No summary available.
የሰ/መ/ ግንቦት 30 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ አልማው ወላ ነጋ ደፍሣ አዲነ ንጉሴ አመልካች፡- ኤርሚያስ ኬስታንትኖስ ግሉፔትስ -ወኪል ጸሐይ መለሰ - ቀረበር ተጠሪ፡- ሰለሞን ከስታንቲኖስ ግሉፔትስ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወቀረቀት ይሰጠኘ በሚል በቀረበው ጥያቄ መነሻነት የተካሄደውን ክርክር የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን መዝገቡ የተከፈተው አሁኑ አመልካች ባቀረበው የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጠን ጥያቄ መሰረት ነው። ፍ/ቤትም ጥያቄውን በመቀበል የምስክር ወረቀቱን ሰጥቶአል። በልላ በኩል ደግሞ የአሁኑ ተጠሪ የምስክር ወረቀቱ የሚሰጥበት ህጋዊ ምክንያት የለም፤ ኤርሚያስ የሟች ኬስታንቲኖስ ግሉፔትስ ልጅ አይደለም በማለት መቃወሚያ በማቅረቡ መዝገቡ እንደገና ተንቀሣቅሶ ሁለቱ ወገኖች እንዱከራከሩ ተደርጏአል። በመጨረሻም የአሁኑ አመልካች የሟች ኪስታንቲኖስ ግሉፔትስ ልጅ ስለመሆኑ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት /የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት/ አረጋግጦ ማስረጃ አልመጣም በማለት ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል ሰጥቶት የነበረውን ማስረጃ ሰርዞአል። በየደረጃው ይግባኝ እና የሰበር አቤቱታ የቀረበላቸው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እና የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በሰር ችልትም በመጀመሪያው ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሣኔ አጽንተዋል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
በበኩላችንም አመልካች ሰኔ 24 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በጻፈው ማመልከቻ ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። ክርክሩ የተሰማው ለአመልካች ተሰጥቶ የነበረው የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የተሰረዘው በአግባቡ ነው ወይ በሚለው ጭብጥ ላይ ነው።
በዚህ መሰረትም ግራ ቀኝ ወገኖች ጭብጡን በማስመልከት ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከህጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል።
ከስር ጀምሮ የተደረገውን ክርክር እና የተሰጡትን ውሣኔዎች ይዘት በዝርዝር ተመልክተናል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የሰማው ፍ/ቤት ከሰጠው ውሣኔ መገንዘብ እንደቻልነው ለአመልካች ተሰጥቶ የነበረው የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሉሰረዝ ይገባል በማለት ተጠሪ ባቀረበው መቃወሚያ ላይ ውሣኔ ከመስጠቱ በፉት አመልካች በሚመለከተው /ስልጣን ባለው/ ፍ/ቤት ልጅነቱን አረጋግጦ ይቅረብ የሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ነበር። ውጤቱን ለመጠበቅ በሚልም ቀጠሮ ተይዞ ነበር።
በልላ በኩል ደግሞ የልጅነት ይረጋገጥ ጥያቄ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን ልጅነት አረጋግጦ የሰጠው ውሣኔ የለም የሚል ምክንያት በመስጠት ፍ/ቤቱ የተጠሪን መቃወሚያ በመቀበል ውሣኔ እንደሰጠ ተመልክተናል። ይግባኝ የቀረበለት የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤትም ሆነ የይግባኝ ሰሚው ሰበር ችልትም ይህን መስመር ተከትለው ነው የወሰኑት።
በበኩላችን እንዲየነው የልጅነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ /አቤቱታ/ የቀረበለት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ያቀረበውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ በእርግጥ አመልካች የሟች አቶ ኬስታንቲኖስ ግሉፔስ ልጅ ነው። ወይስ አይደለም የሚለውን ጭብጥ በመያዝ የሰጠው ውሣኔ የለም። ፍ/ቤቱ ከአመልካች ካቀረበው አቤቱታ /ማመልከቻ/ ይዘት በመነሣት ብቻ መዝገቡን እንደዘጋው እና የሰጠው ምክንያትም በጋብቻ ውስጥ ተወልጃለሁ ካልክ በህጉ ልጅ መሆንህ ስለሚገመት ጥያቄህ በፍ/ቤት የሚረጋገጥ አይደለም የሚል እንደሆነ በመዝገቡ ተያይዞ ከቀረበው ውሣኔ ለማረጋገጥ ችለናል።
