No summary available.
መጋቢት 20 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቶች፡- 1- ወ/ሮ እቴቱ ሽፈራው 2- አቶ አሸናፉ ሽፈራው ጠበቃ አቶ ግርማቸው ይላላ ቀረቡ ተጠሪዎች፡- 1- ወ/ሮ መንበረ ሽፈራው 2- አቶ ይድነቃቸው ሽፈራው ጠበቃ አቶ ሀይለ ነጏ ቀረቡ 3- አቶ ዮናስ ሽፈራው መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ አመልካቾች የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ጭብጥ ተይዞ ለሰበር ችልት የቀረበ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪዎች አመልካች አመልካቶች ጣልቃ ገብ በመሆን ተከራክረዋል። ተጠሪዎች ለሥር ፍርድ ቤት የአንደኛ ተጠሪ ወላጅ አባት አቶ ሽፈራው ወልደማርያም ህዲር 7 ቀን 2000 ዓ.ም ምንም አይነት ኑዛዜ ሣይተው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። እንደዚሁም የአንደኛ ተጠሪ ወላጅ እናትና የሁለተኛና የሶስተኛ ተጠሪዎች አያት የሆኑት ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ ፈንታ ጥር 17 ቀን 2000 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩና ጥር 7 ቀን 2000 ዓ.ም ተጠሪዎችን የኑዛዜ ተጠቃሚ የሚያደርግ ኑዛዜ ያደረጉ መሆኑን በመግለፅ አንደኛ ተጠሪ የሟች ሽፈራው ወልደማርያም ያለኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዱሰጣቸውና ተጠሪዎች የሟች የወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸው እንዱረጋገጥላቸው ጠይቀዋል።
የአሁኑ አመልካቶች በሥር ፍርድ ቤት ጣልቃ ገብ ተከራካሪ በመሆን ገብተው የሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ ልጆችና ህጋዊ ወራሾች ነን። ጥር 7 ቀን 2000 ዓ.ም እናታችን ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ አደረጉት የተባለው ኑዛዜ ሟች ካላቸው ንብረት እኛ ብር 500/አምስት መቶ ብር / እንዱሰጠን የሚልና እኛን ከውርስ የመንቀል ያህል ውጤት ያለው ነው። ሟች ኑዛዜውን ያደረጉት በትክክለኛ አእምሮ አለመሆኑን ሁለተኛና ሶስተኛ ተጠሪዎች የልጅ ልጆቻቸው ሆነው እያለ ልጆቼ በማለት ያደረጉት ኑዛዜ ያስረዲል ስለዚህ ኑዛዜው ውድቅ ላደረግልን ይገባል የሚል መቃወሚያ አቅርበዋል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ኑዛዜ አድራጊዋ ሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ አንድ ሚሉዮን ከሚያወጣው የውርስ ሀብት ውስጥ አመልካቾች ብር 500 /አምስት መቶ ብር / እንዱወስደ ኑዛዜ ሲያደርጉ የሰጡት ምክንያት በቂ ምክንያት ባለመሆኑ ኑዛዜው እንዱሻሻል በማድረግ አመልካቶች ጣልቃ ገቦች የሟችን የውርስ ሃብት እኩል ይካፈለ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። ተጠሪዎች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሟች በኑዛዜ የፈለጋችውን ያህል ሀብት ለወራሾች በኑዛዜ የመስጠት ስልጣን እንዲላቸው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 913 የተደነገገ በመሆኑ የሥር ፍርድ ቤት የሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ ኑዛዜ እንዱሻሻል የሰጠው ውሣኔ የህግ መሰረት የለውም በማለት የሥር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በመሻር በሟች ኑዛዜ መሰረት ተጠሪዎች ይወርሳለ በማለት ወስኗል።
ይህ ውሣኔ የህግ ስህተት ያለበት መሆኑን በመግለፅ አመልካቾች የሰበር አቤቱታ በአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤት የሰበር ችልት አቅርበዋል። የከተማው የሰበር ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ ለአመልካቾች ብር 5ዐዐ/አምስት መቶ ብር/ የሰጡበትን ምክንያት በኑዛዜው የገለፁ ስለሆነ የአመልካቾች ተቃውሞ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 913 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1123/1/ ድንጋጌን የሚቃረን ነው በማለት ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት አፅንቶታል።
አመልካቾች ሚያዝያ 26 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የአዱስ አበባ ከተማ የሰበር ችልት ሟች እናታችን ያደጉት ኑዛዜ ከሟች ውርስ ከሚደርሰን አንድ አራተኛ በላይ ጉዲት እንደሚያደርስብን ካረጋገጠ በኋላ ሟች በኑዛዜያቸው ምክንያት የገለፁ መሆኑን ብቻ በማየት የሟች ምክንያት በቂ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ሣይመዝን የፍታብሓር ሀግ ቁጥር 1113/1/ በመጥቀስና በመተርጎም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል። ተጠሪዎች በበኩላቸው ህዲር 28 ቀን 2003 ዓ.ም በተፃፈ መልስ ሟች የአመልካቾችን ድርሻ ዝቅ በማድረግ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ እንዱወስደ ያደረጉት ኑዛዜ ተገቢ ነው አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1123ን በመጥቀስ ያልተከራከሩ በመሆኑ በሰበር ደረጃ ማንሣታቸው የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 329ን የሚጥስና በሰበር ያቀረቡት አዱስ ክርክር ነው የከተማው የሰበር ችልት ለፍታብሓር ህግ ቁጥር 1123/1/ የሰጠው ትርጉም ተገቢ ነው የሚል ክርክር አቅርበዋል። አመልካቾች ታህሣሥ 8 ቀን 2003 ዓ/ም የተፃፈ የመልስ መልስ የስር ፍርድ ቤት ሟች ያደረጉትን ኑዛዜ ያሻሻለው በህግ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ነው የተጠሪዎች ክርክር የህግ መሰረት የለውም የሚል ይዘት ያለው ክርክር አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የአመልካቾች እናትና አውራሽ የሆኑት ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ አመልካቾች ከውርስ ከሚደርሳቸው አንድ አራተኛ /ሩብ/ በላይ ጉዲት እንደደረሰባቸው በማሰብ ጥር 7 ቀን 2000 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ ሙለ በሙለ ተፈፃሚ መሆን ይገባዋል በማለት የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ችልትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1123 ንዐስ አንቀፅ 1 በስጦታው አከፊፈል ውስጥ ተቃራኒ ቃል ከላላ በቀር ወደ ታች ከሚቆጠሩ ተወላጆች አንደ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዲት ደርሶበት እንደሆነ የስጦታ አከፊፈለ እንዱቀር ለመጠየቅ እንደሚችል ይደነግጋል። የበታች ፍርድ ቤቶች ሟች ካላቸው የውርስ ንብረት አመልካቾች እያንዲንዲቸው ብር 5ዐዐ /አምስት መቶ ብር/ ብቻ እንዱሰጣቸው ያደረጉት ኑዛዜ ሙለ በሙለ ተፈፃሚ ላሆን ይገባል ከሚለው መደምደሚያ ላይ ያደረሱት ሟች በኑዛዜው ውስጥ ይህንን ያደረጉበትን ምክንያት ገልፀዋል በማለት ነው።
ሟች አመልካቾች የአብራካቸው ክፊይ ልጆቻቸው መሆናቸውን ገልፀው እነርሡ ግን ያልጠየቁኝ ያልረደኝ በመሆኑ ከውርሱ ንብረት ብር 5ዐዐ/አምስት መቶ ብር / እንዱወስደ በማለት በኑዛዜው ገልፀዋል። ሆኖም ሟች በኑዛዜው ውስጥ የገለፁት ምክንያት እውነት ነው ብለን ወስደን ምክንያቱ አመልካቾችን ከሟች ውርስ ከሚደርሳቸው ድርሻ ከሩብ በላይ ለማሣጣት በቂ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ መወሰን ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ከዚህ አንፃር ሲታይ ሟች ወ/ሮ ዲርቻ በኑዛዜው ውስጥ የሰጡት ምክንያት አመልካቾች ከውርሱ ንብረት ከሚደርሳቸው ድርሻ ከሩብ /አንድ አራተኛ/ በላይ ለማሳጣት የሚያስችል በቂ ምክንያት ባለመሆኑ የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የከተማው የሰበር ችልት የፍታብሓር ህግ ቁጥር 913 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 1123 ንዐስ አንቀፅ 1ን በመጥቀስ የሟች ኑዛዜ ሙለ በሙለ ተፈፃሚ መሆን ይኖርበታል በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም ሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ አመልካቾች ብር 500/አምስት መቶ ብር/ ብቻ እንዱወስደ ያደረጉበትን ምክንያት የገለፁ ቢሆንም ሟች በኑዛዜቸው የገለፁት ምክንያት ዕውነት እንደሆነ በመውሰድ ምክንያቱ በቂ ነው ወይስ አይደለም የሚለውን ነጥብ ዳኞች መመዘን የሚችለ ስለመሆኑ የፍትብሓር ህግ ቁጥር 1123 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ከፍታብሓር ህግ ቁጥር 938 ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌ ጋር በጣምራ በመተርጎም ለመረዲት የሚቻል በመሆኑ ወ/ሮ ዲርቻ አመልካቶች ስላልረዶቸውና ስላልጠየቋቸው ከውርሱ ከሚደርሳቸው ድርሻ ከአንድ አራተኛ /ሩብ/ በላይ እንዱያጡ ለማድረግ የሚያስችል በቂ ምክንያት ባለመሆኑ ኑዛዜው አመልካቾች የሚያጡት መብት ከድርሻቸው አንድ አራተኛ /ሩብ/ በላይ መሆን አይገባውም። ስለሆነም የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ ኑዛዜ ሙለ በሙለ ተፈፃሚ መሆን ይገባዋል በማለት የሰጠት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
ሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ ያደረጉት ኑዛዜ አመልካቾች ከውርሱ ንብረት ከሚደርሳቸው ከሩብ /አንድ አራተኛ/ በላይ ሉያሳጣቸው የሚችል አይደለም በማለት ወስነናል።
ሟች ወ/ሮ ዲርቻ መንግስቱ ያደረጉት ኑዛዜ አመልካቾች ከውርሱ ከሚደርሳቸው ድርሻ እስከ አንድ አራተኛ /ሩብ/ ድረስ ብቻ የሚያሳጣቸው በመሆኑ ኑዛዜው በዚሁ መንገድ ህጋዊ ውጤት እንዱኖረው ተደርጎ ሉተገበር ይገባዋል በማለት ወስነናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።
ሃ/ዱ የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
No topics extracted.