No summary available.
ታህሣሥ 13 ቀን 2ዐዐ3 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ነጋሲ አየለ ኢትቻ ጠበቃ ገመቹ ደሬሣ ቀረበ ተጠሪዎች፡- 1/ ሣሙኤል ዮሐንስ ገ/እግዚአብሓር /ጠበቃ ገ/ሚካኤል 2/ የሕፃን ዮሐንስ ሐጎስ ሞግዚት ወ/ሮ ማንአሰበሽ በየነ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ ከውርስ ሐብት ክፍፍል ጥያቄ ጋር ተያይዞ የተነሣውን ክርክር የሚመለከት ነው።
ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሣሾች የነበሩት ተጠሪዎች ናቸው።
በአመልካች ላይ ክስ የመሰረቱት የሟች እናታችን ወ/ሮ ዘነበች በየነ ወራሾች ስለሆንን የውርስ ንብረት ይጣራልን በማለት ነው። አመልካችም በበኩለ ለክሱ በሰጠው መልስ ከከሣሾች እናት ጋር የጋብቻ ግንኙነት የለኝም። አብረን በጋራ ያፈራነው ንብረት የለም። ከሣሾች እኔን በመክሰስ የሚጣራላቸው ንብረት የለም በማለት ስለመከራከሩ ከመዝገቡ ተመልክተናል። ከዚህ በኋላ ፍ/ቤቱ ከሣሾች የሟች እናታቸው ወራሾች እስከሆኑ ድረስ እናታቸው የተጠሪ ሚስት ብትሆንም ባትሆንም የአውራሻቸው ውርስ እንዱጣራ የመጠየቅ መብት አላቸው በማለት የሟች የውርስ ሐብት ይጣራ በማለት ወስኖአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙ የቀረበው የመጨረሻ ውሣኔ ከመሰጠቱ በፉት ነው የሚል ምክንያት በመስጠት ይግባኙን ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካች ሰኔ 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈው ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች በተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ ስህተት ተፈጽሞአል የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታውን አቅርቦአል።
በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል።
አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ከተጠሪዎች አውራሽ /ሟች/ ጋር የጋብቻ ግንኙነት የለም የሚለው የአመልካች ክርክር አስቀድሞ ሣይወሰን ውርስ እንዱጣራ የመወሰኑን አግባብነት ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በዚህ መሰረትም ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሣኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
እንደምንመለከተው የክርክሩ መነሻ የሟች ውርስ ይጣራ የሚል ቢሆንም፤ አመልካች ግን ወደውርስ ማጣራቱ ከመገባቱ በፉት በእሱ እና በሟች /የተጠሪዎች እናት/ መካከል ስላለው ግንኙነት በሚመለከት ክርክር አንስቶአል። ክርክሩም ከሟች ጋር የጋብቻ ግንኙነት የለኝም፤ በጋራ ያፈራነው ንብረት የለም በሚል በግልጽ የቀረበ ነው። ይህ ማለት ደግሞ የሟች ውርስ ይጣራ በሚል ጥያቄ እኔ ተከሣሽ የምሆንበት ምክንያት የለም የሚል ክርክር ከአመልካች ቀርቦአል ማለት ነው።
አንድ ሰው በሞተ ጊዜ ትቶት የሄደውን ንብረት መካፈል የሚችለት በሕጉ አግባብ ወራሾቹ እንደመሆናቸው የውርስ ሐብቱን ይዞ በሚገኝ ሰው ላይ ክስ በማቅረብ ሐብቱን ሉያገኙ እንደሚችለ ይታወቃል። ውርስ ከመጣራቱ በፉት መከፊፈል ያልተቻለ በሆነ ጊዜም ወራሾቹ ወይም ከወራሾቹ አንደ ውርሱ ይጣራ ዘንድ እንዱታዘዝላቸው ለፍ/ቤት አቤቱታ ማቅረብ እንደሚችለ በፍትሐብሕር ሕጉ ከፍ/ብሓር ህ/ቁ. 942 እና ቀጥለው ካለት ድንጋጌዎች እንገነዘባለን። ውርሱ እንዱጣራ ሲጠየቅም ተከሣሽ መሆን ያለበት የውርሱን ሐብት የያዘ ወይም ወራሽ በሆነው ሰው ላይ ነው።
