No summary available.
ሚያዚያ 3 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡- የወ/ሮ ጥሩነሽ አያለ ወራሾች
ጉዲዩ አመልካቾች የአዱሰ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ የአዱስ አበባ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ያቀረቡት ማመልከቻ በሰበር የሚጣራ ነጥብ ያለው መሆኑ ተገልፆ ለሰበር ችልት የቀረበ ነው። ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአቃቂ ቃሉቲ ምድብ ችልት የመዝገብ በማስቀረብ ለመረዲት እንደቻልነው በሥር ፍርድ ቤት የአመልካቾች አውራሽ ወ/ሮ ጥሩነሽ አየለ የፍርድ ተቃዋሚ ተጠሪ ደግሞ የመቃወም ተጠሪ በመሆን ተከራክረዋል።
በሥር ፍርድ ቤት የአመልካቾች አውራሽ በመቃወም አመልካች ሆነው በመቅረብ በመዝገብ ቁጥር 0068/96 ወ/ሮ ወጋየሁ ሰለሞን የሟች የወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ውሣኔ ተሰጥቷል። ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ የኑዛዜ ወራሽ መሆኔ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 3680 ጥር 23 ቀን 1995 የወሰነ በመሆኑ የመቃወም ተጠሪዋ የሟች የወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ የልጅ ልጅና ተተኪ ወራሽ ናት በማለት የሰጠውን ውሣኔ ይሰርዝልኝ በማለት አመልክተዋል። የአሁን ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት የመቃወም ተጠሪ ሆነው ቀርበው ወንድ አያቴ ታፈሰ በላቸውን ታህሣሥ 7 ቀን 1968 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ሴት አያቴ ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ የካቲት 24 ቀን 1994 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የአቶ ታፈሰ በላቸውና የወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ልጅ አባቴ አቶ ሰለሞን ታፈሰ ታህሣሥ 28 ቀን 1977 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ስለዚህ ፍርድ ቤቱ የሁለቱ ሟቾች ተተኪ ወራሽ ናት በማለት የሰጠውን ውሣኔ የሚሰርዝበት ምክንያት የለም በማለት ተከራክረዋል።
አመልካች ተጠሪን ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ታህሣሥ 2 ቀን 1993 ዓ.ም ከውርስ የነቀሎት መሆኑን በመግለፅ ተከራክረዋል።
የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሟች አቶ ታፈሰ እና የወ/ሮ እታለማሁ ያልጅ ልጅ ናት። ተጠሪ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 በሚደነግገው መሰርት ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ላይ የመግደል ሙከራ ወንጀል የፈፀመች መሆኑ በፍርድ አልተረጋገጠም። ስለሆነም ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ተጠሪዋ የመግደል ሙከራ እንደፈፀመችባቸው በኑዛዜያቸው የገለፁ ቢሆንም የመቃወም ተጠሪ ወ/ሮ ወጋየሁ ሰለሞን በመግደል ሙከራ ወንጀል ጥፊተኛ ያልተባለ በመሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 መሰረት የቀረበ ማስረጃ ስለላለ ተቀባይነት የለውም ስለሆነም የመቃወም ተጠሪ ወ/ሮ ወጋየሁ ሰለሞን የሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ተተኪ ወራሽ ናቸው በማለት የሰጠሁት ውሣኔ የሚሰርዝበት ምክንያት የለም በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
