No summary available.
ጥር 27 ቀን 2ዐዐ3 ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ዲኜ መላኩ ተሻገር ገ/ሥላሴ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ፍቃደ ሽፈራው - ቀረቡ መልስ ሰጪ፡- አቶ ግሩም ኤርሚያስ - ጠበቃ ወርቅነህ በረደድ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው ክርክር ስለውርስ ንብረት ክፍፍል የተደነገጉትን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች አተረጓጎምን የሚመለከት ነው። ለጉዲዩ መነሻ የሆነው ነገር ሟች ወ/ሮ በላይነሽ ገ/እየሱስ ሚያዚያ ዐ8 ቀን 1998 ዓ.ም የተውት ኑዛዜ ነው። አመልካች የሟቿ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ፣ተጠሪ ደግሞ የሟቿ የልጅ ልጅና የኑዛዜም ወራሽ መሆናቸው በስር ፍርድ ቤቶች ተረጋግጧል። አሁን ግራ ቀኙን እያከራከረ ያለው ሟች የተውት ኑዛዜ ነው። የአሁኑ አመልካች ሟች ወ/ሮ በላይነሽ ገ/እየሱስ የተውት ኑዛዜ የሕጉን ፍርማሉቲ ያልጠበቀና ከውርስ የነቀለኝ በመሆኑ ሉፈርስ ይገባል፣ ተጠሪ የሟቿ የኑዛዜ ወራሽ ናቸው ተብል የተሰጠው ውሣኔም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 358 እና 36ዐ መሰረት ሉሰረዝ የሚገባው ነው በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪ ደግሞ ኑዛዜው በሕጉ የሚፈለገውን ፍርማሉቲ ያሟላ ከመሆኑም በላይ ሟች ለአመልካች ብር 1ዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ / እንዱሰጣቸው በኑዛዜው ላይ የተገለፀ በመሆኑ አመልካችን ከውርስ ነቅሎል ሉያስብል የሚችል አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ኑዛዜው ፍርማሉቲውን ያሟላ ነው፣ አመልካች ብር 1ዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ ብር/ እንዱሰጣቸው ሟች የተናዘዙ መሆናቸው ደግሞ ከውርስ ነቅለዋል ለማለት የሚያስችል አይደለም የሚለትን ምክንያቶችን በመያዝ ተጠሪ የሟች የኑዛዜ ወራሽ ናቸው በማለት የሰጠውን ውሣኔ ሉሰረዝ አይገባም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለከተማው ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ሲሆን የአቤቱታው መሰረታዊ ነጥብም ሟች ወ/ሮ በላይነሽ ገ/እየሱስ የተውት ኑዛዜ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ የሆኑት አመልካች ከውርስ የነቀለና የጎዲ በመሆኑ ሉፈርስ የሚገባው ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። ይህ የሰበር ችልትም የሰበር አቤቱታውን በመመርመር አመልካች በኑዛዜው ላይ ብር 1ዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ያገኛል ተብል መወሰኑ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1123 ድንጋጌ አንፃር ተገቢነቱ ላታይ የሚገባ መሆኑን በማመን ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ ከአዘዘ በሁዋላ ለተጠሪ ጥሪ አድርጎላቸው ተጠሪ ቀርበው ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሐፍ አቅርበዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም ጉዲዩን ከውርስ ሕጉ አግባብነት ያላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምሮአል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ሟች ወ/ሮ በላየነሽ ገ/እየሱስ ሚያዚያ ዐ8 ቀን 1998 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በፍርማሉቲ በኩል ፈራሽ ሉያደርገው የሚገባ ሕጋዊ ምክንያት የላለ መሆኑ በሚገባ የተረጋገጠ እና አመልካችም በዚህ ረገድ የተሰጠውን ውሣኔ ሕጋዊ አይደለም በማለት ያቀረቡት የሰበር ክርክር የላላቸው መሆኑን ነው። ኑዛዜው የሕጉን ፍርማሉቲ ያሟላ ነው ከተባለና በኑዛዜ አንድ ወራሽ አለአግባብ ተነቀለ የሚባል ቢሆን በውርሱ አከፊፈል ላይ የሚታይ እንጂ በአግባቡ የተሰጠን ኑዛዜ ፈራሽነት የሚያስከትል የሕግ ምክንያት አይኖርም። በመሆኑም ቀጥል መታየት ያለበት ጉዲይ የኑዛዜ ስጦታው የፀና መሆን በውርስ ክፍፍለ የሚያስከትለው ውጤት ምንድነው? የሚለው ጥያቄ ነው። ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ተያያዥነት ያላቸውን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎች መመለከት ያስፈልጋል። አሁን ከያዝነው ጉዲይ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የፍትሐብሕር ሕጉ አንቀጽ 913 ሲሆን ይህ ድንጋጌ የኑዛዜው ቃል የተናዛዥን ተቃራኒ ሐሣብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር ከውርስ ሃብት አንድ ድርሻን ወይም አንድ ንብረትን ሟቹ ለወራሾች መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ ነው ተብል አይቆጠርም በማለት ያስቀምጣል።
አሁን በቀረበልን ጉዲይ ሟች አዱስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘውንና ብቸኛ ንብረት የሆነውን ቤታቸውን በኑዛዜው ይሰጥልኝ ያለት የእህት የልጅ ልጅ ለሆነው ለአሁኑ ተጠሪ ሲሆን ልጅ ለሆነው የአሁኑ አመልካች ደግሞ በተጠሪ ብር 1ዐዐ.ዐዐ/ አንድ መቶ/ ብቻ እንዱሰጣቸው ነው።
ተጠሪ የሟች እህት ልጅ ልጅ በመሆናቸው ክርክሩ የሚያረጋግጥ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1123 ስር የተመለከተው ድንጋጌ መሰረቱ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1117 በመሆኑ በዚህ አግባብ የሚታይ ሁኖ አላገኘነውም። ምክንያቱም አሁን የቀረበው ክርክር በተወላጆች መካከል አይደለምና። በመሆኑም ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ በዚህ ረገድ የተያዘውን ጭብጥ አልፈነዋል። በጭብጥነት ተይዞ መታየት ያለበት ጉዲይ አመልካችን ሟች ከውርስ ነቅለዋል ልባል ይቻላል? ወይስ አይቻልም?፣ ነቅለዋል ከተባለስ ተግባሩ በሕግ ፉት ተቀባይነት አለው? ወይንስ የለውም? የሚለት ነጥቦች ሁነው አግኝተናል።
ከቀረበልን ጉዲይ ለመገንዘብ እንደቻልነው ሟቿ ኑዛዜአቸው ላይ ያሎቸውን ንብረቶች በሙለ የሰጡት ለተጠሪ ነው። የዚህ ዓይነት ክፍፍል ሕጉ የሚደግፈው ቢሆንም አንድ ወላጅ ተወላጅን ከውርሱ ያለሕጋዊ ምክንያት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ሲነቅል ግን ተቀባይነት ሉኖረው የማይችል መሆኑን ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 937፣938 እናና 939 ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ /ነጥብ/ ነው። ሟች ወ/ሮ በላይነሽ ገ/እየስ ልጃቸው የሆኑትን አመልካችን ካላቸው ንብረታቸው ብር 1ዐዐ.ዐዐ /አንድ መቶ/ ብቻ እንዱሰጣቸው በኑዛዜው ላይ ገልፀዋል። ሟች ተጠሪ እንዱወስደ የተናዘዙት በአዱስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኝ የማይንቀሣቀስ ንብረት ነው።
ከዚሁ ንብረት አይነትና ካለው ዋጋ አንፃር ሲታይ ሟች በኑዛዜው ላይ ለአመልካች ብር 1ዐዐ.ዐዐ ብቻ እንዱሰጣቸው መጥቀሣቸው ከውርሱ በተዘዋዋሪ ነቅለዋቸዋል ከሚባል በስተቀር ላላ ምክንያት ሉሰጠው የሚችል ሁኖ አላገኘነውም። ሟች አመልካችን በተዘዋዋሪ ነቅለዋል ከተባለ ደግሞ የነቀለበት ምክንያት በቂና ሕጋዊ መሆን ላታይ የሚገባው ሲሆን ሟች በዚህ ረገድ በኑዛዜው ላይ ያስቀመጡት ምክንያት የለም። በመሆኑም አመልካች በተዘዋዋሪ መልኩ በዝምታ ከሟቿ ውርስ የነቀለ መሆኑን ይህ ችልት ተገንዝቧል። ወላጅ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሹን ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት ወይም በዝምታ ከነቀለም ውጤቱ ምን ላሆን እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 915 ከላይ ከተጠቀሱት ድንጋጌዎች ጋር ተዲምሮ ሲታይ ምላሽ ይሰጣል። በዚህም መሰረት ከውርስ በዝምታ ወይም ያለበቂና ሕጋዊ ምክንያት የተነቀለ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ ሁነው የውርስ ንብረቱን ሉከፊፈለ የሚችለ መሆኑን ሕጉ ያስገነዝባል። ይሁን እንጂ ፍርድ ቤቱ ወደዚህ ድምዲሜ ከመድረሱ በፉት በወላጅ የተደረገ የኑዛዜ ስጦታ አይነቱ ጠቅላላ ወይም ልዩ ኑዛዜ ስጦታ መሆን ያለመሆኑን በቅድሚያ መለየት አለበት። