No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 25 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ ዓሉ መሀመድ አመልካች፡- አቶ ኃይላ ስሙጋ - ጠበቃ አቶ መኸዱ ሁሴን ቀረቡ ተጠሪ፡- ሰላማዊት ተኮላ - ጠበቃ አቶ አንተነህ ተካልኝ ቀረቡ መዝገቡን የቀጠረው ለምርመራ ሲሆን መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር ጉዲይ ማየት የተሳነው ሰው የሚያደርገውን የኑዛዜ አደራረግ ሥርዓት በሚመለከት ግራ ቀኙ ያደረጉትን ክርክር ተመልክቶ ተገቢውን ትርጉም ለመስጠት በሚል ነው።
የጉዲዩ መነሻ ሟች ወ/ሮ መሰረት መንገሻ ሚያዚያ 6 ቀን 1999 ዓ.ም ያደረጉት የኑዛዜ ሰነድ ሲሆን፣ የአሁን ተጠሪ ይኸው የኑዛዜ ሰነድ በፍ/ቤት እንዱፀድቅላቸው ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቤቱታ በማቅረባቸው ፍ/ቤቱ ጉዲዮን ተመልክቶ በን/ላ/መ/ቁ/ 1806/99 ሚያዚያ 05 ቀን 2000 ዓ.ም በዋለው ችልት ተቀብል አፅድቆታል።
ከዚህ በኋላ የአሁኑ አመልካች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁጥር 358 መሰረት የሟች ወ/ሮ መሰረት መንገሻ አባት ነኝ ሟች ልጅ የላትም ዓይነስውርና የስኳርና HIV/AIDS በሽተኛ የነበረች ስለሆነ በአዋዋይ ፉት ያልተደረገው የኑዛዜ ሰነድ ህጋዊ ውጤት የለውም። ስለሆነም ቀደም ሲል ኑዛዜው ፀድቋል በሚል የተሰጠው ውሳኔ ሉሰረዝ ይገባል በማለት ዲኝነት ጠይቀዋል።
የአሁኑ ተጠሪም ዓይነ ስውር፣ የስኳር እና የ HIV/AIDS በሽተኞች ኑዛዜ ማድረግ አይችለም የሚል ህግ የለም ኑዛዜውን ሲያደርጉ አእምሯቸው ጤነኛ እንደነበር ይኸው ፍ/ቤት በምስክሮች አረጋግጦታል። ውሳኔው ሉሰረዝ አይገባም በማለት መልስ ሰጥተዋል።
ፍ/ቤቱም የመቃወም አመልካችን ምስክሮች ከሰማ በኃላ ጉዲዩን መርምሮ ድዲ፣ ደንቆሮ፣ ዕውር የሆኑና ነዋሪ በሆነ ደዌ ምክንያት እራሳቸውን ችለው ለመተዲደር ወይም ንብረታቸውን ለማስተዲደር ችልታ ለላላቸው ሰዎች ስለ አእምሮ ጎደልዎች የተነገሩትን እርዲታዎች ለመጠየቅ ይችላለ ተብል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 340 ተደንግጓል። ሟችም አይነ ስውር እንደመሆናቸው መጠን የኑዛዜ ሰነደን በእገዛ አይተውና ለይተው የፈረሙበት መሆኑ አልተረጋገጠም። ስለሆነም የኑዛዜ ሰነደ ፀድቋል ተብል የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 360(2) መሰረት ተሽሯል። በማለት ወስኗል።
የአሁን ተጠሪ ሟች ኑዛዜውን ሲያደርጉ አእምሯቸው ደህና የነበረ ስለመሆኑ ፍ/ቤቱ ኑዛዜውን ሳያፀድቅ ያረጋገጠው ጉዲይ ነው፣ ዓይነስውር በአዋዋይ ፉት ኑዛዜ ማድረግ አለበት የሚል ህግ የለም የኑዛዜ አደራረግ ሥርዓት በልዩ የህግ ክፍል የተደነገገ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1728 ለዚህ ጉዲይ አግባብነት የለውም የሚለትን ነጥቦች መሰረት አድርገው ውሳኔው በይግባኝ እንዱታረም የይግባኝ አቤቱታ በማቅረባቸው ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የአሁን አመልካች ባለበት ጉዲዩን ተመልክቷል።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 340 ድንጋጌ ዓይነስውራን ድጋፍ ሉጠይቁ እንደሚችለ እንጂ በአዋዋይ ፉት ያልተደረገ ኑዛዜ ፈራሽ ነው ብል በአስገዲጅነት አላስቀመጠም።