አመልካቾች የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለአዱስ አበባ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት የአምልካቾችን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካቾች የሰበር አቤቱታ ለከተማው ሰበር ችልት አቅረበዋል። የከተማው ሰበር ችልት የአመልካቾችን የሰበር አቤቱታ አልተቀበለውም። አመልካቾች ጥቅምት 9 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ የተጠሪ አባት ከሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ በፉት የሞተ በመሆኑ የፍታብሓር ህግ ቁጥር 830 በሚደነግገው መሰረት ሟችን የመውረስ ችልታ የለውም። ስለዚህ ተጠሪ አባቴን በመተካት ሟችን እወርሳለሁ በማለት ያቀረቡት ጥያቄ የህግ መሰረት የለውም።
ሟች ወ/ሮ እታፈራሁ ተጠሪ በተኙበት ቦታ ላሉት ልትገድላቸው በደላ ስትደበድባቸው ጎረቤት ደርሶ ህይወታቸውን እንዲተረፊቸው በኑዛዜቸው በመግለጽ ከውርስ የነቀሎት ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ የሟች ወ/ሮ እታለማሁ ተተኪ ወራሽ ናት በማለት የሰጠውን የተሣሣተ ውሣኔ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤትና የከተማው የሰበር ችልት ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩላቸው ግንቦት 26 ቀን 2002 ዓ/ም በተፃፈ መልስ እኔ የሟች ወ/ሮ እታለማሁ ተተኪ ወራሽ መሆኔን በማረጋገጥ የሰጠው ውሣኔ የህግ ስህተት የለበትም። አመልካቾች ተጠሪን ሟች በኑዛዜ ነቅለዋታል በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ህጋዊ መሰረት የለውም። መከራከሪያም በሰበር ደረጃ የቀረበ ነው። ሟች የተናዘዘችው በራሷ ንብረት ላይ ብቻ ሣይሆን በወንድ አያቴ ንብረት ላይ ነው በማለት መልስ ሰጥተዋል። አመልካቾች ሰኔ 14 ቀን 2002 ዓ.ም የተፃፈ የመልስ መልስ አቅርበዋል።
No topics extracted.
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራቀኙ ያቀረቡት ክርክር ይዘት ከላይ በአጭሩ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፣ የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ችልት ተጠሪ የሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ተተኪ ወራሽ ናቸው በማለት የሰጡት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም; የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ከላይ የተገለፀውን ጭብጥ ለመወሰን የበታች ፍርድ ቤቶች የተጠሪን ጥያቄ በመቀበል የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 0068/96 መጋቢት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ሉሰረዝ አይገባውም በማለት የሰጠውን ውሣኔ በአግባቡ ነው በማለት የደረሡበትን መደምደሚያ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ መሰረት የተሰጠ መሆኑንና በውሣኔው ይዘት ተገቢ መሆኑን መመርመር ያስፈልጋል።
በልላ በኩል ተጠሪ ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ በህይወት ዘመናቸው ያደረጉት ኑዛዜ የላለ መሆኑን በመግለፅ ተጠሪ የሟች የልጅ ልጅና ተተኪ ወራሽ እንደሆኑ እንዱወሰንላቸው ለአዱስ አበባ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ጥያቄ አቅረበዋል። የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የተጠሪን ማስረጃ በመዝገብ ቁጥር 0068/96 በመስማት ተጠሪ የሟች የልጅ ልጅና ተተኪ ወራሽ መሆናቸውን በማረጋገጥ መጋቢት 15 ቀን 1997 ዓ.ም ውሣኔ ሰጥቷል።
