No summary available.
ግንቦት 17 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጎስ ወልደ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ ነጋ ደፍሳ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ወ/ሮ አስናቀች ደለለኝ ጠበቃ ዘውዳ ተሰማ ቀረቡ ተጠሪ፡- የጽርሐ አርያም ቅደስ ሩፊኤል ቤተክርስቲያን ጠበቃ በርናባስ ደስታ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የውርስ ሕግ ድንጋጌዎችን መሰረት ያደረገ የድርሻ ክርክርን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ታህሣሥ 14 ቀን 1993 ዓ/ም ባደረጉት ኑዛዜ በወረዲ 08 ቀበላ 05 ቁጥሩ 145/ለ/ የሆነ ፣ የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር ቁጥር 8/02601 የተሰጣቸውን መኖሪያ ቤት ለተጠሪ እንዱሆን በኑዛዜ መስጠታቸውን ገልጻ በኑዛዜ መሰረት የወራሽነት ማስረጃ እንዱሰጣት ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቤቱታ ስታቀርብ የአሁኗ አመልካች ይኸው የኑዛዜ ወራሽነት ማስረጃ ይሰጠኝ ጥያቄ ተገቢነት የለውም የሚለባቸውን ምክንያቶችን በመዘርዘር ጣልቃ ገብተው ተከራክረዋል። አመልካች የተጠሪ የዲኝነት ጥያቄ ተገቢነት የለውም በማለት በስር ፍርድ ቤት ያቀረቧቸው ምክንያቶች ሟች ትተውታል በተባለው ኑዛዜ የባለቤታቸውን የአቶ ደለለኝ ስሻን ድርሻ ንብረትን የሚያካትት በመሆኑ ኑዛዜው ሕጋዊነት ያለውም፣ በኑዛዜው ላይ የሰፈረው ፊርማም የሟቿ አይደለም፣ ኑዛዜውን ባደረጉበት ወቅትም በእድሜ መግፊት ምክንያት የሚሰሩትን አያውቁም ነበር ከውርስ ንብረቱም ያለ በቂ ምክንያት ነቅለውኛል የሚለ ናቸው። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም ፊርማውን በተመለከተ በተገቢው አካል ተመርምሮ ውጤቱ እንዱቀርብለት በማድረግ ፊርማው የሟች ማርታ ዲኛቸው መሆኑን ውጤቱን አረጋግጦ ከቀረበለት በሁዋላ በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጎ በላልች ነጥቦች ላይ የቀረቡትን የአመልካችን መከራከሪያ ነጥቦችን ተመልከቷል። በዚህም መሰረት ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ኑዛዜውን ያደረጉት ከባላቸው ጋር ባፈሩት የጋራ ንብረት ላይ በመሆኑና ይህም ሕጋዊነት የላለው መሆኑን እንዱሁም አመልካችን ያለሕጋዊና በቂ ምክንያት ከውርስ የነቀሎቸው መሆኑን ዘርዝሮ ኑዛዜው እንዱፀድቅ የቀረበውን አቤቱታ ሙለ በሙለ ውድቅ አድርጎ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኗን ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አቅርባ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በሁዋላ ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ባደረጉት ኑዛዜ መሰረት ተጠሪ ወራሽ ናት በማለት የስር ፍርድ ቤትን ውሣኔ በመሻር ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ባለመስማማት ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት የሰበር አቤቱታውን ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የአመልካች የሰበር አቤቱታ መሰረታዊ ይዘት ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ኑዛዜውን ያደረጉት ከነባለቤታቸው ድርሻ ጭምር ሁኖ እያለና አመልካችን ከውርሱ ያለሕጋዊና በቂ ምክንያት የነቀለ መሆኑ ተረጋገጦ እያለ ተጠሪ የኑዛዜ ወራሽ ናት ተብል መወሰኑ ከሕጉ ውጪ ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልት ላታይ ይገባዋል ተብል ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ጠበቃው ቀርበው መጋቢት 20 ቀን 2003 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ አመልካችን ሟች ከውርስ የነቀሎት