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1728 ተፈፃሚነቱ ውልች ላይ እንጂ ይህንን ጉዲይ አይመለከትም፤ በዚህ ጉዲይ የኑዛዜው አደራረግ የፍርማሉቲ ጉድለት አለት፣ አልተባለም። ስለሆነም የሥር ፍ/ቤት ኑዛዜውን ውል ለማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት ቀርበው ያላደረጉት ስለሆነ አጠራጣሪ ነው በሚል ምክንያት የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል ሲል ዲኝነት ሰጥቷል። የከተማው ፍ/ቤቶች ሰበር ሰሚ ችልት ይህ የይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ውሳኔ የህግ ስህተት አልተገኘበትም የሚል የመጨረሻ ዲኝነት ስለሰጠበት ይህ የሰበር ጉዲይ ለዚህ ችልት ላቀርብ ችሎል።
በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ግራ ቀኙ ያቀረቡት ክርክር ከዚህ በፉት በየደረጃው ባለት ፍ/ቤቶች ከቀረቡት በይዘቱ የተለዩ አይደለም።
የጉዲዩ አመጣጥ ባጭሩ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
እንደመረመርነውም ግራ ቀኙን የሚያከራክራቸው የኑዛዜ ሰነድ በህግ ፉት የፀና ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነጥብ ነው።
ኑዛዜ አድራጊዋ ሟች ወ/ሮ መሰረት መንገሻ ኑዛዜ ባደረጉበት ጊዜ ማየት የተሳናቸው የነበሩ ስለመሆኑም በግራ ቀኙ የተካደ ጉዲይ አይደለም።
ማየት የተሳነው ሰው ኑዛዜ የማድረግ ተግባር ሲፈፀም ይህ ተግባር በህግ ፉት የፀና፤
ማናቸውንም ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል እንደሆነ በህግ መሟላት የሚገባቸው ነጥቦች ምን ምን ናቸው? በሚለው ነጥብ ላይ ነው የተለያዩት።
ይህን አከራካሪ ነጥብ ለማስረዲት በግራ ቀኙ የቀረቡት የፍሬ ነገር ክርክሮች እና ጉዲዩን ለመወሰን የሥር ፍ/ቤቶች በሰጡት ዲኝነት የጠቀሱት ትንታኔ በህግ ፉት የፀና ተግባር ለመፈፀም አስፈላጊ ሁኔታዎች ናቸው በሚል ህጉ በየቅል ያስቀመጣቸውን ማሟያ ሁኔታዎች አንደን ከላላው በማቀላቀል እየተጠቀሱ የቀረቡ እና የተተቹ መሆኑን ከውሳኔዎች ግልባጭ ተገንዝበናል።
ይኸውም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 340 ድውዮች በሚል ርዕስ በተቀመጠው ድንጋጌ ማናቸውንም ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ተግባር ለመፈፀም ችልታ አስፈላጊ ነው። ችልታ አለ ወይስ የለም? ማለት የሚቻለው መቼ እና እንዳት ነው የሚለውን በዝርዝር በሚደነግገው ክፍል የሚገኝ ነው። ችልታ ከዕድሜ፣ ችልታ በከባድ ወንጀል ጥፊተኛ ሆኖ መገኘት፣ ችልታ ከአእምሮ በሽታ ጋር በተያያዘ የእያንዲንደን ዝርዝር ሁኔታ በያዘው የህግ ክፍል የሚገኝ ሆኖ በተለይም በአእምሮ መጎደል ወይም በድውይነት የተነሣ አንድ ሰው የሚሰራው ተግባር ምን ውጤት እንደሚያስከትል የማያውቅ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ይህ ሰው ማናቸውንም ተግባር እንዲያከናውን በማድረግ በፍርድ በመከልከል በህግ ጥበቃ ከሚደረግበት ክፍል ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች በፍርድ ሉከልክለ የሚገባቸው ስዎች የትኞቹ ናቸው የሚለውን ለመለየት በመሰረትነት ለተቀመጠው ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 339 ቀጠል የሚገኝ ድንግጌ ነው።
