መልስ በሥር ፍ/ቤቶች የተፈፀመውን የህግ ስህተት የሚያስተባብል ባለመሆኑ የተሰጠው ውሳኔ ይሻርልኝ በሚል ክርክሩን አጠናክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር ከዚህ በላይ እንደተመለከተው የቀረበ ሲሆን እኛም የሰበር አመልካች ተጠሪው የሟች ብሥራት ኪዲኑ ልጅ ነው ተብል የተሰጠው ውሳኔ እንዱሻር ያቀረበውን የመቃወሚያ አቤቱታ የሥር ፍ/ቤቶች ውድቅ ማድረጋቸው በአግባቡ ነው? ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ ይዘን እንደሚከተለው ክርክሩን መርምረናል።
አመልካች የፍታብሐር ሥ/ሥ/ህግ ቁጥሮችን 35/፣359 እና 360 በመጥቀስ ባቀረበው የፍርድ መቃወሚያ በ29/8/2002ዓ.ም በዋለው ችልት ተጠሪ የሟች ብሥራት ኪዲኔ ልጅ ነው ተብል የተሰጠው ውሳኔ ይሻርልኝ በማለት ሲሆን ለዚህም እንደምክንያት የጠቀሰው ተጠሪ ከሟች ብሥራት ኪዲኔና ከወ/ሮ ውድነሽ ይደግልኝ አልተወለደም የሚል ነው። እንደ አመልካች አባባል የተጠሪ አባት አቶ መኮንን በላይ እናቱ ደግሞ ወ/ሮ ሰማያት ይደግልኝ ናቸው። ከተጠሪ በኩል ከቀረቡት የመከራከሪያ ሐሳቦች ምላሽ ማግኘት ያለበት አመልካች ተጠሪው የሟች ብሥራት ኪዲኔ ልጅ አይደለም በማለት የመከራከር ህጋዊ መብት የለውም የሚል ነው። ለዚህም ተጠሪው ጠቅሶ የሚከራከረው የተሻሻለውን የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/92 አንቀጽ 177 /1-3/ ያለ ድንጋጌዎችን ነው።
በመሰረቱ በአባት በኩል ያለን መወለድ መቃወም የሚቻለው የመካድ ክስ በማቅረብ ብቻ ሲሆን ክሱንም የሚያቀርበው የልጅ አባት ነህ የተባለ ሰው ነው። ሆኖም በህግ ግምት የልጁ አባት ነህ የሚባለው ሰው የሞተ ወይም የመካድ ክስ ለማቅረብ በተወሰነው ጊዜ ውስጥ አባት ነህ የተባለው ሰው ችልታያጣ እንደሆነ ከተወላጆች አንደ በርሱ ፊንታ ሆኖ የመካድ ክስ ማቅረብ እንደሚችል የፋዳራል የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 177/1/ ይደነግጋል።
ነገር ግን ተወላጆች የላለ እንደሆነ አባት እና እናት የመካድ ክስ የማቅረብ መብት ያላቸው ሲሆን እነዚህም በላለ ጊዜ ደግሞ ወደ ላይ ከሚቆጠሩ ወላጆች አንደ መብቱን ሉሰራበት እንደሚችል ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ህግ አንቀጽ 177/2/ ተጠቅሷል። በመጨረሻም ወደ ላይ የሚቆጠሩ ወላጆች የላለ እንደሆነ በመካድ መብት ሉሰራበት የሚችለው ከወንድሞቹ ወይም ከእህቶቹ አንደ እንደሆነ የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 177/3/ ይናገራል።
በዚህ በተያዘው ጉዲይም አመልካች የሟች ወንድም በመሆኑ የሟች ተወላጆች ወይም ወላጆች (Descendants or Ascendants) በሕይወት አለመኖራቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ በቤተሰብ ህጉ አንቀጽ 177/3/ መሰረት የመካድ ክስ ወይም ሟች ብሥራት ኪዲኑ የተጠሪ አባት አይደለም በማለት ሟች የተጠሪ አባት ነው ተብል የተሰጠውን ፍርድ እንዱነሳ መቃወሚያ ማቅረብ አይችልም።
በመሆኑም ከዚህ በላይ በተጠቀሱት ምክንያቶች የተነሳ በስር ፍ/ቤቶች በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት አላገኘንም።
የሥር የመ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ በቀን 29/8/2002ዓ.ም በዋለው ችልት የሰጠውን ውሳኔና የሥር ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 96603 በ25/01/2003ዓ.ም የሰጠውን ትዕዛዝ አጽንተናል።
የዚህን ፍ/ቤት ወጪና ኪሳራ አመልካችና ተጠሪ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ወደ መዝገብ ቤት ተመላሽ ይሁን።
No topics extracted.