ምክንያት ጠቅሰው በመሆኑ ኑዛዜው ሕጋዊ አይደለም የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም በማለት በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሣኔ እንዱፀና ዲኝነት ጠይቀዋል። የአመልካች ጠበቃም የካቲት 16 ቀን 2003 ዓ/ም በጻፊት ሁለት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመርነውም ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ታህሣሥ 14 ቀን 1993 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ ሕጋዊ ነው ወይስ አይደለም አመልካችንስ ከሟች ውርስ ነቅሎል ወይስ አልነቀለም? ውጤቱስ ምን ላሆን ይገባል? የሚለት ነጥቦች በጭብጥነት ሉታዩ የሚገባቸው ሁነው አግኝቷቸዋል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የቻለው ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ታህሣሥ 14 ቀን 1993 ዓ.ም ግልፅ ኑዛዜ የተው መሆኑን አመልካች የሟቿ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ/ልጅ/ ተጠሪ ደግሞ የሟች የኑዛዜ ወራሽ መሆኗን ሟች ይኖራቸዋል ተብል የተጠቀሰው ንብረት መኖሪያ ቤትና የቤት ቁሣቁስ ሁኖ ለአመልካች ብር 1000 እና የቤት ቁሳቁስ እንዱሰጣቸው የገለፁ መሆኑን ይህንን ለማድረግ በምክንያትነት የጠቀሱት ደግሞ አመልካች ትዲር ከያዘች ጊዜ ጀምሮ ተገቢውን እንክብካቤ አላደረገችልኝም ስታመምም እናቴ ብላ አላስታመመትኝም የሚል መሆኑን ነው። አከራከሪው ቤት የተናዛዧ እና የአቶ ደለለኝ ስሻን የጋራ ሃብት ስለመሆኑ አከራካሪ አለመሆኑንም በክርክሩ ሂደት ከተረጋገጡት ፍሬ ነገሮች ጭምር ተገንዝበናል።
No topics extracted.
የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና የከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ኑዛዜው ሕጋዊ ነው በማለት የወሰኑት ሟች ለአመልካች ድርሻቸውን ሰጥተዋል፣ የድርሻ ማነስ ደግሞ የውርስ መነቀል ነው ልባል የሚችል አይደለም የሚል እንድምታ ያለውን ምክንያት መሰረት በማድረግ ነው።
በእርግጥ በኑዛዜው የሚከናወኑ ተግባሮች የኑዛዜ ስጦታ /legacy/ ወይም የክፍያ ደንብ /Rule of partition/ ሉሆኑ ይችላለ። በመህር ደረጃ ደግሞ አንድ ሰው ከውርስ ሀብቱ መካከል አንድን ንብረት ለወራሾቹ መስጠቱ የኑዛዜ ስጦታ አያሰኘውም። ይልቁንም ይህ አይነት ኑዛዜ ሕጉ የሚቀበለው እንደ አንድ የክፍያ ደንብ ነው። በመሆኑም አንድ አውራሽ ለወራሹ አንድን ንብረት ቢናዘዝለት የኑዛዜው አፈፃፀም የስጦታ /legacy/ አፈፃፀምን በመከተል ሳይሆን የክፍያ ደንብ /partition/ በመከተል የሚከናውን ይሆናል። ሆኖም በኑዛዜው ላይ የሚሰጠውን ክፍያ መጠን በመገለፁ ብቻ ሁል ጊዜ የክፍያ ደንብ ነው ልባል የሚችል አይሆንም። በመሆኑም የተሰጠው የንብረት መጠን ከሟቹ የውርስ ንብረት ግምት ጋር ታይቶ ውጤቱም በዚህ ረገድ መለየት ያለበት ጉዲይ ነው።
በልላ አገላለፅ ሟች በኑዛዜው ላይ የሚያስፍረው የንብረት መጠን ከሟቹ የውርስ ንብረት መጠን ጋር እየታየ የመነቀል ጉዲይ ነው ወይስ የክፍያ ማነስ ነው? የሚለው ነጥብ የሚለይ ይሆናል።
በልላ በኩል ከሥር ፍ/ቤቶች ውሣኔዎች ለመገንዘብ እንደቻልነው በአዱስ አበባ ከተማ ውስጥ በወረዲ 8 ቀበላ ዐ5 ክልል ውስጥ የሚገኝ የቤት ቁጥር 145/ለ/ በሚል የተመዘገበውና በ343 ካ.ሜትር ስፊት ቦታ ላይ የሰፈረው መኖሪያ ቤት የባለቤትነት ደብተር ስሙ ተመዝግቦ የሚገኘው በአቶ ደለለኝ ስሻን ስም መሆኑን ንብረትነቱም የአቶ ደለለኝ ስሻን እና የወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው የጋራ ሃብት መሆኑን የጉለላ ክፍለ ከተማ መሬት አስተዲደር ለስር ፍርድ ቤት በፃፈው ደብዲቤ በፍሬ ነገር ደረጃ የተረጋገጠ መሆኑ ያላከራከረ መሆኑን ነው። በመሆኑም ሟቿ የተናዘዙት የራሳቸው የግል ንብረት ብቻ ባልሆነ ንብረት ነው ማለት ነው። አንድ ሰው በራሱ ባልሆነና ሙለ በሙለ ሉያዝበት በማይችል ንብረቱ የተናዘዘ እንደሆነ ኑዛዜው የሚኖረው ሕጋዊ ሁኔታ ምንድነው?