ድውዮችም አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ የአእምሮ ጎደልነት እንዲለባቸው ሰዎች ተቆጥረው የፍርድ ክልከላ እንደሚደረግባቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 351(3) መመልከቱ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 340 ድንጋጌ ይዘትና አስፈላጊነት አንድ ሰው ተግባሩን ለመፈፀም ችልታ ነበረው ወይስ አልነበረውም የሚለውን ለመለየት እንጂ አካላዊ ጎድለነት ያለባቸው ሰዎች ህጋዊ ተግባር ለመፈፀም በፈለጉ ጊዜ የአደራረጉ ሥርዓት በምን አኳኋን ሉፈፀም ይገባል ከሚለው ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት የለውም የሚሰሩት ሥራ ምን ውጤት እንደሚያስከትል የማያውቁ ሰዎች ስለሆኑ የፈፀሙት ተግባር ሉፈርስ ይገባል ወይስ አይገባም? በማለት ያደረጉትን ተግባር ህጋዊነት (Validity) ለመመርመር መሰረት የሚሆን ድንጋጌ እንጂ እነዚህ ስዎች ተግባራቸውን የት? እና እንዳት ማከናወን አለባቸው ከሚለው የውል አደራረግ ሥርዓት ጋር የተዛመደ አይደለም።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 368(1) የተከለከለ ሰው ክልከላው በፍርድ ከተነገረ በኋላ ኑዛዜ ለማድረግ አይችልም በሚል የተደነገገውን በፍ/ብ/ሕ/ቁ 340 እና 351(3) ጋር በማገናዘብ ስንመለከተው ይህንኑ የትርጉም መስመር፣ ይበልጥ የሚያጠናክር ሆኖ ይገኛል።
እንደዚሁም ኑዛዜ ዋጋ እንዱኖረው የሚያስፈልጉ ሁኔታዎች በሚለው ክፍል ችልታ አስፈላጊ ከሆኑ የሥራ ነገር ሁኔታዎች አንደ ሆኖ ኑዛዜ ለማድረግ ችልታ ከዕድሜ አንፃር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 860፣ ችልታ ለአእምሮ መጓደል ጋር በተያያዘ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 861 – 864 በዝርዝር መደንገጉና የኑዛዜ አደራረግ ሥርዓትን በማመልከት ግን እራሱን በቻለ የኑዛዜ ፍርምና ማስረጃ በሚል ንዐስ ክፍል መቀመጡ ኑዛዜ የሚያደርጉ እነማን ናቸው? ኑዛዜ የሚደረግበት ሥርዓት እንዳትና በምን አኳኋን ነው? የሚለት ነጥቦች በየቅል የሚታዩና ጉዲዮቹን የሚገባው የህግ ክፍል በየነጥቦቹ አግባብ የተቀመጠ መሆኑ እየታወቀ የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 340 የተመለከተውን ድንጋጌ ከውል አደራረግ ሥርዓት ጋር በማያያዝ የሰጠው ትንታኔ እና ትችት አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
ከዚህም አንፃር ሟች ወ/ሮ መሰረት መንገሻ ማየት የተሳናቸው መሆኑ ከመረጋገጡ በቀር በዚህ አካላዊ ጉድለት ምክንያት ለእራሳቸውም ሆነ ላልች መብታቸው የሚያከብሩላቸው ሰዎች ጥቅም ለማስጠበቅ ሲባል በፍርድ የተከለከለ አይደለም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ 343(2) መሰረት በፍርድ ባይከላከለም ድውይነታቸው አከራካሪ የሆነውን ተግባር ለመፈፀም የሚያስችላቸው ነበረ ብል ከችልታ ጋር በማያያዝ ለመተርጎምም መነሻ የሆኑ ፍሬ ነገሮች አላገኘንም።
በዚህ ሁለ ምክንያት የአዱስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 340 አንፃር በማየት አከራካሪ የሆነው ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት አያስከትልም በሚል የሰጠው ውሳኔ ከተሳሳተ መነሻ የመነጨ በመሆኑ አተረጓጉሙ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
በሁለተኛ ደረጃ ላታይ የሚገባው ነጥብ ማየት የተነሳው ሰው ኑዛዜ የሚያደርግበትን የአደራረግ ሥርዓት የሚመለከት ነው።
