No summary available.
ግንቦት 03 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሪት ዝባድ ታዬ ጠበቃ አማረ ጋሻው ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
ብፁአን ታዬ ሞግዚት አሰለፈች ለገሰ ቀረቡ።
ዲኛቸው ታዬ
አቶ አቤል ታዬ ጠበቃ ዘለቀ ደሬሣ ቀረቡ።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የኑዛዜ ተጠቃሚነት ይሰረዝልኝ ጥያቄን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው። የአቤቱታው ይዘትም ባጭሩ ፡- ተጠሪዎች የሟች አቶ ታዬ ድንቅነህ ኑዛዜ ወራሾች ነን በማለት ያቀረቡት ሰነድ በሟች ያልተደረገና ፊርማውም የሟች ባለመሆኑ ፊርማው ሉመረመር ይገባል በማለት ዘርዝረው ፍርድ ቤቱ ተጠሪዎች የሟች ታዬ ድንቅነህ የኑዛዜ ወራሾች ናቸው ሲል የሰጠውን ማስረጃ ሉሰርዝ ይገባል በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪዎችም በፍርድ ቤቱ በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ቀርበው ኑዛዜው የሟች ነው፣ ፊርማውም የሟች ነው፣ ኑዛዜው የተደረገውም ምስክሮች ባለበት ነው በማለት ገልፀው በፍርድ ቤቱ የተሰጣቸው የኑዛዜ ወራሽነት ሉሰረዝ እንደማይገባ ጠቅሰው ተከራክረዋል። የስር ፍርድ ቤትም በኑዛዜው ላይ አለ የተባለውን ፊርማ በፍረንሲክ እንዱመረመር አድርጎ በኑዛዜው ላይ ነበሩ ተብል ስማቸው የጠቀሰውን ሰዎች በምስክርነት ሰምቶና ፊርማውን በተመለከተ ፍረንሲክ ምርመራ ውጤቱ የሟች ነው ወይም አይደለም ብል ለመለየት መቸገሩን የሚመለከተው አካል ከገለፀለት በኋላ ጉዲዩን መርምሮ ለጉዲዩ በምስክርነት የቀረቡት ሰዎች ኑዛዜው ሲደረግ የነበሩበት ሁኔታ እርስ በራሱ ሉጣረስ በሚችል ሁኔታ የመሰከሩ ስለሆነ ቃላቸው ታዓማኒነት የለውም የሚል ምክንያት በመያዝ የአመልካቾችን የኑዛዜ ወራሽነት በማረጋገጥ የተሰጠውን ማስረጃ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/ 360/2/ መሰረት ሰርዞታል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪዎች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ ጉዲዩን መርምሮ የአመልካች ዲኝነት ጥያቄ በኑዛዜው ላይ ያለው ፊርማ የሟች አይደለም የሚል ሆኖ እያለ የምስክሮችን ቃል በመመርመር ስለኑዛዜው መነበብ መሰረት ተደርጎ ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም ተብል መወሰኑ በመቃወሚያነት ከተጠቀሱት ነጥቦች ውጪ የተሰጠ ውሳኔ ነው የሚል ምክንያት በመያዝ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሙለ በሙለ በመሻር የተጠሪዎችን የኑዛዜ ወራሽነት ሕጋዊ ነው በማለት ወስኗል። የአሁኑ አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት የሰበር አቤቱታቸውን ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም ። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ነሐሴ 05 ቀን 2002 ዓ/ም በተጻፈ ሶስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለባቸውን ምክንያቶች ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠውን ውሳኔ የሻረው በቂና ሕጋዊ ምክንያት ሳይኖረውና በፍ/ብ/ሕ/ቁ/881 - 883 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎችን ባግባቡ ባላገናዘበ ሁኔታ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ስህተቱ እንዱታረምላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 881 እስከ 883 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ያገናዘበ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ግራ ቀኙ በፁሐፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ብቻ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች ታዬ ድንቅነህ ሰኔ 1ዐ ቀን 1999 ዓ/ም አደረጉ የተባለው ኑዛዜ አይነቱ በግልጽ የሚደረግ ኑዛዜ ዓይነት መሆኑን ነው። ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው ግራ ቀኙ የሚከራከሩበትና ይህም ችልት አቤቱታው ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱጣራ ያደረገበት ነጥብ ሟች አቶ ታዬ ድንቅነህ ያደረጉት ኑዛዜ በሕጉ ላይ የተመለከተውን መስፈርት ያሟላል? አያሟላም ? የሚለው ነው። ከላይ እንደተጠቀሰው ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ግልጽ ኑዛዜ መሆኑ ያላከራከረ ጉዲይ ነው። ግልጽ ኑዛዜ ሉያሟላ የሚገባው ስርዓቶች በፍ/ሕ/ቁ/881 ሥር ተዘርዝረዋል፣፡ ይኸውም 1ኛው ኑዛዜው በአራት ምስክሮች ፉት መነበብ ያለበት መሆኑ፣ ይህም ስርዓት መፈፀሙና በተፃፈበት ጊዜ በኑዛዜው ላይ መመልከቱ ፣ተናዛዥና ምስክሮቹ በኑዛዜው ላይ ወዱያውኑ ፊርማቸውን ወይም ያውራ ጣት ምልክታቸውን ማድረጋቸው መረጋገጡ አስፈላጊ መሆኑ ነው። በሟች ተሰጠ የተባለው ኑዛዜም ሰነደ ሲታይ አራት ምስክሮች የፈረሙበት ፣ ኑዛዜው በምስክሮች ፉት ስለመነበቡ የሚገልጽ እና ተናዛዡ የጣት አሻራቸውን ፣ምስክሮቹ ደግሞ ፈርማቸውን ያኖሩበት መሆኑን ተገንዝበናል። በመሆኑም ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በፍ/ሕ/ቁ/ 881 ሥር የተመለከቱትን ስርዓቶች የሟላ ነው። የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ኑዛዜው ፈራሽ ነው ወደሚለው ድምዲሜ የደረሰው የሕጉን ሥርዓት አልተከተለም በሚል ግልጽ ምክንያት ሳይሆን በኑዛዜው ላይ የተጠቀሱት ምስክሮች ኑዛዜው ሲደረግ የነበሩትን ምስክሮችንና ተጠሪዎችን እንዱሁም ኑዛዜውን ያነበበውን ሰው ማንነት በሚጣረስ መልኩ መስክረዋል በሚል ምክንያት ሲሆን ይህንኑ የስር ፍርድ ቤት ድምዲሜ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት ውድቅ ያደረገው በአመልካች በኩል ከቀረበው መቃወሚያ ይዘት ውጪ ነው በሚል ነው። በመሰረቱ የምስክሮች ዋና አስፈላጊነት ኑዛዜ አድራጊው ኑዛዜውን በነፃ ፍላጎቱ እና በትክክለኛ አእምሮው የሰጠ መሆኑንና የኑዛዜ ቃለም የእርሱ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው። ይህ ደግሞ የሕግ ጥያቄ ነው። አመልካች ኑዛዜው ፈራሽ ነው ብለው እስከተከራከሩ ድረስ የሕጉን ሥርዓት ያሟላ መሆን ያለመሆኑን መርምሮ ተገቢውን መወሰን የፍርድ ቤት የስራ ድርሻ ከሚሆን በስተቀር በየትኛው ሕጋዊ ምክንያት ኑዛዜው ፈራሽ እንደሆነ ተከራካሪ ወገን ለይቶ ሉከራከር ይገባል የሚባልበት ሕጋዊ አካሄድ የለም። በመሆኑም ሟች አደረጉ የተባለው ኑዛዜ የሕጉን መስፈርት ያሟላ አለመሆኑን፣ አመልካች ተጠሪዎች የሟች ታዬ ድንቅነህ የኑዛዜ ወራሽ አይደለም፣ ኑዛዜው ፈራሽ ነው በማለት የሥር ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ በከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት መሻሩ በፍ/ብ/ሕግ ከቁጥር 881– 883 የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን ባላገናዘበ መልኩ በመሆኑ ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ቁ/ 11876 መጋቢት 15 ቀን 2002 ዓ/ም ተሰጥቶ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 10 ቀን 2002 ዓ.ም በፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
የአዱስ አበባ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ/938/2001 በ19/02/2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ/348/1/ መሰረት ፀንቷል፣ሟች አደረጉት የተባለው ኑዛዜ የሕጉን መስፈርት ያላሟላ በመሆኑ ተጠሪዎች የሟች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው ሉባለ አይገባም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።