የሚለው ጥያቄ በውርስ ሕግ በግለጽ ምላሹ ያገኘ ነው። የውርስ ሕግ ውስጥ ይህንን ጉዲይ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 1047 እንዱህ ይነበባል።
‛በኑዛዜው የተደረገው ስጦታ በተለየ ነገር እንደሆነና ሟቹ በሞተበት ቀን በዚህ ነገር ላይ አንዲችም መብት የላለው እንደሆነ የኑዛዜው ስጦታ ፍርስ ነው።
ስለሆነም ሟቹ ይህን ሁኔታ እያወቀ በኑዛዜው ሰጥቶ እንደሆነ ስጦታው ዋጋ ያለው ይሆናል።
እንደዚህ በሆነ ጊዜ አጣሪው በኑዛዜ የተሰጠውን እቃ ዋጋ መስጠት አለበት“ ከዚህ ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው በመርህ ደርጃ ማንም ሰው ምንም መብት በላለው ንብረት ላይ የተናዘዘ እንደሆነ የተሰጠው ኑዛዜ ዋጋ አይኖረውም። በሕግ ፉት የሚፀና ኑዛዜ ለመስጠት ሟቹ ኑዛዜ በተደረገበት ንብረት ላይ መብት ሉኖረው ይገባል በልላ በኩል በንዐስ አንቀጽ /2/ በግልጽ እንደሰፈረው ሟቹ ኑዛዜ በሚያደርጉበት ንብረት ላይ ምንም መብት የላለው መሆኑን እያወቀ ስጦታ የሰጠው እንደሆነ በስጦታው ሕጋዊነት የፀና ይሆናል። በመሆኑም ኑዛዜ አድራጊው መብት ያለው መሆን አለመሆኑ ብቻ ሳይሆን ስለዚህ ጉዲይ የነበረው ግንዛቤ በኑዛዜው ፍረስ መሆን አለመሆን ላይ ውጤት ይኖረዋል። ኑዛዜው ፍርስ የሚሆነው ተናዛዡ ስጦታ ባደረገበት ንብረት ላይ መብት እንደላለውና ይህንም ያውቅ እንዲልነበረ ሲታወቅ ብቻ ነው ። ይህ መደምደሚያ የሚገኘው ከላይ የተጠቀሰው አንቀጽ አንድና ሁለት ንዐስ ቁጥሮችን አጣምሮ በማንበብ ነው።
አሁን በቀረበልን ጉዲይ ተናዛዧ በአከራካሪው ቤት ለአሁኗ ተጠሪ በስጦታ በሰጡት ቤት ላይ ሙለ የባለቤትነት መብት አልነበራቸውም። ቤቱ በጋብቻ የተፈራ የባልና ሚስት የጋራ ንብረት በመሆኑና ከአቶ ደለለኝ ስሻን ሞት በሁዋላ ይዘውት ይጠቀሙበት ስለነበር ሟቿ ቤቱ ላይ ሙለ መብት እንደላላቸው ሳያውቁ ኑዛዜ ማድረጋቸው ግልጽ ነው። በመሆኑም ኑዛዜው የተሰጠበት ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ 1047/1/ ን መስፈርት የሚያሟላ ነው። በመሆኑም ምንም እንኳ ቤቱ የጋብቻ የጋራ ንብረት በመሆኑ ምክንያት ሟቿ በቤቱ ላይ ሙለ መብት ባይኖራቸው የኑዛዜ ስጦታውን ያደረጉት ይህ መብት እንደላላቸው ሳያውቁ በመሆኑ በሟች አቶ ደለለኝ ስሻን ድርሻ ላይ የተደረገው ኑዛዜ ሉፈርስ የሚገባው ነው። ኑዛዜው ፍርስ ላሆን አይችል የነበረው ሟቿ በቤቱ ላይ ሙለ መብት እንዲላቸው የሚያውቁና ከሟች ደለለኝ ስሻን የተላለፈላቸው መብት ያለ መሆኑ ማስረጃ ቢቀርብ ነበር ። በዚህ ረገድ ተጠሪ ያቀረበችው ክርክርም ሆነ ማስረጃ የለም። በመሆኑም በአቶ ደለለኝ ስሻን ድርሻ ላይ የተደረገው የኑዛዜ ክፍል በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1047/1/ መሰረት ፈራሽ ላሆን የሚገባው ሁኖ አግኝተናል። ሆኖም ይህ ምክንያት በሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ድርሻ ላይ የተደረገውን ኑዛዜ ሙለ በሙለ ፈራሽ የሚያደርገው አይደለም።
ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው አመልካችን ከድርሻ ንብረታቸው ውርስ ነቅለዋል ወይስ አልነቀለም? የሚለውን ነጥብም ተመልክተናል። በመሰረቱ አንድ ተናዛዥ/ወላጅ/ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሹን ያለህጋዊና በቂ ምክንያት እንዱሁም በዝምታ ከውርስ ለመንቀል እንደማይችል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938 እና 939 ድንጋጌዎች ይዘት በግልፅ ያሳያል። ወላጅ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሹን ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት ወይም በዝምታ ከነቀለም ውጤቱ ምን ላሆን እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 915 ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች ጋር ተዲምሮ ሲታይ ምላሽ ይሰጣል። በዚህም መሰረት ከውርስ በዝምታ ወይም ያለበቂ ሕጋዊ ምክንያት የተነቀለ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ ሁነው የውርስ ንብረቱን ሉከፊፈለ የሚችለ መሆኑን ሕጉ ያስገነዝባል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤት ወደዚህ ድምዲሜ ከመድረሱ በፉት በወላጅ የተደረገ የኑዛዜ ስጦታ አይነቱ ጠቅላላ ወይም ልዩ ኑዛዜ ስጦታ መሆን አለመሆኑን በቅድሚያ መለየት አለበት። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 912 ስር እንደተመለከተው የኑዛዜ ስጦታ ጠቅላላ ወይም ልዩ ኑዛዜ ስጦታ ላሆን ይችላል። ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ሲባልም ተናዛዡ ሀብቱን ጠቅላላ ወይም ከመላ ንብረቱ አንደን ክፍል በሙለ ሀብትነት ወይም በላጣ ርስትነት ለአንድ ወይም ለብዙ ሰዎች የሚያወርስበት የኑዛዜ ቃል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 912/1/ ድንጋጌ ያሳያል። የዚሁ ቁጥር ንዐስ ቀጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ ማንኛውም ላላ የኑዛዜ ቃል ሁለ እንደ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ እንደሚቆጠር ይነደገጋል። አንድ ኑዛዜ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ እንደውርስ እዲ ተቆጥሮ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1014 ድንጋጌ ቅደም ተከተል መሰረት የሚከፈል ይሆናል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ሀብታቸውን ሙለ በሙለ ተጠሪ እንድትወርስ ለአመልካች ደግሞ ብር 1000 እና የቤት ቁሳቁስ የሰጡ መሆኑ ከኑዛዜው ሰነድ ይዘት ተረጋግጧል። ሆኖም ሟች አላቸው ከተባለው የማይንቀሳቀስ የውርስ ንብረት አንፃር አመልካች እንዱወስደ በማለት የተናዘዙት የንብረት መጠን ሁኔታ ሲታይ እግምት ውስጥ የሚገባ ወይም የድርሻ ጥያቄ አነሰ የሚል ክርክር የሚያስነሳ ነው ልባል የሚችል ሳይሆን በውጤቱ የመነቀል ውጤትን ያስከተለ ነው ልባል የሚችል ነው። ሟች ለአመልካች ብር 1000 እና የቤት ቁሣቁስ እንዱሰጥ በማለት የተናዘዙት ‛ትዲር ከመሰረተች በሁዋላ አልተንከባከበችኝም ፣ ስታመምም እናቴ ነች ብላ አልጠየቀችም “ በሚል ምክንያት ነው። የዚህ ሐረግ አገላለፅ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938/2/ መሰረት እንደእውነት የሚወሰድ መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከውርስ ለመንቀል የሚያስችል ሕጋዊ እና በቂ ምክንያት መሆኑን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938/3/ መሰረት መመልከቱ ተገቢ ነው። ከዚህም አንጻር በሟች የተሰጠው ምክንያት አመልካችን ከውርስ ለመንቀል ሕጋዊና በቂ ምክንያት ሁኖ አላገኘነውም።