የአሁን አመልካች ከሥር ጀምሮ አንስቶ የተከራከረበት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1728(3) ድንጋጌ ስለውልች አደራረግ ሥርዓት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1678(ሐ) የተመለከተውን መሪ ድንጋጌ በሚያብራራው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1719(2) እስከ 1730 በተመለከተው የውል አደራረግ ሥርዓት ከሚደነግጉት ዝርዝር ድንጋጌዎች አንደ በመሆኑ ክርክሩ አግባብነት ያለው ነው። ሆኖም ይህ ድንጋጌ የሚገኘው ስለውልች በጠቅላላው ክፍል እንደ መሆኑ መጠን ስለውልች በጠቅላላው የተመለከቱት ደንቦች ከውልች ባሻገር ስለላልች ጉዲዮች ያላቸው አግባብነትና ተፈፃሚነት በመሸጋገሪያ ድንጋጌው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1676 በተመለከተው መሰረት ነው። በዚህም ድንጋጌ አነጋገር የኑዛዜ አደራረግ ሉከተል የሚገባውን ሥርዓት በተመለከተ ስለኑዛዜ በሚያወራው ልዩ ህግ የኑዛዜዎች ፍርምና ማስረጃ በሚለው ርዕስ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 880 ጀምሮ የተደነገገ በመሆኑ ገዥው ህግ ይህ የልዩ ሕግ ክፍልእንጂ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1719 – 1730 የተመለከቱት ድንጋጌዎች አንደ የሆነው ቁጥር 1728(3) ላሆን አይችልም።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 881 በግልፅ የሚደረግ ኑዛዜ ተናዛዡና ምስክሮች በኑዛዜው ላይ ወዱያውኑ ፊርማቸውን ወይም የአውራ ጣት ምልክታቸውን ማድረግ እንዲለባቸው እንጂ አካላዊ ጉድለት፣ ያለበትን ተናዛዠ አካለ ከተስተካከለው ለይቶ ያስቀመጠው መስፈርት የለም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1728(3) መሀይማን የጣት ምልክት ፊርማቸውን በአዋዋይ ፉት ማድረግ እንደሚገባ ሲደነግግ ኑዛዜን አስመልክቶ በተቀመጠው በዚህ ልዩ ድንጋጌ 881(3) ማህይማን የጣት ምልክታቸውን ወዱያውኑ ማስቀመጥ ያለባቸው መሆኑን እንጂ በተለይ በአዋዋይ ፉት እንዱያደርጉ አልደነገገም። ይህም በአንድ ጉዲይ ላይ በተለያዩ መንገድ በተለያዩ የህግ ክፍል መደንገጉ ጉዲዮች እንደየ አግባብነታቸው ሉታዩ የሚገባ መሆኑን ስለሚያስገነዝብ ለዚህ ለተያዘው ጉዲዩ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1728(3) የተመለከተው ድንጋጌ ተፈፃሚነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች አንፃር የአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ሆነ ሰበር ሰሚው የሰጡት ዲኝነት መሰታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም በኢ.ፉ.ዱ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 80(3) እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 እንደተደነገገው የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን መሰረታዊ የህግ ስህተት በተፈፀመባቸው የመጨረሻ ውሳኔዎች ላይ የተመረኮዘ በመሆኑ የሚከተለውን ውሳኔ ሰጥተናል፡
(1) የአዱስ አበባ ከተማ ፍ/ቤቶች ሰበር ሰሚ ችልት በፍ/መ/ በ17/03/2002 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንቷል።
(2) የአመልካች የሰበር አቤቱታ ተቀባይነት ያለው አይደለም ብለናል።
በዚህ የሰበር ጉዲይ ግራ ቀኙ ላወጡት ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል።
No topics extracted.