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 912 ስር እንደተመለከተው የኑዛዜ ስጦታ ጠቅላላ ወይም ልዩ ኑዛዜ ስጦታ ላሆን ይችላል። ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ ሲባልም ተናዛዡ ሀብቱን ጠቅላላ ወይም ከመላ ንብረቱ አንደን ክፍል በሙለ ሀበትነት ወይም በላጣ ርስትነት ለአንድ ወይም ለብዙ ሰዎች የሚያወርስበት የኑዛዜ ቃል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 912/1/ ድንጋጌ ያሣያል። የዚሁ ቁጥር ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌ ደግሞ ማንኛውም ላላ የኑዛዜ ቃል ሁለ እንደ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ እንደሚቆጠር ይደነግጋል። አንድ ኑዛዜ ልዩ የኑዛዜ ስጦታ መሆኑ ከተረጋገጠ ደግሞ እንደውርስ እዲ ተቆጥሮ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐ14 ድንጋጌ ቅደም ተከተል መሰረት የሚከፈል ይሆናል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ወ/ሮ በላይነሽ ገ/እየስ የነበራቸውን አንድ መኖሪያ ቤት ለአሁኑ ተጠሪ እንዱሆን በኑዛዜ ስጦታ ሰጥተዋቸዋል። ላልች ንብረቶች ያላቸው መሆኑን የክርክሩ ሂደት አያሣይም። በመሆኑም ከዚህ አንፃር ተናዛዧ ያደረጉት ኑዛዜ ስጦታ አይነቱ ሲታይ ጠቅላላ የኑዛዜ ስጦታ እንጂ ልዩ የሆነ የኑዛዜ ስጦታ አይነት አይደለም ነው። እንዱህ ከሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1ዐ14/ሰ/ ስር በተመለከተው መሰረት እንደውርስ እዲ ተቆጥሮ ለልዩ ኑዛዜ ተቀባዩ የሚከፈል ሣይሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 938 እና 939 እንዱሁም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 915 ድንጋጌዎች ታይቶ ተወላጅ ከውርስ ተነቅሎል፣ ከኑዛዜ ተቀባዩ ጋር እኩል ሉካፈል ይገባል ልባል የሚገባው ነው። ስለሆነም የበታች ፍርድ ቤቶች ወ/ሮ በላይነሽ ገ/እየስ ያደረጉት ኑዛዜ አመልካችን በተዘዋዋሪ መንገድ ከውርስ የነቀለ መሆኑን በመለየት የኑዛዜ ስጦታ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 912፣ 915፣937፣938 እና 939 አንፃር በማየት መወሰን ሲገባቸው የአመልካችን ጥያቄ ሙለ ሙለ ውድቅ ማድረጋቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሁኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዱስ አበባ ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 51/2ዐዐ1 መጋቢት ዐ9 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም ተሰጥቶ በከተማው ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር ዐ9721 መጋቢት 23 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በትእዛዝ፡ በከተማው ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁጥር 1ዐዐ29 ጥር 28 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በውሣኔ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 348/1/ መሰረት ተሻሽሎል።
በአጠቃላይ ፍርስ ባይሆንም ከላይ በፍርድ ሐተታው ላይ በተጠቀሰው መሰረት አመልካችና ተጠሪ የሟችን ንብረት እኩል የመውረስ መብት አላቸው ብለናል።
የስር ፍርድ ቤት ውሣኔው መሻሻለን እንዱያውቀው የውሣኔው ኮፑ ይላክለት።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻለ።
No topics extracted.