ከላይ እንደተመለከተው ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በፍርማሉቲ ረገድ ፈራሽ ላሆን የሚችልበት ምክንያት የላለ ሲሆን ሟች የአቶ ደለለኝ ስሻንን ድርሻ አጠቃልለው መናዘዛቸው ግን ሕጋዊ አይደለም። ሟቿ አላቸው ከተባለው ጠቅላላ የውርስ ንብረት መጠን አንፃር ሲታይ ለአመልካች የተሰጠው የገንዘብ መጠን በውጤት ደረጃ አመልካችን ነቅሎል ከሚባል በስተቀር ድርሻቸውን አግኝተዋል፣ ውጤቱም በፍ/ብ/ሕቁጥር 1123 ላታይ የሚችል ነው ልባል የሚችል ሁኖ አላገኘነውም። በመሆኑም ከዚህ አንጻር ተናዛዧ ያደረጉት ኑዛዜ ስጦታ ሲታይ በውጤቱ አመልካችን ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት ከውርስ የነቀለ ሁኖ ዓይነቱ ልዩ የሆነ የኑዛዜ ስጦታ ሳይሆን ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ አይነት ነው። እንዱህ ከሆነ በፍ/ብ/ሕቁጥር 1014/ሰ/ ስር በተመለከተው መሰረት እንደውርስ እዲ ተቆጥሮ ለልዩ ኑዛዜ ተቀባዩ የሚከፈል ሣይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938 አና 939 እንዱሁም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 915 ድንጋጌዎች ታይቶ ተወላጅ ከውርስ ተነቅሎል ፣ ከኑዛዜ ተቀባዩ ጋር እኩል ሉከፈል ይገባል የሚባልበት ጉዲይ ሆኖ አግኝተናል። የክፍያ ማነስ አለማነስ ነው በማለት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር ጉዲዩ እንዲይስተካከል ደግሞ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1117 የተቀመጠው መርህ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1123 ጋር ተዛምድ ሲታይ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው ነው። ምክንያቱም ተጠሪ የሟች ተወላጅ ወይም ወደ ላይ የምትቆጠር ወላጅ አይደለችምና። ስለሆነም ተጠሪ በሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ድርሻ ላይ በፍ/ሕ/ቁጥር 915 መሰረት እንደጠቅላላ ኑዛዜ ወራሽ ተወስዲ ከአመልካች ጋር እኩል ተካፊይ ናት ተብል ሉወሰን ሲገባው የከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤትና ሰበር ሰሚ ችልት ጉዲዩን ከውርስ ንብረት ክፍያ ማነስ ጋር በማያያዝ የሰጡት ውሣኔ የኑዛዜውን ውጤት ሟች አላቸው ከተባለው ንብረት ግምት መጠን ጋር ባለማገናዘብ በመሆኑ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 23 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 18 ቀን 2002 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1178/96 ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ/ም የሰጠው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
ሟች ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው ታህሣሥ 14 ቀን 1993 ዓ/ም ያደረጉት ኑዛዜ በውጤቱ ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት አመልካችን የነቀለ በመሆኑ በአመልካች ላይ ተፈፃሚነት የለውም ብለናል፤
ኑዛዜው ተጠሪን በሟቿ /ወ/ሮ ማርታ ዲኛቸው/ ድርሻ ንብረት ላይ አንድ ወራሽ የሚያደርግ በመሆኑ አመልካች የሟችን ድርሻ ንብረት ከተጠሪ ጋር እኩል እንዱካፈለ ብለናል።
የአቶ ደለለኝ ስሻን ድርሻ ላይ ተጠሪ በኑዛዜው ተጠቃሚ የምትሆንበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል። መዝገቡ ተዘግቷል፣ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ።