No summary available.
ሕዲር 13 ቀን 2003 ዓ/ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ተሻገር ገ/ሥላሴ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሙለወርቅ ዋቼ - የቀረበ የለም።
ተጠሪ፡- ማህበራዊ ዋስትና ባለስልጣን - ነ/ፈጅ ተስፊዬ ሞገደገኝ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የጡረታ ተጠቃሚነት የሚቋረጥበትን አግባብ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ ባሁኑ አመልካች ላይ በሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው።
የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- አመልካች የሟች አቶ ጋቲሶ ሚስት ስለነበሩ የጡረታ አበል ተወስኖላቸው ሲቀበለ ከቆዩ በሁዋላ ላላ ባል አግብተውም ከሕግ ውጪ አበለን መቀበለን መቀጠላቸውን ገልጾ ባል ሲያገቡ መቋረጥ ሲገባው የተቀበለትን መጠኑ ብር 5478.56 /አምስት ሺህ አራት መቶ ሰባ ስምንት ብር ከሃምሳ ስድስት ሳንቲም/ የጡረታ አበል እንዱመልሱ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አመልካች ለተጠሪ ክስ በሰጡት መከላከያ መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል። በመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያነት ያቀረቡት ክርክርም በልላ መዝገብ በቀረበ ክርክር ሟች አቶ ጋቲሶ አዱሶ ከሞቱ በሁዋላ ላላ ባል ያላገቡ መሆኑ መረጋገጡን የሚገልጽ ሲሆን በፍሬ ነገር ደረጃ ያቀረቡት ክርክርም የጡረታ አበለን እየተቀበለ ባለበት ጊዜ ላላ ባል ያላገቡ መሆኑን ገልጸው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ ሰምቶ ጉዲዩን ከመረመረ በሁዋላ የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጎ ለክሱ መሰረት የሆነውን ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ መልስ ሰጪን ሳይጠራ አጽንቶታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
የአመልካች ጠበቃ ጥር 17 ቀን 2ዐዐ2 ዓ/ም ፅፈው ባቀረቡት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- አመልካች ላላ ባል ያላገቡ መሆኑ በልላ መዝገብ ተረጋግጦ ውሳኔ አግኝቶ እያለ ይኸው ታልፍና ተጠሪም አመልካች ላላ ባል ስለማግባታቸው ሳያስረዲ ላላ ባል አግብተዋል ተብል የጡረታ አበለን እንዱመልሱ የተሰጠው ውሳኔ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ የሚገባው ነው ተብል በመታመኑ ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎለት ቀርቦ የጽሐፍ መልሱን ሰጥቷል። የአመልካች ጠበቃም የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም የዚህን ችልት ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ነጥብ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል ለማለት ይቻላል; ወይስ አይቻልም; የሚለው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ላላ ባል ያገቡ መሆን ያለመሆኑ ጉዲይ የፍሬ ነገር ክርክር ሲሆን ይኸውም አመልካች ላላ ባል ያገቡ መሆን ያለመሆኑ ጉዲይ የፍሬ ነገር ክርክር ሲሆን ይኸው ፍሬ ነገር በሕጉ አግባብ ተቀባይነት ባለው ማስረጃ ተረጋግጧል ተብል ውሳኔ መስጠቱን ነው። ይኸውም አመልካች ላላ ባል አግብተው የሚኖሩ መሆኑ በማስረጀ የተረጋገጠ ነጥብ ስለመሆኑ በበታች ፍርድ ቤቶች ተቀባይነት ማግኘቱን ነው። አመልካች በዚህ ረገድ የቀረቡትን የተጠሪ ማስረጃዎችን ያላስተባበለ ስለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ በግልፅ ያሳያል። የስር ፍርድ ቤት የአመልካችን መከላከያ ምስክሮች ቃል ውድቅ ያደረገው ቃላቸው አመልካች ባል ማግኘቷን የሚገልፅ ቢሆንም ታአማኒነት የለውም በሚል ነው። ውሳኔው በግልፅ የሚያሳየው የአመልካች ምስክሮች ቃል ውድቅ የተደረገው የግራ ቀኙ ምስክሮች ቃል ክብደቱ ተመዝኖ መሆኑን ነው። አንድ ጡረታ አበል የሚቀበል ተጋቢ ላላ ተጋቢ ማግባት አለማግባቱን በሰው ምስክር ለማረጋገጥ የሚከለክል ሕግ የለም። ይህ ሁኔታ በሰው ማስረጃ ሉረጋገጥ የሚችል ነው ከተባለ ደግሞ ጉዲዩ የማስረጃ ምዘና ጉዲይ እንጂ የሕግ አተረጎጎምን የሚመለከት አይደለም።
እንዱህ ከሆነ ደግሞ በኢ.ፋ.ዱ.ሪፐብላክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና አዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 መሰረት ይህ ችልት ጉዲዩን የሚመለከትበት አግባብ የለም። አመልካች ባል ማግባታቸው በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው ከተባለ በአዋጅ ቁጥር 209/1955 አንቀጽ 21 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 345/1995 አንቀጽ 35/2/ መሰረት ባል አግብተው እያለ የጡረታ አበል መቀበል ሕጋዊ ባለመሆኑ ገንዘቡን የማይመልሱበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በአጠቃላይ የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ሁኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጉዲዩ ላይ በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.