No summary available.
የካቲቲ 11 ቀን 2003 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ጥሩወርቅ ወርድፊ - ጠበቃ ብርሃኑ ወልደዮሐንስ ቀረቡ ተጠሪ፡- ጥሩነሽ ወርድፊ - ጠበቃ ደጀኔ አባተ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ልጅነትን የሚመለከት ክርክርን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ የሟች አቶ ወርድፊ በዲሳ ልጅነት ይረጋገጥልኝ በማለት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻነት ፍርድ ቤቱ የሰጠው የልጅነት ማስረጃ በሐሰት የተሰጠ በመሆኑ ሉሰረዝ ይገባል በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 መሰረት ባቀረቡት የመቃወም አቤቱታ መነሻነት ነው። በአቤቱታቸው ላይም የአሁኑ ተጠሪ ከሟች አቶ ወርድፊ በዲሳ እና ከወ/ሮ አፀደ ወ/ጊዮርጊስ ተወልጄአለሁ ያለት ሐሰት ነው፣ ሕጋዊ ግንኙነት አልነበራቸውም፣ የአቶ ወርድፊ በዲሳ ብቸኛ ልጅ አመልካች ነኝ፣ ተጠሪ የሟች ልጅ ነኝ የሚለ ከሆነ የደም ምርመራ(DNA) ላደረግ ይገባል በማለት ገልፀው ለተጠሪ የተሰጣቸው የልጅነት ማስረጃ እንዱሰረዝላቸው ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኗ ተጠሪም ለአሁኗ አመልካች የመቃወም አቤቱታ መልስ እንዱሰጡበት ተደርጎም ባቀረቡት መከራከሪያ የሟቹ ልጅ ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆኑንና የደም ምርመራም የመቃወም አመልካች ሉጠይቁ እንደማይችለ ገልፀው የመቃወም አመልካች አቤቱታ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የ‛DNA“ ምርመራ ጥያቄን አልፍ የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር የአመልካችን መቃወሚያ አቤቱታ ውድቅ አድርጎ ተጠሪ የሟች አቶ ወርድፊ በዲሳ ልጅ ናቸው በማለት የሰጠውን ውሳኔ ሉሰረዝ አይገባም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው። የሰበር አቤቱታው መሰረታዊ ይዘትም ተጠሪ የሟች ወርድፊ ልጅ ናቸው ተብል የተሰጠው የልጅነት ማስረጃ ሉሰረዝ አይገባም ተብል የተወሰነው በተገቢው ማስረጃ ባልተረጋገጠበት ሲሆን የ‛DNA“ ምርመራ ጥያቄም የታለፈው ያላግባብ በመሆኑ ውሳኔው ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም ተጠሪ የሟች አቶ ወርድፊ በዲሳ ልጅ ናቸው ተብል መወሰኑም ሆነ የ‛DNA“ ምርመራ ጥያቄ የመታለፈን ተገቢነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎአል። በዚህም መሰረት ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው የግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሐፍ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች ያቀረቡት በሳይንሳዊ መንገድ የደም ምርምራ ጥያቄ ታልፍ ተጠሪ የሟች አቶ ወርድፊ ልጅ ናቸው ተብል መወሰኑ ባግባቡ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሁኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ሟች አቶ ወርድፊ በዲሳ ልጅ እና ወ/ሮ የሺመቤት አየነው በጋብቻ ተሳስረው የተወለደ ስለመሆናቸው የተረጋገጠ ሁኖ በተጠሪ በኩል የቀረበ ማስተባበያ ክርክር የላለ መሆኑን፣ ተጠሪ የሟቹ ልጅ ነኝ በማለት የሚከራከሩት ሟች እንደአባት በመሆን ሲንከባከቧቸው የነበረ በመሆኑና ይህም በማስረጃ መረጋገጡን መሰረት በማድረግ መሆኑን ነው። አመልካች የተጠሪን ማስረጃዎች ለማስተባበል በማስረጃነት እንዱቀርብላቸው ከሚፈልጉት ማስረጃዎች አንደ ደግሞ ሳይንሳዊ የደም ምርመራ ዘዳ ነው። ሆኖም የስር ፍርድ ቤት በዚህ ረገድ የቀረበውን የአመልካችን የማስረጃ ይቅረብልን ክርክር ሳያጠናቅቅ ማለፈን መዝገቡ ያሳያል።
በመሰረቱ የተጠሪ የሟች አቶ ወርድፊ በዲሳ ልጅነት ተረጋግጧል የተባለው በተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁጥር 213/1992 አንቀጽ 143(ሰ) መሰረት ሲሆን በአንቀጽ 143 ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች አባትነት በፍርድ ሉነገር የሚገባቸው ሁኔታዎች መሆኑ፣ ከእነዚህ ሁኔታዎች ውጪ አባትነት በፍርድ ሉነገር የማይችል ስለመሆኑ የተጠቀሰው አዋጅ በአንቀጽ 145 ስር በግልፅ ደንግጓል። አዋጁ አባትነት በፍርድ ሉነገር የሚችልባቸው ሁኔታዎች ላይ ማስተባበያ ማስረጃ ላቀርብ የሚችለው በአንቀጽ 144 ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች ስለመሆኑ በዝርዝር አስቀምጧል። ከእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ደግሞ ‛ሣይንሣዊ“ ደም ምርመራ አንደ ስለመሆኑ ተመልክቷል። የስር ፍርድ ቤት አመልካች በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ጥያቄ ያልተቀበለበት ሕጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ በውሳኔው ላይ የገለጸው ነገር የለም። ይህ ደግሞ የፍርድ አካሄደን የተሟላ ሳያደርግ ፍርድ የሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ሲሆን አመልካች ሟቹ በሕጋዊ ጋብቻ ውስጥ የወለዶቸው ስለመሆኑ በተረጋገጠበት ሁኔታ ከተጠሪ ጋር የደም ምርመራ ይደረግልኝ ብለው ያቀረቡት ክርክር የሚታለፍበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በአጠቃላይ የአመልካች የደም ምርመራ ጥያቄ የታለፈው ያላግባብ በመሆኑ በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሐምል 16 ቀን 2002 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 25 ቀን 2003 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
በአመልካች ወጪ የአመልካችና የተጠሪ የ‛DNA“ ምርመራ እንዱካሄድ በማድረግ የሚቀርበውን ውጤት መሰረት አድርጎ ጉዲዩን እንደገና በመመርመር ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥበት ለፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን መልሰንለታል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.