በያዝነው ጉዲይ በተጠሪዎች ክስ ይጣራ የተባለው ንብረት የሟች እናታቸው መሆኑ ቢገለጽም የተከሰሰው ግን አመልካች ነው። ተጠሪዎች አመልካችን በተከሣሽነት ያጣመሩት በእሱ እና በእናታቸው መካከል የጋብቻ ግንኙነት አለ /ነበረ/ በማለት እንደሆነ ከክርክራቸው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል። ይህ ፍሬ ነገር በአመልካች ተክድአል። የተጠሪዎችን እናት አላገባሁም አብረንም ያፈራነው ንብረት የለም በማለት እንደተከራከረም ተመልክተናል። ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት በዚህ አይነት የቀረበን ክርክር ለመወሰን የሚያስችለውን የነገር ጭብጥ መሥርቶ ግራ ቀኝ ወገኖችን አላከራከረም።
አመልካች አጥብቆ እንደሚከራከረው በተጠሪዎች እናት እና በእሱ መካከል በሕግ የሚታወቅ ግንኙነት ከላለ በሟች ውርስ ማጣራት ሂደት እሱ ተከሣሽ የሚሆንበት አግባብ የለም። በልላ በኩል ደግሞ በእሱ እና በተጠሪዎች እናት መካከል በእርግጥም በሕግ የሚታወቅ ግንኙነት መኖሩ እና ንብረትም በጋራ ማፍራታቸው ከተረጋገጠ በቀረበው ክስ መሰረት ውርሱ እንዱጣራ ይደረጋል።
አሁን እያየን ያለው ግን በተጠሪዎች እናት እና በአመልካች መካከል ያለው ግንኙነት ምን እንደሆነ ከመረጋገጡ ወይም በዚህ ረገድ የተነሣው ክርክር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 247/1/ በተደነገገው መሰረት ተገቢው ጭብጥ ተይዞለት ከመወሰኑ በፉት ወደውርስ ማጣራት እንዱገባ ነው የተበየነው በመሆኑም አካሄደ የክርክር አመራር ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም። የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤትም ክርክሩ በሥርዓት አልተመራም የሚል ይግባኝ ቀርቦለት እያለ ውርሱ እንዱጣራ በማለት የተሰጠው ብይን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 32ዐ/3/ እንደተመለከተው ጊዜአዊ አገለግልት እንዲለው ትእዛዝ አድርጎ መቁጠሩ ትክክል አይደለም። ጉዲዩ እኔን በተከሣሽነት አስገብቶ ንብረቴን በውርስ ሐብትነት ተይዞ እንዱጣራ የሚያስደርግ አይደለም በማለት አመልካች ያቀረበውን ክርክር አለመቀበል ጊዜአዊ አገልግልት ያለው ትእዛዝ እንደመሰጠት የሚቆጠር አይደለም። ስናጠቃልለው አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ በሕጉ አተገባበር ረገድ መሰረታዊ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 47254 መጋቢት 15 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.ቁ. 79397 ሚያዝያ 3ዐ ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አመልካች ከተጠሪዎች እናት ጋር ግንኙነት የለኝም። ንብረትም በጋራ አላፈራንም በማለት ያነሣው ክርክር ተጠሪዎች ከሚያቀርቡት የመከራከሪያ ነጥብ ጋር በማገናዘብ የፍሬ ነገር ጭብጥ በመመሥረት በቅድሚያ በዚህ ጭብጥ ላይ ውሣኔ ይሰጥ በማለት ጉዲዩ ይመለስለት ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራ ይቻቻለ።
No topics extracted.