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት የአመልካችን የይግባኝ ክርክር ያልተቀበለው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከሰጠው ውሣኔ ላይ ይግባኝ ከምትጠይቅ ውጪ በዚህ በኩል የሚደረግ የለም በማለት እንደሆነም ተመልክተናል።
እንደምናየው አመልካች የሟች ልጅ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ አከራካሪ ሆኖአል። ተጠሪ ቀደም ሲል የተሰጠው የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሉሰረዝ ይገባል በማለት የሚከራከረው አመልካች ሟች እና እናቴ በጋብቻ ተሳስረው ይኖሩ በነበሩበት ጊዜ የተወለድኩ ልጅነኝ የሚል መከራከሪያ ይዞ ነው የምስክር ወቀረቱን እንዱሰጠው የጠየቀው በእርግጥ አመልካች በጋብቻ ውስጥ ስለመወለደ ከመግለጽ አልፍ ይህ ሁኔታ በፍሬ ነገር ረገድ ተረጋግጦ ስልጣን ባለው ፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ የለም። በዚህ ምክንያትም ነው አመልካች አቤቱታውን ለፋደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረበው። በመሆኑም የወራሽነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት እንዱሰጥ የተጠየቀው የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ፍ/ቤት አመልካች የሟች ልጅ ነኝ የሚለውን ክርክር አለመቀበለ ትክክል ነው። በልላ በኩል ግን የልጅነት ማረጋገጫ ውሣኔ መስጠት ያለበት የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን አቤቱታ በአግባቡ ሣያስተናግድ በመቅረቱ ብቻ አመልካች ፍትህ የሚያገኝበትን መድረክ እንዱያጣ ማድረጉ አግባብ አይሆንም።
No topics extracted.
በፍርድ ሉወሰን የሚገባው ጉዲይ ያለው ማንኛውም ሰው ጉዲዩን ለፍ/ቤት ወይም ለላላ በህግ የዲኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብ እና ውሣኔ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ. ህገመንግስት አንቀጽ 37 /1/ ተደንግጏአል።
በያዝነው ጉዲይ እንደምናየው አመልካች በጋብቻ ውስጥም ይወለድ ከጋብቻ ውጪ ልጅነቱን ይረጋገጥላት ዘንድ ለፍርድ ቤት አቤቱታ /ጥያቄ/ የማቅረብ መብት አለው። ጥያቄው በፍርድ ሉወሰኑ ከሚገባቸው ጉዲዮች አንደ ነው። ስለዚህም የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የአመልካችን አቤቱታ በመደበኛው የክርክር አመራር ስርዓት መሰረት አለማስተናገደ ወይም ከወዱሁ መዝጋቱ ትክክል አይደለም። በጋብቻ ውስጥ ተወልጃለሁ የሚል ሰው ልጅ መሆኑን የህግ ግምት መውሰድ የሚቻለው ሰውየው በእርግጥም በጋብቻ ውስጥ ስለመወለደ በቅድሚያ በፍሬ ነገር ረገድ ሲረጋገጥ እንደሆነም ልብ ልባል ይገባል። በእኛ ግንዛቤ እና እምነት በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተያዘው ጉዲይ እልባት ከማግኘቱ /ከመወሰኑ/ በፉት አመልካች ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረበው የልጅነት ይረጋገጥልኝ ጥያቄ /አቤቱታ/ ውሣኔ ማግኘት አለበት። አመልካች ፍትህ እንዱያገኝ ማድረግ የሚችለውም በዚህ አግባብ ጉዲዩ ሲሰራ ነው ስለዚህም ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር በመ/ቁ. 1803/96 ሚያዝያ 18 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣ የአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13497 ሰኔ 2 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት በመ/ቁ. 13689 ሰኔ 16 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
በአመልካች አቤቱታ /ጥያቄ/ አቅራቢነት በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተከፈተው የሆነው መዝገብ እንዱንቀሣቀስ እና ፍ/ቤቱም የአመልካችን ጥያቄ መሰረት በማድረግ እንደዚሁም ለጉዲዩ አወሣሰን ተገቢ የሆነውን ጭብጥ በመያዝ ውስጥ ይስጥ ብለናል።
ተጠሪም የፍደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በሚሰጠው ውሣኔ መሰረት ተጠቃሚ ነኝ የሚል ከሆነ ለአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርቦት የነበረውን መቃወሚያ መሰረት በማድረግ ክርክሩን ሉቀጥል ይችላል ብለናል።
በዚህ ሰበር ችልት ለተደረገው ክርክር ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።