የአመልካቾች አውራሽ ተጠሪ ሟች ወ/ሮ እታለማሁ በህይወት ዘመናቸው ኑዛዜ አላደረጉም በማለት ያቀረቡት አቤቱታ የተሣሣተ ነው። የአዱስ አበባ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ይህንን የተሣሣተ አቤቱታ በመቀበል መጋቢት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ስህተት ያለበትና የእኔን መብትና ጥቅም የሚጎዲ ነው። ሟች ታህሣሥ 2 ቀን 1993 ዓ.ም ኑዛዜ ያደረጉ መሆኑን እና የሟች ኑዛዜ ህጋዊ መስፈርት የሟላ መሆኑ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አስቀድሞ በፍርድ የተወሰነ ነው በማለት ባቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ መሰረት ሲጣራ ሟች ታህሣሥ 2 ቀን 1993 ዓ.ም ኑዛዜ ያደረጉ መሆኑንና ኑዛዜው ህጋዊ መስፈርቶችን ያሟላና ህጋዊ ውጤት ያለው መሆኑን በማረጋገጥ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጥር 23 ቀን 1995 ዓ.ም ውሣኔ የሰጠ መሆኑ ተረጋግጧል።
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሟች ወ/ሮ እታለማሁ በነፃ ፈቃዲቸው በህግ የተደነገገውን መስፈርት በሟሟላት ያደረጉትና ህጋዊ ውጤት ያለው ኑዛዜ መሆኑን በማረጋገጥ ጥር 23 ቀን 1995 ዓ.ም ውሣኔ የሰጠበት ሟች ታህሣሥ 2 ቀን 1993 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በይዘቱ ተጠሪን ከውርስ የሚነቅልና የአመልካቾችን አውራሽ የሟች ወ/ሮ እታለማሁ የኑዛዜ ወራሽ የሚያደረግ መሆኑን ለማስረዲት የአመልካቾች አውራሽ በማስረጃነት ካቀረቡት የኑዛዜ ሰነድ ለመገንዘብ ይቻላል። የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ የቀረበለት የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተጠሪ ህጋዊነቱ በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተረጋግጦ ጥር 23 ቀን 1995 ዓ.ም የተሰጠውን ውሣኔ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 በሚደነግገው መሰረት ውሣኔውን ለሰጠው ፍርድ ቤት የፍርድ መቃወሚያ በማቅረብ ካላሻሩት በስተቀር በመዝገብ ቁጥር 0068/96 መጋቢት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በተሣሣተ ፍሬ ጉዲይ ላይ የተመሰረተና በልላ ፍርድ ቤት አስቀድሞ ውሣኔ በተሰጠበት ጭብጥ ላይ የተሰጠ መሆኑ የአመልካቾች አውራሽ ካቀረቡት የፍርድ መቃወሚያ ማመልከቻ ጋር አያይዘው ባቀረቡት የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ውሣኔና ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ባደረጉት የኑዛዜ ሰነድ ተረጋግጧል። በመሆኑም የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 0068/96 መጋቢት 15 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ያደረጉት ኑዘዜ የለም በማለት ተጠሪ ያቀረቡትን የተሣሣተ ፍሬ ጉዲይ መሰረት በማድረግ የተሰጠና ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ያደረጉት ኑዛዜ የህጉን መስፈርት ያሟላና ህጋዊ ውጤት ያለው መሆኑን በማረጋገጥ አስቀድሞ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ የሰጠበት መሆኑን ባለማወቅ መሆኑን ገልፆ ውሣኔውን በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 360/2/ መሰረት መሰረዝ ነበረበት። የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩ በፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5/1/ መሰረት አስቀድሞ በፍርድ ያለቀ መሆኑንና ተጠሪ የኑዛዜውን ህጋዊነትና የሚያስከትለውን ህጋዊ ውጤት አስመልክቶ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 3680 ጥር 23 ቀን 1995 የሰጠውን ውሣኔ ላይ የፍርድ መቃወሚያ በማቅረብ ሣያሰርዙ ከውርስ የተነቀለ መሆኑን የሚገልፅ ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ያደረጉት ኑዛዜ መኖሩን በማረጋገጥ የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ እያለ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ እታለማሁ ተተኪ ወራሽ ናቸው በማለት የሰጠሁትን ውሣኔ የምሰርዝበት ምክንያት የለም በማለት ውሣኔ መስጠቱ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ህግ ቁጥር 5/1/ የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል።
የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ያደረጉት ኑዛዜ ህጋዊ መስፈርቱን የሚያሟላና ህጋዊ ውጤት ያለው ነው በማለት አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ ይዘት እንደ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመመርመር ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ በኑዛዜቸው የገለፁት ምክንያት ተጠሪን ከውርስ ለመንቀስ የሚያበቃ አይደለም በማለት መወሰኑ መሰረታዊ የሆኑትን የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 5/1/ ፣ የፍታብሓር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 358 እና የፍታብሓር ስነ ስርዓት ህግ ቁጥር 360/2/ ድንጋጌዎች የሚጥስና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች አውራሽ ይህንን የኑዛዜ ሰነድ በመጥቀስ ያቀረቡትን የፍርድ መቃወሚያ ውድቅ ያደረገው ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ታህሣሥ 2 ቀን 1993 ዓ.ም ባደረጉት ኑዛዜ ተጠሪ የመግደል ሙከራ የፈፀመችባቸው መሆኑን የገለጹ ቢሆንም ተጠሪ በመግደል ሙከራ ወንጀል ጥፊተኛ ያልተባለ በመሆኑ ኑዛዜው የፍታብሓር ህግ 838 ድንጋጌ መስፈርት አያሟላም በማለት ነው። የስር ፍርድ ቤት ለውሣኔ መሰረት በማድረግ የጠቀሰው እና የተረጉመው የፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነው።
የፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 ከተዘረዘሩት ወንጀልች አንደኛውን መፈፀሙ በፍርድ ተረጋግጦበት ጥፊተኛ የተባለ ወራሽ ሟችን እንዲይወርስ በውርስ ህግ ክልከላና ማዕቀብ ይደረግበታል።
የፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 የሚደነግገው በሟች ወይም በሟች ሚስት ወይም ባል ወይም በሟች ወላጆችና ተወላጆች ላይ በህጉ ከተመለከቱት አንደኛውን ወንጀል የፈፀመ መሆኑ በወንጀል ችልት ተረጋግጦ የጥፊተኝነት ውሣኔ የተሰጠበት ሰው በፍታብሓር ህግ ቁጥር 830 መሰረት ሟችን የመውረስ ችልታ እንዲይኖረው በህግ ክልከላና ማዕቀብ የሚደረግበትና ሟችን ለመውረስ ያልተገባ /unworthy/ በመሆኑ በህግ ክልከላ /ማዕቀብ/ ይደረግበታል። ሟች በፍታብሓር ህግ ቁጥር 841 በተደነገገው መሰረት ይቅርታ ካላደረገለት በስተቀር በፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 ከተዘረዘሩት ተግባራቶች አንደኛውን መፈፀሙ ተረጋግጦ በፍርድ ጥፊተኛ የተባለ ወራሽ በሟች ወርስ እንዲይካፈል ክልከላ የሚያደርግበትና ማዕቀብ የሚጥልበት ሟች ሣይሆን በውርስ ህግ ድንጋጌ ህግ አውጭው በደነገገው የፍታብሓር ቅጣት /civil sanction/ መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 830 እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 ድንጋጌዎች ይዘትና ህጋዊ ውጤት በማገናዘብ ለመረዲት ይቻላል።
የአመልካቾች አውራሽ የፍርድ መቃወሚያ ያቀረቡት ተጠሪ ሟች ለመውረስ ያልተገባች ናት በማለት አይደለም። የአመልካቾች አውራሽ የተከራከሩት ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰን ታህሣሥ 2 ቀን 1993 ባደረጉት ኑዛዜ ከውርስ ነቅለዋታል በማለት ነው። ሟችን ለመውረስ ያልተገባ ስለመሆን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 በተደነገገውና አንድ ሰው በግልፅ በሚያደርገው ኑዛዜ ተወላጆቹን ከውርስ ለመንቀል ስለሚችልበት ሁኔታ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 937 እና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 938 በተደነገገው መካከል ሰፉ ልዩነት አለ። ከውርስ መንቀል "Dishersion" የሚባለው ተናዛዡ የውርስ ህግ በሚደነግገው መሰረት ባደረገው ኑዛዜ ውስጥ ምክንያቱን በመግለጽ ወይም በዝምታ ከወራሾቹ አንደን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑት ወራሾቹ በውርሱ እንዲይካፈለ ያደረገውን ኑዛዜ በውርስ ህግ ዕውቅናና ውጤት የሚሰጠው በሆነ ጊዜ ከውርሱ እንዲይሣተፍ የሚደረግበት ሥርዓት ነው። ተናዣዡ ከወራሾቹ አንደኛውን ከወራሽነት ለመንቀል የሚችል መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 937/1/ የሚደነግግ ሲሆነ ተናዣዡ ልጅን ወይም ወደታች የሚቆጠረውን በኑዛዜ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለፀ በቀር ልጅን ወይም ተወላጅን ለመንቀል ያደረገው ኑዛዜ እንደማይፀና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 938/1/ ተደንግጓል።
ተጠሪ የሟች እታለማሁ ታፈሰ የልጅ ልጅ መሆናቸው ተረጋግጧል። ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ተጠሪን ከውርስ ለመንቀል የደረሱበትን ምክንያት ተጠሪ አደረገቸው ያለትን ተግባር በኑዛዜያቸው ገልፅዋል። ሟች በኑዛዜ ፈፀመችው በማለት የገለፁት ተግባር ማለትም ሟች "ሣያስቡት ላሉት ከተኙበት የደበደበቻቸው መሆኑንና ጎረቤት ደርሶ ህይወታቸውን ያተረፊቸው መሆኑን ገልፀዋል። ሟች በኑዛዜያቸው የገለፁት ምክንያት ሙለ በሙለ ዕውነት ነው የሚል የህግ ግምት ያለ ሲሆን ህጉ ተጠሪ ተቃራኒ ማስረጃ ሉያቀርቡበት የማይችለና /የማይስተባበል የህግ ግምት/ መሆኑ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 938/3/ ተደንግጓል። የሥር ፍርድ ቤት ሟች ወ/ሮ እታለማሁ ተወላጆቻቸውን ተጠሪን ከውርስ ለመንቀል በኑዛዜቸው የገለፁትን ምክንያት ዕውነት ነው ብል በመቀበል ሟች የሰጡት ምክንያት ተጠሪን ከውርሰ ለመንቀል በቂ ነው ወይስ አይደለም; የሚለውን ነጥብ መርምሮ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 938/2/ መሰረት መወሰን ነበረበት። ሟች በኑዛዜቸው የገለፁት ምክንያት ከባድና ተጠሪውን ከውርስ ለመንቀል የሚያስችል በቂ ምክንያት መሆኑ ሟች በኑዛዜቸው ከገለፁት ምክንያት ለመረዲት ይቻላል። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት ጉዲዩን በፍታብሓር ህግ ቁጥር 937/1/ እና የፍታብሓር ህግ ቁጥር 938 ድንጋጌዎች መሰረት መርምሮ ውሣኔ መስጠት ሲገባው ለጉዲዩ አግባብነት የላለውን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 በመጥቀስ ተጠሪ በፍታብሓር ህግ ቁጥር 838 መሰረት በሟች ላይ የመግደል ሙከራ ወንጀል የፈፀመች መሆኑ በፍርድ ጥፊተኛ የተባለችበት ማስረጃ አልቀረበም በማለት የአመልካቾችን መቃወሚያ ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 310/98 ሚያዚያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣ የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ የካቲት 3 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣ የአዱስ አበባ ከተማ ሰበር ችልት በመዝገብ ሀምላ 17 ቀን 2001 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
የሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ ለተጠሪ ከተናዘዙት ብር 1‚000/አንድ ሺህ ብር/ ውጭ በውርሳቸው እንዲይሳተፈ በኑዛዜ የነቀሎቸው ስለሆነ ተጠሪ የሟች ተተኪ ወራሽ አይደለም ብለናል።
አመልካቾች የሟች ወ/ሮ እታለማሁ ታፈሰ የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን በማረጋገጥ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 3690